Health care service

Health care service የድካማችን ዋጋ የማህበረሰብ ዕሪካታ !

አብሽ (Fenugreek)፦ የወገብና የመገጣጠሚያ ህመም ተፈጥሮአዊ ፋርማሲ በመባል ይታወቃል! ​አብሽ በኢትዮጵያ ወጥ ውስጥ እንደ ቅመም ብቻ ሳይሆን፣ በባህላዊ ህክምናው ዘርፍ "የመገጣጠሚያዎ...
22/01/2026

አብሽ (Fenugreek)፦ የወገብና የመገጣጠሚያ ህመም ተፈጥሮአዊ ፋርማሲ በመባል ይታወቃል!

​አብሽ በኢትዮጵያ ወጥ ውስጥ እንደ ቅመም ብቻ ሳይሆን፣ በባህላዊ ህክምናው ዘርፍ "የመገጣጠሚያዎች ወዳጅ" ተብሎ ይታወቃል። በተለይ በወገብ ህመም ለሚሰቃዩ ሰዎች አብሽ ተወዳዳሪ የሌለው ተፈጥሮአዊ መፍትሄ ነው።

​🇪🇹 በኢትዮጵያ ባህላዊ ህክምና (Traditional Wisdom)
​በባህላችን አብሽ ለብዙ ህመሞች መፍትሄ ሆኖ ያገለግላል፦
​ለወገብ ህመም (Back Pain) ፦ አብሽ በውስጡ "ብርድን" የመሳብ እና የጡንቻ መሸማቀቅን የመፍታት ኃይል እንዳለው ይታመናል። የአብሽ ሻይ ወይም በንጹህ ማር ተበጥብጦ መወሰዱ የቆየ የወገብ ህመምን፣ የዲስክ መንሸራተትን ተከትሎ የሚመጣ ህመምን እና የቁርጥማት ችግርን በከፍተኛ ሁኔታ ያቃልላል።
​ለመገጣጠሚያ ጤና (Joint Health)፦ የመገጣጠሚያ ፈሳሽ (Synovial fluid) እንዲመረትና ግጭቶች እንዲቀንሱ በማድረግ ረገድ በባህል ደረጃ ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል።
​ለጨጓራና አንጀት ጤና፦ ሆድ እንዳይነፋና የምግብ መፈጨት እንዲፋጠን ይረዳል።
​ለጡንቻ ጥንካሬ፦ በተለይ ለወለዱ እናቶች ብርታትን እንዲሰጥና የወተት ምርትን እንዲጨምር ይደረጋል።
​🔬 ዓለም አቀፍ ሳይንሳዊ ጥናቶችና ውጤቶች
​ዘመናዊው ላብራቶሪ ስለ አብሽ ምን ይላል? 🧪
​የመገጣጠሚያ እብጠት (Anti-inflammatory)፦ * ጥናት ያደረገው ተቋም፦ Annamalai University (India)
​ግኝቱ፦ በአብሽ ውስጥ የሚገኙት Diosgenin እና Petroleum ether extract ንጥረ ነገሮች በመገጣጠሚያ ላይ የሚከሰትን እብጠትና ህመም (Arthritis) በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንሱ በላብራቶሪ ተረጋግጧል። ይህም እንደ ኢቡፕሮፌን (Ibuprofen) ያሉ የህመም ማስታገሻዎችን ያህል ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።
​የነርቭና የጡንቻ ማስታገሻ (Nerve & Muscle Relaxation)፦
​ጥናት ያደረገው ተቋም፦ Journal of Ethnopharmacology
​ግኝቱ፦ አብሽ በውስጡ ባለው ከፍተኛ የማግኒዚየም እና ፖታሲየም ይዘት ምክንያት ለወገብ ጡንቻዎች መላላትና ለነርቭ መረጋጋት ወሳኝ መሆኑ ተረጋግጧል።
​የደም ስኳር ቁጥጥር፦
​ተመራማሪዎች፦ Dr. Richard Anderson እና ቡድናቸው በዩኤስ አሜሪካ የአግሪካልቸር ዲፓርትመንት (USDA)።
​ግኝቱ፦ አብሽ የደም ስኳርን ለማመጣጠንና ኢንሱሊን እንዲነቃቃ በማድረግ ረገድ ድንቅ ውጤት አሳይቷል።
​🌍 በተለያዩ ሀገራት ያለው አጠቃቀም
​በግብፅና በመካከለኛው ምስራቅ፦ ለወገብ ህመም ማስታገሻነትና ለኩላሊት ጤና በሰፊው ይጠቀሙበታል።
​በቻይና፦ የኩላሊት ኃይልን (Qi) ለማደስ እና በሰውነት ውስጥ ያሉ ብርዶችን ለማስወገድ እንደ ዋና ግብዓት ይወሰዳል።
​በአውሮፓ (ዘመናዊ መድኃኒቶች)፦ አሁን ላይ አብሽ በካፕሱልና በዱቄት መልክ ተዘጋጅቶ እንደ "Supplements" ለስኳር ህመምተኞችና ለጡንቻ እድገት በፋርማሲዎች ይሸጣል።
​💡 አጠቃቀም
​የአብሽ ሻይን በየቀኑ መጠጣት ወይም አብሽን ዘፍዝፎ ውሃውን መጠቀም ለወገብና ለመገጣጠሚያ ጤናዎ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። በተለይ ከእንቅልፍ በፊት መጠጣቱ ጡንቻዎች እንዲያርፉ ይረዳል።

