Tocha Woreda Science And Information Technology Sector

Tocha Woreda Science And Information Technology Sector Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Tocha Woreda Science And Information Technology Sector, Public & Government Service, Tarch'a Sodo.

03/06/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Gosi Ye Geta Ligi, Tekilu Tadesse

11/05/2022

ጀግና ልጅ‼ ነገ ህልሙን ለመኖር፣ ፣ ዛሬ እያሰመዘነ ያጠናል። በሀገራችን ላይ ተስፋ የማንቆርጠው እንዲህ ልባም ልጆች ኢትዮጵያን እንደሚረከቡ ስናውቅ ነው።

04/02/2022
31/01/2022

እስከ 2021 አጋማሽ ብቻ 1,097 በሚሆኑ አነስተኛና ትላልቅ ተቋማት ሊደርስ ችሏል፡፡
ይህ የሳይበር ስጋት በየትኛውም ሁኔታና አጋጣሚ የግል ኮምፒውተራችንን አልያም የተቋም ሰርቨርና የኔትወርክ ደህንነትን አደጋ ውስት ሊከት በመቻሉ ሁልግዜም ወሳኝ የምንላቸውን የመረጃ ግልባጭ ወይም (Back up) መያዝና ማስቀመጥ እጅግ የሚመከር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ አደገኛ ሶፍትዌሮች በግል ኮምፒውተራችንን እና በተቋሞቻችን ሃብት ላይ ጥቃት ከማድረሳቸው በፊት ልንወስዳቸው የሚገቡ መሰረታዊ ጥንቃቄዎች መካከል ሁሉንም አይነት ሶፍትዌሮች፣ አፕሊኬሽኖችንና ኦፕሬቲንግ ሲስተሞችን በየወቅቱ ማሻሻል፤ የታደሱ ፀረቫይረሶችን በመጠቀም በየጊዜው ኮምፒዩተራችንን ስካን ማድረግ፤ ተጋላጭነታችን ሊያሰፉ ከሚችሉ አጠራጣሪ ድረ-ገፅች፣ መተግበሪዎችና ፋይሎች ረሳችንን መጠበቅ፤ የማናውቃቸውን ኢሜይሎች አለመክፈትና የተላኩ አባሪዎችንም ዳውንሎድ አለማድረግ፤ በየጊዜው የሚመጡ ማስታወቂያዎችን ምላሽ ከመስጠታችን በፊት በጥንቃቄ መመልከት እና የራንሰምዌር ጥቃት እየደረሰ መሆኑ ከታወቀ ባለሙያ በማማከር ማልዌሩን በአፋጣኝ ማጥፋትና ቫይረሱ ወደሌሎች እንዳይሰደራጭ ጥቃት የደረሰበትን ኮምፒውተር ለይቶ ማስቀመጥ እጅግ ይመከራል፡፡

