Soddo Zuria Wereda Health Office

Soddo Zuria Wereda Health Office Soddo Zuria Woreda Health Office is governmental Sector which woks to promote Health & prevent disea

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የCatch up Campaign ኦርንቴሽን እየሰጠ መሆኑን ገለጸ፡፡      መጋቢት 07/2018 ዓ.ም ወላይታ ሶዶ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የCatch ...
16/03/2026

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የCatch up Campaign ኦርንቴሽን እየሰጠ መሆኑን ገለጸ፡፡

መጋቢት 07/2018 ዓ.ም ወላይታ ሶዶ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የCatch up Campaign ኦርንቴሽን እየሰጠ መሆኑን ገልጹዋል፡፡

መድረኩን የመሩት የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የወረዳዉ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ሲ/ር መስከረም በቀለ ፡- በዚህ ዘመቻ ኦርንቴሽን ላይ የCatch up Campaign፣ የጤናማ እናትነት፣ የጽዱ ኢትዮጵያ/ወረዳ መፍጠር፣ የማዐጤመ ሰነዶች እንደሚቀርቡ አንስተዉ ከዚህ ዘመቻ ጋር በቅንጅት የሚሠሩ የመደበኛ ክትባት አገልግሎት፤ የህጻናት የዕድገት ክትትል፤ የህጻናት፣ የነፍሰጡርና አጥቢ እናቶች የምግብ እጥረት ልዬታ ሥራ እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡

ዘመቻዉ በሁሉም ቀበሌ ቤት ለቤት በመግባት ክትባት ያልጀመሩና ያቋረጡ ህጻናትን በማግኘት አንድም ሳይቀር መከተብ እንዳለባቸዉ ተናግረዉ ሁሉም ከታቢና ሱፔርቫይዘሮች በተጠያቂነት መምራት እንዳለባቸዉ አንስተዋል፡፡ ከዘመቻዉ ጋር በቅንጅት የሚሠሩ ተግባራትም ትኩረት ተሰጥተዉ መመራት እንዳለባቸዉ ተናግረዉ የእያንዳንዱ ሥራ በጤና ኬላም ሆነ በጤና ጣቢያ ተደራጅቶ መቀመጥ እንዳለባቸዉ አንስተዋል፡፡

የጤናማ እናትነት በተመለከተ ሁሉም ነፍሰጡር እናቶች እርግዝናቸዉ ከተከሰተ ከ12 ሳምንት በፊት ጀምሮ ክትትል እንዲጀምሩ ለማድረግ የልየታና ምዝገባ ሥራ በሁሉም ጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ተጠናሮ መሠራት እንዳለበት አንስተዋል፡፡ የነፍሰጡር እናቶች ኮንፍራንስም ያለምንም መቆራረጥ በየወሩ በሁሉም ቀበሌ መደረግ እንዳለበት፤ ሁለቱም ጤና ጣቢያ እናቶች የቅድመ ወሊድ ክትትል እስከ 8ኛ ዙር እንዲደርሱ ክትትልና ምርመራ አገ/ሎት ማጠናከር እንዳለባቸዉ፤ የማቆያ ቤት አገ/ሎት ግብዓት ከማሟላትም አንጻር ማጠናከር እንዳለባቸዉ፤ የጤና ጣቢያ አገ/ሎት ሳቢና ማራኪ እንዲሆን በኃላፊነት መምራት እንዳለባቸዉ ተናግረዋል፡፡

የጽዱ ኢትዮጵያ/ወረዳ መፍጠር ዙሪያ ሁሉም ጤና ኤክስቴንሽን የቤተሰብና የጋራ መጸዳጃ ቤት ፣ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ኢዲት መሠራት እንዳለበት፤ አንስተዉ ባለፈዉ የተጀመረዉ ንቅናቄ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል፡፡