➳➳➳➳Dr Abiy

"ምች" - Oral Herps /Cold Soresበብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከንፈራችን ላይ፣ አፋችን አካቢቢ እና ውስጥ በድንገት የህመም ስሜት ያላቸው ትንንሽ ውሃ የቋጠሩ ሚመስሉ አይነት እብጠ...
05/01/2026

"ምች" - Oral Herps /Cold Sores

በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከንፈራችን ላይ፣ አፋችን አካቢቢ እና ውስጥ በድንገት የህመም ስሜት ያላቸው ትንንሽ ውሃ የቋጠሩ ሚመስሉ አይነት እብጠቶች ወይም ቁስለት ሲያጋጥመን 'ምች መቶኝ ነው' የሚል የተለመደ የህመም አገላለፅ አለን።

በተለይ' የተወሰኑ ምግቦችን ከተጠቀምኩ ቡሀላ አፌን በደንብ ሳልታጠብ ወደ ፀሀይ ስወጣ... ነው ምች ያገኘኝ' እንላለን።

'ፀሀይ ላይ ምግብ አትብላ ምች ይመታሀልም' ስንባል ያደግንም ብዙዎች ነን።

'ምች ይደጋገምብኛል : ይፀናብኛል: ያስቸግረኛል... እያሉ 'የሚናገሩም ብዙ ሰዎች አሉ።

'ምች ይምታህ' .. የሚለው ቃል ደግሞ የልጅነት የእርግማን ወይም ስድብ ትዝታችን ነው

ምች ምንድነው?

በአብዛኛው ማህበረሰባችን ዘንድ' ምች ተብሎ' ተብሎ የሚታወቀው ፦በአፍ ውስጥ ከንፈር እና አካባቢው የሚከሰት እና በትንንሽ ህመም ያላቸው ውሃ የቋጠሩ ሚመስሉ እብጠቶች ወይም ቁስለት ምልክቶቹ በዋናነት የሚገለፀው ሲሆን ፥በሳይንሳዊ መጠሪያው 'Oral Herps/Cold sores' ወይም አንዳንዴ ከንፈረ ላይ ብቻ ሲወሰን 'Herps labialis' ተብሎ ከሚጠራው የቫይረስ ኢንፌክሽን ጋር የሚስተካከል ህመም ነው።

ሆኖም ግን ሌሎች ከ Herps ቫይረስ ውጪ ባሉ ምክንያቶች የሚከሰቱ የአፍ ውስጥ እና አካባቢው ቁስለቶችም አንዳዴ በምልክት መመሳሰል የተነሳ በሰዎች ዘንድ ምች ተብለው ሊገለፁ እንደሚችሉም ማስተዋል ያስፈልጋል።

እናም በዚህ ፅሁፍ ላይ' ምች' ስል ለመገልፅ እየሞከርኩ ያለሁት በ herps ቫይረስ ሚከሰተውን እና ከአብዛኛው ማህበረሰባችን የምች ምልክቶች አገላለፅ ጋር የሚጣጣመውን 'Oral Herps' መሆኑን ቀድሜ ላስገነዝብ እፈልጋለሁ።

