South Ethiopia Regional State

South Ethiopia Regional State Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from South Ethiopia Regional State, Government Organization, Sodo.

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ሰራተኞች ጋር በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተወያዩ ነውርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ሰራተኞች...
05/12/2023

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ሰራተኞች ጋር በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተወያዩ ነው

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ሰራተኞች ጋር በወላይታ ሶዶ ከተማ ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ውይይት እያካሄዱ የሚገኙት
የክልሉ የፖለቲካ እና የአስተዳደር ማዕከል በሆነው ሶዶ ከተማ ከሚገኙ የክልል ተቋማት ሰራተኞች ጋር ነው።

የመንግስት ሰራተኞች እኩልነት እና ፍትሀዊነትን ብሎም የክልሉን ተጨባጭ አቅም ማዕከል ባደረገ አግባብ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባቸውም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለፁት።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከሰራተኞች ለሚነሱ ጥያቄዎች ሚላሽ ከመስጠት ባሻገር በመንግስት ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎትን ውጤታማና ህዝብን የሚያረኩ ማድረግ የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከ580 ሚሊዮን ብር በላይ ከተለያዮ ክልሎች እና ባለሃብቶች ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በስጦታ መልክ ተበረከተ በአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የምስረታ እና  ይፋዊ የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር...
24/11/2023

ከ580 ሚሊዮን ብር በላይ ከተለያዮ ክልሎች እና ባለሃብቶች ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በስጦታ መልክ ተበረከተ

በአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የምስረታ እና ይፋዊ የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የታደሙ ወንድም ህዝቦችና ባለሀብቶች ለክልሉ ማቋቋሚያ የሚሆን የገንዘብ ስጦታ አበርክተዋል።

በዚህም
1, የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 100 ሚሊዮን ብር ፣
2, አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 60 ሚሊዮን፣
3, ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት 30 ሚሊዮን ብር፣
4, ሶማሌ ክልላዊ መንግሥት 20 ሚሊዮን ብር ፣
5, አማራ ክልላዊ መንግስት 20 ሚሊዮን ብር፣
6, ሲዳማ ክልላዊ መንግስት 20 ሚሊዮን ብር ፣
7, የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት 15 ሚሊዮን ብር 8, አፋር ክልላዊ መንግስት 10 ሚሊዮን ብር፣
9, ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት 10 ሚሊዮን ብር፣
10, ጋምቤላ ክልላዊ መንግስት 5 ሚሊዮን ብር፣
11, ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 10 ሚሊዮን ብር እንዲሁም
12, ባለሀብት ፍሬው ቱፋ 50 ሚሊዮን ብር አበርክተዋል።

በተያያዘም በክልሉ ከሚገኙ ዞኖች 215 ሚሊዮን 710 ሺህ 912 ብር፣ ከልማት ድርጅቶች 20 ሚሊዮን 300 ሺህ በአጠቃላይ ከክልሎች ፣ ዞኖችና ልማታዊ ባለሀብቶች 580 ሚሊዮን ብር በስጦታ ተበርክቷል።

በሥፍራው የተገኙ ክልሎች ተወካዮችም ሁላችንም ተጋግዘንና ተባብረን በመስራት የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን እናደርጋለን ብለዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር ከወላይታ ሶዶ ከተማ እና አካባቢው ማህበረሰብ ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ ናቸው። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር ከወላይታ ሶዶ ከተማ እና አ...
20/11/2023

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር ከወላይታ ሶዶ ከተማ እና አካባቢው ማህበረሰብ ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ ናቸው።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር ከወላይታ ሶዶ ከተማ እና አካባቢው ማህበረሰብ ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛሉ። ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ጥላሁን ከበደ በክልሉ የማብሰሪያ ፕሮግራም ቅድመ ዝግጅት ላይ አፅንኦት የሰጡት ሲሆን ጠንከረን በመሥራት እና ውበታችን የሆነውን ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አጉልተን በተግባር እናረጋግጣለን ሲሉም ተናግረዋል።

ልዩ የሆነ ከተማ አቀፍ እና ክልላዊ የሰላም የፍቅር እና የመቻቻል ተምሳሌት ክልል መስርተን ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ገብተናል ሲሉም የክልሉ ርእሰ መስተደድር አቶ ጥላሁን አክለዋል።

