South Ethiopia Regional State Police Commission

South Ethiopia Regional State Police Commission ይህ የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ነው። ገፁን ላይክ ሼርና ኮሜንት በማድረግ ፖሊሳዊ መረጃዎችን በየዕለቱ ይከታተሉ! https://t.me/Southpolicecomm

በጊዜያዊ ግጭት ምክንያት ትዳር አጋሯን የገደለችው ግለስብ በ20 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቷን የኮሬ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ።ወላይታ  ሶዶ ነሐሴ 1/2018 ዓ/ም (ደ.ኢ.ፖ.ኮ) ተከ...
07/08/2026

በጊዜያዊ ግጭት ምክንያት ትዳር አጋሯን የገደለችው ግለስብ በ20 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቷን የኮሬ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

ወላይታ ሶዶ ነሐሴ 1/2018 ዓ/ም (ደ.ኢ.ፖ.ኮ)

ተከሳሽ ተስፋነሽ ዘለቀ በእስራት ልትቀጣ የቻለችው በኮሬ ዞን ሳርማላ ወረዳ ቢደርባ ማናና ቀበሌ ውስጥ ታህሳስ 21/2018 ዓ/ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ላይ የትዳር አጋሯን በቆጮ መቁረጫ ቢላዋ ቆርጣ በመግደሏ ነው።

ግለሰቧ በእለቱ ቤት ውስጥ በተፈጠረ አለመግባባት ከቤት በመውጣቷ ምክንያት ሟች ባለቤቷ ፍለጋ ጀምሯል ጎረቤት በመሔድም ጠይቆ እዛ እንዳልሔደች አረጋግጦ በምሽት የት ገብታ ይሆን በሚል ባትሪ አብርቶ ወደ ጓሮ ሲገባ ስለት ይዛ አድፍጣ ትጠብቀው የነበረ ሲሆን አንገቱ ላይ በጭካኔ በማሳረፍ ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጓ ተረጋግጧል።

ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱ እንደተፈጸመ ተጠርጣሪዋን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራውን በሰውና በሰነድ ማስረጃ አስደግፎ ለአቃቤ ህግ ልኳል።

አቃ-ዐቤ ህግም ክስ መስርቶ ለኮሬ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል።

የኮሬ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የተከሳሽ ተስፋነሽ ዘለቀን መዝገብ ከተመለከተ በኋላ ጥፋተኛ ሆና በመገኘቷ ሐምሌ 29/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን ያስተምራል ሌላውን ያስጠነቅቃል በሚል በ20 ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኗል።

ምንጭ የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት ነው።

ሳምንታዊ የትራፊክ መረጃባሳለፍነው አንድ ሳምንት በክልሉ የተለያዩ ዞኖች በደረሰ ስድስት የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰው ህይወት ማለፉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከ...
06/08/2026

ሳምንታዊ የትራፊክ መረጃ

ባሳለፍነው አንድ ሳምንት በክልሉ የተለያዩ ዞኖች በደረሰ ስድስት የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰው ህይወት ማለፉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሮክቶሬት አስታወቀ።

ወላይታ ሶዶ ሀምሌ 30/2018 ዓ.ም (ደ.ኢ.ፖ.ኮ)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የትራፊክ አደጋ ግንዛቤ መፍጠር ዲቪዥን ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ፍሬው ክፈለው በላኩልን መረጃ መሠረት በሳምንቱ ውስጥ ስድስት የትራፊክ አደጋ መመዝገቡን ገልጿል።

በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ሁለት ቀናት በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሁለት ሰው ላይ የሞት አደጋ የደረሰ ሲሆን የአደጋው መንስኤ ጥንቃቄ ጉድለት እንደሆነ መረጃው አትቷል።

በጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ከመላ ናሆ ወደ ሰላም በር ሲንቀሳቀስ የነበረው ባለሶስት እግር ባጃጅ ተገልብጦ አንድ ሰው ላይ ከባድና አንድ ሰው ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ማድረሱ ታውቋል።

በጎፋ ዞን በቶ ከተማ አስተዳደር ከኡባ ደብረፀሀይ ወደ በቶ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሞተር ሳይክል ከሞተር ሳይክል ጋር ተጋጭተው አንድ ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት አስከትሏል።

በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በተለያዩ ሁለት ቀናት በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሁለት ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት አድርሷል።

ባሳለፍነው አንድ ሳምንት ከደረሱ ስድስት የትራፊክ አደጋዎች ውስጥ አራት በባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል መሆኑን የተላከልን መረጃ ይናገራል።

በሪፖርተር ፅጌረዳ እያሱ

 የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ንብረት የሆነውን ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣውን ሶስት ማይክሮስኮፕ ማሽን የሰረቀ ግለሰብ...
05/08/2026



የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ንብረት የሆነውን ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣውን ሶስት ማይክሮስኮፕ ማሽን የሰረቀ ግለሰብ በ7 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ ።

ወላይታ ሶዶ ሐምሌ 29/11/18 ዓ.ም (ደኢፖኮ)

ተከሳሽ እንድሪያስ ቶማስ ግያ የተባለው ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪና ሪፈራል ሆስፒታል የጥበቃ ሠራተኛ ሆኖ እያለ በቀን 22/11/2018 ዓ/ም ረቡዕ ዕለት ከምሽቱ 4:00 እስከ 6፡00 ባለዉ ጊዜ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪና ሪፈራል ሆስፒታል ንብረት የሆነውን በቁጥር 03/ሶስት/ ማይክሮስኮፕ የእያንዳንዳቸዉ ዋጋ ብር 350,000/ሶስት መቶ ሀምሳ ሺ/ በድምሩ ብር 1,050,000/አንድ ሚሊዮን ሀምሳ ሺ/ የሚያወጣዉን ከክፍሉ ሠራተኞች ጋር በመተባበር ንብረቱ ያለበትን ክፍል በቁልፍ ከፍቶ ከወሰደ እና ንብረቱን በተቋሙ ዉስጥ ባለዉ ሳርና ሀረግ ዉስጥ ደብቆ ካቆዬ በኋላ በአራተኛዉ ቀን በቀን 25/11/2018 ዓ/ም ከምሽቱ 9፡00 ንብረቱን ከደበቀበት ሥፍራ አንስቶ ይዞ ሲሔድ መያዙ ይታወቃል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፍትህ መምሪያ ዐ/ሕግ ያቀረበውን ክስ ሲያከራክር የቆየው የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ ሙሉ በሙሉ ያመነ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት የጥፋተኝነት ውሳኔ ካሳለፈ በኃላ ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ ያመነ መሆኑን፣ የቤተሰብ አስተዳደር እንዲሁም ቀደም ስል የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት በ7 አመት ጽኑ እስራት እንድቀጣ ውሳኔ አሳልፎል።

የተሰረቀው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዋጋ የሚያወጣው ማይክሮስኮፕ ለኦቶና ሪፌራል ሆስፒታል ተመላሽ መደረጉንም ከመዛግብቱ ማረጋገጥ ተችሏል ።

ባሳለፍነው በጀት አመት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 371የትራፊክ አደጋዎች ማጋጠማቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ አስታወቀ።ወላይታ ሶዶ ሐምሌ 29/2018 ዓ...
05/08/2026

ባሳለፍነው በጀት አመት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 371የትራፊክ አደጋዎች ማጋጠማቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ አስታወቀ።

ወላይታ ሶዶ ሐምሌ 29/2018 ዓ/ም(ደ.ኢ.ፖ.ኮ)አደጋው ከ2017 ዓ/ም ጋር ሲነፃፀር 9.7% ቀንሷል።

በክልሉ ስር ባሉ የተለያዩ አከባቢዎች 371 የትራፊክ አደጋዎች ማጋጠማቸው የተገለጸ ሲሆን ከ2017 ዓ/ም ጋር ሲነፃፀር የአደጋ ብዛት በ21 ሞት 6 ከባድ የአካል ጉዳት በ17 የቀነሰ ሲሆን ቀላል የአካል ጉዳት ግን በ45 ጨምሯል ተብሎአል።

