Wolaita Sodo Agricultural College

Wolaita Sodo Agricultural College Home of Agricultural Vocations!
(1)

Soddo ATVET College
Situated in Southern Nations Nationalities and People’s Region (SNNPR)
Established in 1972 by Wolaita Agricultural Development Unit (WADU)

Soddo became an ATVET college in 2002

: Crop Production, Livestock Production, Natural Resources, Small Scale Irrigation, Artificial Insemination, & Basic and Supportive Sciences Department By Regular as we

ll as Continues Education Program (CEP)



Striving to see farmers/pastoralists who can contribute to agriculture led industry development apart from food self-sufficiency in the region through strong vocational education and training.



Producing well trained experts in terms of theoretical & practical aspects in modern agriculture, sugar cane crop production, and sugar and ethanol production in order to boost production and productivity, conserve and properly utilize natural resources, produce quality products intended for the industry and for the export market thereby improving the livelihoods of farmers/pastoralists.

ከኢፌዴሪ ትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን የተውጣጣ ልዑክ በኮሌጃችን የግንዛቤ ማሰጨበጫ ሥልጠና እየሰጠ ነው::ወ/ሶ/ግ/ኮ  ነሐሴ 12/2018 ዓ/ምከኢፌዴሪ ትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን የተው...
18/08/2026

ከኢፌዴሪ ትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን የተውጣጣ ልዑክ በኮሌጃችን የግንዛቤ ማሰጨበጫ ሥልጠና እየሰጠ ነው::

ወ/ሶ/ግ/ኮ ነሐሴ 12/2018 ዓ/ም

ከኢፌዴሪ ትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን የተውጣጣ ልዑክ በኮሌጃችን በመገኘት የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ሁለተኛ ዲግሪና ሦስተኛ ዲግሪ መርሐ-ግብሮች ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት መገምገሚያ መስፈርቶችን በተመለከተ ለሚመለከታቸው የሥራ ክፍል ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሌጃችን ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ዲን አቶ ታሪኩ ጨመረ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ መርሐ-ግብር ትምህርት መጀመር ለተቋማችንና ለባለድርሻ አካላት የረጅም ጊዜ ጥያቄ ሆኖ መቆየቱን አውስተው፤ መርሐ-ግብሩን ለመጀመር የሚያስችሉ የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቀው በመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሳቸውንም ገልጸዋል።

አቶ ታሪኩ አክለውም፣ ወቅቱ ለተቋማችን ወርቃማ መሆኑን በመጠቆም፣ ሠልጣኞች ሥልጠናውን በትኩረት በመከታተል ለህደቱ ስኬታማነት ድርሻቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል።

በባለሥልጣኑ የከፍተኛ ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ ባለሙያ አቶ መንግሥቱ ጠና እንደገለጹት፣ ባለሥልጣኑ “ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል በትምህርት ጥራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

ሥልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ የተገለጸ ሲሆን፣ ሥልጠናው ከተጠናቀቀ በኋላ ልዑኩ የመጀመሪያ ዲግሪ መርሐ-ግብር ለመጀመር ከሚያስችሉ መስፈርቶች አንፃር የኮሌጁ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እንደሚገመገሙ ተጠቅሷል።

በግምገማውም ተቋማችን በመርሐ-ግብሩ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችሉ የሰነድ ዝግጅቶችንና ግብዓቶችን በመስክ ምልከታ እንደሚገመግም ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ ከባለሥልጣኑ የተውጣጡ አሰልጣኞች፣ የኮሌጃችን ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ዲን አቶ ታሪኩ ጨመረ፣ የኮሌጃችን አስተዳደርና ልማት ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ዲን አቶ አበባየሁ መንኤና ሌሎች አካዳሚክ ኮሚሽን አባላትና የመጀመሪያ ዲግሪ መርሐ-ግብር የቅድመ-ዝግጅት ሥራ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና ሠራተኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በ2018 በጀት ዓመት ክንውን ሪፖርትና የ2019 መነሻ ዕቅድ ላይ ውይይትና ግምገማ ተካሄደወ/ሶ/ግ/ኮ ነሐሴ 07/2018 ዓ/ምየኮሌጃችን አመራሮች ከመምህራን እና አስተዳደር ሠራተኞች ጋር በ...
13/08/2026