ምች/Oral Herps

ይህ 'Herps simplex virus 1 (HSV-1) ተብሎ በሚታወቅ የቫይረስ አይነት የሚመጣ በአፍ ውስጥ ስጋዎች (ምላስ : ድድ...): ከንፈር እና አካባቢው ባለው ቆዳ ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን ነው።

ሁለት አይነት የ HSV አይነቶች ሲኖሩ HSV-1 አፋ እና አካባቢውን ሲያጠቃ HSV-2 ተመሳሳይ ኢንፌክሽን በመራቢያ አካላት ላይ ያስከትላል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ 3.8 ቢሊየን (64%) እድሜያቸው ከ50 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች የOral Herps (ምች) የሚያመጣው ቫይረስ ተጠቂዎች ናቸው።

ቫይረሱ እንዴት ነው የሚሰራው?

ምች (Oral herps) በከፍተኛ ሁኔታ ተላላፊ ኢንፌክሽን ሲሆን በዋነኝነትም በቀጥታ የበሽታው ምልክት (ቁስለት : እብጠት : ምራቅ..) ጋር በሚደረግ ቀጥተኛ ንክኪ ይተላለፋል።

አንዳንድ ጊዜ ምንም ምልክቱ ከማይታይባቸው (ከሌለባቸው) የቫይረሱ ተሸካሚ ሰዎችም ጋር በሚደረጉ የጠበቁ ንክኪዎች (በመሳሳም : በምራቅ...) ሊተላለፍ ይችላል።

አንድ ሰው አንዴ በዚህ ቫይሰረስ (HSV-1) ከተጠቃ (ቫይረሱ ወደ ሰውነቱ ከገባ) ቡሀላ; ቫይረሱ እድሜ ልኩን አብሮት የሚኖሮ ሲሆን ፤ አብዛኛውን ወቅት ላይ ግን ምንም አይነት ምልክቶችን (ህመሞችን) አያሳይም።

ቫይረሱ አንዴ ወደሰውነታችን ከገባ ቡሀላ አብዛኛው ጊዜውን ፊታችን አካባቢ በሚገኝ ነርቭ ህዋስ (Trigeminal ganglion) ውስጥ ተደብብቆ(ፀጥ ብሎ/አድፍጦ/Dormant/inactive) የሚቀመጥ ሲሆን ፤ ምቹ አጋጣሚዎችን ሲያገኝ ግን ከመጠን በላይ በመራባት እና በመሰራጨት ጥቃት መፈፀሙን ጀምሮ ጉዳቶቹን/ምልክቶችን በአፍ ውስጥ ከንፈር እና አካባቢው ላይ ያሳያል። የዚያኔ 'ምች መታኝ' ወይም Oral Herps ተከሰተ እንላለን።

ምልክቶቹ

1. የህመም ስሜት ያለቸው ውሀ የቋጠሩ ሚመ

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ስቅለቱ በሰላም አደረሳችሁ! !
02/05/2024

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ስቅለቱ በሰላም አደረሳችሁ!
!

The 4 most common   conditions are:🦷 tooth decay🦷 gum disease🦷 tooth loss🦷 oral cancersFortunately, most cases are preve...
01/05/2024

The 4 most common conditions are:

🦷 tooth decay
🦷 gum disease
🦷 tooth loss
🦷 oral cancers

Fortunately, most cases are preventable and can be treated in their early stages.

27/04/2024
በዳሞት ወይዴ ወረዳ በሚገኘው የመንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና በ4ቱ ጤና ጣቢያዎች የ3ኛ ሩብ ዓመት የጤና ተቋማት የህዝብ ፎረም መድረክ ተካሄደ ዳሞት ወይዴ ፤ ሚያዝያ 11/2016...
19/04/2024

በዳሞት ወይዴ ወረዳ በሚገኘው የመንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና በ4ቱ ጤና ጣቢያዎች የ3ኛ ሩብ ዓመት የጤና ተቋማት የህዝብ ፎረም መድረክ ተካሄደ

ዳሞት ወይዴ ፤ ሚያዝያ 11/2016 ዓ/ም በዳሞት ወይዴ ወረዳ በሚገኘው የመንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና በ4ቱ ጤና ጣቢያዎች የ3ኛ ሩብ ዓመት የጤና ተቋማት የህዝብ ፎረም መድረክ ተካሂዷል ።