ሌላዉ ማዐጤመ የአባላት መታወቂያ ከፋይዳ ጋር የማስተሳሰር ሥራ በሁሉም ቀበሌ ተጠናክሮ መሠራት እንዳለበት አንስተዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የወረዳ ሱፔርቫይዘሮች፣ የሁለቱም ጤና ጣቢያ ኃላፊዎችና የሁሉም ቀበሌ ጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የCatch up Campaign ኦርንቴሽን እየሰጠ መሆኑን ገለጸ፡፡
መጋቢት 07/2018 ዓ.ም ወላይታ ሶዶ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የCatch up Campaign ኦርንቴሽን እየሰጠ መሆኑን ገልጹዋል፡፡
መድረኩን የመሩት የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የወረዳዉ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ሲ/ር መስከረም በቀለ ፡- በዚህ ዘመቻ ኦርንቴሽን ላይ የCatch up Campaign፣ የጤናማ እናትነት፣ የጽዱ ኢትዮጵያ/ወረዳ መፍጠር፣ የማዐጤመ ሰነዶች እንደሚቀርቡ አንስተዉ ከዚህ ዘመቻ ጋር በቅንጅት የሚሠሩ የመደበኛ ክትባት አገልግሎት፤ የህጻናት የዕድገት ክትትል፤ የህጻናት፣ የነፍሰጡርና አጥቢ እናቶች የምግብ እጥረት ልዬታ ሥራ እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡
ዘመቻዉ በሁሉም ቀበሌ ቤት ለቤት በመግባት ክትባት ያልጀመሩና ያቋረጡ ህጻናትን በማግኘት አንድም ሳይቀር መከተብ እንዳለባቸዉ ተናግረዉ ሁሉም ከታቢና ሱፔርቫይዘሮች በተጠያቂነት መምራት እንዳለባቸዉ አንስተዋል፡፡ ከዘመቻዉ ጋር በቅንጅት የሚሠሩ ተግባራትም ትኩረት ተሰጥተዉ መመራት እንዳለባቸዉ ተናግረዉ የእያንዳንዱ ሥራ በጤና ኬላም ሆነ በጤና ጣቢያ ተደራጅቶ መቀመጥ እንዳለባቸዉ አንስተዋል፡፡
የጤናማ እናትነት በተመለከተ ሁሉም ነፍሰጡር እናቶች እርግዝናቸዉ ከተከሰተ ከ12 ሳምንት በፊት ጀምሮ ክትትል እንዲጀምሩ ለማድረግ የልየታና ምዝገባ ሥራ በሁሉም ጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ተጠናሮ መሠራት እንዳለበት አንስተዋል፡፡ የነፍሰጡር እናቶች ኮንፍራንስም ያለምንም መቆራረጥ በየወሩ በሁሉም ቀበሌ መደረግ እንዳለበት፤ ሁለቱም ጤና ጣቢያ እናቶች የቅድመ ወሊድ ክትትል እስከ 8ኛ ዙር እንዲደርሱ ክትትልና ምርመራ አገ/ሎት ማጠናከር እንዳለባቸዉ፤ የማቆያ ቤት አገ/ሎት ግብዓት ከማሟላትም አንጻር ማጠናከር እንዳለባቸዉ፤ የጤና ጣቢያ አገ/ሎት ሳቢና ማራኪ እንዲሆን በኃላፊነት መምራት እንዳለባቸዉ ተናግረዋል፡፡
የጽዱ ኢትዮጵያ/ወረዳ መፍጠር ዙሪያ ሁሉም ጤና ኤክስቴንሽን የቤተሰብና የጋራ መጸዳጃ ቤት ፣ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ኢዲት መሠራት እንዳለበት፤ አንስተዉ ባለፈዉ የተጀመረዉ ንቅናቄ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል፡፡
ሌላዉ ማዐጤመ የአባላት መታወቂያ ከፋይዳ ጋር የማስተሳሰር ሥራ በሁሉም ቀበሌ ተጠናክሮ መሠራት እንዳለበት አንስተዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የወረዳ ሱፔርቫይዘሮች፣ የሁለቱም ጤና ጣቢያ ኃላፊዎችና የሁሉም ቀበሌ ጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የኤች አይ ቪ ኤድስ ሜንስትሪሚንግ ማካሄዳቸዉን ገለጸ።ታህሳስ 23/2018 ወላይታ ሶዶ፡ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የኤች አይ ቪ ኤድስ ሜንስትሪሚንግ ማካ...
01/01/2026

