ወላይታዎች ለወላይታ Wolayitawoch lewolyiata

ወላይታዎች ለወላይታ Wolayitawoch lewolyiata ለአድስ ዓመት አቅሜ ደካማ እናት አባቶችን መርዳት የምትፈልጉ
(2)

በካራት ከተማ ለምለም ሰፈር የተከሰተ ድንገተኛ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰበኮንሶ ዞን ካራት ከተማ ለምለም ሰፈር ዛሬ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ የተከሰተ ድንገተኛ ...
30/08/2026

በካራት ከተማ ለምለም ሰፈር የተከሰተ ድንገተኛ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ

በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ ለምለም ሰፈር ዛሬ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ የተከሰተ ድንገተኛ የእሳት አደጋ በሱቆች፣ በሆቴሎችና በመኖሪያ ቤቶች ላይ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት አድርሷል።

በአደጋው ከጅንካ፣ ያቤሎ፣ አርባምንጭና ከሌሎች አጎራባች ከተሞች የሚመላለሱ መንገደኞችን በየዕለቱ ያስተናግድ የነበረው ማሙሽ ደጉ ሆቴል ከባድ ጉዳት ደርሶበታል።

እሳቱ የተነሳው ከቀኑ 4፡00 ሰዓት አካባቢ እና ዕለቱም ዕሁድ በመሆኑ፣ አብዛኛው ሰው ወደ መኖሪያ ቤቱ በመሄዱ የእሳቱን መቆጣጠርና ማጥፋት ሥራ ፈታኝ እንዲሆን አድርጎታል።

የካራት ከተማ ከንቲባ አቶ ጋሻው ኩሲያ እንደገለጹት፣ ጠንካራ የእሳት ማጥፋት ልምድ ያለው የኮንሶ ሕዝብ ከከተማው ማዕከልና ከአቅራቢያው ሰፈሮች በመረባረብ በእሳቱ ሊደርስ የነበረውን ሰፊ ጉዳት መቀነስ ችሏል።

ከንቲባው አክለውም፣ እሳቱን ለመቆጣጠርና ለማጥፋት በከተማው የሚገኙ የፌዴራል ፖሊስና የከተማው ህብረተሰብ ያደረጉት በሙያ የታገዘ ርብርብ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው፣ በተለይም የከተማው ሕዝብ ያደረገውን ብርቱ ርብርብ አድንቀዋል።

የአደጋው መንስኤና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት መጠን በሚመለከተው አካል እየተጣራ ሲሆን፣ የተሟላ መረጃ ሲደርስ ለሕዝብ የሚቀርብ ይሆናል።

በኮንሶ ሕዝብ ዘንድ ከእሳት አደጋ መከሰት በኋላ ተጎጂዎችን በመደገፍና በመጽናናት የሚታወቀው ማኅበራዊ ባህል እንዳለ የሚታወቅ ሲሆን፣ በቀጣይም ተጎጂዎችን ለመደገፍና የደረሰባቸውን ጉዳት ለማቃለል የሚደረገው የጋራ ርብርብ እንደሚጠናከር ይጠበቃል።

ዘገባዉ የኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን ነዉ

አዶናይ ዛሬም ለበርካታ ድርጅቶች አንባሳደር መሆኑን ቀጥሏልፖፑላር  ኤሌክትሮኒክስ በአዲስ አበባ ፒያሳ  ከኤሊያና ሆቴል አጠገብ አዲስ ሾውሩም በይፋ አስመርቋል። ሾውሩሙ የተለያዩ የኤሌክትሮኒ...
30/08/2026

አዶናይ ዛሬም ለበርካታ ድርጅቶች አንባሳደር መሆኑን ቀጥሏል

ፖፑላር ኤሌክትሮኒክስ በአዲስ አበባ ፒያሳ ከኤሊያና ሆቴል አጠገብ አዲስ ሾውሩም በይፋ አስመርቋል። ሾውሩሙ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ለደንበኞች በዘመናዊ አቀራረብ ለማቅረብ የተዘጋጀ ነው።