ዘርፉ በተለያዩ የወንጀል መከላከል ተግባራት በወንጀል መከላከል፣ በተቋማትና ቪአይፒ ጥበቃእንዲሁም የከፍተኛ አመራሮች አጀባ፣ሀገራዊ ምርጫን በሰላም በማጠናቀቅ፣ህገ-ወጥ የሰዎችና የጦር መሳሪያ ዝውውርና በድንበር አከባቢና ድንበር ተሻጋሪ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ከመከላከል አንፃር የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ የሚንቀሳቀስ ኮንትሮባንድ ለመቆጣጠር በተደረገ ጥረት አዘዋዋሪ ናቸው የተባሉ 112ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም ታውቋል።

ከህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ቁጥጥርና ሌሎች ተግባራት ዘርፉ በትኩረት መስራቱን የገለጹት የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነርና የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ቁጥጥር ዘርፍ ሀላፊ ኮማንደር ደግፌ ደበላ በበጀት አመቱ በጥንካሬ የታዩ ስራዎችን አጠናክረን በመቀጠልና ክፍተት የታየባቸውን በማረም በቀጣይ የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።

ማህበረሰቡን የሚመጥን የፖሊስ ተቋም ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኑንበጌዴኦ ዞን የጮርሶ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።ወላይታ ሶዶ ሐምሌ 28/2018 ዓ/ም(ደኢፖኮ)፦ፖሊሳዊ አገልግሎቶችን ለ...
04/08/2026

ማህበረሰቡን የሚመጥን የፖሊስ ተቋም ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኑንበጌዴኦ ዞን የጮርሶ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።

ወላይታ ሶዶ ሐምሌ 28/2018 ዓ/ም(ደኢፖኮ)፦

ፖሊሳዊ አገልግሎቶችን ለማህበረሰቡ ማድረስ ተቀዳሚ የፖሊስ ተግባር ሲሆን አገልግሎቱን ለሚጠቀሙ ማህበረሰባችን የሚመጥን የፖሊስ ተቋም እንዲኖር ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን የጮርሶ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታዉቋል።

ከሪፎርም ተግባራት መካከል አንዱ የሆነዉ የፖሊስ ተቋማቶች ለፖሊስ እና ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ምቹ ለማድረግ በማሰብ ጥር 16/2018 ዓ/ም ለወረዳዉ ፖሊስ ህንጻ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ መቀመጡን ተመላክተናል።

በዚህ የፖሊስ ህንጻ ግንባታ ዙርያ የጌዴኦ ዞን አስተዳደርና የወረዳ አስተዳደር እንዲሁም የአከባቢዉ ባለሀብትና የጮርሶ ወረዳ ነዋሪዎች በጉልህ ተሳትፈዉበታል።

የፖሊስ ህንጻ ግንባታን በታለመለት ግዜ ጀምሮ ለማጠናቀቅ ቃል የገቡ የመንግስት እና የግል ድርጅቶች በገንዘብ እና በአይነት ድጋፍ እያደረጉ ሲሆን በቅርብ ቀን ግንባታዉን ለማስጀመር ዝግጅት ላይ እንደሚገኙ የጮርሶ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገልጿል።

ግንባታዉን ለማከናወን የዲዛይን ስራ እና ቦታዉን ለግንባታ ምቹ የማድረግ ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ የጌዴኦ ዞን ፖሊስ አዛዥ እና የወረዳዉ አስተዳደር በተገኙበት በይፋ ግንባታ የሚጀምር ሲሆን ለዚህ ግንባታ ድጋፍ ቃል የገባችሁ ገቢ እንድታደርጉ እየጠየቅን ለዚህ ተግባር ስኬት ሁሉም መረባረብ እንደሚገባዉ ተጠይቋል።

የጮርሶ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የህንጻ ግንባታ ኮሚቴ ግንባታዉ በታለመለት ግዜ ለማጠናቀቅ ያስችለን ዘንድ ድጋፍ ማድረጊያ አካዉንት ቁጥር ይፋ ያደረገ ሲሆን ከዚህ በታች ባለዉ አካዉንት ቁጥር ድጋፍ እንድታደርጉ ከወዲሁ ይጠይቃል።

1000743750113 ኢንትዮጵያ ንግድ ባንክ

"ኮንሶ በጥበብ ስራው አለምን  ያስደመመ፣ ተፈጥሮን ቀጥቅጦ ያስገበረ ብልሃተኛና ታታሪ ሕዝብ ሲሆን እኩይ ተግባር በሚፈጽሙ አካላት ዝናው ሊኮስስ  አይገባም" — የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ...
04/08/2026

