06/09/2026
ጳጉሜ 1 — የእመርታ ቀን
ከተስፋ ወደ እመርታ!
ሀገራችንን ከተረጂነት ለማላቀቅና በራሷ አቅም የምትቆም ኢትዮጵያን ለመገንባት የተያዘው የእመርታ አቅጣጫ ከቃል ባሻገር ወደ ተጨባጭ ተግባር እየተቀየረ ይገኛል።
በምግብ ራስን መቻል፣ ምርታማነትን ማሳደግ፣ የሥራ ዕድል መፍጠርና ሀገራዊ ሀብትን ወደ ምርት መቀየር የዚህ የእመርታ ጉዞ ዋና አቅጣጫዎች ናቸው።
ይህንን ሀገራዊ ጉዞ በክልላዊ ደረጃ በማጠናከር፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የሕዝቡን አቅምና ያሉትን የልማት ሀብቶች በማስተሳሰር ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ እየሠራ ይገኛል።
በግብርናና መስኖ፣ በቡናና ኮረሪማ፣ በኢንዱስትሪና ንግድ፣ በውሃና መንገድ ልማት፣ በትምህርትና ጤና፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በቱሪዝምና ባህል፣ እንዲሁም በበጎ ፈቃድና የሕዝብ ተሳትፎ የተደረጉ ጥረቶች የእመርታው ጉዞ ተጨባጭ አካላት ናቸው።
እመርታ የአንድ ቀን ውጤት ሳይሆን፣ በየቀኑ በተግባር የሚፈጠር ውጤት ነው።
በአዲሱ ዓመትም የተጀመረውን የእመርታ ጉዞ የበለጠ ለማፋጠን፣ ክልላዊ አንድነታችንንና ትብብራችንን በማጠናከር ሁላችንም የየበኩላችንን አስተዋጽኦ በማበርከት ለእመርታው ጉዞ መረባረብ ይጠበቃል።