በ2018 በጀት ዓመት ክንውን ሪፖርትና የ2019 መነሻ ዕቅድ ላይ ውይይትና ግምገማ ተካሄደ

ወ/ሶ/ግ/ኮ ነሐሴ 07/2018 ዓ/ም
የኮሌጃችን አመራሮች ከመምህራን እና አስተዳደር ሠራተኞች ጋር በ2018 በጀት ዓመት ክንውን ሪፖርትና 2019 መነሻ ዕቅድ ላይ ውይይትና ግምገማ መድረክ አካሂደዋል።

የኮሌጃችን ዲን ዶ/ር አሉላ ታፈሰ መድረኩን በከፈቱበት ወቅት እንደገለጹት፣ መድረኩ በ2018 በጀት ዓመት የተመዘገቡ ጠንካራ ነገሮችን ለማስቀጠልና ክፍተቶችን ለመሙላት በቀጣዩ 2019 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ያለመ ነው።

በመድረኩ የኮሌጃችን ልማት ዕቅድ ዝግጅት፣ክትትልና ግምገማ ቡድን መሪ አቶ ፋንቱ ወ/መስቀል በ2018 በጀት ዓመት በትምህርትና ሥልጠና፣አስተዳደርና ልማት ዘርፎች ታቅደው በተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ ባጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አቶ ፋንቱ ቀጥለውም፣ በ2019 በጀት ዓመት መነሻ ዕቅድ ላይ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆኑ፣ በገለጻቸውም በበጀት ዓመቱ ትኩረት በሚደረግባቸው ጉዳዮች፣ በትምህርትና ሥልጠና፣አስተዳደርና ልማት ዘርፎች ስር የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት እንዲሁም ክትትልና ድጋፍ ዘዴዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የቀረበውን ሪፖርትንና ዕቅድን መነሻ በማድረግ አስተያየታቸውን የሰጡ የኮሌጃችን መምህራንንና አስተዳደር ሠራተኞች ፣በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡንና የተዘመገበው ውጤት ሁሉም ሠራተኛ በመሳተፍና ተቀናጅቶ በመስራት የተገኘ መሆኑ አመላክተው፤ለተመዘገበው ውጤት የድርሻቸውን ያበረከቱ አመራሮችንና ሠራተኞችን አመስግነዋል።

የኮሌጃችን ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ኃላፊና ም/ዲን አቶ ታሪኩ በመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት፣ በ2018 የመማር ማስተማር ሥራ፣የምርምርና ማህበረሰብ አልግሎት ሥራዎች አመርቂ ከመሆናቸውም በላይ የሙያ ብቃት ምዘና ከወሰዱ ተማሪዎች 81% ብቁ መሆናቸውን አመልክተዋል ::

በ2019 በጀት ዓመት የገበያ ፍላጎትን መሠረት በማድረግ በሰው ሠራሽ አዳቃይ (Artificial Insemination) እና በሜካናይዜሽን ሙያ ዘርፎች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የኮሌጃችንን ሞዴል የማህበረሰብ ትምህርት እንደስሙ ሞዴል ለማድረግ በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን እና እየተሰሩ እንደሚገኙ በማብራራት በ2018 በጀት ዓመት 6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የተፈተኑ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማለፍ ለዚህ ጥሩ ማሳያ መሆኑን አቶ ታሪኩ አመላክተዋል።

