Gozamin woreda communication affairs

Gozamin woreda communication affairs ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ለሁሉም እናደርሳለን

02/09/2026

ነሀሴ 26/2018 ዓ.ም ( ): በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎዛምን ወረዳ ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት አስተባባሪነት የእንግጫ ነቀላ እና ከስይ አጨዳ በዓል በወረዳው በፈንድቃ ቀበሌ በድምቀት ተከብሯል።

ምስራቅ ጎጃም ዞን በ2018  በጀት ዓመት አጠቃላይ አፈፃፀም  በክልሉ ከሚገኙ አቻ ዞኖች  ጋር ተወዳድሮ 3ኛ ደረጃ በመያዝ እውቅናና ምስጋና ተበረከተለት።*የአማራ ክልል መንግስት በተጠናቀቀ...
01/09/2026

ምስራቅ ጎጃም ዞን በ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ አፈፃፀም በክልሉ ከሚገኙ አቻ ዞኖች ጋር ተወዳድሮ 3ኛ ደረጃ በመያዝ እውቅናና ምስጋና ተበረከተለት።
*
የአማራ ክልል መንግስት በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖችና ከተማ አስተዳድሮች እውቅና እና ሽልማት ሰጠ።

የአማራ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ መሪዎች ለተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ እና የመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክ ተጠናቋል።

የአማራ ክልል መንግስት በመድረኩ ማጠቃለያ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በሠላም፣ በልማት በመልካም አስተዳደር ዘርፎች የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖች እና ከተማ አስተዳድሮች እውቅና እና ሽልማት አብርክቷል።

በዚህም የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር በክልሉ ከሚገኙ ዞኖች መካከል 3ኛ ደረጃ በመያዝ እውቅናና ምስጋና ተሰጥቶታል።

በተገኘው እውቅና እና ምስጋና እንኳን ደስ ያላችሁ!

መረጃው የምስራቅ ጎጃም ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ነው።

ለበለጠ መረጃ የጎዛምን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንን ይወዳጁ
‎ቲክቶክ : tiktok.com/
‎ቴሌግራም : https://t.me/+0lEq6W4-HkxjMzBk
‎ዩቲዩብ :https://youtube.com/?si=q5oxnXn3EmC4ABrq

በጎዛምን ወረዳ የእንግጫ ነቀላ እና ከስይ አጨዳ በዓል በድምቀት ተከበረ። ====================ነሀሴ 26/2018 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙዩኒኬሽን): በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎዛምን ወረ...
01/09/2026

በጎዛምን ወረዳ የእንግጫ ነቀላ እና ከስይ አጨዳ በዓል በድምቀት ተከበረ።
====================
ነሀሴ 26/2018 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙዩኒኬሽን): በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎዛምን ወረዳ ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት አስተባባሪነት የእንግጫ ነቀላ እና ከስይ አጨዳ በዓል በወረዳው በፈንድቃ ቀበሌ በድምቀት ተከብሯል።

የወረዳው ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉቀን መኩሪያው የእንግጫ ነቀላ እና ከስይ አጨዳ በዓል ከነሐሴ 16 ቀን ጀምሮ እስከ አዲስ ዓመት መባቻ ድረስ በድምቀት የሚከበር ባህላዊና ታሪካዊ በዓል መሆኑን ገልፀዋል።

በዓሉ የክረምቱን ጨለማና ጭቃን ማለፍን፣የአዲሱ ዓመትን ብርሀን፣ሰላምና ልምላሜን የሚያበስር እንደሆነ ኃላፊው ተናግረዋል።

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሄለን መልካየሁ በዓሉ ልጃገረዶች በነፃነት ወደ አደባባይ በመውጣት፣ በባህላዊ አለባበስ አምረውና ደምቀው የሚያከብሩት የነፃነት ፣የፍቅርና የእኩልነት መገለጫ በዓል ነው ብለዋል።

ኃላፊዋ አክለውም በዓሉ የባህላዊ አለባበስ፣ የአመጋገብ ሥርዓትና ሌሎች ባህላዊ መገለጫዎች በተለያዩ ክዋኔዎች የሚንጸባረቁበት መሆኑን ጠቁመው ይህም የህብረተሰቡን አንድነትና ማህበራዊ ትስስር ለማጠናከር የጎላ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል።