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የኤች አይ ቪ ኤድስ ሜንስትሪሚንግ ማካሄዳቸዉን ገለጸ።
ታህሳስ 23/2018 ወላይታ ሶዶ፡ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የኤች አይ ቪ ኤድስ ሜንስትሪሚንግ ማካሄዳቸዉን ገልጿል።
መድረኩን የመሩት የወረዳዉ ጤና ጽ/ቤት ም/ሃላፊ የሆኑት አቶ አስፋዉ አድማሱ የኤች አይ ቪ ኢድስ በሽታ የመከላከሉ ሥራ እየተቀዛቀዘ የመጣ መሆኑንና ህብረተሰቡም ወደ መዘናጋት የገቡ መሆናቸውን ጠቅሰው የመከላከሉን ሥራ ለማጠናከር ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት አንስተዋል።
የሜንስትሪሚንግ ሰነድ ያቀረቡት የኤች አይ ቪ መ/ዳይሬክቶረት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ብርሃኑ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንና የህብረተሰቡም ግንዛቤ ዝቅተኛ እንደሆነ፣ በጤና ተቋማትና በትም/ት ቤቶች የሚስጠዉ ትም/ት በቋሚነት እየተሰጠ ያለመሆኑን አንስተዋል።
ለቀጣይ ጊዜ በተለያዩ ሚዲያዎች የቅስቀሳ ሥራ መጠናከር እንዳለበት እና በጤና ተቋማትም ሆነ በትም/ት ቤቶች የሚሰጠዉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትም/ት መጠናከር እንዳለበት፣ የትኛዉም ተጋላጭ ህብረተሰብ ክፍል የኤች አይ ቪ የደም ምርመራ መደረግ እንዳለበት፣ ኤች አይ ቪ በደማቸዉ ዉስጥ የተገኘባቸው በመድሃኒት ላይ መቀመጥ እንዳለባቸውና የቫይራል ሎድ ምርመራ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በአጽንኦት ተነስቷል።
በመድረኩ ላይ ሁሉም የጤና ጽ/ቤት ሠራተኞችና የጤና ጣቢያ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የዚትሮማክስ ዘመቻ የመጀመሪያ ቀን ውሎ ግምገማ እያካሄደ መሆኑን ገለጸ።ታህሳስ 21/2018:ወላይታ ሶዶ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የዚትሮማክስ ዘመቻ የ...
30/12/2025

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የዚትሮማክስ ዘመቻ የመጀመሪያ ቀን ውሎ ግምገማ እያካሄደ መሆኑን ገለጸ።
ታህሳስ 21/2018:ወላይታ ሶዶ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የዚትሮማክስ ዘመቻ የመጀመሪያ ቀን ውሎ ግምገማ ሁሉም ሱፔርቫይዘሮች በተገኙበት እያካሄደ መሆኑን ገልጿል ።
መደረኩን የመሩት የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የጤና ጽ/ቤት ሃላፊ ሲ/ር መስከረም በቀለ ሁሉም ሱፔርቫይዘር ሁሉም ቲም ዘመቻ አጀማመርና ከግብዓት፣ ከመዝገብ አጠቃቀም፣ እንደ ችግር ያጋጠሙ ና እንደተፈቱ መቅረብ እንዳለበት አንስተዋል።
አቶ ቆስቴ እማሞ የዞን ጤና መምሪያ ከፍተኛ ባለሙያ በሁሉም ቀበሌ ያጋጠሙ ችግሮች፣ የተፈቱና ያልተፈቱ መቅረብ እንዳለባቸው እና ለቀጣይ መፈታት እንዳለበት አንስተዋል።

28/12/2025
የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ማህበረሰብ ዐቀፍ የትራኮማ መከላከያ መድኃኒት/ዚትሮማክስ ዕደላ ዘመቻ ዙሪያ ወረዳ አቀፍ የኦረንቴሽን መድረክ እያካሄደ ነው *********ሶዶ ዙሪያ፤ ታ...
28/12/2025

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ማህበረሰብ ዐቀፍ የትራኮማ መከላከያ መድኃኒት/ዚትሮማክስ ዕደላ ዘመቻ ዙሪያ ወረዳ አቀፍ የኦረንቴሽን መድረክ እያካሄደ ነው
*********
ሶዶ ዙሪያ፤ ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ማህበረሰብ ዐቀፍ የትራኮማ መከላከያ መድኃኒት/ዚትሮማክስ ዕደላ ዘመቻ ዙሪያ ወረዳ አቀፍ የኦረንቴሽን መድረክ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሃላፊና የወረዳ ም/አስተዳዳሪ የሆኑት ሲ/ር መስከረም በቀለ እንዳሉት
በወረዳችን ባሉት ሁሉም ቀበሌ መዋቅሮች ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጥ መድሀኒት በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተለይም የጤና ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ልዩ ትኩረት ሰጥተው መምራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