የኮሌጃችን አስተዳደርና ልማት ዘርፍ ኃላፊና ም/ዲን አቶ አበባየሁ ሙንኤ በበኩላቸው፣ በ2018 በጀት ዓመት በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸው፤ ይህም በአመራርና በሠራተኞች የጋራ ጥረትና ተቀናጅቶ በመሥራት የተገኘ መሆኑን በመግለጽ ለተመዘገቡ ስኬቶች የራሳቸውን ድርሻ ላበረከቱ አካላት ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

በ2018 በጀት ዓመት ምቹ፣ ሰላማዊና ውጤታማ የሥራ ሁኔታ ለመፍጠር በተቋሙ የተለያዩ ሥራዎች መከናወናቸውን ያስታወሱት አቶ አበባየሁ፣ እነዚህን ተግባራት በ2019 በጀት ዓመትም በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

የኮሌጃችን ዲን ዶ/ር አሉላ ታፈሰ መድረኩን ሲያጠቃልሉ ፣ በ2018 በጀት ዓመት ከተለያዩ ተቋማት ጋር ውጤታማ የሥራ ግንኙነትና ትስስር ለመፍጠር የተሰሩ ሥራዎች አመርቂ ውጤት ማስገኘታቸውን በመግለጽ በዚህም አዳዲስ የጸደቁና በሂደት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

በ2019 በጀት ዓመት አዲስ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐ-ግብር ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን አብራርተዋል።

ኮሌጃችን በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት በጥቂቱ ስናስታውስ፦ኮሌጃችን በ2018 ትምህርት ዘመን ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በመደበኛና ተከታታይ መርሐ-ግብር ተማ...
12/08/2026

ኮሌጃችን በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት በጥቂቱ ስናስታውስ፦

ኮሌጃችን በ2018 ትምህርት ዘመን ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በመደበኛና ተከታታይ መርሐ-ግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ ከማስተማር ባሻገር፣ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመዋዋል 215 የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማር ሥራ አከናውኗል።

በትምህርት ዘመኑም ከክልሉ ግብርና ቢሮ ጋር በመተባበር ለ1,400 ለሚያህሉ የቀበሌ ሰብል ልማት፣ ተፈጥሮ ሀብት አያያዝ፣ እንስሳት እርባታና እንስሳት ጤና ባለሙያዎች የተግባር ተኮር የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ሰጥቷል።

በተጨማሪም፣ ከወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ ጋር በመተባበር በዞኑ ለሚገኙ 500 የሚሆኑ የቀበሌ ሰብል ልማት፣ ተፈጥሮ ሀብት አያያዝ፣ እንስሳት እርባታና እንስሳት ጤና ባለሙያዎች የተግባር ተኮር የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጥቷል።

በበጀት ዓመቱ ከመማር ማስተማር ሥራ ጎን ለጎን በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት መስክ ተቋሙን ለሥራ ምቹና ማራኪ ለማድረግ የግሪነሪና ላንድስኬፕ ሥራዎችን፣ የአፈር ለምነትን ለማሻሻል የቨርሚ ኮምፖስት ሥራን፣ ለአረንጓዴ አሻራና ለምግብነት የሚውሉ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች የማፍላት ሥራን እንዲሁም ለሌማት ትሩፋት ስኬታማነት አስተዋጽኦ ለማበርከት የእንስሳት ዝርያን ለማሻሻል የሰው ሰራሽ አዳቃይ ማዕከል የማቋቋም ፕሮጀክቶችን ቀርጾ በመተግበር ሰፊ ሥራዎችን ሰርቷል።

በበጀት ዓመቱ የግቢውን አጥር የመጠገን፣ የማስዋብና የተማሪዎች መጸዳጃ ግንባታ፣መምህራን መኖሪያና ሌሎች ካፒታል ፕሮጀክቶች የተሻለ አፈጻጸም አስመዝግቧል።

በበጀት ዓመቱ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ውጤታማ የሆነ የሥራ ግንኙነት የመፍጠር ሥራ ተሰርቷል። በዚህም ኮሌጃችን አመርቂ የሆነ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል።