አቶ ጥላሁን ክልሉ ተመስርቶ ስራ የጀመርን ቢሆንም በይፋ ታሪኳዊ የማብሰሪያ ቀኑን በጋራ እናበስራለን ሲሉም ተናግረዋል።

ይበልጥ መቀራረብ እና አብሮ በመስራት ከምስረታው ማግስት ጀምሮ ህዝቡን የለውጥ ማእከል በማድረግ ብልፅግናችንን እውን እንዲሆን በቁርጠኝነት እንሠራለን ብለዋል።

የወላይታ ዞን አስተዳደሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ በህዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አብሮ የመበልፀግ እድል የተፈጠረበት ምእራፍ መሆኑን ገልፀዋል።

ይፋዊ የክልል ማብሰሪያ ፕሮግራም ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ እንግዶች እየተጠበቁ እንደሚገኝ አቶ ሳሙኤል አስረድተዋል።

በአሁኑ ሰአት የመድረኩ ተሳታፊዎች የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ በሚሰጡት አስተያየት ላይ እየገለፁ ይገኛሉ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ይፋዊ የማብሰያ ፕርግራም የፊታችን ሐሙስ ይካሄዳል

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአስተዳደርና የፓለቲካ ማዕከል ስለሆነችው ስለ ዎላይታ ሶዶ ከተማ ከብዙ በጥቂቱ እነሆ ! ዎላይታ ሶዶ ስያሜዋን ያገኘችው ከ150 ዓመታት በፊት በአከባቢው ይኖሩ ከነበ...
18/11/2023

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአስተዳደርና የፓለቲካ ማዕከል ስለሆነችው ስለ ዎላይታ ሶዶ ከተማ ከብዙ በጥቂቱ እነሆ !

ዎላይታ ሶዶ ስያሜዋን ያገኘችው ከ150 ዓመታት በፊት በአከባቢው ይኖሩ ከነበሩ "ሞቼና ቦራጎ ሶዶ" ከተባሉ አንድ ታዋቂ ነጋዴ ስምና ከተማዋ አሁን በምትገኝበት አቅራቢያ ይገኝ ከነበረው "ሶዷ ሹቻ" ከሚባለው ሲሆን ትርጓሜውም "የሶዶ ድንጋይ" ተብሎ ከሚታወቅ ትልቅ የድንጋይ አለት የተወሰደ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ውቧ ዎላይታ ሶዶ ከተማ ከአዲስ አበባ በሻሸመኔ 390 ኪ.ሜ፤ በቡታጅራ ሆሳዕና 329 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች።

16 ሺ 164 ሄክታር ላይ ነው ከተማዋ ያረፈችው፡፡ የመልክዓ ምድር አቀማመጡ ከባህር ጠለል በላይ 1784-2346 ኪ.ሜ ከፍታ ላይ ትገኛለች፡፡

በከፍተኛ ዕድገትና ለውጥ ጎዳና የምትገኘው ውቧ ዎላይታ ሶዶ ከተማ በርካታ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች የሚደረጉባት 7 መግቢያና መውጫ በሮች ባለቤት ነች።

ዎላይታ ሶዶን ከሌሎች አጎራባች ከተሞች ያስተሳሰሯት ዋና ዋና መንገዶቿም ከሶዶ ሻሸመኔ አዲስ አበባ፣ ከሶዶ አርባምንጭ ጂንካ፣ ከሶዶ ጎፋ ሳውላ፣ ከሶዶ ታርጫ ጅማ፣ ከሶዶ ቢጣና ሞሮቾ ሐዋሳ፣ ከሶዶ ሆሳዕና አዲስ አበባ እና ከሶዶ ጉልጉላ ዲላ ናቸው።

በአሁኑ ጊዜ 340 ሺህ የሚጠጋ ሕዝብ ተቻችሎ፤ ተከባብሮ በጋራ ተፈቃቅሮ ይኖርባታል፡፡

በሆቴልና ቱሪዝም፤ በኢንዱስትሪ፤ በማህበራዊ አገልግሎትና በከተማ ግብርና በከፍተኛ ሁኔታ ኢንቨስት ለማድረግ ምቹ አቅም አላት።

ዎላይታ ሶዶ የፍቅርና የመቻቻል ከተማ ናት።

በሶስተኛው ዙር የመንግስት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ርዕስ በዎላይታ ሶዶ ስልጠና ማዕከል እየተሳተፉ ላሉ አመራሮች የዎላይታ ዞን እና የሶዶ ከተማ አሰተዳደር...
16/11/2023

