ወላይታ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ/Wolaita Zone Culture & sport Department

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • ወላይታ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ/Wolaita Zone Culture & sport Department

ወላይታ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ/Wolaita Zone Culture & sport Department የአከባቢ አገራቀፍና አለማቀፍ ትኩስ መረጃዎች ተደራሽ ይሆናሉ!
(2)

የወላይታ ብሔር ባህላዊ የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል “ጊፋታ”  አከባበር ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን የክልሉ ባህልና ስፖርት ቢሮ ድጋፋዊ ክትትል አድርጓልወላይታ ሶዶ: ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም በ...
28/08/2026

የወላይታ ብሔር ባህላዊ የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል “ጊፋታ” አከባበር ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን የክልሉ ባህልና ስፖርት ቢሮ ድጋፋዊ ክትትል አድርጓል

ወላይታ ሶዶ: ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም

በተባበሩት መንግስታት ትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት የተመዘገበው የወላይታ ብሔረሰብ ባህላዊ የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል“ጊፋታ” አከባበር ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ የባህል ልማት ዘርፍ የተደራጀ ድጋፋዊ ክትትል አድርጓል።

የቢሮው ምክትል እና የባህል ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታሪኩ ኦይቻ የተመራው የቢሮ የባህል እሴቶችና ብዝሃ-ባህል ሀብቶች ጥናት ጥበቃና ልማት ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያዎች በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ተገኝተው ከዞኑ ባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊና የማኔጅመንት አባላት ጋር ተወያይተዋል።

የቢሮው የባህል እሴቶችና ብዝሃ-ባህል ሀብቶች ጥናት ጥበቃና ልማት ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያዎች በድጋፍና ክትትል ወቅት በቅድመ-በዓሉ ዝጅት የሚከናወኑ ባህላዊ የእርቅና የሽምግልና ስርዓቶችን፣ የእደጥበብ ውጤቶችን፣ የባህላዊ ምግብና መጠጥ፣ ባህላዊ መድኃኒት እንዲሁም የአገር በቀል ዕውቀቶች እና የኪነጥበብ ሥራዎች በዕቅድ እስከ ታችኛው መዋቅር እየተሰሩ መሆናቸውን በመስክ ምልከታው ማየት ችለዋል።

በተጨማሪም የብዝሃ-ባህል ሀብቶች፣ የሀገረሰብ ባህልና ቱባ ባህላዊ እሴቶችን ለማልማት በተደራጀ መልኩ ለኤግዝቪሽን መዘጋጀቱንና በዕቅድ እየተመራ መሆኑን የክትትል ቡድኑ ተመልክቷል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊና የባህል ልማት ዘርፍ አቶ ታሪኩ ኦይቻ ክብረ በዓሉ ለአብሮነት፣ ለዘላቂ ሰላም፣ ለህዝብ ትስስርና የፍቅር የመተባበር በዓል እንድሆንና ያልተበረዘ በቀድምት ባህላዊ ሥርዓት መከተል እንዳለበት በአፅንኦት አሳስበዋል ።

አያይዘውም የወላይታ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ጊፋታ” የክልሉ ብቻ ሳይሆን የሀገርና የዓለም ሀብት ሆኖ የተመዘገበ በመሆኑ የበዓሉ ዓከባበር ከቅድመ ዝግጅቱ ጀምሮ የሚከውኑ የክብረ በዓሉ ኩኔቶች በተደራጀ መልኩ ቱባ ባህሉን በጠበቀ መልኩ ለትውልድ እንዲተላለፍ በትኩረት መሠራቱ እንዲጠናከር አሳስበዋል ።

የወላይታ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ፤ የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ እና የሁለቱ መዋቅሮች የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ነው ውይይቱ የተደረገው።

/

28/08/2026
በኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ውድድር እና ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ዳርጌ የተመራው ልኡክ በወላይታ ዞን እየተከናወኑ ያሉ የክረምት ስፖርት ውድድር  እ...
28/08/2026

በኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ውድድር እና ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ዳርጌ የተመራው ልኡክ በወላይታ ዞን እየተከናወኑ ያሉ
የክረምት ስፖርት ውድድር እና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ያለበትን ደረጃ የመስክ ምልከታ አደረገ

ወላይታ ሶዶ፣ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም

ልኡኩ በዞኑ እየተሠሩ ያሉ የክረምት በጎ አገልግሎት ሥራዎችን እንዲሁ የክረምት ወራት የስፖርት ውድድርና የማዘውተሪያ ሥፍራዎች የመስክ ምልከታ በማድረግ የዞኑ ባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ስምዖን ስላሎ እና የዘርፉ ባለሙያዎች በተገኙበት ግብረ መልስ ሰጥቷል።

ልኡክ ቡድኑ በዞኑ እየተሠሩ ያሉ ለፕሮጀክቶች የሚሰጡ ሥልጠናዎች ለሌሎች አርዓያ መሆኑን በማመልከት የመንግሥት መዋቅር ለስፖርት የሚሰጠው ድጋፍ፣ የባለሙያው እና የአመራሩ ቅንጅታዊ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በስፖርት ዘርፍ የውድድር ሞዳሊቲዎችን በማዘጋጀት በዞኑ እየተደረገ ያለው ሥራ ለተሞክሮ የሚሆን ነው ያለው ልኡኩ የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራዎች ለአብነት ደም የማሰባሰብ ሥራ፣ የሜዳ ገቢ አሰባሰብ፣ ገቢን ለስፖርት ሥራ ማዋል መቻሉ እና ለአገር የሚበቁ ስፖርተኞችን የማፍራት ሥራ ሊበረታታ የሚገባ ነው ብሏል።

ቡድኑ በፕሮጀክቶች ላይ የሚሠሩ ሥራዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ምቹ እንዲሆኑ ቢሠራ የሚል አስተያየት ነው የተሰጠው።

የዞኑ ባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ስምዖን ስላሎ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ዞኑ ካለው ስፖርተኞችን ከማፍራት አቅም አንፃር በፕሮጀክቶች ላይ ሳይሆን አካዳሚ ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲደግፍ ጠይቀዋል።

ዞኑ ውድድሮችን መምራት የሚችሉ በዳኝነት የሚያገለግሉ ባለሙያዎች ዕጥረት መኖሩን ገልጸው የሥልጠና ዕድል በመስጠት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ኃላፊው ድጋፉ ባለሙያውን የሚያበቃ እንደ መምሪያም ሥራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

27/08/2026
የጊፋታ በዓል ዋዜማ ማብሰሪያ የሆነው የ"ኮርማ ጪሻ" መፍካት መጪው አዲስ ዓመት የሰላም፣ የልማትና የአብሮነት ስለመሆኑ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ነው። ወላይታ ሶዶ፤ ነሐሴ 2018 በፌዴራል ብልጽ...
26/08/2026

የጊፋታ በዓል ዋዜማ ማብሰሪያ የሆነው የ"ኮርማ ጪሻ" መፍካት መጪው አዲስ ዓመት የሰላም፣ የልማትና የአብሮነት ስለመሆኑ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ነው።

ወላይታ ሶዶ፤ ነሐሴ 2018

በፌዴራል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መስከረም አበበ የተመራው ከፍተኛ ልዑክ በሽግግር ሙዚየም የሚገኙ ዕድሜ ጠገብ የወላይታ ብሔር ቅርሶችን የጎበኘ ሲሆን፣ ጉብኝቱ በዓሉ በዩኔስኮ ከተመዘገበበት ማግስትና በጊፋታ መዳረሻ ወቅት መሆኑ ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸው አመራሮቹ ገልጸዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ክንፍ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ብሩክ ባልቻ በበኩላቸው፣ ሴቶች ለአንድ ዓመት ሙሉ የፈጀ ቅድመ-ዝግጅት ካደረጉ በኋላ በባህላቸው አምረውና ደምቀው በአደባባይ የሚያከብሩት በመሆኑ በዓሉ የሴቶችን የላቀ ሚና የሚያሳይ ድንቅ እሴት እንደሆነ አብራርተዋል።