ኮሌጃችን ተማሪዎችን በሰብል ልማት፣ እንስሳት እርባታ፣ ተፈጥሮ ሀብት አያያዝ፣ እንስሳት ጤና፣ መስኖና ፍሳሽ እንዲሁም ሕብረት ሥራ ሂሳብ አያያዝና ኦዲቲንግ ተቀብሎ ከማስተማር ባሻገር፣ የመጀመሪያ ድግሪ መርሐ-ግብር ማስተማር ለመጀመር ሰፊ የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን እያጠናቀቀ ይገኛል።

በበጀት ዓመቱ ከመማር ማስተማር ሥራ ጎን ለጎን የተግባር ትምህርትን ውጤታማ ለማድረግ፣ የውስጥ ገቢ ምንጮችን ለማጎልበት፣ ለሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭና ለአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ውጤታማነት አስተዋጽኦ ለማበርከት የተለያዩ የግብርና ልማት ሥራዎችን በማከናወን አመርቂ ውጤቶችን ያስመዘገበበት ዓመት ነበር።

ከነዚህ የልማት ሥራዎች መካከል የሙዝ ልማት፣ የቡና ልማት ፣ የጓሮ አትክልት ልማት፣ የቅባት እህል ልማት፣ የጥራጥሬ ሰብሎች፣ የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የአቮካዶና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን የማፍላትና የማምረት ሥራ እንዲሁም የወተት ላሞች ፣የዶሮ፣የአሳና አሳማ እርባታ ልማት ሥራዎች በዋናነት ይጠቀሳሉ።

በአዲሱ የ2019 በጀት ዓመትም በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት፣ በግብርናና በመሠረተ-ልማት ዘርፎች የተጀመሩና የተከናወኑ ሥራዎችን በማጠናከርና በማስፋት፣ በተቋሙ የተያዙ ዕቅዶችን በተገቢው ሁኔታ በመፈጸም የበለጠ ውጤታማ የሆነ የሥራ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል።

በልማት ማህበሩ አስተባባሪነት ከዳሞት ጋሌና ዳሞት ፑላሳ ወረዳዎች የተውጣጡ አርሶአደሮች በኮሌጃችን የልምድ ልውውጥና መስክ-ምልከታ አካሄዱወ/ሶ/ግ/ኮ ነሐሴ 02/2018 ዓ/ምበጠረጴዛ ልማት ...
08/08/2026

በልማት ማህበሩ አስተባባሪነት ከዳሞት ጋሌና ዳሞት ፑላሳ ወረዳዎች የተውጣጡ አርሶአደሮች በኮሌጃችን የልምድ ልውውጥና መስክ-ምልከታ አካሄዱ

ወ/ሶ/ግ/ኮ ነሐሴ 02/2018 ዓ/ም
በጠረጴዛ ልማት ማህበር አስተባባሪነት ከዳሞት ጋሌና ዳሞት ፑላሳ ወረዳዎች የተውጣጡ አርሶአደሮች ወደ ኮሌጃችን በመምጣት የልምድ ልውውጥና መስክ-ምልከታ አካሄደዋል።

አርሶአደሮቹ በቆይታቸው የዶሮና የወተት ላሞች እርባታን፣ ቨርሚ ኮምፖስትን፣ ሽቅብ ግብርና፣ የጓሮ አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችን ተዘዋውረው ከመመልከት በተጨማሪ ከዘርፉ ባለሙያዎች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

በማጠቃለያው ላይ በልማት ማህበሩ የምግብ ዋስትና ማሻሻያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ መሪሁን መንግስቱ፣ አርሶአደሮቹ በልምድ ልውውጡና በመስክ-ምልከታው ያገኙትን ዕውቀት በተግባር ላይ ሊያውሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የኮሌጃችን ተከታታይ ትምህርት መርሐ-ግብር ማስተባበሪያ ኃላፊ፣ የትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ኃላፊ እና የምክትል ዲን ተወካይ መምህር ሂርቦ ሻንቆ፣ ማህበሩ ወደ ኮሌጃችን አርሶአደሮችን በመጋበዝ የልምድ ልውውጥና መስክ-ምልከታ እንዲያደርጉ ዕድል ስለፈጠረ በማመስገን፣ ከማህበሩ ጋር በትብብር መስራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