በሶስተኛው ዙር የመንግስት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ርዕስ በዎላይታ ሶዶ ስልጠና ማዕከል እየተሳተፉ ላሉ አመራሮች የዎላይታ ዞን እና የሶዶ ከተማ አሰተዳደር እንግዳ ተቀባይ የሆነውን የዎላይታ ህዝብ በመወከል የራት ግብዣ እያደረጉ ይገኛሉ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ ሥራ ማስጀመርያና ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር ላይ የሚዲሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንዲታደሙ ጥሪ ተደረገ ።  ህዳር 13 /2016 ዓም በወላይታ ...
13/11/2023

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ ሥራ ማስጀመርያና ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር ላይ የሚዲሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንዲታደሙ ጥሪ ተደረገ ።

ህዳር 13 /2016 ዓም በወላይታ ሶዶ ከተማ ለሚካሄደው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ ሥራ ማስጀመርያና ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር ላይ የሚዲሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ጀማል አህመድ እንዲታደሙ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ክብር አቶ ተስፋዬ ይገዙ በሚዲሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ጽ/ቤት በመገኘት ጥሪ አቅርበዋል ።

የሚዲሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ጀማል አህመድ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ ሥራ ማስጀመርያና ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር ላይ እንዲገኙ የቀረበውን ጥሪ ተቀበለው በዓሉ ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል ፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተደድር ጽ/ቤት

አቅም ግምባታ ስልጠናው የመንግስት አመራሩ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት እንዲኖረው የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል እየተሰጠ የሚገኘው አቅም ግምባታ ስልጠና የመንግስት አመራሩ የአስተሳሰብና የ...
11/11/2023

አቅም ግምባታ ስልጠናው የመንግስት አመራሩ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት እንዲኖረው የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል

እየተሰጠ የሚገኘው አቅም ግምባታ ስልጠና የመንግስት አመራሩ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት እንዲኖረው የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል ።

ሀገራች ከነበረባት ዕዳ ወጥታ ወደ ምንዳ ለመድረስ የአመራሩን አቅም መገንባት ወሳኝ በመሆኑ ስልጠናው ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዴሞክራሲና አቅም ግምባታ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዮሐንስ በየነ አብራርተዋል።

የሀገራችንን ብልጽግና በጋራ እውን ለማድረግ በሚያስችል ምዕራፍ እንደምንገኝ ያብራሩት አቶ ዮሐንስ ለሁለንተናዊ ብልጽግና ስኬት ስንቅ የሚሆን ስልጠና በመሆኑ አመራሩ በአቅም ግምባታው የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በመላበስ ለመፍጠንም ሆነ ለመፍጠር ያለው ሚና ትልቅ መሆኑንም አስረድተዋል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ሳሙኤል ፎላ በበኩላቸው መንግስት የአመራር አቅም በመገንባት የህባችንን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን አመራሩ በብቃት ለማስተናገድ የሚያስችለውን ብቁ እውቀት እንዲቀስሙ፤ ከጥላቻና ከተሳሳተ ትርክት እንዲወጣ የሚያደርግ ስልጠና መሆኑን ነው የገለፁት ።

አቶ ሳሙኤል አያይዘውም ስልጠናው የአመራሩን የአፈፃፀም ውስንነቶችንና ክፍተቶችን ለመሙላት የታለመ መሆኑንም አብራርተዋል።

ወንድማማችነትን/ እህትማማችነትን የበለጠ በማጎልበት ለህዝብ ጥቅም ተግቶ ለመስራት የሚያስችል ስልጠና በመሆኑ እምቅ ፀጋዎቻችንን በላቀ ደረጃ በማልማት በእኩል ተጠቃሚ መርህ፣ በመተሳሰብና በመተጋገዝ እሴቶቻችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን ብለዋል አቶ ሳሙኤል።

የስልጠናው ቆይታቸው ያማረ እንዲሆላቸው የተመኙት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ለሰልጣኙ አመራር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያጉም ገልፀዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ ምስረታ ህዳር 13 ቀን 2016 ይካሔዳልየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ ምስረታ ህዳር 13 ቀን 2016 እንደሚካሄድ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ አ...
09/11/2023

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ ምስረታ ህዳር 13 ቀን 2016 ይካሔዳል

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ ምስረታ ህዳር 13 ቀን 2016 እንደሚካሄድ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ አስታወቁ።

