Wolaita Zone Youth Association/ ወላይታ ዞን ወጣቶች ማህበር

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • Wolaita Zone Youth Association/ ወላይታ ዞን ወጣቶች ማህበር

Wolaita Zone Youth Association/ ወላይታ ዞን ወጣቶች ማህበር በብቃት እና በጥረት የተካኑ ወጣቶችን ለማፍራት እንተጋለን !

‎የወላይታ ዞን ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከዞኑ ወጣቶች አደረጃጀት ጋር በመሆን ለአንድ አቅም ደካማ ቤተሰብ የቤት ግንባታ አስጀመረ‎ወላይታ ሶዶ፤ ነሐሴ 23/...
29/08/2026

‎የወላይታ ዞን ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከዞኑ ወጣቶች አደረጃጀት ጋር በመሆን ለአንድ አቅም ደካማ ቤተሰብ የቤት ግንባታ አስጀመረ

‎ወላይታ ሶዶ፤ ነሐሴ 23/ /2018 ዓ.ም የወላይታ ዞን ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከዞኑ ወጣቶች አደረጃጀት ጋር በመሆን በወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ቶሜ ከተማ "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፍቃድ አካል የሆነው ለአንድ አቅም ደካማ ቤተሰብ የቤት ግንባታ አስጀምሯል።

‎የወላይታ ዞን ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገለግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምራት ከበደ ይህ ተግባር ተጀመረ ብለን የሚናቆመው ሳይሆን እሰከ መጨረሻው ድረስ ተጠናቅቆ አገለግሎት መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል።

‎የክረምት በጎ የሚሰሩ ቤቶች በብሎኬት የሚሠራው ከጊዜ አንፃርም ቶሎ ተገንብቶ ተጠናቅቆ አገለግሎት እንዲሰጥና ዘለቀታ ያለው ዕድሜ እንዲኖርም ታስቦ እንደሆነም ገልፀዋል።

‎የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ወንድሙ ታከለ የጎነት የኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል እየተሠራ በሶዶ ዙሪያ ወረዳ በግንባታም በጥገናም በርካታ ቤቶች እየተገነቡ እንደሚገኙ በመጥቀስ ሌሎችም በርካታ በጎ ሥራዎች እየተከናወኑ እንዳሉ አሳስበዋል።

‎የክረምት በጎ ሥራው አንድ ጊዜ ብቻ ተሠርቶ የሚቆም ሳይሆን የሁል ጊዜ ተግባር ቀጣይነት ባለው መንገድ የሚሠራ መሆኑን ተገልጿል።

‎ ! የወላይታ ዞን ወጣት አደረጃጀት አመራሮችና የጉኑኖ ከተማ ወጣት አደረጃጀቶች በጋራ አረንጓዴ አሻራ አኖሩ‎‎ወላይታ ሶዶ፤ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ጉኑኖ ሐሙስ ከተማ የ20...
03/08/2026

‎ ! የወላይታ ዞን ወጣት አደረጃጀት አመራሮችና የጉኑኖ ከተማ ወጣት አደረጃጀቶች በጋራ አረንጓዴ አሻራ አኖሩ

‎ወላይታ ሶዶ፤ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም

በወላይታ ዞን ጉኑኖ ሐሙስ ከተማ የ2018 አንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ ወላይታ ዞን ወጣቶች አደረጀጀት ከ10 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ተከላ መርሃግብር ተጠናክሮ ቀጥሏል።

‎8ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ሐምሌ እንደ ሀገር 800 ሚሊየን ችግኝ ተከላ አካል በሆነው በጉኑኖ ከተማ ከ10 ሚሊዮን በላይ የተለያየ ጥቅም ያላቸው ችግኞች ይተከላሉ።

‎አረንጓዴ አሻራችን የልማትና የብልጽግና መሰረት በመሆኑ ልዩ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው ያሉት የችግኝ ተከላው በብልጽግና ጉዟችን ውስጥ ባሕል ሆኖ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

‎የሚተከሉት ችግኞች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚሰጡ ለደን ልማት፣ ለምግብነትና ለውጭ ገበያ የሚሆኑ ችግኞች መብዛት እንዳለበትም ተገልጿል።

በአንድ ጀንበር መርሃግብሩ የወላይታ ዞን ወጣት አደረጃጀት አመራሮችና የጉኑኖ ሐሙስ ከተማ ወጣት አደረጃጀቶች በጋራ አረንጓዴ አሻራ አከናውኗል።

የወላይታ ዞን ወጣቶች በተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች በነቂስ ወጥተው የዜግነት ኃላፊነት ስወጡ! #ኢትዮጵያ እየመረጠች ነዉ ! #ወጣቶች እየመረጡ ነው ! #ምርጫ 2018 ዓ/ም!
01/06/2026

የወላይታ ዞን ወጣቶች በተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች በነቂስ ወጥተው የዜግነት ኃላፊነት ስወጡ!
#ኢትዮጵያ እየመረጠች ነዉ !
#ወጣቶች እየመረጡ ነው !
#ምርጫ 2018 ዓ/ም!