የወላይታ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል ጊፋታ ሰፊ ነባር እሴቶች ያሉት የዓለም ቅርስ መሆኑን ጠቅሰው፣ በዓሉ የሴቶችን የቁጠባ ባህልና አንድነት ይበልጥ እንደሚያጎለብትና አበቦች በመስኩ መታየታቸው የብርሃንና የተስፋ ብስራት መሆኑን አስገንዝበዋል።

የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ጸጋ ፋንታ አክለው እንደገለጹት፣ ጊፋታን ልዩ የሚያደርገው ቂምና ቁርሾን እንዲሁም ዕዳን በፍቅርና በይቅርታ ሽሮ፣ አሮጌውን ዓመት ከነጓዙ ትቶ ወደ አዲስ ሕይወት የሚሻገርበት ታላቅ መድረክ መሆኑ ነው።

ልዑኩ "ኑ በአገር ውስጥና ከባሕር ማዶ ያላችሁ የወላይታ ልጆችና ወዳጆች ይህንን ብሩህ ተስፋ ሰንቀን የምንሻገርበትን የጊፋታ በዓል በአንድነት እናክብር" ሲል ጥሪውን አስተላልፏል።

የሰመር ካፕ ሻምፒዮናው ጉኑኖ ወደ ከተማው ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት ወላይታ ሶዶ፡ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ስፖርት ምክር ቤት አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው ሰመር ካፕ ...
26/08/2026

የሰመር ካፕ ሻምፒዮናው ጉኑኖ ወደ ከተማው ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

ወላይታ ሶዶ፡ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም

በወላይታ ዞን ስፖርት ምክር ቤት አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው ሰመር ካፕ እግር ኳስ ውድድር በጉኑኖ ከተማ አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን ሻምፒዮናው ሶዶ ፍቅርን 1ለ0 በማሸነፍ ነው ዋንጫውን ያነሳው።

ቡድኑ በውድድሩ ድንቅ ብቃት ያሳየ ሲሆን ለማሸነፍ ከፍተኛ ግምት የተሰጠውን ሶዶ ፍቅርን በመርታት የዋንጫ ባለቤት መሆን ችሏል።

ሻምፒዮናው ጉኑኖ ምርጥ ትላንት ማምሻውን ወደ ጉኑኖ ከተማ ሲደርስ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ብርሃኑ ዋጃ፣ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተሰማ ባልቻን ጨምሮ ሌሎች አመራሮ፣ የከተማው ነዋሪዎች እና የስፖርት ቤተሰቦች በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

አዝናኝ ፉክክር የታየበት ሰመር ካፕ ውድድር አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ በማድረግ ተጠናቀቀ ወላይታ ሶዶ፡ ነሐሴ 19-2018 ዓ/ምበወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው...
25/08/2026

አዝናኝ ፉክክር የታየበት ሰመር ካፕ ውድድር አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ በማድረግ ተጠናቀቀ

ወላይታ ሶዶ፡ ነሐሴ 19-2018 ዓ/ም

በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው 5ኛው ዙር ሰመር ካፕ የእግር ኳስ ውድድር በጉኑኖ አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቤት መስሪያ የሚሆን የብሎኬት ድጋፍ በማድረግ የወገን አለኝታነትን በማሳየት ተጠናቋል።