በዝግጅቱ ዙሪያ ከክልሉ ተወላጅ አመራሮች ጋር በአዲስ አበባ ውይይት እየተደረገ ነው።

በአዲስ አበባ እና በፌዴራል ተቋማት ለሚገኙ የክልሉ ተወላጅ አመራሮች የቅድመ ዝግጅቶችና የይፋዊ ምስረታ ዓላማዎች ላይ ገለጻ አድርገዋል።

በህዳር 13ቱ ይፋዊ ምስረታ ላይ ከቀበሌ ጀምሮ ያሉ የክልሉ ተወላጆች ተሳትፎና ይሁንታ የሚያደርጉበት እንደሚሆን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

ህደር 13 ቀን 2016 ዓ.ም በሚካሄደው የክልሉ ይፋዊ ምስረታ የተለያዩ ክልሎችና ተቋማት ድጋፍና አጋርነት የሚገልጹበት እንደሚሆንም አቶ ጥላሁን አስታውቀዋል።

የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቹ በአብይና ንኡሳን ኮሚቴዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡

ህደር 13 ቀን 2016 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በሚካሄደው በዚሁ ይፋዊ ምስረታ የአዲስ አበባ እና የፌዴራል ተቋማት አመራሮች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ዘገባ ያመለክታል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 12 ዞኖችን ይዞ የተዋቀረ እና በ6 ማዕከላት የተደራጀ ክልል መሆኑ ይታወቃል።

ክልሉ የመንግሥት ሠራተኞች የማጓጓዝና የማቋቋም ሥራ እያከናወነ ነው የመንግሥት ሠራተኞች እንዳይጉላሉ ልዩ ውሳኔ በመወሰን ከሀዋሳ ወደ ክልሉ የማጓጓዝና የማቋቋም ሥራ እያከናወነ መሆኑን ደቡብ...
07/11/2023

ክልሉ የመንግሥት ሠራተኞች የማጓጓዝና የማቋቋም ሥራ እያከናወነ ነው

የመንግሥት ሠራተኞች እንዳይጉላሉ ልዩ ውሳኔ በመወሰን ከሀዋሳ ወደ ክልሉ የማጓጓዝና የማቋቋም ሥራ እያከናወነ መሆኑን ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገለጸ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግሥት ከሀዋሳ ወደተመደቡበት ስድስቱ የክልሉ ማዕከላት የሚንቀሳቀሱ የመንግሥት ሠራተኞች የሚጋጥማቸው ኢኮኖሚያዊ ጫና ለማቃለል ውሳኔ አሳልፏል። በውሳኔው መሠረትም የዕቃ ማጓጓዣ ፣ ቤት መፈለጊያ እንዲሁም በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች እንዳይቸገሩ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ሠራተኞችን የማጓጓዝ ሥራ እየሠራ ነው።

የቀድሞው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል በአራት ክልሎች ከተከፈለ በኋላ በቀመር ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚደርሰው የሠራተኛ ቁጥር በላይ መቀበል አለብን ብለን እየሠራን ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ክልሉ ይህንን አቋም የያዘው ሠራተኞች እንዳይጉላሉና እንዳይቸገሩ በማሰብ መሆኑን አስረድተዋል።

ሠራተኞቹ ረዥም ጊዜ መንግሥትን ያገለገሉና ባለውለታ መሆናቸውን አመላክተው፤ የትኛውንም ዋጋ ከፍለን ሠራተኞቻችን እንዳይቸገሩ መሥራት ያለብንን ነገር ሠርተን ወደ ሥራ እንዲገቡ እያደረግን እንገኛለን ብለዋል።

ሠራተኞች ከነበሩበት አካባቢ ሲዛወሩ ቅሬታ ሊኖር እንደሚችል የተናገሩት አቶ ጥላሁን፤ የክልሉ መንግሥት ለሠራተኞች ቅድሚያ እንስጥ በሚል መርህ የሚንቀሳቀሱት ሠራተኞች ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስ የሚችለውን እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በሠራተኛው በኩል በአንደኛ ምርጫችን አልተመደብንም የሚሉ ቅሬታዎች መነሳታቸውን አውስተው፤ የሠራተኛው ቅሬታ ዝርዝሮች ነጻና ገለልተኛ በሆነ መልኩ በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ቡድን መሪነት እየታዩ እየተፈቱ መሆናቸውን አብራርተዋል።