"ኮንሶ በጥበብ ስራው አለምን ያስደመመ፣ ተፈጥሮን ቀጥቅጦ ያስገበረ ብልሃተኛና ታታሪ ሕዝብ ሲሆን እኩይ ተግባር በሚፈጽሙ አካላት ዝናው ሊኮስስ አይገባም" — የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሐ ጋርደው።

ወላይታ ሶዶ ሐምሌ 28/11/2018 (ደኢፖኮ)በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ ዞንና አከባቢው የመዋቅር ጥያቄን ሰበብ በማድረግ የህዝቡን ሰላም ያውኩ የነበሩ አካላት በእርቀ ሰላም ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለዋል።

በኮንሶ ዞንና አከባቢው በህገ-ወጥ መንገድ በመደራጀት የመዋቅር ጥያቄን ሽፋን በማድረግ በአከባቢው ነዋሪዎች ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በመፈጸም ሰላም ይነሱ የነበሩ አካላት ያሰቡትን ለማሳካት የሔዱበት መንገድ ፍጹም የማያዋጣ መሆኑን በመረዳት ትጥቃቸውን በመፍታት በእርቀ ሰላም ከማህበረሰባቸው ጋር ተቀላቅለዋል።

ይህ ይሆን ዘንድ ዋጋ የከፈሉ የሀገር ሽማግሌዎች፣የሀይማኖት አብቶች፣ የመስተዳድር አካላት፣ በተለያየ አደረጃጀት የሚገኙ የፀጥታ አካላት፣የእርቀ ሰላም ኮሚቴዎችና የአከባቢው ህዝብ ባደረጉት ጥረት ከህግና ስርዓት ውጪ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላት መንግስትና ህዝብ ይቅርታ አድርጎላቸው ወደ ሰላማዊ ኑሮአቸው እንዲመለሱ ተደርጎአል።

በመድረኩ የተገኙት ‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሰሃ ጋርደው ባስተላለፉት መልእክት በሰው ልጆት ህይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሠላም ካለ በጎ ነገሮች ሁሉ ይኖራሉ ያሉ ሲሆን ሠላሙን ያጣ ህዝብ በምድር ላይ ያሉ በረከቶችን ሁሉ ያጣል ብለዋል።

ይህን የተረዳ ማህበረሰብ ደግሞ ሰላሙን ሊነሱ የሚችሉ ሁኔታዎችን አስቀድሞ በመከላከል የበረከት ፍሬውን ያለአንዳች አደናቃፊ መልቀም ይችላል ነው ያሉት።

የሀገራችንን ሰላምና ልማት ከማይወዱ ሀይሎች የማይጠቅም አፍራሽ ተልእኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላት የትኛውም ጥያቄ ከህግና ስርዓት ውጪ መመለስ አንደማይቻል ተረድተው በሰላማዊ መንገድ ከህዝባቸው ጋር ለመኖር ጠይቀዋል ያሉት ኮሚሽነሩ መንግስትና ህዝብም በሆደ ሰፊነት ይቅርታቸውን ተቀብለው በዛሬው እለት ከህዝባቸው ጋር መቀላቀላቸውን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ በሌላም የክልሉ አካባቢ ሀሳብን ወይም ማንኛውንም ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ከማቅረብ ይልቅ ኃይል ለመጠቀም የሚሞክሩ ቡድኖች ከዛሬው ዕለት እርቅ ትምህርት ይወስዳሉ ብዬ አምናለሁ ያሉት ኮሚሽነሩ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት በሚያውኩ ኃይሎች ላይ የማስተካከያ እርምጃ የመውሰድ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስበዋል።
‎‎
‎ሁሉ አቀፍ ወረዳዊ እርቀ ሠላም ኮንፈረንሱ በኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ ሲካሔድ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ዳርጌ ዳሼ የክልሉ ረዳት የመንግስት ተጠሪ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ኢንጂነር ፍሬዘር ኮርቦይዶ፣፣ የክልሉ ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎች፣የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ እና የዞኑ የፊት አስተባባሪዎች፣የዞኑና የወረዳው አመራሮች፣የሠገን ዙሪያ ወረዳ ቀበሌያት ተወካዮች፣ከአጎራባች ዞኖች የጋርዱላ ዞን ዲራሼ ወረዳ፣የኧሌ ዞን፣የኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ፣የቡርጂ ዞን ሶያማ ዙሪያ ወረዳ አመራሮችና የቀበሌያት ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።