በዚሁ ዝግጅት ላይ ወጣቱ ተፅዕኖ ፈጣሪና የTikTok ይዘት ፈጣሪ አዶናይ ብርሃኔ ለ6 ወራት የፖፑላር ኤሌክትሪክስ ብራንድ አምባሳደር እንዲሆን ስምምነት ተፈራርሟል።

በስምምነቱ መሠረት አዶናይ በዲጂታል ይዘቶች፣ በማስተዋወቂያ ዘመቻዎችና በተለያዩ የብራንዱ እንቅስቃሴዎች ከ10 ዓመታት በላይ በኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ የቆየው ፖፑላር ኤሌክትሪክስ ከአዶናይ ጋር የጀመረው አጋርነት ከወጣቱ ትውልድ ጋር ያለውን የዲጂታል ትስስር ለማጠናከር ያለውን ሰፊ አቅጣጫ ያሳያል ተብሎአል።

➡  የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጥቀሱ ብትባሉ ለሁለቱ የትኛዉን የመፅሐፍ ቅዱስ ቃል ትጠቅሱላቸዋላችሁ?
30/08/2026

➡ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጥቀሱ ብትባሉ ለሁለቱ የትኛዉን የመፅሐፍ ቅዱስ ቃል ትጠቅሱላቸዋላችሁ?

ብዙ ከታዊቂ  ሰዎች ጋር የሚመሳሰሉትን በማፈላለግ ለሚዲያ እያቀረበ ያለው ቲክታከር አዶናይ ዛሬ ደግሞ ተወዳጁን ድምፃዊ  ቴዲ አፍሮን የሚመስል ሰው ይዞ መቷል።
30/08/2026

ብዙ ከታዊቂ ሰዎች ጋር የሚመሳሰሉትን በማፈላለግ ለሚዲያ እያቀረበ ያለው ቲክታከር አዶናይ ዛሬ ደግሞ ተወዳጁን ድምፃዊ ቴዲ አፍሮን የሚመስል ሰው ይዞ መቷል።

🥊🔥 ኢትዮ ፋይት ናይት የፍልሚያ ካርዱን ይፋ አደረገ! 🔥🥊 #በሀገራችን የሚካሄደው አለም አቀፍ የፍልሚያ ውድድር “ኢትዮ ፋይት ናይት” የውድድሩን የፍልሚያ ካርድ በይፋ አስታውቋል! 🇪🇹💪በአ...
30/08/2026

🥊🔥 ኢትዮ ፋይት ናይት የፍልሚያ ካርዱን ይፋ አደረገ! 🔥🥊

#በሀገራችን የሚካሄደው አለም አቀፍ የፍልሚያ ውድድር “ኢትዮ ፋይት ናይት” የውድድሩን የፍልሚያ ካርድ በይፋ አስታውቋል! 🇪🇹💪

በአጠቃላይ በ5 የንክኪ ስፖርት ዘርፎች — MMA, Boxing, Kickboxing, Muay Thai እና Wushu Sanda — 10 አስደናቂ ፍልሚያዎች ይካሄዳሉ! 🔥

🥇 የዕለቱ ዋና ፍልሚያ – MMA
🔴 🇪🇹 ቢንያም ሽብሬ “ቢኒ”
⚔️
🔵 🇪🇹 አገረሰላም አርባ “ቦንጆ”

🥈 2ኛ ዋና ፍልሚያ – MMA
🔴 🇵🇹 ጆአዎ ፍሊፕ ኔቶ “ሚሞሴ”
⚔️
🔵 🇪🇸 ጆሴ አጉስቲን ጂሜኔዝ

🥉 3ኛ ፍልሚያ – MMA
🔴 🇦🇴 ጋርሲያ ፒንቶ “አናኮንዳ”
⚔️
🔵 🇧🇷 ጄፈርሰን ኮስታ “ሱፐር ኮኩዌ”