ለማህበረሰቡ ከመድኃኒት ዕደላ ጋር ተያይዘው ግንዛቤ የማሳደግ ሥራ መጠናከር እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት።

ይህ መድሀኒት በዋናነት የትራኮማ በሽታ እና ዓይነ ስውርነትን የሚያስከትለውን ችግር ለመቅረፍ የሚሰጥ በመሆኑ የመድሀኒት ተደራሽነት ላይ በተቀመጠው አቅጣጫና የጊዜ ገደብ ልክ ሊሠራ እንደሚገባም ልዩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ለበሽታው መንስኤ የሚሆኑትን የግልና የጋራ መጸዳጃ ቤት ሽፋንና አጠቃቀም ላይም ትኩረት መሰጠት እንዳለበትና ቅድመ መከላከል ሥራዎችን ማጠናከር አሰፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጽያ የዓይን ጤና እንክብካቤ ሥራዎች ወደ ማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረጉ በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውንም አመላክቷል።

የዘመቻውን ውጤታማነት በየጊዜው ክትትል የሚያደርጉ ቡድን ተዋቅሯል በማለት አሰፈላጊ ድጋፍም ሁሉ የሚደረግ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ ሲ/ር መስከረም በቀለ በበኩላቸው ትራኮማ በሽታ በሀገራችን መሠረታዊ ከሆኑ የጤና ችግሮች መካከል በቀላሉ መከላከልና መቆጣጠር የምንችላቸው ተላላፊ በሽታዎች መሆናቸውን በመግለጽ እንደ ሌሎች በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራሞች ተነድፈው ሰፊ ተግባራት እየተሰሩ መሆኑን አብራርተዋል።

አክለውም የንጹህ የመጠጥ ውሀ አቅርቦት፣ የግልና የአካባቢ ንጽህና አጠባበቅ፣ እንዲሁም ማህበረሰቡ ለእነዚህ በሽታዎች ያለው ግንዛቤ ከፍ የማድረግ ስራን እንደ ቁልፍ ተግባር አድርጎ በመውሰድ የተሰሩ ስራዎችን እና የተገኙ ውጤቶችን ዘላቂነትን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ በጤና ተቋማት ብቻ የሚሰራው አለመሆኑን በመጥቀስ በየደረጃው የሚመለከታቸው ተቋማት፣ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀራረብና የተቀናጀ አሰራር በመፍጠር ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ተሰጥተው ሊሠራ ይገባል ብለዋል።

የዚትሮማክስ መድሀኒት ዕደላው ለሁሉም የወረዳችን ህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሰጥም ገልጿል።

ዘመቻው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ መደበኛ የጤና ተግባራት ጎን ለጎን የሚመሩ መሆናቸውንም አመላክቷል።

የዘመቻው ኦርንቴሽን እየሰጡ ያሉ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ከፍተኛባለሙያ ስሆን በመድረኩ የወረዳው አሰተባባሪ አካላት፣የጤና ጽ/ቤት አመራሮች፣ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ሶሻል ሞብላይዜሮች፣የጤና ጣቢያ ሥራአስኪያጆች እና ሱፐርቫይዘሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የየሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ4ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የ4ኛ ቀን ዉሎ ግምገማ ማድረጉን ገለጸ፡፡ወላይታ ሶዶ ታህሳስ 7/2018 ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ4ኛ ዙር የፖሊ...
16/12/2025

የየሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ4ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የ4ኛ ቀን ዉሎ ግምገማ ማድረጉን ገለጸ፡፡
ወላይታ ሶዶ ታህሳስ 7/2018 ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ4ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የ4ኛ ቀን ዉሎ ግምገማ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማድረጉን ገልጹዋል፡፡
መድረኩን የመሩት የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊና የወረዳ ም/አስተዳዳሪ የሆኑት ሲ/ር መስከረም በቀለ የሁሉም ቀበሌ በአፈጻጸምም ሆነ በጥራትም የተሻለ ዉጤት ለማስመዝገብና ህጻናትን ተጠቃሚ ለማድረግ የተከደዉን እርምጃ አመስግነዉ ሁሉም ሱፔርቫይዘሮች ሞፕአፕ ለቅመዉ ለማስጨረስ ኃላፊነታቸዉን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
አቶ ደገፉ ዳካ የእናቶችና ህጻናት ሥራ ሂደት ቡድን መሪ የሆኑት የሪፖርት አፈጻጸምን ጠቅለል ያለ አቅርበዉ እንደ ወረዳ የ4 ቀን (8282) ህጻናትን በማስከተብ ሽፋን (98%) ማሳካት እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡ የሞፕአፕ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡፡፡
አቶ ዮናስ ዮሐንስ የጤ/ጤ/ድ/አ/ቅ/ም ቡድን መሪ የሆኑት የቤትና የጣት ምልክት በአግባቡ መደረጉን በቼክ ሊስት መታዬት እንዳለበትና ኦዲኬ መሞላት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ሲ/ር መስከረም በቀለ ስያጠቃልሉ ዘመቻዉ በአንጻራዊ ከሌሎች ዘመቻ ጊዜ የተሻለ እንደተሰራ አንስተዉ በአፈጻጸም ብቻ ሳይሆን በጥራት ላይም የተደረጉ ርብርቦች የተሻሉ መሆናቸዉን አንስተዋል፡፡ አሁንም ማንቴ ጌሬራ 84% ላይ ያለዉም ሆነ 100% ላይ ያሉትም አንድም ህጻን እንዳይቀር ለቅመዉ ሞፕአፕ መሥራት እንዳለባቸዉ ገልጸዋል፡፡
በግምገማዉ መድረክ የወረዳና የጤና ጣቢያ ሱፔርቫይዘሮች ተገኝተዋል፡፡

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ4ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የ2ኛ ቀን ዉሎ ግምገማ ማድረጉን ገለጸ፡፡ወላይታ ሶዶ ታህሳስ 5/2018 ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ4ኛ ዙር የፖሊዮ...
14/12/2025

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ4ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የ2ኛ ቀን ዉሎ ግምገማ ማድረጉን ገለጸ፡፡
ወላይታ ሶዶ ታህሳስ 5/2018 ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ4ኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የ2ኛ ቀን ዉሎ ግምገማ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማድረጉን ገልጹዋል፡፡
መድረኩን የመሩት የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊና የወረዳ ም/አስተዳዳሪ የሆኑት ሲ/ር መስከረም በቀለ የሁሉም ቀበሌ በአፈጻጸምም ሆነ በጥራትም የተሻለ ዉጤት ለማስመዝገብና ህጻናትን ተጠቃሚ ለማድረግ ሁሉም ሱፔርቫይዘሮች ሚናቸዉን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
አቶ ደገፉ ዳካ የእናቶችና ህጻናት ሥራ ሂደት ቡድን መሪ የሆኑት የሪፖርት አፈጻጸምን ጠቅለል ያለ አቅርበዉ ዝቅተኛ አፈጻጸም ያለባቸዉ ቀበሊትን በልዩ ትኩረት ድጋፍ መደረግ እንዳለባቸዉ ተናግረዋል፡፡
አቶ ዮናስ ዮሐንስ የጤ/ጤ/ድ/አ/ቅ/ም ቡድን መሪ የሆኑት የቤትና የጣት ምልክት በአግባቡ መደረጉን በቼክ ሊስት መታዬት እንዳለበትና ኦዶኬ መሞላት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
አቶ አስፋዉ አድማሱ የጤና ጽ/ቤት ም/ኃላፊ የሆኑት የክትባት ደህንነት የተጠበቀ ሆኖ እስከ ህጻናት መድረስ እንዳለበት ተናግረዉ ክትትልና ድጋፍ ሥራ መጠናከር እንዳለበት አንስተዋል፡፡
በግምገማዉ መድረክ የወረዳና የጤና ጣቢያ ሱፔርቫይዘሮች ተገኝተዋል፡፡

የሶዶ ሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት 4ኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ወረዳዊ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በቶሜ ከተማ ቀበሌ አካሂዷል።ወላይታ ሶዶ ታህሳስ 3/2018እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ...
12/12/2025

