Wolaita Zone Police Department new

Wolaita Zone Police Department new Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wolaita Zone Police Department new, Government Official, south Ethiopia wolaita zone, Sodo.

ጳጉሜ 3 "የፅናት ቀን" በሚል መሪ ሐሳብ በወላይታ ሶዶ ማዕከል በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል ጳጉሜ 3/2018 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበ...
08/09/2026

ጳጉሜ 3 "የፅናት ቀን" በሚል መሪ ሐሳብ በወላይታ ሶዶ ማዕከል በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል

ጳጉሜ 3/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በተገኙበት ጳጉሜ 3 "የፅናት ቀን" በሚል መሪ ቃል በወላይታ ሶዶ ማዕከል በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።

የ2018 የጳጉሜ ቀናት በተለያዩ ስያሜዎች እና በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በመላው ሀገሪቱ የኢትዮጵያን የትግል፣ የፅናትና የተስፋ ታሪክ በማስታወስ የተሻለ ነገን ለመገንባት የጋራ ኃላፊነት ለማጠናከር ታስቦ ነው እየተከበረ የሚገኘው።

"የጽናት ቀን" በሀገራችን ብሎም በክልላችን ውስጥ በየቀኑ የሚታዩትን የማይናወጡ የቁርጠኝነትና የመስዋዕትነት ታሪኮች የምናስብበት ልዩ ዕለት መሆኑ ተመላክቷል።

የመርሃ ግብብሩ አካል የሆነው የእግር ጉዞ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ፍሰሃ ጋረደው ፣ የክልል የወላይታ ዞን እና የሶዶ ከተማን አመራሮችና የፀጥታ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

በወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ አረካ ከተማ ፖሊስ ለሠራተኞች ምቹ አካባቢ ለመፍጠር የተሰራ የሪፎርም ሥራ የሚያሳይ  ገጽታ  በከፊል በፎቶ
08/09/2026

በወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ አረካ ከተማ ፖሊስ ለሠራተኞች ምቹ አካባቢ ለመፍጠር የተሰራ የሪፎርም ሥራ የሚያሳይ ገጽታ በከፊል በፎቶ

የሁምቦ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት  ፖሊስ አመራርና አባላት ወቅታዊ ፀጥታ፥ ጊፋታ በዓል አከባበር ዙሪያና የትራፍክ ቁጥጥር ውይይት ተደርጓል።ወላይታ ሶዶ፦በቀን 02/13/2018 ዓ/ም የሁምቦ ወረዳ...
07/09/2026

የሁምቦ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ፖሊስ አመራርና አባላት ወቅታዊ ፀጥታ፥ ጊፋታ በዓል አከባበር ዙሪያና የትራፍክ ቁጥጥር ውይይት ተደርጓል።

ወላይታ ሶዶ፦በቀን 02/13/2018 ዓ/ም
የሁምቦ ወረዳ ፖሊስ በ2018 ዓ/ም በአለም በዩንስኮ የማይዳሰሱ ቅርስ የተመዘገበው የወላይታ ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል አከባበር ላይ የፀጥታ ችግር እንዳይኖር ከወትሮ በተሻለ ሁነታ የአከባብ ፀጥታ ለመጠበቅ እንዳለበት እና በየአከባብው ጥበቃ በማጠናከር የማህበራዊ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ በትኩረት እንድሰራ ውይይት ተደርጓል።

የህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ዝውውር እንዳይካሄድ ድንገተኛ ፍተሻ መጠናከር እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ የትራፍክ ፍሰት ስለሚጨመር አደጋ እንዳይከሰት የእግረኛኞች በጉዞ ግራ ጠርዝ በመያዝ እንድራመዱ፥ አስፋልት ስቋረጡ በዘብራ እንድሆን ፥ ለህ/ሰብ ከወድው ግንዛቤ መስጠት እንዳለበት ተደርጓል።
አሽከርካሪዎች ትርፍና ከታርፍ በላይ ማስከፈል ችግር ለመፍታት ለእግረኛ ቅድሚያ በመስጠት ፍጥነት ማሽከርከር እንደለለበት የቁጥጥር ስልት መዘመን አለበት ብሏል ኢ/ር እሸቱ ብንያም የሁምቦ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ።

በማዕከል ፖሊስ አባላት ውሎ አድሮ በመስራት ህ/ሰብን ለወንጀል መከ/ል ባለበት በማድረግ አጋዥ ኃይል እንድሆን ማስታጠቅ አለበት ብሏል።

በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!!