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ እንዳዘዘ ጓዴ በበኩላቸው በዓሉ በመጤ ባህሎች ሳይበረዝ በትክክለኛ ክዋኔ በማክበር ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ለበለጠ መረጃ የጎዛምን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንን ይወዳጁ
‎ቲክቶክ : tiktok.com/
‎ቴሌግራም : https://t.me/+0lEq6W4-HkxjMzBk
‎ዩቲዩብ :https://youtube.com/?si=q5oxnXn3EmC4ABrq

01/09/2026

በጎዛምን ወረዳ የእንግጫ ነቀላ እና ከስይ አጨዳ በዓል አከባበር

ነሀሴ 26/2018 ዓ.ም

"ከተረጂነት ወደ ምርታማነት!በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎዛምን ወረዳ የምግብ ሉዓላዊነትን በራስ አቅም ለማረጋገጥ የተጀመረውን “ከተረጅነት ወደ ምርታማነት” ኢንሼቲቭ እውን ለማድረግ በሊባኖስ ቀበ...
31/08/2026

"ከተረጂነት ወደ ምርታማነት!

በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎዛምን ወረዳ የምግብ ሉዓላዊነትን በራስ አቅም ለማረጋገጥ የተጀመረውን “ከተረጅነት ወደ ምርታማነት” ኢንሼቲቭ እውን ለማድረግ በሊባኖስ ቀበሌ እየለማ የሚገኝ የስንዴ ቡቃያ ከፊል ገፅታ፦

ለበለጠ መረጃ የጎዛምን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንን ይወዳጁ
‎ቲክቶክ : tiktok.com/
‎ቴሌግራም : https://t.me/+0lEq6W4-HkxjMzBk
‎ዩቲዩብ :https://youtube.com/?si=q5oxnXn3EmC4ABrq

በጎዛምን ወረዳ "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው የክረምት የዜጎች የበጎ ፈቃድ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።   ===================ነሀሴ 25/2018 ዓ.ም (ጎዛ...
31/08/2026

በጎዛምን ወረዳ "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው የክረምት የዜጎች የበጎ ፈቃድ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
===================
ነሀሴ 25/2018 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙዩኒኬሽን ) በምስራቅ ጎጃም ዞን የጎዛምን ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጎዳዮች ጽ/ቤት ሰራተኞች "አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ" በሚል ንቅናቄ 17 ደርዘን ደብተርና የተለያየዩ የአልባሳት ድጋፎችን አድርጓል።

የጎዛምን ወረዳ ሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሰራተኞች በቦታው ተገኝተው ድጋፉን ተቀብለዋል።

ለበለጠ መረጃ የጎዛምን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንን ይወዳጁ
‎ቲክቶክ : tiktok.com/
‎ቴሌግራም : https://t.me/+0lEq6W4-HkxjMzBk
‎ዩቲዩብ :https://youtube.com/?si=q5oxnXn3EmC4ABrq

ከመሬት ሥር የተደበቀው ቢሊዮን ዶላር በአማራ ክልል!​የአማራ ክልል ከፍተኛ የማዕድን ክምችት የሚገኝበት አካባቢ ነው። ወርቅ፣ ኦፓል፣ የድንጋይ ከሰል፣ እምነበረድ፣ ብረት፣ ግራናይት፣ ጋብሮ ...
30/08/2026

ከመሬት ሥር የተደበቀው ቢሊዮን ዶላር በአማራ ክልል!