የሶዶ ሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት 4ኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ወረዳዊ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በቶሜ ከተማ ቀበሌ አካሂዷል።
ወላይታ ሶዶ ታህሳስ 3/2018እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት ቤት ለቤት የሚሰጠው የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።
በማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የተገኘው የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ከፍተኛ ባለሙያዎች አቶ መርዕድ አሰፋ እና ሲ/ር ዉባየሁ አካለወልድ፡- ክትባቱ ቤት ለቤት እንደሚሰጥ ገልጸዉ የወባ መከላከልና ቁጥጥር፣ የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ተጠርጣሪዎችን የመለየት፣ ስለቫይረሱ ግንዛቤ መስጠት፣ ክትባት ያልጀመሩና ያቋረጡ ሕፃናት ክትባት ማስጀመር፣ ሕፃናትና ነፍሰጡር እናቶች የምግብ እጥረት በሽታ ልየታ፣ የከንፈርና ላንቃቆ መሰንጠቅና ቆልማማ እግር ያለባቸዉ ህፃናት መለየት ሥራም እንደሚቀናጅ ገልጸዋል።
የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ሲ/ር መስከረም በቀለ በበኩላቸው የፖሊዮን በሽታ መከላከል የሚቻለው ህጻናትን በመደበኛና በዘመቻ መልክ የሚሰጠውን ክትባት ስናስከትብ በመሆኑ ከዚህ በፊት የፖሊዮ ክትባት ቢከተቡም ባይከተቡም በዘመቻው እንዲከተቡ ወላጆችና አሳዳጊዎች እንድሁም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በመርሃ ግብሩ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ከፍተኛ ባለሙያዎች ፣ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊና ም/ኃላፊ፣ የጤና ጽ/ቤት ከፍተኛ ጤና ባለሙያዎችና ሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በሶዶ ዙሪያ   ወረዳ  ጤና  ጽ/ቤት የ4ኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ  አስመልክቶ ለጤና ኤክስቴንሽን፣ ለጤና ባለሙያዎችና ለሱፔርቫይዘሮች ኦሬንተሽን መድረክ ተካሂዷል።‎ሶዶ ዙሪያ ...
11/12/2025

በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ4ኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ አስመልክቶ ለጤና ኤክስቴንሽን፣ ለጤና ባለሙያዎችና ለሱፔርቫይዘሮች ኦሬንተሽን መድረክ ተካሂዷል።
‎ሶዶ ዙሪያ ፣ ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ኦሬንቴሽን ለጤና ኤክስቴንሽን፣ ለጤና ባለሙያዎችና ለሱፔርቫይዘሮች የሥልጠና መድረክ ተካሂዷል።

‎ በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያ ያደረጉት የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እስጢፋኖስ ዋቴ ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር ክትባት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ውጤታማ የሆነ የተቀናጀ የፖሊ ክትባት ዘመቻ ለማካሄድ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል።
‌‎አክለው ዘመቻ ስካሄድ ሌላ የጤና ተግባራቶችን በጎን ይዛችሁ ጠንክረው እንድሰሩና በዘመቻው የተቀመጠውን እቅድ ለማሳካት ቀደም ሲል ለባለድርሻ አካላት ኦሬንቴሽን መስጠቱንና የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን መጠናቀቅ እንዳለበት ገልጿል።
‎ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ም/አስተዳደርና የጤና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ መስከረም በቀለ እንደገለጹት
‎የ4ኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከታህሳስ 3-6 2018 ዓ.ም በወረዳው በሚገኙ በሁሉም ቀበሌዎች ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ቤት ለቤት የሚሰጥ መሆኑን ገልፀው በተጨማሪ በመደበኛው የክትባት መርሐ ግብር ክትባት ያልጀመሩና ጀምረው ያቋረጡ ህጻናትን በመለየት ክትባት እንድያገኙ የማቀናጀት ሥራ ይሠራል ብለዋል።
በተጨማሪ ከዘመቻው ጋር በቅንጅት የሚሠሩ ተግባራት ፖሊዮ መሰል ኬዝ ቅኝትና አሰሳ ፣ ቆልማማ እግር ያለባቸውን ልየታ ማድረግ ፣ የማርቨርግ በሽታ አሰሳ ሥራዎች ተጠናክሮ መሠራት እንዳለበት አሳስበዋል ።
ዘመቻውን ውጤታማ ለማድረግ እና የተሳካ እንዲሆንሁሉምየሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል።
‎በስልጠና ላይ የጤና ጽ/ቤት ከፍተኛ ባለሞያዎች፣ የጤና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ የ EPI ፎካሎች፣ የጤና ጣቢያ ጤና ኬላ ትስስር ፎካሎች፣ ሁሉም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል ።