‎የጌዴኦ ዞን ፖሊስ አዛዥ ሆነው በፍጹም ቅንነት አገልግለው ጡረታ ለወጡት ኮማንደር ይልማ ታደሰ ቤት አስገንብቶ ለማስረከብ ግንባታ አስጀመረ። ወላይታ ሶዶ ሐምሌ 28/2018 ዓ/ም(ደኢፖኮ)፦...
04/08/2026

‎የጌዴኦ ዞን ፖሊስ አዛዥ ሆነው በፍጹም ቅንነት አገልግለው ጡረታ ለወጡት ኮማንደር ይልማ ታደሰ ቤት አስገንብቶ ለማስረከብ ግንባታ አስጀመረ።

ወላይታ ሶዶ ሐምሌ 28/2018 ዓ/ም(ደኢፖኮ)፦

‎በኢትዮጵያ ሀገራችን ዳር ድንበር በመጠበቅና ዕድሜአቸውን ሙሉ ለህዝብ ሰላም በመስጠት በጡረታ ተገልለው የሚገኙ ኮማንደር ይልማ ታደሰ ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ የቦታ ጥርጊያ ተደርጓል።

‎የጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያና ዲላ ከተማ በጋራ በመሆን የቦታ ማጽዳት እና የግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አከናውኗል።

‎የጌዴኦ ዞንን በመሩት ፖሊስ አዛዦች መካከል ጨዋና ኩሩ፣ እጃቸውና ልባቸው ንጹሕ ፣ ከራሳቸው ጥቅም ይልቅ ለሀገርና ለህዝብ ቅድሚያ በመስጠት የሚታወቁ ቅን መሆናቸው ይነገርላቸዋል ኮማንደር ይልማ ታደሰ።

‎ቀደም ሲል ይኖሩበት የነበረ መኖሪያ ቤታቸው እጅግ የደከመ እና እኝህን የሀገር ባለውለታ የማይመጥን በመሆኑ ዳግም መገንባት እንዳለበት ከስምምነት ተደርሷል።

‎ይህን አስመልክተው ባለፈው ሳምንት የክልላችን ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሐ ጋረደው በዲላ ከተማ ከሚገኙ በጎ ስራ ተባባሪ ባለሀብቶች ጋር ውይይት አድርገው እንቅስቃሴ መጀመሩ ተመላክቷል።

‎የአገልግሎት ዘመናቸውን ቅንነታቸውን ለህዝብ ያላቸውን ክብር የሚመጥን መኖሪያ ቤት በአጭር ጊዜ ተገንብተው እንዲያልቅ ኮሚቴ ተቋቁመው ወደ ስራ የተገባ ሲሆን መላ የዞናችንና የሀገራችን ልቤ-ቅን ተባባሪዎች የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ እንዲደረግ የከበረ ጥሪ ቀርቧል።

የአስተባባሪ ኮሚቴ ፦
መብራቴ &መሰረት &መስፍን
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከታች ባለዉ አካዉንት ቁጥር ድጋፍ ማድረግ ይቻላል

1000776307312


በጋሞ ዞን የዲታ ወረዳ ፖሊስ ጽፈት ቤት ያስገነባው ቢሮ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አደረገ።ወላይታ ሶዶ ሐምሌ 28/2018 ዓ/ም (ደ.ኢ.ፖ.ኮ)በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሪፎርም እቅድ መሠረት...
04/08/2026

በጋሞ ዞን የዲታ ወረዳ ፖሊስ ጽፈት ቤት ያስገነባው ቢሮ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አደረገ።

ወላይታ ሶዶ ሐምሌ 28/2018 ዓ/ም (ደ.ኢ.ፖ.ኮ)

በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሪፎርም እቅድ መሠረት በሁሉም የፖሊስ መዋቅሮች ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የስራ ቦታን ምቹ የማድረግ ተግባር በተለያዩ የፖሊስ ተቋማት ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