የአረካ ከተማ ከንቲባ ክቡር ኢ/ር ጥበቡ ሳሙኤል ፣የከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘለቀ ዛራን ጨምሮ ሌሎች አስተባባሪ አካላት በከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት እየተሠሩ ያሉ የልማት ተ...
07/09/2026

የአረካ ከተማ ከንቲባ ክቡር ኢ/ር ጥበቡ ሳሙኤል ፣የከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘለቀ ዛራን ጨምሮ ሌሎች አስተባባሪ አካላት በከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት እየተሠሩ ያሉ የልማት ተግባራትን ተመለከቱ።

ወላይታ ሶዶ፤ጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም (ወዞፖመም)

የአረካ ከተማ ከንቲባ ክቡር ኢ/ር ጥበቡ ሳሙኤል ፣የከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘለቀ ዛራን ጨምሮ ሌሎች አስተባባሪ አካላት በከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት እየተሠሩ ያሉ የልማት ተግባራትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በከተማው አስተማማኝ ሰላም እንዲረጋገጥ የሚያስችል ጠንካራ ተቋም ለመገንባት እንዲሁም ለሥራ ምቹና ማራኪ አከባቢ ለመፍጠር በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

ጠንካራ ተቋም በመገንባት ለስራው ምቹ አካባቢ መፍጠር የፀጥታ ስራ ለማሳለጥ ጉልህ ሚና እንዳለው ተመላክቷል።

ከፀጥታ ስራ ጎን ለጎን ተቋሙን ውብና ማራኪ ለማድረግ እንዲሁም በቅጥር ግቢ የከተማ ግብርና ስራዎችን በማከናወን የውስጥ ገቢ ለማሳደግ እየተደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑ ተገልጿል።

ጠንካራ ተቋም በመገንባት ምቹ ፣ውብና ማራኪ አከባቢ እንዲሁም አስተማማኝ ሰላም የተረጋገጠበት አከባቢ ለመፍጠር የሚደረገው ርብርብ ተጠናክሮ እንዲጥል ተጠቁሟል።

በወላይታ ዞን የዳሞት ሶሬ ወረዳ ፖሊስ አመራሩና አባላት የደንብ ልብስ አለባበስ እና የፖሌን ቆጠራ ላይ ያተኮረ ቁጥጥር አካሄዱ።ወላይታ ሶዶ፦ጳጉሜ 2 / 2018  ዓ/ም      በየሳምንቱ ዘ...
07/09/2026

በወላይታ ዞን የዳሞት ሶሬ ወረዳ ፖሊስ አመራሩና አባላት የደንብ ልብስ አለባበስ እና የፖሌን ቆጠራ ላይ ያተኮረ ቁጥጥር አካሄዱ።

ወላይታ ሶዶ፦ጳጉሜ 2 / 2018 ዓ/ም

በየሳምንቱ ዘውትር ሰኞ ዕለት ወደ ሥራ ከመገባቱ በፊት በአመራሩና በአባላት ላይ የሚደረገው የደንብ ልብስ እና የግል ንጽህና እንድሁም የፖሌን ቆጠራ ቁጥጥር ሳይቋረጥ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ።

#በጀግንነት መጠበቅ፣ በሰብዓዊነት ማገልገል!!

የኦፋ ወረዳ ፖሊስ  አመራርና አባላት ሰኞ የሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ሥራ ከመጀመራቸዉ በፊት የሰልፍ ትርዕትና  የአለባበስ ሥነ ሥርዓት ቁጥጥር አካሄደ።ወላይታ ሶዶ ፦ጳጉሜ 02/13/2018 ዓ/...
07/09/2026

የኦፋ ወረዳ ፖሊስ አመራርና አባላት ሰኞ የሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ሥራ ከመጀመራቸዉ በፊት የሰልፍ ትርዕትና የአለባበስ ሥነ ሥርዓት ቁጥጥር አካሄደ።

ወላይታ ሶዶ ፦ጳጉሜ 02/13/2018 ዓ/ም

ሰኞ የሳምንቱ ሥራ መጀመሪያ ቀን የሰልፍ ትርዕት ላይ አጠቃላይ የወረዳ ፖሊስ አባላት ተገኝተዋል።

የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር ዘገዬ ዘካሪያስ በሥነ ሥርዓቱ ላይ በደንብ ልብስ አለባበስ ሁሉም አመራርና አባላት የተመሰገኑ ሲሆን ጉድለት የታየባቸዉ በቀጣይ እንዲያስተካክሉ አስተያዬት ተሰጥቷል።

በጀግንነት መጠበቅ፤በሰብአዊነት ማገልገል!!