🥊 ቀሪ ፍልሚያዎች
🔥 ክብሮም ንጉሴ “ዘ ፕሪዴተር” 🆚 ሳሙኤል ጥበቡ “ሳሚ” — Kickboxing

🔥 አዲሱ ደሳለኝ “ዘ ቻምፕ” 🆚 ከሚል ሲራጅ “ሳቦም” — Kickboxing

🔥 ሰራዊት ፀጋ “ሞተረኛው” 🆚 ፍሬው ጮሮ — Boxing

🔥 መልካሙ ውቤ “ጎንደሬው” 🆚 ይድነቃቸው ብርሃኑ — Boxing

🔥 ሐይማኖት መክብብ “ሐይሚ” 🆚 ለሊስቱ ዳንኤል “ለሊ የአዳማ” — Muay Thai

🔥 ጳውሎስ ማለዳ “ንስር” 🆚 ከሐብታሙ ለታ — Wushu Sanda

🎟️ የመግቢያ ትኬት ሽያጭ በቴሌብር በቅርቡ ይጀምራል!

🔥 ለየት ያለ የፍልሚያ ምሽት… ለስፖርት ወዳጆች የማይቀር ዝግጅት! 🥊🇪🇹

🔥 Hala ላይ የገቢ እድል ይፈልጋሉ? 🔥💰 በቤትዎ ሆነው የገቢ እድልዎን ይሞክሩ!🎙️ Voice Chat ይሳተፉ🎁 Gifts ይቀበሉ💵 የገቢ እድል ያግኙ🚀 ከዛሬ ጀምሮ ይሞክሩ!👇 Hala ላይ ...
30/08/2026

🔥 Hala ላይ የገቢ እድል ይፈልጋሉ? 🔥
💰 በቤትዎ ሆነው የገቢ እድልዎን ይሞክሩ!
🎙️ Voice Chat ይሳተፉ
🎁 Gifts ይቀበሉ
💵 የገቢ እድል ያግኙ
🚀 ከዛሬ ጀምሮ ይሞክሩ!
👇 Hala ላይ ለመግባት ይህን ID ይጠቀሙ 👇
⭐ 3827060 ⭐
📲 ID: 3827060
🔥 እድሉን አታምልጥ! ዛሬውኑ ይጀምሩ!
app ከ play story hala አውርዳቹ ዛሬውኑ ጀምሩ
https://web.hehala.com/h5/index.html #/share_agentPage?uid=3827060

በደቡብ ትግራይ ስለዋ ወረዳ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ዴላ ቅርንጫፍ በጥበቃ ሥራ ላይ የሚገኙት አቶ ሰይፉ ተስፋይ፣ እድሜና የሥራ ሁኔታ ሳይገድባቸው ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት በ2018 ዓ....
29/08/2026

በደቡብ ትግራይ ስለዋ ወረዳ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ዴላ ቅርንጫፍ በጥበቃ ሥራ ላይ የሚገኙት አቶ ሰይፉ ተስፋይ፣ እድሜና የሥራ ሁኔታ ሳይገድባቸው ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት በ2018 ዓ.ም በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 320 ውጤት በማምጣት ወደ ዩኒቨርሲቲ ከሚያልፉ ተማሪዎች አንዱ ለመሆን በቅተዋል።

አቶ ሰይፉ ላሳዩት አስደናቂ ጽናትና ላስመዘገቡት ውጤት የባንኩ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሓጎስ መዝገበ እና የሥራ ባልደረቦቻቸው በሙሉ የተሰማቸውን ታላቅ ኩራት የገለጹ ሲሆን፣ ለመጪው የትምህርት ጉዟቸውም መልካም ተመኞታቸውን አስተላልፈዋል።

የ41 ዓመት የባለቤቱን እናት  ላይ የግብረ-ስጋ ግንኘነት ወንጀል በማድረግ ያስረገዛት ቀስስ በ12 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት ተቀጣ ።                    ደቡብ ኢትዮጵ      ...
29/08/2026

የ41 ዓመት የባለቤቱን እናት ላይ የግብረ-ስጋ ግንኘነት ወንጀል በማድረግ ያስረገዛት ቀስስ በ12 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት ተቀጣ ።