መድረኩ በዋናነት በጤና ተቋማት የሚነሱ የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለቶችን በቀጣይነት በማረም የጤና አገልግሎት ተደራሽነት እና ጥራት ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ሲሆን በመድረኩም በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት እና በ2016 ዓ/ም በ3ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ዙሪያ ከህዝብ ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

ለጤናው ዘርፍ ግቦች በዘላቂነት መሳካት፣ የጤና ተቋማት እየጠነከረ እንዲሄድና ህብረተሰቡ መብቱን እና ግዴታውን በመለየት በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን መጠየቅ እንዲሁም በሚችለው ልክ በመለካት ባለድርሻ አካላት ሆኖ እንዲሠሩ በጤና ተቋማት የህዝብ ፎረም መድረክ ላይ ተጠይቋል ።

በውይይት መድረክ ላይ በሆስፒታሉና በጤና ጣቢያ እየተሰጠ ያለው የአልግሎት አሰጣጥ ከበፊቱ የተሻለ ሆኖ እንድቀጥል እና ለህብረተሰቡ የሚሰጠው አገልግሎት የተቀላጠፈና የዘመነ እንዲሆን የውይይቱ ተሳታፊዎች ጠይቋል ።

በመድረኩ ከተሳታፊዎች ሀሳብና አስተያየት እንዲሁም ጥያቄ ተነስቶ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ከመድረኩ በመስጠት ውይይት ተጠናቋል።

በህዝብ ፎረም መድረክ ላይ በም/ማዕረግ የዳሞት ወይዴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታሁን ተረፈ ፣ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አስራት ወ/ጊዮርጊስ ፣ የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ዋናና ምክትል ኃላፊዎች ፣ የጤና ጣቢያ ኃላፊዎች ፣ የወረዳው ደጋፊ አመራሮች እና ከተለያዩ ማህበራዊ መሰረት የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል ።

15/04/2024

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
__________

የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Health Officer, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Technology, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatrics Nursing እና Emergency & Critical Care Nursing ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በግንቦት 2016 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
ስለሆነም አዲስም ሆነ ነባር፣ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን የኦንላይን ምዝገባው ከሚያዚያ 7/2016 እስከ ሚያዚያ 21/2016 ዓ.ም ብቻ የሚቆይና ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ print አድርጋችሁ በመያዝ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፦

- የግል ትምህርት ተቋማት ተመዛኞች ከምዝገባ በፊት የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን (ETA) Authenticate ማስደረግና ስማችሁን ከባለስልጣኑ ወደ ጤና ሚኒስቴር ማስላክ ይጠበቅባችኋል፡፡

- ከጥር 1/2015 ዓ.ም በኋላ የተመረቃችሁ የጤና ባለሙያዎች የትምህርት ሚኒስቴር መውጫ ፈተና(Exit Exam) ማለፍ ይጠበቅባችኋል፡፡

- ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

14/04/2024
መልካም የሥራ ዘመን ይሁንላቹ!!!
12/04/2024

መልካም የሥራ ዘመን ይሁንላቹ!!!

የዳሞት ወይዴ ወረዳ ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 4ኛ ዙር 11ኛ አመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶቾን አፀደቀ

ዳሞት ወይዴ ፤ ሚያዝያ 4/2016 ዓ/ም የዳሞት ወይዴ ወረዳ ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 4ኛ ዙር 11ኛ አመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶቾን አፅድቋል ።

በዚህም :-
1ኛ- - አቶ ኢሳያስ ያዕቆብ - የዳሞት ወይዴ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ
2ኛ- አቶ ተስፋዬ ወልዴ - የዳሞት ወይዴ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ
3ኛ- አቶ አስራት ዶኮ - የዳሞት ወይዴ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ
4ኛ- አቶ መስፍን ዳዊት - የዳሞት ወይዴ ወረዳ ኘላንና ልማት ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ ሆኖ በመሾም ቃለ መሀላ ፈጽሟል።

29/03/2024

Vaccines protect against more than 20 diseases:
Cervical cancer
Cholera
Diphtheria
Ebola
Hepatitis B
Influenza
Japanese encephalitis
Measles
Meningitis
Mumps
Pertussis
Pneumonia
Polio
Rabies
Rotavirus
Rubella
Tetanus
Typhoid
Varicella
Yellow fever
COVID-19

Talk to your health worker to ensure vaccination is up to date for you and your family

Address

Wolaita Sodo
Sodo
HABTEPH

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Health care service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share