​የአማራ ክልል ከፍተኛ የማዕድን ክምችት የሚገኝበት አካባቢ ነው። ወርቅ፣ ኦፓል፣ የድንጋይ ከሰል፣ እምነበረድ፣ ብረት፣ ግራናይት፣ ጋብሮ እና ሌሎችም ከ50 በላይ ማዕድናት በክልሉ መኖራቸው በጥናት የተረጋገጠ ነው።

የአማራ ክልል ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ኀላፊ ኃይሌ አበበ ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት በክልሉ ለማዕድን ክምችት መሠረት የሆኑት ሦስቱም የአለት አይነቶች በስፋት ይገኛሉ።

በአሁኑ ወቅት የማዕድን ዘርፉ ለኢኮኖሚ እድገት እና ለመዋቅራዊ ሽግግር መሠረታዊ መኾኑ ታምኖበት ከዋና ዋና የኢኮኖሚ ዘርፎች አንዱ ኾኖ በትኩረት እየተሠራበት ነው ብለዋል።

​ማዕድን ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት እና የመንግሥትን ገቢ ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም አብራርተዋል። በዚህም ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመኾን የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ነው ያሉት።

📌በክልሉ የማዕድን ጸጋዎች ፍለጋ ምን ላይ ነው?

ከክልሉ መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ሪፖርት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በበጀት ዓመቱ:-

✍️ በ20 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት መሬት ላይ በተካሄደው የላብራቶሪ ጥናት ከ146 ነጥብ 7 ሜትሪክ ቶን በላይ ብረት ተገኝቷል።

✍️ በ10 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት በተደረገ ጥናት ከ5 ነጥብ 1ሚሊዮን ቶን በላይ የብረት ማዕድን ክምችት ማግኘት ተችሏል።

✍️በ440 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ የኮንስትራክሽን ማዕድናት ፍለጋ ጥናቶች ተሠርተው 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ቶን ግራናይት እና ከ1ነጥብ 6 ቢሊዮን ቶን በላይ ጥቁር ድንጋይ ማግኘት ተችሏል።

✍️ከ6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ኖራ ለማምረት የሚያስችል የኖራ ማዕድን የክምችት ቦታዎች በጥናት ተለይተዋል።

📌ከማዕድን ሃብት የተገኘ ገቢ
ቢሮ ኀላፊው እንዳብራሩት:-
💎 ጥሬ ኦፓል:- በበጀት ዓመቱ 27 ሺህ 127 ኪሎ ግራም ጥሬ ኦፓል ለገበያ ቀርቧል። ከዚህም 3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።

🔹የተዋበ ኦፓል:-729 ኪሎ ግራም እሴት የተጨመረበት የተዋበ ኦፓል ለገበያ በማቅረብ 1 ነጥብ4 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት ተችሏል።💎

🔹ወርቅ:- 357 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ በማቅረብ 61 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።🪙

🔹ድንጋይ ከሰል፣ ጂፕሰም እና ግራናይት የመሣሠሉ ምርቶችን በክልሉ በማምረት ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ተችሏል።

🔹በዘርፉ በበጀት ዓመቱ ከ55 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል።

🔹 በተለያዩ የገቢ አማራጮች ከ346 ሚሊዮን ብር በላይ ለክልሉ ገቢ ማስገኘቱን በአብነት አንስተዋል።

🔹 ይህንን ከመሬት ስር የተደበቀውን የቢሊዮን ዶላር ጸጋ በአግባቡ መጠቀም ጊዜው አሁን ነው በሚል እሳቤ የክልሉ መንግሥት በአሻጋሪ የዕድገት እና የልማት ዕቅዱ አካትቶ በመሥራት ላይ ይገኛል።

✅​ የክልሉን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ስልጠናን ማጠናከር ፣ የስነ-ምድር ካርታ ዝግጅት ማስፋፋት፣ የፋይናንስ አቅርቦትን ማመቻቸት፣ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና ሕጋዊነት የማስፈን ሥራዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ መሆኑን ቢሮ ኀላፊው አመላክተዋል።

#አሚኮ

በጎዛምን ወረዳ አዲስና ጉሊት ቀበሌ በሪጌይን (RE-GAIN) ፕሮጀክት ድጋፍ የተከናወኑ የድህረ ምርት አያያዝና አጠቃቀም  ተግባራት የመስክ ምልከታ ተካሄደ።=====================...
29/08/2026