ደቡብ ኢትዮጵ
ያቡታጅራ ነሃሴ_21/2018 ዓ.ም

ተከሳሽ ቀሲስ ከበበ ነገዎ ቀንና ስዓቱ በዉል በማይታወቅበት ጊዜ በመስቃን ወረዳ መሰረተ ወገራም ቀበሌ ልዩ ቦታው ዋሹኔ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የግል ተበዳይ የሆነችዉ ወ/ሮ ተስፋነሽ ግዛ ከባለቤቷ ጋር ተጣልታ ልጇ ቤት ልታድር በሄደችበት የልጇ ባል የሆነዉ ተከሳሽ አስገድዶ ግብረ ስጋ ግንኙነት ከደረጋ በኋላ ሆድሽ ላይ ጽንስ ሳላይ ከዚህ የትም አትሄጂም በማለት እና ይህንን ለአንድ ሰዉ ከተናገርሽ አንቺንም ልጅሽንም አቃጥላቹዋለዉ በማለት አስፈራርቷት እቤቱ አንድትቀመጥና በተደጋጋሚ ግዜ አስገድዶ በመድፈር እንድታረግዝ በማድረግ ወንጀል ፈፅሟል።

በዚህም የተጣራ የምርመራ መዝገብ የደረሰው የመስቃን ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ዐ/ህግ በተከሳሽ ላይ በ1997 ዓ/ም በስራ ላይ ዋለውን የኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 628(ሀ) የተመለከተውን በመተላለፍ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል መፈፀም ወንጀል እንዲሁም የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 101 መሰረት የግል ተበዳይ ከላይ በተፈጸመባት የወንጀል ድርጊት ለደረሰባት ከፍተኛ የሆነ የሞራል ጉዳት ካሳ ጥያቄን በማያያዝ ክስ አቅርቦበታል፡፡

ክሱ የቀረበለት የመስቃን ወረዳ ፍ/ቤትም ዐ/ህግ ባቀረባቸው ማስረጃዎች ከበቂ በላይ ያስረዳ በመሆኑ ተከሳሽ መከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ ብይን የተሰጠ በመሆኑ ተከሳሽ መከላከያ ማስረጃዎቹን አቅርቦ የተከራከረ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ማስረጃ ከሰማ በኃላ መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ በተከሰሰበት የወንጀል ህግ ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ ነው በማለት የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፏል ፡፡

በዚህ መሰረት ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ከሰማ በኃላ በቀን 04/12/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን ያርማል ሌላውንም የማህበረሰብ ክፍል መሰል ወንጀሎችን ከመፈፀም እንዲቆጠቡ ያርጋል ያለውን በ12 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንዲሁም በግል ተበዳይ ላይ በተፈፀመው ወንጀል ድርጊት በተከሳሽ ላይ በደረሰባት የሞራል ስብራት ተከሳሽ በፍ/ህ/ቁ 2114 እና 2105(1) መሰረት ተከሳሽ ለግል ተበዳይ የሞራል ካሳ 10‚000 (አስር ሺህ) ብር ሊከፍል ይገባል በማለት ወስኗል ፡፡

ማህበረሰቡ መሰል የወንጀል ድርጊቶችን ከመፈፀም እንዲቆጠብ በማለት መልክታችንን እናስተላልፋለን ፡፡

የመስቃን ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

#ፍትህለሴቶች

ጃኒ ቴሌቭዥን ጣቢያ live ላይ  አንድን ተወዳዳሪ የሚዋርድ አገላለጽ  ቃለመጠይቅ ማድረጓ ብዙዎችን አስቆጣ ።ቲክቶከር ጃኒ  ብከስርም  ጆኒን ብየ 2 ሚሊዮን ብር  አስይዣለሁ ። (ሴዶስ?)...
28/08/2026

ጃኒ ቴሌቭዥን ጣቢያ live ላይ አንድን ተወዳዳሪ የሚዋርድ አገላለጽ ቃለመጠይቅ ማድረጓ ብዙዎችን አስቆጣ ።

ቲክቶከር ጃኒ ብከስርም ጆኒን ብየ 2 ሚሊዮን ብር አስይዣለሁ ። (ሴዶስ?) አለቻት ጋዜጠኛዋ... ሴዶማ.... በሚዋርድ አገላለጽ ይጋፋል እንጂ አይችልም አለች

እንግዲህ ቲክቶከሯ ጃኒን ሰማችኃት አይደል የትኛውም ማይክ ሲጠጋላት ቲክቶክ ነው የሚመስላት...