መምህር ሂርቦ አክለውም፣ አርሶአደሮቹ የኮሌጃችን አምባሳደር በመሆን ያገኙትን ዕውቀትና ልምድ በራሳቸው ተግባራዊ ከማድረግ ባለፈ ለሌሎች አርሶአደሮች ማካፈል እንዳለባቸው በማሳሰብ፣ ኮሌጃችንም አርሶአደሮችን በሙያና በግብዓት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኮሌጃችን ሰብል ልማት ትምህርት ደረጃ ማሻሻያ መርሐ-ግብር ተማሪዎች በሽቅብ ግብርና ቴክኖሎጂ ላይ የተግባርና የንድፈ ሐሳብ ሥልጠና ወሰዱወ/ሶ/ግ/ኮ ነሐሴ 01/2018 ዓ/ምየኮሌጃችን ሰብል...
07/08/2026

የኮሌጃችን ሰብል ልማት ትምህርት ደረጃ ማሻሻያ መርሐ-ግብር ተማሪዎች በሽቅብ ግብርና ቴክኖሎጂ ላይ የተግባርና የንድፈ ሐሳብ ሥልጠና ወሰዱ

ወ/ሶ/ግ/ኮ ነሐሴ 01/2018 ዓ/ም

የኮሌጃችን ሰብል ልማት ትምህርት ደረጃ ማሻሻያ መርሐ-ግብር ተማሪዎች በሽቅብ ግብርና (Vertical Farming) ቴክኖሎጂ ላይ የተግባርና የንድፈ ሐሳብ ሥልጠና ወስደዋል።

ሥልጠናውን የሰጡት የሽቅብ ግብርና ቴክኖሎጂ ፕሮጀክት አስተባባሪ መ/ር ደበበ ደጉ፣ ለተማሪዎቹ ከአፈር ዝግጅት ጀምሮ እስከ ችግኝ ተከላ ድረስ ባሉ የሽቅብ ግብርና ሥራ ሂደቶች ላይ የተግባርና የንድፈ ሐሳብ ሥልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል።

ይህ ሥልጠና ተማሪዎቹ በዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎች ላይ ያላቸውን እውቀትና ክህሎት በማሳደግ ሙያቸውን እንዲያበለፅጉ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

ከኤስ ኤን ቪ ሆርቲ ላይፍ ፕሮጀክት የተውጣጣ ልዑክ ወደ ኮሌጃችን በመምጣት ምክክርና የመስክ ምልከታ አካሄደ።ወ/ሶ/ግ/ኮ ነሐሴ 01/2018 ዓ.ምከኤስ ኤን ቪ ሆርቲ ላይፍ ፕሮጀክት (SNV ...
07/08/2026

ከኤስ ኤን ቪ ሆርቲ ላይፍ ፕሮጀክት የተውጣጣ ልዑክ ወደ ኮሌጃችን በመምጣት ምክክርና የመስክ ምልከታ አካሄደ።

ወ/ሶ/ግ/ኮ ነሐሴ 01/2018 ዓ.ም
ከኤስ ኤን ቪ ሆርቲ ላይፍ ፕሮጀክት (SNV Horti-LIFE Project) የተውጣጣ ልዑክ ወደ ኮሌጃችን በመምጣት በጋራ ለመሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር እና የመስክ ምልከታ አካሂዷል።