በጎዛምን ወረዳ አዲስና ጉሊት ቀበሌ በሪጌይን (RE-GAIN) ፕሮጀክት ድጋፍ የተከናወኑ የድህረ ምርት አያያዝና አጠቃቀም ተግባራት የመስክ ምልከታ ተካሄደ።
=====================
ነሀሴ 22/2018 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙዩኒኬሽን ) በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎዛምን ወረዳ በአዲስና ጉሊት ቀበሌ በሳሳክዋ አፍሪካ አሶሴሽን በሪጌይን ፕሮጀክት የበጀት ድጋፍ የተከናወኑ የድህረ ምርት አያያዝና አጠቃቀም ስራዋች ያሉበትን ሁኔታ አስመልክቶ የመስክ ምልከታ ተካሂዷል።

በመስክ ምልከታው ላይ የተገኙት በሳሳክዋ አፍሪካ አሶሴሽን የግብርና ተኮር ስርዓተ ምግብ ክፍል አስተባባሪና የሪጌይን ፕሮጀክት መሪ ወይዘሮ አበራሽ ፀሐይ በፕሮጀክቱ የበጀት ድጋፍ በወረዳው የድህረ ምርት ብክነትን የሚቀንሱ ቴክኖሎጅዎችን ማለትም የብረት ጎተራ፣ፒክስ ባግ፣የሰብል መውቂያ ማሽን እና የእርጥበት መለኪያ ሜትር ለአርሶ አደሮች ለማስተዋወቅና አቅርቦቱን ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ስራዋች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

ወይዘሮ አበራሽ አያይዘውም በዘርፉ በቀበሌው በተሰሩ ስራዋች አበረታች ውጤቶች እየታዩ መሆኑን ጠቁመው ተግባሩን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዋች እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን የድህረ ምርት ብክነት ቅነሳ (RE-GAIN)ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ታደሰ ስንቴ የድህረ ምርት አያያዝ የምርት ጥራትን ለመጠበቅ፣ ለምግብ ደህንነት፣ የተሻለ ገቢ ለማግኘት፣ ከተባይ እንዲጠበቅ ለማድረግ፣‎የምርት ብክነትን ለመቀነስ እና የተሻለ የገበያ ዕድል ለመፍጠር የጎላ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል።

በጎዛምን ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የዘር ብዜት ባለሙያና የፕሮጀክቱ ፎካል የሆኑት አቶ ልንገረው አበባው በበኩላቸው በወረዳው በፕሮጀክቱ በታቀፉ አዲስና ጉሊት፣ሊባኖስና አሳብአቦ ቀበሌዋች በዘርፉ አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ በሌሎች ቀበሌዋች ተግባሩን ለማስፋት በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው አስተያየታቸውን የሠጡት ቄስ በዕደ መላኩ ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩት እንደ ጎታ፣ ባህላዊ ጎተራ፣ጉድጓድና ሌሎች ባህላዊ የእህል ማከማቻዋች ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ ለብልሽት ይዳርጉት እንደነበር በመጠቆም በአሁኑ ሰዓት የተሻሻሉ ዘመናዊ የእህል ማከማቻ ዘዴዋችን መጠቀማቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳስገኛቸው ተናግረዋል።

ለበለጠ መረጃ የጎዛምን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንን ይወዳጁ
‎ቲክቶክ : tiktok.com/
‎ቴሌግራም : https://t.me/+0lEq6W4-HkxjMzBk
‎ዩቲዩብ :https://youtube.com/?si=q5oxnXn3EmC4ABrq

"ከተረጂነት ወደ ምርታማነት''በሚል መሪ ሀሳብ በምግብ ራስን ለመቻል  የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።  ==================== ነሀሴ 22/2018 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙዩኒ...
28/08/2026

"ከተረጂነት ወደ ምርታማነት''በሚል መሪ ሀሳብ በምግብ ራስን ለመቻል የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።
====================
ነሀሴ 22/2018 ዓ.ም (ጎዛምን ኮሙዩኒኬሽን) በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎዛምን ወረዳ "ከተረጅነት ወደ ምርታማነት" በሚል መሪ ሀሳብ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈንና ከጥገኝነት ለመላቀቅ በአዲስና ጉሊት ቀበሌ የጤፍ ዘር መርሀ ግብር ተካሂዷል።

