04/09/2026
የኢትዮጵያ ማንሰራራት!
የዘንድሮው የጳጉሜን ወር "የኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮች ይከበራል።
ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ዘርፈ-ብዙ ድሎችን እያስመዘገበች፣ ውስብስብ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎችን በፅናትና በፈጠራ በመሻገር፣ በአሁን ወቅት በማንሠራራት ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።
የጳጉሜን ወር በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ዘይቤ ውስጥ ወደ አዲሱ ዓመት መሸጋገሪያ ድልድይ በመሆን የተገኙ ወረቶች የሚደመሩበት እንዲሁም ለቀጣዩ ዓመት የከፍታ ጉዞ አዲስ ተስፋ የሚሰነቅበት ልዩ ሀገራዊ መለያችን ነው።
የዘንድሮው የጳጉሜን ቀናት አከባበር የነበሩ ጥንካሬዎችን የሚያስቀጥል፣ የታዩ ክፍተቶችን የሚያርም፣ አዳዲስ የፈጠራ ስልቶችን ታሳቢ ያደረገ፣ የቴክኖሎጂ አቅሞችን በሚገባ የሚጠቀም፣ የተመዘገቡ ትላልቅ ስኬቶችን የሚያስታውስ፣ አዳዲስ ብስራቶችን የሚያበስር በመሆሃ በሳቢ ኹነቶችና የንቅናቄ መንገዶች የሚመራ ይሆናል።
የ 2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት ከቀደሙት ዓመታት በተለየ መልኩ በብሥራት፣ በተስፋ እና በሁለንተናዊ የብልጽግና ራዕይ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚከበርም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ተናግረዋል።
የ 2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት፤ ጳጉሜን 1 (የእመርታ ቀን)፣ ጳጉሜን 2 (የማንሰራራት ቀን)፣ ጳጉሜን 3 (የጽናት ቀን)፣ ጳጉሜን 4 (የኅብር ቀን) እንዲሁም ጳጉሜን 5 (የነገ ቀን) በሚሉ መርሃ-ግብሮች በድምቀት የሚከበሩ ይሆናል።