የክልል አደረጃጀት ጥያቄ በዋናነት የሕዝብ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ እና በእያንዳንዱ አካባቢዎች የሚነሱ ጉዳዮችን መፍታት በሚችል መልኩ እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።
የአሁኑ ጊዜ ለክልሉ የሽግግር ወቅት በመሆኑ የልማት ሥራዎች እንዳይጎዱ የ 120 ቀናት ዕቅድ በማዘጋጀት ሕዝቡ ከአስተዳደሩ ምን ይጠብቃል የሚለውን በመገምገም ወደ ሥራ መገባቱን ጠቁመው፤ ክልሉ ያሉትን ጸጋዎች በመጠቀም ለማሳካት እንደሚሠራም ተናግረዋል።

የክልሉ ህዝብ የክልሉ ስድስቱም ማዕከላት በእኩል ደረጃ ተደራጅተው ወደ ተግባር በመገባቱ በእጅጉ መደሰቱን ገልጸው፤ ይህንን ደስታ ወደ ልማት መቀየር ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ በስኬት የተመዘገቡ ሥራዎችን ለማሳደግ ወደ ኋላ የቀሩ ተግባራትን በማረም ለመስራት መታቀዱን ተናግረዋል።

የአመራር ሥርዓታችን ህዝብን መሠረት አድርገን ፍትሓዊነትን፣ አሳታፊነትንና ግልጸኝነትን መሠረት ያደረገ መሆን አለበት ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የተሻለ ጸጋ ያለው ክልል በመሆኑ ሕዝቡን አንቀሳቅሰን ያለንን ሀብት በቁጠባ በመጠቀም ተጨማሪ ሀብት ለማፍራት በጋራ እንደሚሠሩ አመልክተዋል።

እንደ አቶ ጥላሁን ገለጻ፤ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማጠናከር፣ የሀብት ጸጋን የመፍጠርና የማስተዳደር እንዲሁም የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ክልሉ ከሰላምና ጸጥታ ቀጥሎ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራባቸው ጉዳዮች ናቸው ማለታቸውን ኢፕድ በዘገቧው አመላክቷል ።
አሳታፊ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሥርዓት መፍጠርና ከቀበሌ ጀምሮ ያሉ መዋቅሮች የሕዝቦችን ጥያቄ በብቃት መመለስ እንዲችሉ ማድረግም የክልሉ የትኩረት አቅጣጫዎች ይሆናሉ ብለዋል። ክልሉ ለሰላም መደፍረስ ምክንያት በሆኑ በወሰን ጉዳዮች ላይ ከአቻና ከአጎራባች ክልሎች ጋር በቅንጅትና በመተባበር እንደሚሠራም ጠቁመዋ

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ከጂንካ-መንድር ያለውን የ53 ኪሎ ሜትር ኮንክሪት የአስፋልት መንገድ ግንባታ ሂደት ጎበኙ የደቡብ  ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደን ...
07/11/2023

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ከጂንካ-መንድር ያለውን የ53 ኪሎ ሜትር ኮንክሪት የአስፋልት መንገድ ግንባታ ሂደት ጎበኙ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች ከጂንካ-መንድር 53 ኪሎ ሜትር ኮንክሪት የአስፋልት መንገድ የግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል፡፡

በ2008 ዓ.ም የኮንትራት ውል ፈርሞ በሦስት ዓመት ግንባታውን ለማጠናቀቅ ጨረታውን በማሸነፍ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ፕሮጀክቱን የተረከበ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ግንባታውን ሳያጠናቅቅ ቆይቷል፡፡

መንገዱ መጠናቀቅ ከነበረበት ከአምስት ዓመታት በላይ የተጓተት መሆኑም ተገልጿል ።

የግንባተ ቁሳቁሶች የዋጋ ንረት፣ የካሳ ክፍያ እና መሰል ምክንያቶች መንገዱ እንዲጓተት እንደምክንያት በተቋራጩ በኩል ተጠቅሷል።

መንገዱ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ባለመጠናቀቁ ምክንያት መንግስት ተጨማሪ ወጪዎችን እንዲያወጣ የሚያደርግ በመሆኑ መንገዱ አሁን ያለበት ሁሉ አቀፍ ችግር ተፈትቶ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ በርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ አቅጣጫ ተቀምጧል ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ እና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባውዲ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ እና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች የመንገዱን የግንበታ ሂደት ተመልክተዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት ሴክቶሪያል ጉባኤ እያካሄደ ነው፣የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት ሴክ...
06/11/2023