በዘር ስራው ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ እንዳዘዘ ጎዴ ይህ እንቅስቃሴ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ በተጨማሪ የሥራ ባህልን የሚያጎለብት፣ ራስን በራስ የመቻል አቅምን የሚያሳድግና ትውልድን ከጥገኝነት ነፃ የሚያወጣ ታላቅ ሀገራዊ የለውጥ ጉዞ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የወረዳው የግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀብታሙ ይታይህ ሰባዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን በሚደረገው እንቅስቃሴ እንደ ወረዳ እስካሁን ድረስ 15.45 ሄ/ር መሬት በስንዴ ዘር የተሸፈነ መሆኑንና በዛሬው ዕለት ደግሞ በአዲስና ጉሊት ቀበሌ 17.5 ሄ/ር መሬት በጤፍ ዘር የተሸፈነ መሆኑን ገልፀዋል።

"ከተረጅነት ወደ ምርታማነት" አጀንዳ ሀገሪቱ በበጎ አድራጎትና በለጋሾች እርዳታ ያላትን ጥገኝነት አስወግዳ ፣ በራሷ አቅም የለማች ፣ራሷን የቻለች እና የምግብ ዋስትናዋን ያረጋገጠች ሀገር ለመፍጠር ያለመ ትልቅ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ትርጉም ያለው አጀንዳ ነው ሲሉ አቶ ሀብታሙ አክለው ገልፀዋል።

የፈንድቃ ታዳጊ ከተማ አስተዳዳሪ አቶ የሰራህ ገበየሁ በበኩላቸው በዕለቱ የአካባቢው አርሶ አደር በንቅናቄ ወጥቶ ላደረገው ተሳትፎ ልባዊ ምስጋና አቅርበው በቀጣይም ከቀበሌ የግብርና ባለሙያዋች ጋር በመተባበር ሰብሉን በመንከባከብ ለፍሬ ለማብቃት በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የጤፍ ዘር ስራው ከተረጂነት እሳቤ በመላቀቅ ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር፣ በራስ አቅም ምግብን ለማምረትና የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ተግባር መሆኑም ተገልጿል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ እንዳዘዘ ጎዴን ጨምሮ ሌሎች የወረዳው አመራሮችና የግብርና ባለሙያዋች በቦታው ተገኝተው አስተባብረዋል።

ለበለጠ መረጃ የጎዛምን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንን ይወዳጁ
‎ቲክቶክ : tiktok.com/
‎ቴሌግራም : https://t.me/+0lEq6W4-HkxjMzBk
‎ዩቲዩብ :https://youtube.com/?si=q5oxnXn3EmC4ABrq

የኢቢሲ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘላለም እንደሻው በምስራቅ ጎጃም ዞን አነደድ ወረዳ  የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎችን አስጀመሩ።****የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ ) አቶ...
28/08/2026

የኢቢሲ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘላለም እንደሻው በምስራቅ ጎጃም ዞን አነደድ ወረዳ የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎችን አስጀመሩ።
****
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ ) አቶ ዘላለም እንደሻው እና የተቋሙ ሰራተኞች በምስራቅ ጎጃም ዞን አነደድ ወረዳ የተቋሙን የ2018 ክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎችን አስጀምረዋል።

የተቋሙ የስራ ኀላፊዎች በአቅመ ደካማ ቤት ግንባታ ፣ ለ357 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁሶስ ድጋፍን ጨምሮ በሌሎች የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች እንደሚሳተፉ በመርሀ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኢቢሲ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ዘላለም እንደሻው ጨምሮ የተቋሙ የስራ ኀላፊዎች፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምርት መምሪያ ኀላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ ጨምሮ ሌሎች የዞን እና የአነደድ ወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

መረጃው የምስራቅ ጎጃም ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ነው።

ለበለጠ መረጃ የጎዛምን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽንን ይወዳጁ
‎ቲክቶክ : tiktok.com/
‎ቴሌግራም : https://t.me/+0lEq6W4-HkxjMzBk
‎ዩቲዩብ :https://youtube.com/?si=q5oxnXn3EmC4ABrq

Address

T'is Abay

Telephone

+251587713817

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gozamin woreda communication affairs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gozamin woreda communication affairs:

Shortcuts

Share