ፕሮጀክቱ ከኮሌጃችን ጋር በአማራጭ ኃይል አቅርቦት ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ተቀናጅቶ በመሥራት ኮሌጃችንን የሥልጠና ማዕከል በማድረግ የተግባር ትምህርትን ውጤታማ ለማድረግና የአካባቢው ማህበረሰብ አማራጭ የኃይል ምንጮችን በስፋት እንዲጠቀም የቴክኒክና የመሠረተ ልማት ድጋፍ ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ልዑኩ ገልጿል።

በተለይም የፀሐይ ታዳሽ ኃይልን በመጠቀም የመስኖ ውሃን ወደ ማሳ ለማሰራጨት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች፣ ባዮጋዝ (Biogas) እና መሰል ቴክኖሎጂዎች ላይ በጋራ ለመሥራት መታቀዱንም ተናግሯል።

ልዑኩ በቆይታው የመስኖና ፍሳሽ ላቦራቶሪ፣ የቨርሚ ኮምፖስት ማምረቻ፣ ባዮጋዝ፣ የካልተ መስኖ ግድብ ናይት ስቶሬጅ እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን በመዘዋወር ተመልክቷል።

የኮሌጃችን አመራሮች ፕሮጀክቱ እስካሁን ድረስ ለኮሌጃችን ላደረገው አስተዋጽኦ በማመስገን፣ በቀጣዩ የትምህርት ዘመን በፕሮጄክቱ ታቅደው እየተሰሩ ባሉ የአማራጭ ኃይል አቅርቦትና ሌሎች ዘርፎች ላይ በጋራ በመሥራት የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥና የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግሮች በመፍታት አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገብ እንደሚቻል አረጋግጠዋል።

ኮሌጃችን ከክልሉ ምርጥ ዘር ድርጅት ጋር በመቀናጀት በማሳው ያባዛውን ምርጥ የጤፍና የቦሎቄ ጥሬ ዘር የማሸግ ሥራ አጠናቀቀ።ወ/ሶ/ግ/ኮ ሀምሌ 30/2018 ዓ/ምኮሌጃችን በተጠናቀቀው 2018 ...
06/08/2026

ኮሌጃችን ከክልሉ ምርጥ ዘር ድርጅት ጋር በመቀናጀት በማሳው ያባዛውን ምርጥ የጤፍና የቦሎቄ ጥሬ ዘር የማሸግ ሥራ አጠናቀቀ።

ወ/ሶ/ግ/ኮ ሀምሌ 30/2018 ዓ/ም
ኮሌጃችን በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ውጤታማ የሆነ የሥራ ግንኙነት በመፍጠር አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችሏል።

ከእነዚህ መካከል ከደቡብ ኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት ጋር የተደረገው የሥራ ግንኙነት ለአብነት የሚጠቀስ ነው።
በበጀት ዓመቱ ኮሌጃችን ከድርጅቱ ጋር በመቀናጀት "ሐዋሳ ዱሜ" የተሰኘ የተሻሻለ የቦሎቄ ዝርያ እና "ክሮስ-37" የተሰኘ የተሻሻለ የጤፍ ዝርያ የብዜት ሥራ አከናውኗል።

በአሁኑ ወቅት የተባዛውን የቦሎቄና የጤፍ ጥሬ ዘር የማሸግ ሥራ ተጠናቋል። ይህ ጥራት ያለው ጥሬ ዘር በክልሉ ለሚገኙ አርሶ አደሮች ተሰራጭቶ የሰብል ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

በያዝነው 2019 በጀት ዓመትም መሰል የሥራ ግንኙነቶችን አጠናክሮና አስፍቶ ለማስቀጠል ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል።

በትምህርት ዘመኑ 6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የተፈተኑ የኮሌጃችን ሞዴል ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ሙሉ በሙሉ (100%) ወደ 7ኛ ክፍል ማለፋቸውን ትምህርት ...
05/08/2026

በትምህርት ዘመኑ 6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የተፈተኑ የኮሌጃችን ሞዴል ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ሙሉ በሙሉ (100%) ወደ 7ኛ ክፍል ማለፋቸውን ትምህርት ቤቱ አስታወቀ።