ነገ ኢትዮጵያ ትመርጣለችታሪካዊውን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለማከናወን የመጨረሻው ቀን ላይ እንገኛለን ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመላው አገሪቱ ይከናወናል በዚህ ታሪካዊ ቀን ድም...
31/05/2026

ነገ ኢትዮጵያ ትመርጣለች

ታሪካዊውን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለማከናወን የመጨረሻው ቀን ላይ እንገኛለን

ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመላው አገሪቱ ይከናወናል

በዚህ ታሪካዊ ቀን ድምፅዎን ሰጥተው ኃላፊነትዎን ለመወጣት እና አሻራዎን ለማሳረፍ ዝግጁ ነዎት?

ነገ በጠዋት ወጥተን በተመዘገብንበት ምርጫ ጣቢያ ድምፅ እንሰጣለን።

#ኢትዮጵያ #ምርጫ #በምርጫብቻ #ኢትዮጵያ #ምርጫ #በምርጫብቻ

ለምርጫ የተመዘገቡ እጩዎች ልዩ መብቶች1. ለምርጫ የተመዘገቡ እጩዎች ከባድ ወንጀል ሲፈፅሙ እጅ ከፍንጅ ካልተያዙ በስተቀር ምርጫው እስከሚጠናቀቅ ድረስ በወንጀል ተጠርጥረው አይያዙም፡፡2. እ...
28/05/2026

ለምርጫ የተመዘገቡ እጩዎች ልዩ መብቶች

1. ለምርጫ የተመዘገቡ እጩዎች ከባድ ወንጀል ሲፈፅሙ እጅ ከፍንጅ ካልተያዙ በስተቀር ምርጫው እስከሚጠናቀቅ ድረስ በወንጀል ተጠርጥረው አይያዙም፡፡

2. እጅ ከፍንጅም ባይሆንም ዕጩዎች ሕገወጥ ድርጊት የፈፀሙ እንደሆነ ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው የሚችለው፣ የምርጫው ውጤት በቦርዱ አማካኝነት በይፋ ለህዝብ ከተገለፀ በኋላ ብቻ ይሆናል፡፡

3 እጩው በምርጫ ካሸነፈ፣ አሸናፊው ሰው በምርጫ ወቅት በፈፀመው ወንጀል የሚጠየቀው በሚመለከተው ምክር ቤት የሕግ ከለላው ሲነሳ ብቻ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ትመርጣለች!

‎መልካም የጥሞና ጊዜ ይሁን!!‎የጥሞና ጊዜ ነገ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ይጀምራል!‎የምርጫ ስነ- ምግባር ህግን በመጠበቅ ሀላፊነታችንን እንወጣ!!
27/05/2026

‎መልካም የጥሞና ጊዜ ይሁን!!
‎የጥሞና ጊዜ ነገ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ይጀምራል!
‎የምርጫ ስነ- ምግባር ህግን በመጠበቅ ሀላፊነታችንን እንወጣ!!

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የድምፅ መስጫ ቀንን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የ7ኛው ጠቅ...
27/05/2026

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የድምፅ መስጫ ቀንን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ እንዲከናወን መወሠኑ ይታወቃል።

በዚህም መሠረት በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ በዕለቱ ድምፃቸውን ለመስጠት ይችሉ ዘንድ እና የደምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር ይከናወን ዘንድ ቦርዱ የሚከተሉት ተግባራዊ እንዲሆኑ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/ 2011 አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታ መሠረት ለመንግሥታዊ እና ለማንኛውም መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ያሳውቃል።

በዚህም መሠረት:-

- ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ፣

- ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በፌዴራል እና በክልሎች የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ዝግ እንዲያደርጉ እያሳወቀ፤

- የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ የሚያከናውኑ ሲሆን፤ የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም።

- የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም፤ ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና ዕቅዶችን እንዳይይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ቦርዱ ያበረታታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም.

በጥሞና ጊዜ (ለምርጫው 4 ቀን ስቀር) በጥብቅ የተከለከሉ ተግባራት!ለሰላማዊ ምርጫ የሁሉም ሰው ትብብር ወሳኝ ነው!
26/05/2026

በጥሞና ጊዜ (ለምርጫው 4 ቀን ስቀር) በጥብቅ የተከለከሉ ተግባራት!
ለሰላማዊ ምርጫ የሁሉም ሰው ትብብር ወሳኝ ነው!