በውድድሩ ፍፃሜ ንግግር ያደረጉት የወላይታ ዞን ስፖርት ም/ቤት ም/ሰብሳቢ እና የባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ስምኦን ስላሎ ሰመር ካፕ ሶስት መሰረታዊ ዓላማዎችን ያነገበ መሆኑን በተለይም በአገርቱ በተለያዩ ሊጎች የሚጫወቱ ስፖርተኞች ወደ ፕሪሚየር ሊግ እንዲያድጉ ዕድል እንደሚፈጥር፣ ታዳጊ ወጣቶች በተለያዩ ሊጎች ከሚጫወቱ ተጫዋቾች ልምድ እንዲቀስሙ እና ወጣቶች በክረምት ወራት በጎ አገልግሎት ተግባራት ተሰማርተው አቅም የሌላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ መታቀዱ-ን ገልጸዋል።

መምሪያው እንደዞናችን ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር በመቀናጀት በርካታ የበጎ አገልግሎት ተግባራትን በክረምት ወራት ለመስራት አቅደው ሰፊ ተግባራትን ማከናወናቸውን የገለጹት ኃላፊ ከእነዚያ አንዱ አቅም ለሌላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ልዩ ልዩ ድጋፎችን ማድረግ ብሎም የቤት ግንባታ ማካሄድ እንደሚጠቀስ ጠቁመዋል።

ዘንድሮ ለአንድ አቅም ለሌላው ግለሰብ ቤት ገንብቶ መስጠት ዋናው የመምሪያው ዓላማ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው ዛሬ ተጨዋቾችን፣ አሰልጣኞችን ፣ የስፖርቱ ደጋፊዎችን፣ ዳኞችንና የመምሪያ ባለሙያዎችን በማሳተፍ ከ400 በላይ ብሎከት መግዛት መቻላቸውን ጠቅሰው ቀሪ ቁሳቁሶች ተሰብስበው የቤት ግንባታ እንደሚከናወንም ነው የገለጹት።

የውድድሩ ሻምፒዮናው ጉኑኖ የ5 ኛውን ዙር ሰመር ካፕ & ሲያነሳ ሶዶ ፍቅር በሁለተኝነት አጠናቋል።

ጉኑኖ  የዘንድሮ የሰመር ካፕ ሻምፒዮን ሆኗል!!!!
25/08/2026

ጉኑኖ የዘንድሮ የሰመር ካፕ ሻምፒዮን ሆኗል!!!!

የ2018 ዓ.ም የወላይታ ሰመር ካፕ ውድድር የፍጻሜ ጨዋታ ጀምሯል  0-0    🏟️ከወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም
25/08/2026

የ2018 ዓ.ም የወላይታ ሰመር ካፕ ውድድር የፍጻሜ ጨዋታ ጀምሯል

0-0

🏟️ከወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም

አዝናኝ ፉክክር ሲታየበት የከረመው ሰመር ካፕ ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል ወላይታ ሶዶ፡ ነሐሴ 19-2018 ዓ/ምበወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው 5ኛው ዙር ሰመር ካፕ የእግር ኳስ ው...
25/08/2026

አዝናኝ ፉክክር ሲታየበት የከረመው ሰመር ካፕ ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል

ወላይታ ሶዶ፡ ነሐሴ 19-2018 ዓ/ም

በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው 5ኛው ዙር ሰመር ካፕ የእግር ኳስ ውድድር ዛሬ ይጠናቀቃል።

አብዘኛዎቹ የሰመር ካፕ ውድድር ተሳታፊ ተጫዋቾች በአገርቱ በተለያዩ ክለቦች እየተጫወቱ የሚገኙ በመሆናቸው በየግጥሚያዎች እጅግ አዝናኝና ማራኪ እንቅስቃሴ በማሳየት የተመልካችን ቀልብ ስበው ቆይተዋል።

ዛሬ በፍፃሜው የተገናኙት Vs የሚያደርጉት ግጥሚያ በጉጉት ይጠበቃል።

:00

Vs


===++++++=======+++===

Address

Wolaita
S**o

Telephone

+251979724115

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወላይታ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ/Wolaita Zone Culture & sport Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ወላይታ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ/Wolaita Zone Culture & sport Department:

Shortcuts

Share