Asaminew Ayza

Call Directions Website Contact the organization

Asaminew Ayza When we move forward together, there is no goal we cannot reach. and for more information use my telegram link
https://t.me/s/asaminew2016

I am an enthusiastic Politician based in Sodo, Wolaita, Ethiopia, with a rich experience of over 20 years in Leadership & Management.

እንኳን ለዚህ ታሪካዊ የሰነድ ርክክብ ቀን አበቃን አጀንዳዎቹና ምክረ ሐሳቦቹ ወደ ተግባር ተለውጠው ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና አንድነት መንገዱን እንደሚጠረጉ ተስፋ እናደርጋለን።
03/10/2026

እንኳን ለዚህ ታሪካዊ የሰነድ ርክክብ ቀን አበቃን አጀንዳዎቹና ምክረ ሐሳቦቹ ወደ ተግባር ተለውጠው ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና አንድነት መንገዱን እንደሚጠረጉ ተስፋ እናደርጋለን።

እንኳን አብሮን አደረሰን!!
03/10/2026

እንኳን አብሮን አደረሰን!!

መልካም የሥራ ጊዜ መሪያችን
02/10/2026

መልካም የሥራ ጊዜ መሪያችን

መሪዎቻችን መልካም የሥራና የስኬት ጊዜ
02/10/2026

መሪዎቻችን መልካም የሥራና የስኬት ጊዜ

መልካም የሥራ ጊዜ
02/10/2026

መልካም የሥራ ጊዜ

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ  መልካም የሥራ ጊዜ
02/10/2026

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ መልካም የሥራ ጊዜ

ክብርት ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክርቤት ዋና አፌ-ጉባኤ በመሆን ተሹመዋል።መልካም የሥራ ዘመን
02/10/2026

ክብርት ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክርቤት ዋና አፌ-ጉባኤ በመሆን ተሹመዋል።
መልካም የሥራ ዘመን

እንኳን የጎፋ ጋዜ ማስቃላ እና የኦይዳ ዮኦ ማስቃላ የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን !!መልካም ጋዜ ማስቃላ መልካም ዮኦ ማስቃላ! !
24/09/2026

እንኳን የጎፋ ጋዜ ማስቃላ እና የኦይዳ ዮኦ ማስቃላ የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን !!

መልካም ጋዜ ማስቃላ መልካም ዮኦ ማስቃላ! !

ወደ ዳሞታ ከፍታ ሲወጡ፣ የሚታዩት ደረጃዎች ብቻ አይደሉም። ከእያንዳንዱ ደረጃ ጀርባ የአካባቢው ህዝብ ተስፋ፣ የቱሪዝም እድል እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ይታያል።
23/09/2026

ወደ ዳሞታ ከፍታ ሲወጡ፣ የሚታዩት ደረጃዎች ብቻ አይደሉም። ከእያንዳንዱ ደረጃ ጀርባ የአካባቢው ህዝብ ተስፋ፣ የቱሪዝም እድል እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ይታያል።

ቅድመ ዝግጅት ሕይወትን ያድናል፤ ትብብር ደግሞ አደጋን ይቀንሳል።
22/09/2026

ቅድመ ዝግጅት ሕይወትን ያድናል፤ ትብብር ደግሞ አደጋን ይቀንሳል።

በድንገተኛ ዝናብ ምክንያት ልከሰት የሚችል የተፈጥሮ አደጋን ለመከላከል ህብረተሰቡ ዝግጅት እንዲያደርግ የክልሉ ጤና ቢሮ ሕበብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ጥሪ አስተላለፈ፡፡

ባለፉት 2 ወራት ተከስቶ የነበረውን የወባ በሽታ ወረርሽኝ እና የተወሳሰበ ሥርዓተ ምግብ አለመመጣጠን በሽታን ለመቆጣጠር የተደረገው ርብብር ውጤት ማስገኘቱን ኢንስትቲዩት አስታውቋል፡፡

የኢንስትቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉ አሾሌ የተፈጥሮ የመሬት ናዳ እና ጎርፍ አደጋን ለመከላከል ህብረተሰቡ ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል
መስከረም 12/01/2019 ሕብረተሰብ ጤና | ጂንካ
__________

የክልሉ ጤና ቢሮ ከክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ጋር በመቀናጀትና ታችኛው የጤና መዋቅርን በማስተባበር በተመረጡ 26 ወባማ ወረዳዎች IMS እና የተወሳሰበ ሥርዓተ ምግብ በስፋት የታየባቸው 32 ወረዳዎችን በመለየት የመከላከል ሥራ ተሰርቷል፡፡