በወላይታ ዞን በሌ አዋሳ ከተማ አስተዳዴር ፖሊስ አባላት ሰኞ የሣምንቱ  መጀመሪያ ቀን ሥራ ከመጀመራቸዉ  በፊት የሰልፈ ትሪዕትና የአለባቤስ ሥነ- ሥራዓት ቁጥጥረ  አካሄዱ ።ወላይታ ሶዶ፦ ጰ...
07/09/2026

በወላይታ ዞን በሌ አዋሳ ከተማ አስተዳዴር ፖሊስ አባላት ሰኞ የሣምንቱ መጀመሪያ ቀን ሥራ ከመጀመራቸዉ በፊት የሰልፈ ትሪዕትና የአለባቤስ ሥነ- ሥራዓት ቁጥጥረ አካሄዱ ።

ወላይታ ሶዶ፦ ጰጉሜ 2/13/2018 ዓ/ም

በሣምንቱ የመጀመሪያ ቀን የሚካሄድ የሰልፍ ትርዕትና የፖሊስ አለባበስ ዲስፒሊን ሥነ ሥርዓት ቁጥጥር አባላቱ ራሳቸዉን በአለባበስ ሞዴል አድርገዉ እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን የባሌ አዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር ተስፋዬ ኡቃ ተናግረዋል።

በጀግንነት መጠበቅ፤በሰብአዊነት ማገልገል

ሰላምና ጸጥታን በማስከበር ወንጀልን ከመከላከል ረገድ በቦዲቲ ከተማ የተሻለ ሁኔታ መፈጠሩን  ነዋሪዎቹ ገለጹ።ወላይታ ሶዶ፣ነሐሴ 30/2018ዓ.ም (ወዞፖመም) ሰላምና ጸጥታን በማስከበር ወንጀ...
06/09/2026

ሰላምና ጸጥታን በማስከበር ወንጀልን ከመከላከል ረገድ በቦዲቲ ከተማ የተሻለ ሁኔታ መፈጠሩን ነዋሪዎቹ ገለጹ።

ወላይታ ሶዶ፣ነሐሴ 30/2018ዓ.ም (ወዞፖመም) ሰላምና ጸጥታን በማስከበር ወንጀልን ከመከላከል ረገድ በቦዲቲ ከተማ የተሻለ ሁኔታ መፈጠሩን ነዋሪዎቹ ገለጹ።

የከተማው ሰላምና ጸጥታ መዋቅርም ከሕብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት፣ በሁሉም ቀበሌዎች ለሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የከተማው ነዋሪዎች አንስተዋል ።

የአንድ አካባቢ ሰላምና ጸጥታን የማስከበር ሥራ የጸጥታ መዋቅሩ ብቻ የሚወጣው ኃላፊነት ሳይሆን፣ የሕብረተሰብና ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ተሳትፎ የሚጠይቅ የጋራ ኃላፊነት እንደሆነ ያነሱት የቦዲቲ ከተማ ነዋሪ ወ/ሮ አይናለም መና ከጸጥታ ስራ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ለውጥ እንዳለ ተናግረዋል ።

የአካባቢውን ሠላም ለማስጠበቅ ከጸጥታ አካላትና ከሕብረተሰቡ ጋር በትብብር በመሠራቱ ቀደም ሲል ይከሰቱ የነበሩ የተለያዩ ወንጀሎች መቀነሱንና አሁን ላይ የተሻለ የሰላም ሁኔታ መፈጠሩን ሌላኛው የከተማው ነዋሪ አቶ አለማየሁ አሰለ አንስተዋል ።

ይበልጥ ሰላምን ለማስጠበቅ የሌሊት ሮንድ ጥበቃ እንዲጠናከር፣ ችግር በሚፈጠርባቸው ቦታዎች የጸጥታ አካላት በፍጥነት እንዲደርሱ እና ሕብረተሰቡ ከአጭበርባሪዎች ራሱን እንዲጠብቅ የግንዛቤ ማሰጨበጥ ሥራ እንዲጠናከር የጠየቁት ደግመው የከተማው ህብረተሰብ አካል የሆኑት አቶ እንድሪያስ ለባ ናቸው።

