Kindo Koysha Woreda Government communication Affairs Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • Kindo Koysha Woreda Government communication Affairs Office

Kindo Koysha Woreda Government communication Affairs Office Government Organization

በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ የ2018 ዓ/ም የበጋ ወራት በጎ ሥራ ማጠቃለያና የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ማስጀመሪያ ''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል ርዕስ ወረዳዊ መድረክ እየተካ...
29/06/2026

በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ የ2018 ዓ/ም የበጋ ወራት በጎ ሥራ ማጠቃለያና የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ማስጀመሪያ ''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል ርዕስ ወረዳዊ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል

‎ኪንዶ ኮይሻ፤ ሰኔ 22/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ የ2018 ዓ/ም የበጋ ወራት የበጎ ሥራ ማጠቃለያና የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ማስጀመሪያ ''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል ርዕስ ወረዳዊ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

‎መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ዕጩ ዶ/ር ደገፉ ዳልኬ እንደተናገሩት የበጎ አገልግሎት ሥራዎች ሰዎች በራሳቸው ፍላጎት በመነሳት ያለምንም ክፍያ የሚያከናውኑት መልካም ተግባር ነዉ ብሏል።

‎አክለዉም ዋና አስተዳዳሪዉ ፓርቲያችን ብልፅግና ሰዉ ተኮር መሆኑን በተግባር አጎልቶ የሚያሳየዉ በዚህ በጎ ሥራ ላይ መሆኑን በማንሳት፤ በዘንድሮ ክረምት በጎ ሥራ 118 አድስ የሚገነባ ቤት መኖሩን ተናግረዋል።

‎ወጣቶች በክረምት ወራት ጉልበታቸውንና ጊዜያቸውን ለህዝባችን በነፃ የሚለግሱበት ወቅት መሆኑን በመጥቀስ ወጣቶች በሁሉም ተግባር በንቃት በመሳታፍ ማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲሁም የእርስ በርስ ግንኙኝነት ማጠናከር ህብረ-ብህራዊ አንድነት ማጠናከር እንደሚገባቸውም አንስተዋል።

‎የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን ሙሉነህ እንደገለፁት ባለፉት በበጋና ክረምት ወራት በተሰሩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎች በተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል።

‎ዘንድሮ በሚካሄደዉ የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በ18 የስራ ዘርፎች ከ37,616 በላይ ወጣቶችን በማሳተፍ በወረዳ በሚገኙ ሁሉም መዋቅሮች እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ዉጤታማ ሥራ እንደሚሰራ ገልጿል።

‎በ2018 ክረምት ወራት የሚካሄደው የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ እንደኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት ለማዳን ግብ እንደተቀመ ተገልጿል።

‎በመድረኩ የወረዳዉ አስተባባሪ ኮሚቴ አካላት፣ አጠቃላይ የወረዳዉ መካከላኛ አመራር፣ የቀበሊያት ዋና አስተዳዳሪዎች፣ የቀበሌ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የቀበሌ ሥራ አስኪያጆች እና የኃይማኖት መሪዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

Address

S**o

Telephone

+251910042504

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kindo Koysha Woreda Government communication Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share