ወ/ሶ/ግ/ኮ ሀምሌ 29/2018 ዓ/ም

የኮሌጃችን ሞዴል ማህበረሰብ ትምህርት ቤት የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች በ2018 ትምህርት ዘመን በተሰጠው ክልላዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ሙሉ በሙሉ (100%) ወደ 7ኛ ክፍል ማለፋቸውን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ አለሙ ዳና አስታውቀዋል።

አቶ አለሙ አክለውም፣ ይህ ስኬት የትምህርት ቤቱ አመራር ለትምህርት ቤቱ መሻሻል በሰጠው ትኩረትና የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል በወሰደው ቁርጠኝነት የተገኘ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣዩ ትምህርት ዘመንም የትምህርት ቤቱን ደረጃ በማሻሻል ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዕቅድ ተይዞ የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁን አቶ ዓለሙ አስታውቀዋል።

በመጨረሻም፣ አቶ ዓለሙ ለተማሪዎቹ፣ ለተማሪ ወላጆች ለትምህርት ቤቱ መምህራንና ሠራተኞች እንዲሁም ለኮሌጁ ማህበረሰብ በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ኮሌጃችን በኤስ.ኤን.ቪ ሆርቲ-ላይፍ ፕሮጀክት (SNV Horti-LIFE project ) አፈጻጸም እና በኤስ.ኤን.ቪ ግሪን ግሮውዝ ፕሮጀክት ዕቅድ በሚቀርበብት የምክክር መድረክ ላይ እየተሳተፈ...
05/08/2026

ኮሌጃችን በኤስ.ኤን.ቪ ሆርቲ-ላይፍ ፕሮጀክት (SNV Horti-LIFE project ) አፈጻጸም እና በኤስ.ኤን.ቪ ግሪን ግሮውዝ ፕሮጀክት ዕቅድ በሚቀርበብት የምክክር መድረክ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

ወ/ሶ/ግ/ኮ ሀምሌ 29/2018 ዓ/ም
በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ባለው ኮሌጃችን ከበኤስ.ኤን.ቪ ሆርቲ-ላይፍ ፕሮጀክት (SNV Horti-LIFE project ) ጋር የጋራ ፕሮጀክት አፈጻጸም እና በቀጣይ የሚተገበር ኤስ.ኤን.ቪ ግሪን ግሮውዝ ፕሮጀክት ዕቅድ ላይ የምክክር መድረክ ላይ ኮሌጃችን በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል።

በኤስ.ኤን.ቪ ሆርቲ-ላይፍ አስተባባሪነት የተዘጋጀው ይህ መድረክ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ የኮሌጅ ኃላፊዎችን በማገናኘት ዋና ዋና አፈጻጸሞችን ለመገምገም፣ መልካም ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ እና የወደፊት ስትራቴጂካዊ ግቦችን ለማቀድ ያለመ ነው።

✨ ከስብሰባው ዋና ዋና ነጥቦች:
ስኬቶችን ማቅረብ፦ በ2018 ዓ.ም (2026) በተግባራዊ የሆርቲካልቸር ትምህርት፣ በተማሪዎች የመለማመጃ ማሳዎች (Student plots)፣ በቤት ውስጥ አትክልት ልማት እና በኮሌጅ ኤክስቴንሽን ስራዎቻችን ያከናወናቸውን ዋና ዋና ስኬቶች ቀርበዋል።

የወደፊት እቅድ፦ የ2019 ዓ.ም (2027) የትኩረት አቅጣጫዎችን እና የተግባር ልምምድ ማሰልጠኛ ቁሳቁሶችንና አጫጭር ስልጠናዎችን የበለጠ ለማስፋፋት የሚያስችሉ እቅዶች ተነድፈዋል።