የቦዲቲ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘላለም ለአ በከተማ ውስጥ የተለያዩ ወንጀሎች እንዳይከሰቱ የመከላከል ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ፣ በተለይም ከፊታችን የሚመጡ በዓላት በሰላም እንድከበሩ ትኩረት በመስጠት፣ ከፖሊስና ከሚሊሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰሩ መሆናቸውን አስረድተዋል።

የቦዲቲ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ኡፋይሳ ለማ፥ ከከተማው ሰላምና ጸጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት ወንጀልን ከመከላከል አንጻር ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆነ አንስተዋል ።

ኢንስፔክተር ኡፋይሳ ለማ አክለውም ፣ የአየር ሁኔታን ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቆጣጠር የተለያዩ የመከላከል ሥራዎችን ከመስራት ባለፈ የሌሊት ሮንድ ጥበቃን በማጠናከር ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን በትኩረት እንደሚሰሩም ገልጸዋል።

ሰላምና ጸጥታን የማስከበር ሥራ የፖሊስና የጸጥታ አካላት ብቻ የሚወጡት ኃላፊነት ባለመሆኑ፣ ሕብረተሰቡ ለጸጥታ አካላት መረጃ በመስጠት እንዲተባበርና ለአከባቢው ዘብ እንዲቆም ጥሪ ቀርቧል።

በቦዲቲ ከተማ አስ/ር በዳሞታ ሻክሾ ቀበሌ አዴ ሻክሾ ቀጠና የአከባቢ ፀጥታ ዙርያ ከህብረተሰቡ ጋር ዉይይት አካሄደ ወላይታ ሶዶ ነሐሴ 29/2018 ዓ/ም (ወዞፖመም)የዘመን መለወጫ በዓል ወቅ...
05/09/2026

በቦዲቲ ከተማ አስ/ር በዳሞታ ሻክሾ ቀበሌ አዴ ሻክሾ ቀጠና የአከባቢ ፀጥታ ዙርያ ከህብረተሰቡ ጋር ዉይይት አካሄደ

ወላይታ ሶዶ ነሐሴ 29/2018 ዓ/ም (ወዞፖመም)

የዘመን መለወጫ በዓል ወቅት
ከመሆኑ አንፃር ማህበረሰቡ ከወትሮ በነቃ ሁኔታ አከባቢውን እንዲጠብቁና ከፖሊስ ጎን በመሆን የማታ ሮንድ ሥራ መስራት እንዳለባቸዉ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ተሰርቷል።ኢ/ር ኡፋይሳ ለማ የቦዲቲ ከተማ ፖሊስ አዛዥ።

የማህበረሰብ ደህንነት ፓትሮል ቅኝት አደረጃጀት ግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ለቀጠናው ማህበረሰብ ተሰጥተዋል።

በዉይይት መድረኩ ላይ የተሳተፉት የአካባቢዉ ህዝብ በሰጡት አስተያየት አካባቢያቸዉን ለመጠበቅ ከፖሊስ ጎን ለመሆን ዝግጁ ነን ብለዋል።

በጀግንነት መጠበቅ በሰብአዊነት ማገልገል

የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የ2018 ዓ/ም ስራ አፈጻጸም ግምገማ ተጠናክሮ ቀጥለዋልወላይታ ሶዶ ፦ነሐሴ 29/2018 ዓ/ም (ወዞፖመም)ዛሬ አራተኛ ቀኑን የያዘዉ የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ...
04/09/2026

የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የ2018 ዓ/ም ስራ አፈጻጸም ግምገማ ተጠናክሮ ቀጥለዋል

ወላይታ ሶዶ ፦ነሐሴ 29/2018 ዓ/ም (ወዞፖመም)
ዛሬ አራተኛ ቀኑን የያዘዉ የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የ2018 ስራ አፈጻጸም በሁሉም ዲቪዥን ተጠናክሮ ቀጥለዋል።

በግምገማዉ ሂደት የዞኑ ፖሊስ ማኔጅሜን አባላት ፈጻሚ ባለሙያ የፖሊስ አባላት እየተገመገሙ መሆናቸዉ ታዉቋል።

Address

South Ethiopia Wolaita Zone
Sodo

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Zone Police Department new posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share