ወጣቶች ለሀገር ግንባታ የበኩላችንን እንወጣ!8 ቀን ቀረው እንዘጋጅ!
24/05/2026

ወጣቶች ለሀገር ግንባታ የበኩላችንን እንወጣ!
8 ቀን ቀረው እንዘጋጅ!

ምርጫን ማወክና ለማወክ መሞከር የሚያስከትለው የሕግ ተጠያቂነት…አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምርጫን ማወክና ለማወክ መሞከር፣ በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ወይም በምርጫ አስፈ...
05/05/2026

ምርጫን ማወክና ለማወክ መሞከር የሚያስከትለው የሕግ ተጠያቂነት…

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምርጫን ማወክና ለማወክ መሞከር፣ በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ወይም በምርጫ አስፈፃሚዎች ገለልተኝነት ላይ ጣልቃ ለመግባት መሞከር፣ መደለያ መስጠት ወይም ለመስጠት መሞከር እንዲሁም የምርጫ ሚስጢራዊነትን መጣስ በሕግ ተጠያቂነትን ያስከትላል።

የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና ይህን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር 1394/2017 አንቀጽ 157፣ 158 እና 159 የክልከላዎችን፣ ክልከላዎችን ለመጣስ መሞከር ወይም መጣስ የሚያስከትለውን የወንጀል የተጠያቂነት ዝርዝር ተግባር በግልጽ ተቀምጧል።

በዚህም መሰረት የፖለቲካ ፓርቲን ዓላማ በኃይል ወይም በማስፈራራት ለማስረፅ ማንኛውንም ሰው ወይም ቡድን ማደራጀት፣ ሰዎችን በግድ መመልመል እንዲሁም ለዚሁ ድርጊት እርዳታ ማድረግም ሆነ መተባባር የተከለከለና አግባብ ባለው ሕግ የሚያስቀጣ ተግባር ነው።

በዋናነት ከምርጫ ቦርድ ፈቃድ ውጪ የምርጫ ሰነዶችና ቁሳቁሶችን ማተም፣ ማባዛት፣ መፈብረክ፣ መያዝ፣ በድምፅ መስጫ ዕለት በድምፅ መስጫ ጣቢያ አካባቢ ድምፅ ከመስጠት ወይም የተሰጠን ሕጋዊ ተግባር ከማከናወን ውጪ ሌላ ማንኛውንም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ የተከለከለ ነው።

እንዲሁም ባልተገባ ወይም በተከለከለ ጊዜ የምርጫን ውጤት ማተም ወይም ማዛባት ከ80 ሺህ ብር እስከ 100 ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እና በእስራት ደግሞ ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት የሚያስቀጣ መሆኑ በወንጀል ሕጉ ተመላክቷል።

በተጨማሪም ምርጫን ለማወክ ወይም እንዳይካሄድ ወይም በምርጫው ሂደት ላይ ጫና ለመፍጠር በማሰብ ጥላቻን ወይም ፍርሀትን የሚቀሰቅስ ወይም በምርጫው ውጤት ላይ ጫና የሚፈጥር የሐሰት መረጃ አሳትሞ ማሰራጨት ወይም ለማሰራጨት መሞከር በገንዘብና በእስራት ያስቀጣል።

ይህ ቅጣትም ከ30 ሺህ እስከ 50 ሺህ የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እና ከስድስት ወር በማያንስ፣ ከአንድ ዓመት በማይበልጥ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው።

የምርጫ ዋና አስፈፃሚ ወይም የቦርዱ ሰራተኛ ስልጣኑን ወይም ተግባሩንና ኃላፊነቱን በሚያከናውንበት ወቅት ሆነ ብሎ እንቅፋት መሆን ወይም ማደናቀፍ፣ የቦርዱ የስብሰባ ሂደት ሆነ ብሎ ማቋረጥ ወይም በእነዚሁ ቦታዎች በማንኛውም ሁኔታ ያልተገባ ተግባር መፈፀም ተመሳሳይ ቅጣት የሚያሰጥ ወንጀል ነው።

ቦርዱ በሚሰጠው ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ ላይ ተገቢ ያልሆነ ተፅዕኖ ለማሳደር የኃይል ተግባር መፈፀም ከብር 30 ሺህ የገንዘብ መቀጮ ወይም ከአንድ ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ያስቀጣል።

ሌላው በምርጫ ጅማሮ ውጤት እስከሚገለፅበት ቀን ድረስ የማንኛውንም እጩ ተወዳዳሪ የምርጫ ማስታወቂያን ማበላሸት፣ ማስወገድ ወይም መቅደድ ከአንድ ዓመት በማይበልጥ እስራት ወይም በመቀጮ እንደሚያስቀጣ ተመላክቷል፡፡

Address

Ligaba
S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Zone Youth Association/ ወላይታ ዞን ወጣቶች ማህበር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Wolaita Zone Youth Association/ ወላይታ ዞን ወጣቶች ማህበር:

Shortcuts

Share