የወባ በሽታ ወረርሽኝ ስርጭት ባለፉት ሁለት ወራት በሣምንት 36 ሺህ ሰዎች በላይ የወባ ህክምና እንደሚያደርጉና ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩቱ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ባደረገው ርብርብ ወደ 11 ሺህ ወባ ታካሚወች ዝቅ ማድረግ ተችሏል፡፡

ከክልል ጀምሮ እስከ ቀበሌ ጤና ኤክስተንሽን ባለሙያች ድረስ የነበረው የተግባር አንድነት ህብረተሰቡን ከወባ ወረርሽኝ ለመታደግና ህፃናትና ነፍሰጡር እናቶች በተወሳሰበ ሥርዓተ ምግብ በሽታ እንዳይጎዱ በቅንጅት ተሰርቶ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡

ሁለቱን ድንገተኛ ቀውሶችን ለመከላከልና አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በክልሉ ጤና ቢሮ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የተቋቋመ IMS ግብረ-ኃይል በሁሉም ዞንና ጤና መዋቅር በማቋቋም ቤት ለቤት ክትትል፣ አጎበር አጠቃቀም ስርዓትን ማሻሻል፣ ኬሚካል ርጭቶችን ማካሄድ፣ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን ማፋሰስና ብንቢ መራቢያ ሥፍራዎችን በማህበረሰብ ተሳትፎ በማጽዳት የወባን በሽታ የስርጭት ምጣነኔ መቀነስ ተችሏል፡፡

የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ በመግለጫቸው በሣምንት 3 ቀናት በአካልና በቨርችዋል ክትትልና ግምገማ በማድረግ ወባ ወረርሽኙ ካለበት በእጅጉ ዝቅ ማድረግ እንደተቻለ አስታውቀዋል፡፡

የተወሳሰበ ሥርዓተ ምግብ በሽታን ለመከላከል በቂ የህክምና ግብዓት ተደራሽ በማድረግ፣ ህፃናት በጤና ተቋማት ብቻ እንዲታከሙ በማድረግ ችግሩን መከላከል ተችሏል፡፡

የአየር ንብረት መዛባት ምክንያት ሊከሰት የሚችል ያልተጠበቀ ከፍተኛ ዝናብ እና የድርቅ አደጋ ክስተት ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ ከወዲሁ ጥቅንቃቄ እንዲያደርግም ጥሪ ተላልፏል፡፡

ባለፉት 3 ሣምንታት ወዲህ ‹‹ከተረጂነት ወደ ምርታማነት!›› በሚል መሪህ ሀብት የማሰባሰብ ሥራ መጀመሩን በመግለጫቸው ያሰሙት አቶ አጉኔ፤ የኢሌኖ ክስተትን ተከትሎ ሊከሰት የሚችል የጎርፍ፣ የመሬት ናዳ፣ ኮሌራ በሽታ እና ሌሎች ችግሮችን ለመከላከል ከወዲሁ ንቁ መሆን ይገባል ብለዋል፡፡

ከአየር ንብረት መዛባት ምክንያት የሚኖር እርጥበታማ ወቅት የክፉኝ በሽታ ክስተትን ለመከላከል ህብረተሰቡ ከወዲሁ ህፃናትን የማስከተብ ባህሉን እንዲያጠናክር ጭምር አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም የወንዞች ሙላትን ህብረተሰቡ ጥንቃቄ በማድረግና ከአደጋ ራሱን በመጠበቅ፤ ውሃን አክሞ በመጠቀም የተለያዩ በሽታዎችን መከላከል ይገባል።

በመጨረሻም ለወረርሽኝ ቁጥጥሩ የክልል ጤና አመራርና ባለሙያዎች፣ ዞን እና ወረዳ አመራርና ጤና ባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላትና ቀበሌ አመራርና ነዋሪዎች በጋራ ቅንጅት የተገኘ ውጤት በመሆኑ አቶ አጉኔ ከልብ አመስግነዋል፡፡

ነገር ግን አሉ ዋና ዳይሬክተሩ በመግለጫ ማጠቃለያቸው፤ የወባ በሽታና የተወሳሰበ ሥርዓተ ምግብ ችግሮቹ ዳግም እንዳያገረሹ በሁሉም የክልሉ አከባቢ የተጀመረውን የመከላከልና ቁጥጥር ሥርዓትን ማጠናከር ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

አቶ አጉኔ አሾሌ
የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር
መስከረም 12/01/2019

Address

Wolaita Sodo, Ethiopia, Arba Mintch, Ethiopia , Addis Ababa
Sodo
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Asaminew Ayza posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Asaminew Ayza:

Shortcuts

Share