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት ሴክቶሪያል ጉባኤ እያካሄደ ነው፣

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት ሴክቶሪያል ጉባኤ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገልገሎ ገልሾ እንደገለፁት ኮንሶ የሰው ልጅ ዕሴት ማበልጸጊያ እንዲሁም የተለያዩ ተፈጥሮአዊና ሰው ሠራሽ ባህላዊ ቅርሶች የሚገኙባት የቱሪስት መስህብ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ገልገሎ በኮንሶ በዓለም የቅርስ መዝገብ የተመዘገቡ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ቅርሶች ሀገራችን ኢትዮጵያ በአፍሪካ አልፎም በዓለም እንዲትታወቅ በማድረግ አስተዋጽኦ ያበረከተ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት ዱባሌ በበኩላቸው የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ለሀገራችን ብልጽግና ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።

ወ/ሮ ፍሬህይወት አክለውም ከአገልግሎት ሰክተሮች መካከል የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ኢኮኖሚ ከማሳደግ ባሻገር በክልሉ የሚገኙ የብሔረሰቦች ቋንቋና ባህልን ለማሳደግ እንዲሁም በህዝቦች መካከል አብሮነትን ለማጎልበት መሠረት የሚጥል እንደሆነ አብራርተዋል።

የእለቱ የክቡር እንግዳ እና የክልሉ መንግስት ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ የቱሪዝሙ ዘርፍ በመንግሥት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ አድስ የሀብት ምንጭ ሆኖ እየተሰራ ይገኛል

ሃላፊው አክለውም ባህል የክልላችን ህዝብ የማንነት መገለጫ ነው ስለሆነም ከቱሪዝም ዘርፍ ባለተናነሰ ትኩረት በማልማት ለሀገራችን ኢኮኖሚ ብልፅግና የላቀ ድርሻ እንድያበረክት መስራት ይገባል።

ጉባኤው በተለያዩ ባህላዊ ጭፈራዎች የተጀመረ ሲሆን በመድረኩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፣የየዞኖች አመራሮች፤ ባለድርሻ አካላት እና ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል ።

የ2015 ዓ.ም  12ኛ ክፍል ተፈታኞች አቅም ማሻሻያ (Remedial Program) መከታተያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ። በ2015 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ...
03/11/2023

የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተፈታኞች አቅም ማሻሻያ (Remedial Program) መከታተያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

በ2015 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም መከታተያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።

የከፍተኛ ትምህርት የአስተዳደርና መሠረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር ) እንደገለጹት በ2016 በግልና የመንግስት ተቋማት የአቅም ማሻሻያ /Remedial Program / የሚከታተሉ ተማሪዎች መቁረጫ ነጥብ እንደተፈተኑት የትምህርት ዓይነት ብዛት 30% እና ከዚያ በላይ ሆኗል ።

በዚህም መሠረት በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር የመቁረጫ ነጥብ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 255 የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 234 መሆኑን አስታውቀዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 218 የማህበራዊ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 200 መሆኑን ተናግረዋል።

ታዳጊ ክልሎች የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 224 ታዳጊ ክልሎች ተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 210 መሆኑን ተናግረዋል።

ታዳጊ ክልሎች የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች መግቢያ 192 ታዳጊ ክልሎች ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች መቁረጫ180 መሆኑን አመልክተዋል።

አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ በሁለቱም ፆታ 210 መሆኑን ተናግረዋል።

አርብቶ አደር አካባቢ ማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ በሁለቱም ጾታ 180 መሆኑን ገልጸዋል።

የዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች መቁረጫ ነጥብ በሁለቱም ጾታ ደግሞ 150 መሆኑንም ዶ/ር ሰለሞን ጠቅሰዋል።

ዶ/ር ሰለሞን እንደገለጹት የ2015 ትምህርት ዘመንን ተሞክሮን ከግምት ውስጥ በማስገባት የገጠመውን የውጤት መቀነስ ለማስተካከል በ2016 ትምህርት ዘመን የማካካሻ ትምህርት (Remedial Program) በድጋሚ እንዲተገበር ተወስኗል።

በመቁረጫ ነጥቡ መሰረት የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራሙን የሚከተተሉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ በቀጣይ ይካሄዳል።

Address

S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Ethiopia Regional State posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share