‎ ሶዶ ዙሪያ 01/04/2018 ዓ.ም

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️...
07/08/2021

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️
የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት በ2013 ዕቅድ አፈጻጸም በዞኑ ዉስጥ ካሉት ወረዳዎች 3ኛ ደረጃ በመዉጣቱ የዕዉቅና ሴርቴፍኬትና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት መከላከልን መሠረት ያደረገዉን የጤና ፖሊሲ ለመፈጻም ለትተቀን እየሠራ መሆኑ ና የህክምና አገ/ሎት ጥራትና ፍትሐዊነትን ለማሻሻል፣ ህብረተሰብን የጤና አገ/ሎት ተጠቃሚ ለማድረግ የማዐጤመ አባል እንዲሆኑ ማድረግ፣ ሞዴል ቀበሌ መፍጠር፣ የእናቶችና ህጻናት ጤና መሻሻል ወ.ዘ.ተ ዙሪያ ሰፊ ሥራዎችን መሥራቱ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ በአጠቃላይ ጤና ሥራ ዙሪያ ባዘጋጀዉ መመዘኛ መስፈርት ተመዝኖ በዞኑ ዉስጥ ካሉ ወረዳዎች መካከል በ3ኛ ደረጃ በመዉጣቱ የዕዉቅና ሴርቴፍኬት ፣ ዋንጫ እና ደስክቶፕ ኮሚፒዉተር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በተጨማሪ በ2013 ዓ.ም የኮቪድ 19 በሽታ መከላከል ዙሪያ ለሠራዉ አኩሪ ተግባር የዕዉቅና ሴርቴፍኬት ተበርክቶለታል፡፡
ይህ የዕዉቅና ና ሽልማት ለ2014 ዓ.ም ካሉበት ደረጃ ለማሻሻልና ህብረተሰብን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ እጅግ የሚያነሳሳ እንደሆነ ና ጤና ተቋማትም ለቀጣይ ተሸላሚ ለመሆን ቁርጠኝነታቸዉንና ቁጭታቸዉን ገልጸዋል፡፡
በዋናነት ህብረተሰባችንን ተጠቃሚ ለማድረግ ሞዴል ጤና ተቋማትን ፣ ሞዴል ትም/ቤትን፣ ሞዴል ቀበሌን፣ ሞዴል ወረዳ ለመፍጠር ካሁኑኑ ወደ ተግባር በመግባት ዉጤት ለማስመዝገብ ትኩረት እንደሚሰጡም ገልጸዋል፡፡
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት የ2013 የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በማስመልከት በወረዳ ዉስጥ ላሉ ወላጅ አጥ ህጻናትና ቫይረሱ በደማቸዉ ዉስጥ ላሉባቸዉ ወገኖች የእህል ድጋፍ አድ...
29/04/2021

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት የ2013 የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በማስመልከት በወረዳ ዉስጥ ላሉ ወላጅ አጥ ህጻናትና ቫይረሱ በደማቸዉ ዉስጥ ላሉባቸዉ ወገኖች የእህል ድጋፍ አድርጓል፡፡
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
በዓሉን በማስመልከት አጠቃላይ 86 ሰዎች እያንዳንዳቸዉ 25 ኪ.ግ የበቆሎ እህል ድጋፍ ያገኙ ሲሆን ከእነሱ 60 ወላጅ አጥና 26 ቫይረሱ በደማቸዉ ዉስጥ ያሉባቸዉ ወጌኖች ናቸዉ፡፡
በቦታዉ የተገኙ ባለድርሻ አካላትየጤና ጥ/ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ጳዉሎስ ሙሴ፣ የወረዳዉ ሴቶች ወጣቶችና ህጻናት ጉ/ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት ዝናሽ በቀለ፣የጽ/ቤታችን የኤች አይ ቪ ዘርፈ ብዙ ቅኝት ና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ሀብታሙ ብርሃኑና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነዉ፡፡

Address

S**o

Telephone

+251925699844

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Soddo Zuria Wereda Health Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share