31/01/2022

የራንሰምዌር ጥቃት መከሰቻ እና መከላከያ መንገዶች
===========================
በአሁኑ ወቅት የሳይበር ጥቃት በአይነትም፣ በመጠንም በዝቶ ተጠቃሚዎችን በከፍተኛ ስጋት ላይ በመጣል ላይ ይገኛል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም እየተለመዱ ከመጡ የጥቃት አይነቶች መካከል ኢንፎርሜሽንን ማገት ወይም ራንሰምዌር የሚባለው ጥቃት ይጠቀሳል፡፡ ራንሰምዌሮች ባእድ የሆኑ አጥፊ ሶፍትዌሮች ሲሆኑ ሶፍትዌሮቹ ዲዛይን ሲደረጉ የኮምፒውተር ሲስተሞችን በመዝጋት ለተዘጋው ሲስተም ክፍያ እንዲፈጽሙ በማሰብ የተዘጋጁ አጥፊ ሶፍትዌሮች ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅትም የእነዚህ ራንሰምዌሮች ጥቃት እየረቀቀና እየሰፋ ብዙ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ኪሳራና ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡
የራንሰምዌር ጥቃት ከማልዌር ቤተሰብ የሚመደብ ሲሆን ጠቃሚ ሶፍትዌር ወይም ፋይል እንዲሁም አፋጣኝ ምላሽ የሚፈልግ ማስጠንቀቂያ (Popup notification) በመምሰል ኮምፒዩተራችን ላይ ከጫንነው በኋላ የተወሰኑ ወሳኝ ፋይሎችን ወይም ኮምፒዩተሩን በአጠቃላይ በመመስጠር ወይም (Encrypt በማድረግ) ፋሎቹን መክፈት እንዳንችልና ተደራሽ እንዳይሆኑ የማድረግ ተግባር ይፈፅማል፡፡ ይህንን ጥቃት ለየት የሚያደርገው ፋይሎቹን ወይም ኮምፒዩተሩን ተጠቃሚዎች መጠቀም ከፈለጉ በቢትኮይን እና በሌሎች የኦንላይን የመክፈያ ስርአቶች በመጠቀም እንዲከፍሉ የሚያስገድድ መሆኑ ነው፡፡ ይሁንና ተጠቃሚዎች ልብ ሊሉት የሚገባው ጉዳይ ገንዘቡ ከተከፈለም በኋላ ኮምፒውተሩ ወይም ሲስተሙ መለቀቁ ዋስትና አለመኖሩ ይህን የቫይረስ ጥቃት ለየት ያለ ያደርገዋል፡፡
ኮምፒውተር በተለያዩ ምክንያቶች በዚህ የራንሰምዌር ማልዌር ጥቃት ሊጋለጥ የሚችል ሲሆን ከነዚህም መካከል በኦፕሬቲንግ ሲስተም ዲዛይን ላይ በሚፈጠር ችግር፣ በአንድ ኔትወርክ ውስጥ ሁሉም ኮምፒውተሮች ተመሳሳይ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀሙ ከሆነ ወይም ለተጠቃሚዎች በርካታ ፈቃዶችን የሚሰጥ ከሆነ በቀላሉ ለጥቃት ሊጋለጥ ይችላል፡፡ ራንሰምዌር ከአጥፊ ሶፍትዌሮች መካከል አንዱ እና በአለማችን ትልቁ የሳይበር ምህዳር ስጋት እንደመሆኑ መጠን በየጊዜው በሰዎች ላይ እያደረሰ ያለው ሁለንተናዊ ጉዳት በቀላሉ የሚገለፅ አይደለም፡፡ በፈረንጆቹ 2019 ብቻ በራንሰምዌር አማካኝነት በተፈጸም የሳይበር ጥቃት 11.5 ቢሊዮን ዶላር ዓለም አቀፍ ኪሳራ ተመዝግቦ እንደነበር መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን ይህ የሳይበር ስጋት ባለፉት ሁለት ዓመታትም ይበልጥ አየጨመረ ይገኛል፡፡
እነዚህ የሳይበር ጥቃቶች የተጠቃሚውን መረጃ በመቆለፍ የመረጃው ባለቤት ያከማቸውን ዳታ መመልከት እንዳይችል በማድረግ የሚፈጸም የሳይበር ወንጀል በመሆኑ ብዙዎች ወሳኝ የሚሉትን መረጃ መልሰው ለማግኘት ለጥቃት አድራሹ ክፍያ ለመፈፀም ሊጋፋፉ ይችላሉ፡፡ ይሁንና ከላይ ለማንሳት እንደተሞከረው አንዴ ገንዘብ ተከፍሎ መረጃው ለባለቤቱ በአስተማማኝ ሁኔታ ይመለሳል የሚለው እና ከዚህ በኋላም ለጥቃት የመጋለጥ እድሉ ጥያቄ የሚነሳበት በመሆኑ ለጥቃት አድራሾች ምንም አይነት ገንዘብ አለመክፈል በብዙዎች የሚመከረው ጉዳይ ነው፡፡
በዚህ የሳበር ጥቃት ዙሪያ የተሰሩ የቅርብ ጥናቶች እንደሚሳዩት የራንሰምዌር ቫይረስ የማኒዩፋክቸሪን ዝርፉን በዋናነት ኢላማ እያደረገ መምጣቱ የሚነገር ሲሆን ከዛ በተጨማሪም የፋይናንስ ዘርፉ፣ ትራንስፖርት፣ የጤና ተቀዋማት እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ዘርፎች በተከታይነት ተቀምጠዋል፡፡ ሳይበር ክራይም የተባለ አለም አቀፍ ጋዜጥ በቅርቡ ይፋ እንዳደረገው የራንሰምዌር ጥቃት በአለማችን ዙሪያ በየአስራ አንድ ሰኮንዱ በአንድ ወይም ተቋም ላይ የሚደርስ ሲሆን እስከ 2021 አጋማሽ ብቻ 1,0

14/01/2022

ኦርጂናልና ፌክ ሚሞሪ እንዴት በቀላሉ መለየት ይቻላል???

1⃣. ኦርጂናል #ሚሞሪዎችን የምናረጋግጥበት የመጀመሪያው ና ቀላሉ መንገድ የሚሆነው ሚሞሪውን ስልካችን📲 ውስጥ በማስገባት #ፎርማት ማድረግ ነው።

☑️ሚሞሪውን ፎርማት(Format) ስናረገው ኦርጂናል ከሆነ ፎርማቱን ያለ ምንም ችግር ይጨርሳል👍 ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ፎርማት መሆን ስለ ማይችል ኢረር(Error) ቦክስ ያሳያቹና ይቋረጣል‼️

2⃣.ሁለተኛው መንገድ ደሞ በ ኮምፒውተሮ💻 ወይም በስልኮ📲 ወደ ሚሞሪው ፋይሎችን ኮፒ በማድረግ ማረጋገጥ ይቻላል።

☑️ለምሳሌ አንድ 1GB የሚሆን ፊልም ወይም ሌላ ፋይል ወደገዛነው ሚሞሪ ኮፒ ስናደርግ በሚወስደው ሰዐት⏰ ማወቅ ይቻላል ኦርጂናል ከሆነ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ በጣም በዛ ከተባለ 5 ደቂቃ ይወስዳል ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ 10 ደቂቃ+ ሊወስድ ይችላል ይህ ማለት ሚሞሪው በጣም ደካማ😡 ነው ማለት ነው።