የአቅም ግንባታ ስልጠና፦ በፕሮጀክት ዲዛይን፣ በክትትልና ግምገማ፣ በበጀት አስተዳደር እና በፕሮፖዛል ዝግጅት ላይ ያተኮረ ተግባራዊ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ስልጠና በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ለኮሌጃችን ተማሪዎች ተግባራዊ የግብርና ትምህርትን ለማስፋፋት፣ አረንጓዴ እድገትንና የግብርና ቴክኖሎጂ ፈጠራን ለማፋጠን ኤስ.ኤን.ቪ ሆርቲ-ላይፍ እና የልማት አጋሮቻችን ለሚያደርጉልን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና እያቀረብን የልማት ትብብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እናረጋግጣለን::

በመሠረታዊ የሥራ ሂደት ማሻሻያ (BPR) ክለሳ ጥናት ዝግጅት በሚመለከት ከክልሉ ግብርና ቢሮ ተጠሪ ማዕከላትና ተቋማት ለተውጣጡ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና የቢሮው የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጻ ተደረ...
04/08/2026

በመሠረታዊ የሥራ ሂደት ማሻሻያ (BPR) ክለሳ ጥናት ዝግጅት በሚመለከት ከክልሉ ግብርና ቢሮ ተጠሪ ማዕከላትና ተቋማት ለተውጣጡ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና የቢሮው የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጻ ተደረገ።

ወ/ሶ/ግ/ኮ ሀምሌ 28/2018 ዓ.ም
በመሠረታዊ የሥራ ሂደት ማሻሻያ (Business Process Reengineering–BPR) ክለሳ ጥናት ዝግጅት ዙሪያ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ተጠሪ ማዕከላትና ተቋማት ለተውጣጡ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና ለቢሮው የዘርፉ ባለሙያዎች በክልሉ ግብርና ቢሮ የተዘጋጀ ገለጻ በኮሌጃችን ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኮሌጃችን አስተዳደርና ልማት ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ዲንና የኮሌጁ ዲን ተወካይ ፣ እንድሁም የቢሮው አስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ሃላፊ ተወካይ አቶ አበባየሁ ሙንኤ፣ ጥናቱ ተቋማት ሥራቸውን በተሻለ ውጤታማነት እንዲያከናውኑ ለማስቻልና ሥራን ከሠራተኛ ጋር በተገቢው ሁኔታ ለማጣጣም ያለመ መሆኑን ገልጸው፣ መድረኩን ላዘጋጀው የክልሉ ግብርና ቢሮ ምስጋና አቅርበዋል።

ተሳታፊዎቹ ጥናቱን በአጭር ጊዜና በጥራት ለማጠናቀቅ የተጣለባቸውን ታሪካዊ ኃላፊነት በከፍተኛ የሥራ ዲስፕሊን መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ጥናቱን በሚመለከት ገለጻ የሰጡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሪፎርም አማካሪ አቶ ፀጋዬ ሳሙኤል፣ በቀድሞው ደ/ብ/ብ/ሕ/ክ የተዘጋጀው መሠረታዊ የሥራ ሂደት ማሻሻያ ጥናት የአዲሱን ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነባራዊ ሁኔታና መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዮች መሠረት በማድረግ መከለስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ሥራው መጀመሩን ገልጸዋል።

ተሳታፊዎችም የጥናቱን ክለሳ በሚያከናውኑበት ወቅት ለተቋማቸው በአዋጅና ደንብ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት መነሻ በማድረግ ሊሠሩ እንደሚገባ አቶ ፀጋዬ አስገንዝበዋል።

የክልልሉ ግብርና ቢሮ ሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አልማዝ ታደሰ፣ ጥናቱ በቢሮው ደረጃ ሲካሄድ መቆየቱና መጠናቀቁን በመግለጽ ወደ ተጠሪ ተቋማትና ማዕከላት መውረዱን አስታውቀዋል።

Address

Woliata S**o
S**o
120

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Sodo Agricultural College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share