ብዙዎች እያዩት ባሉት ቴሌቭዥን ጣቢያ ላይ ነው አንድን ተወዳዳሪ በሚዋርድ አገላለጽ .....እያለች ቃለመጠይቅ ያደረገችው ግብረገብነት እና የቃላት ምርጫ በየትኛው ቦታ ላይ የሚለው አሁን ከንቱ ትምህርት ሆኖ ተቀምጧል ።

ያው ሁለት ሚሊየኑንም በቁማር ያስያዝኩት ሰርቼ ነው ከየት መጣ በዛ ምናምን እያላችሁ አትጩሁ እንደኔ ስሩ ብላናለች ቲክቶከር ጃኒ።

እንዲሁ አይነት live ላይ በቴሌቪዥን ጣብያ የሚደረጉ ኋላፊነት የጎደላቸው Interview ሚዲያውን በህግ የሚስጠይቁ ናቸው ። ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ። ይሄ ቲክቶክ አይደለም የአነጋገር ግብረገብነት ያስፈልጋል።

ከዛ ውጪ ጋዜጠኛዋ live በቴሌቪዥን ላይ ስለ ቁማር ማውራቷ በራሱ ትክክለኛ አይደለም ። ዓባይ ቴሌቪዥን መሰል ችግሮችን ማስተካከል አለበት ። በጣም ብዙ ቲክቶከሮች በብዙ ሚሊዮን ብሮች ይሄንን ድንቅ ዝግጅት ወደ ቁማር መውሰዳቸው ትክክል አይደለም ። ምክንያቱም አደንዛዥ ዕፆችንና ቁማርን በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ወቅት ማስተዋወቅ ትልቅ ወንጀል ነው ።

Via፦ ጋዜጠኛ ሰሎሞን አባቡ
ግዮን ማለዳ

በአዲስ አበባ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተካሄደው የኢትዮጵያ ታፕ ፋይት ቻምፒዮና (ETFC 002፤ Adwa Fight Night) ዋና ፍልሚያ ጆኒ ጁጁትሱ ሰዶን ማሸነፉን ተከተሎ፣ ታዋቂው ...
28/08/2026

በአዲስ አበባ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተካሄደው የኢትዮጵያ ታፕ ፋይት ቻምፒዮና (ETFC 002፤ Adwa Fight Night) ዋና ፍልሚያ ጆኒ ጁጁትሱ ሰዶን ማሸነፉን ተከተሎ፣ ታዋቂው ድምፃዊ ታሪቁ ጋንክሲ በማህበራዊ ሚዲያው ያስተላለፈው የትችት መልእክት ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾችን በሳበው በዚህ ውድድር ዙሪያ ድምፃዊው «ማደሪያ የሌለው ህዝብ - ሲገፋ የኖረ፣ እርግጫ ለማየት - ጎዳና አደረ» የሚል ግጥማዊ ቅሬታ ያቀረበ ሲሆን፣ ይኸውም በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ውስጥ እየተስፋፋ ያለውን የፍትህ ማጣት፣ የጦርነት ስቃይ፣ ተቋማዊ የሌብነትና የዘረፋ ወንጀል እንዲሁም የከፋ የኢኮኖሚ ውደቀት ችላ በማለት ህዝቡ ጥልቅ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ውስጥ እያለ በእንደዚህ አይነት የትግል ትዕይንቶች ላይ ትኩረት ማድረጉን ለመኮነን እንደሆነ ተገልጿል።

ድምፃዊው ይህን ማህበራዊ ተቃርኖ በማንሳት የሰጠው አስተያየት በበርካቶች ዘንድ ድጋፍና የተለያየ ትችት በማስተናገድ በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ሰፊ አከራካሪ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል።

Address

Wolayita Sodo
Sodo
6000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወላይታዎች ለወላይታ Wolayitawoch lewolyiata posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ወላይታዎች ለወላይታ Wolayitawoch lewolyiata:

Shortcuts

Share

Category