በጋሞ ዞን ዲታ ወረዳ ፖሊስም ቢሮውን በአዲስ መልክ አስገንብቶ በዛሬው ቀን ለምርቃት አብቅቷል።

በዚሁ የምረቃ ስነስርዓት ላይ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ገፈሮ ቶማስ ዛሬ የተመረቀው የፖሊስ አገልግሎት መስጫ ማዕከሉ ከ3.5 ሚሊየን ብር ባላይ በሆነ ወጪ የተገነባ ሲሆን ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ 16 ክፍል ያለው መሆኑን ተናግረዋል።

የዚህ አገልግሎት መስጫ ማዕከል የግንባታ ወጪ ሙሉ በሙሉ በህብረተሰቡ መሸፈኑን የገለጹት ሃላፊው በገንዘብ በጉልበትና በሀሳብ ለረዱ አካላት በሙሉ በወረዳው ፖሊስ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የዲታ ወረዳ አስተዳዳሪ ዶክተር አሸናፊ ኦይዳ በበኩላቸው ዛሬ የተመረቀው የወረዳው ፖሊስ ጽፈት ቤት ከዚህ ቀደም የነበረው ቢሮ አገልግሎት ለመስጠት ምቹ ባለመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት በመነጋገር ህብረተሰቡን በማወያየት ወደ ስራ ተገብቶ በዛሬው እለት ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን መደረጉን ተናግረዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ ጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አብርሃም ቡሄ እንደገለጹት ፖሊስ ከመደበኛ ዕቅድ በተጨማሪ የሪፎርም ዕቅድን ተግባራዊ በማድረግ በጋሞ ዞን ባሉ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የፖሊስ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በማስገንባት ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።

ዛሬ የዲታ ወረዳ ፖሊስ ጽፈት ቤት በህብረተሰቡ ድጋፍ የተገነባ የፖሊስ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው ህብረተሰቡ ከእኛ ከአድልዎ ነጻ የሆነ አገልግሎት ፈልጎ ስለሆነ በቅንነትና በታማኝነት ልናገለግል ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈው ሶስት መቶ ሺ ብር ግምት ያለው የቢሮ ቁሳቁስ ከዞኑ አስተዳደር ጋር በመነጋገር ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በመጨረሻም በገንዘብ፣በጉልበትና በሃሳብ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የምስጋናና የእውቅና ሰርተፍኬት አሰጣጥ መርሀ ግብር ተካሂዷል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥና ማናጅመንት፣የዲታ ወረዳ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣የአጎራባች ወረዳና ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዦችና ጥሪ የተደረገላቸው የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የወረዳው ፖሊስ አባላት ተገኝተዋል።

በሪፖርተር ኢትዮጵያ ወንድሙ

በወላይታ የሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት በፖሊስ መደበኛ ስራና በሪፎርም ተግባር ግንባር ቀደም ለሆኑ ክፍለ ከተሞች እውቅና ሰጠ።ወላይታ ሶዶ ሐምሌ 27/2018 ዓ...
03/08/2026

በወላይታ የሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት በፖሊስ መደበኛ ስራና በሪፎርም ተግባር ግንባር ቀደም ለሆኑ ክፍለ ከተሞች እውቅና ሰጠ።

ወላይታ ሶዶ ሐምሌ 27/2018 ዓ/ም (ደ.ኢ.ፖ.ኮ)

ከተማው በአዲስ መዋቅር መምሪያ ሆኖ መስራት ከጀመረ አንድ አመት እንደሞላው የገለጹት የከተማው ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ በመደበኛ የፖሊስ አገልግሎትና የሪፎርም ስራዎች በእቅድ በመመራታቸው ውጤታማ እንደነበሩ አስታውቀዋል።

በበጀት አመቱ ለተገልጋይ ምቹና ጽዱ የሆነ የመስሪያ ቦታ እንዲኖር ለማስቻል የከተማውን ማህበረሰብና ባለሀብቱን በማስተባበር በሶስቱም ክፍለ ከተሞች አዳዲስ ቢሮዎች ከመገንባት ጀምሮ የተጠርጣሪ ማረፍያዎችና የህጻናት ማቆያዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉበት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል።

በመድረኩ የተገኙት የሶዶ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ እታገኝ ሃይለማርያም በበኩላቸው የከተማው ፖሊስ አመራርና አባላት በከተማው ስጋት የነበሩ ወንጀሎችን ለመከላከል ያደረጉት ጥረት የሚበረታታ ውጤት ተመዝግቦበታል ብለዋል።

አሁን የተገኘውን ውጤት በ2019 በጀት ዓመተ ምህረት በቴክኖሎጂ የታገዘ የፖሊስ አገልግሎት በማቅረብ ደህንነቱ የተረጋገጠ ከተማ እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚሠራም ተናግረዋል።

በዚህ መድረክ ከፖሊስ ጎን በመቆም ድጋፍ ላደረጉ አካላትና በፖሊስ ስራቸው ላይ ለተጉ አመራርና አባላት የማበረታቻና የእውቅና የሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ የስራ መመሪያ የሰጡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሰሀ ጋረደው
ዋጋ ከሚሠጣቸው ጉዳዮች ሁሉ ውዱ ለሰው ልጆች ሰላምና ደህንነት ሲባል የሚከፈለው ዋጋ ነው ያሉ ሲሆን ፖሊስነት ደግሞ ለዚህ ሲባል የህይወት መስዋትነት ጭምር የሚከፈልበት ሞያ ነው ብለዋል።

በ2018 በጀት ዓመት የተሰሩ ስራዎችን የቃኘንበት ቢሆንም ሶዶ ከተማ ተዝቆ የማያልቅ ገና ያልተናካ እሴት ያላት በመሆኑ ከተማዋንና ነዋሪዎቿን ተረጋግተውና ደህንነት ተሰምቷቸው የሚኖሩባት እንዴትሆን ከዚህ በላይ ማቀድና መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

በውይይት መድረኩ የወላይታ ዞንና የከተማ ከፍተኛ የመንግስት አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎችና የንግዱ ማህበረ ሰብ አካላት ተገኝተዋል።

በሪፖርተር ኢትዮጵያ ወንድሙ

በወላይታ ሶዶ ከተማ የ2018 በጀት ዓመት የክፍለ ከተሞች ዓመታዊ አፈጻጸም ምዘናና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል ።በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና...
03/08/2026

በወላይታ ሶዶ ከተማ የ2018 በጀት ዓመት የክፍለ ከተሞች ዓመታዊ አፈጻጸም ምዘናና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና በወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ትብብር፣ የ2018 በጀት ዓመት የክፍለ ከተሞች ዓመታዊ አፈጻጸም ምዘናና የ2019 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ ውይይት መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩ በ2018 በጀት ዓመት በክፍለ ከተሞች የተከናወኑ የጸጥታ ሥራዎችን፣ የሕዝብ ተሳትፎን፣ የወንጀል መከላከልና ምርመራ አፈጻጸሞችን በመገምገም የተገኙ ጠንካራ ጎኖችን ለማጠናከር እና የታዩ ክፍተቶችን በመለየት ለ2019 በጀት ዓመት የተሻለ የሥራ አቅጣጫ ለመቀመጥ ያለመ ነው።

በመድረኩ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሳሀ ጋራዶ፣ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማርያም፣ የወላይታ ሶዶ ከተማ የመንግስት ዋና ተጠሪና የከተማው አስተባባሪ አካላት፣ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በስፋት ተሳትፈዋል።

ተሳታፊዎች የ2018 በጀት ዓመት የተመዘገቡ ውጤቶችን በጥልቀት በመገምገም በቀጣይ ዓመት የሕዝብን ሰላምና ደህንነት የበለጠ ለማረጋገጥ፣ የፖሊስና የማህበረሰብ ትስስርን ለማጠናከር፣ ፈጣንና ተጠያቂ የፖሊስ አገልግሎትን ለማስፋፋት እና የወንጀል መከላከል ሥራዎችን በተቀናጀ መልኩ ለማከናወን በሚያስችሉ ዕቅዶች ላይ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።

መድረኩ በመጨረሻም በ2019 በጀት ዓመት የሚተገበሩ የጸጥታ እና የሕዝብ አገልግሎት ሥራዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር ተጨባጭ የተግባር አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

Address

Wolaita
S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Ethiopia Regional State Police Commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to South Ethiopia Regional State Police Commission:

Shortcuts

Share