3⃣. የሚሞሪው ፋይል የመያዝ አቅም

☑️ለምሳሌ 8GB ሚሞሪ ቢኖርዎት ከሆነ ቢያንስ 7.4GB ይሆናል። ስለዚህ 7.4GB የሚሆን ፋይል ይላኩበት በትክክል ከተቀበለ #አስተማማኝ👍 ነው።

4⃣. ስልካችን📲 ውስጥ በማስገባት SD insight የተባለ አፕ ተጠቅመን ማወቅ እንችላለን

09/01/2022

DV 2022 እንዴት ራሳችን መሙላት እንችላለን?
ዲቪ 2022 ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ
በመጀምሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ በአውሮፓ አቆጣጠር ከ ጥቅምት ሀሙስ 07/2020 ጀምሮ ህዳር
10/2020 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው።
DV-2022 Program Instructions
›የዲቪ ፎርሙን ከመሙላታችን በፊት ማሟላት ያሉብን ነገሮች;-
እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት / የሥራ ልምድ ማሟላት አለበት ማለትም በ
ፕሮግራሙ መሰረትም-
ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ, የ 12 ዓመት ትምህርት በሚገባ
ያጠናቀቀ /ያጠናቀቀች። ወይም
ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት አመት የሥራ ልምድ ያለው።
የ DV አሞላል ሂደቶች:-
ጉርድ ፎቶ ግራፍ በመቀጠልም
www.dvlottery.state.gov በሚለው ዌብ ሳይት መግባት
›ዌብ ሳይቱ ዉስጥ ገብተን Entry ሚለውን በመጫን መቀጠል
በፎቶ መልክ የተቀመጠልንን Authentication code በድጋሚ በመጻፍ ወደ ፎርም
መሙያዉ መግባት።
ፎርም አሞላል
1. Name - ስም - Last/Family Name (የመጨረሻ/የቤተሰብ ስም ወይም የአያት
ስም) ፣ Middle Name- (የመካከለኛ ስም ወይም የአባት ስም) ፣
First Name (የመጀመሪያ ስም ወይም የእርሶን ስም) በፓስፖርትዎ ላይ
ያለውን ስም ሳያሳስቱ በእንግሊዝኛ መጻፍ።
2. Gender - ፆታ - ወንድ (Male) ወይም ሴት(Female) መምረጥ።
3. Birth date - የልደት ቀን - መጀመሪያ Month (ወር) ፣ Day (ቀን) ፣ Year ( ዓመት)
በፈረንጆች አቆጣጠር በተሰጠው ቦታ መጻፍ።.
4. City Where You Where Born - የተወለዱበትን ከተማ
5. Country Where You Were Born - የተወለዱበትን ሀገር
6. Country of Eligibility for the DV Program - ለ DV መርኃ-ግብር
ብቁ የሆነ ሀገር ማለትም yes ሚለዉ ላይ በመተው ማለፍ
7. Entrant Photograph - የመግቢያ ፎቶግራፍ ማስገባት - የቅርብ ጊዜ ጉርድ
ፎቶግራፍ -ፎቶ ግራፉ በደንብ የሚታይ ልኬቱ 600ፒክስል
በ600 ፒክስል የሆነ መጠኑ ከ 240 ኪሎባይት የማይበልጥ ከለር ፎቶ ግራፍ
፣JPEG Format መሆን አለበት።
8. Mailing Address - የፖስታ መላኪያ አድራሻ መሙላት
9. Country Where You Live Today - አሁን የምንኖርበትን ሀገር መምረጥ
10. Phone Number - ስልክ ቁጥር ማስገባት ለኢትዮጲያ +251 ብለን
በመጀመር ስልካችንን ማስገባት / አለማስገባትም ይቻላል
11. E-mail Address - የ ኢሜል አድራሻንን ማስገባት
12. What is the highest level of education you have achieved,
as of today?
የትምህርት ደረጃችንን መምረጥ
13. What is your current marital status?- በአሁን ሰአት ያለን የትዳር
ሁኔታ መምረጥ
14 . Number of Children - የልጅ ብዛት በቁጥር መጻፍ እያንዳንዱ የተወለዱ ሕጻናት
እንዲሁም የማደጎ ልጆች፣ የእንጀራ ልጆች በእርስዎ ፎርም ውስጥ እያንዳንዱ ያላገቡ
ህጻናት, ምንም እንኳን ልጅዎ ከእርስዎ ጋር አብረው ባይኖሩም መሞላት አለባቸዉ።
በመጨረሻም continue በማለት Confirmation Number ያለበትን
ወረቀት ፕሪንት በማድረግ ማስቀመጥ እና በ Confirmation Number ን
DV-2022 ሲወጣ ማየት እንችላለን።
DV-2022 Submission Confirmation : Entry success
በዚ መሰረት ፎርሙን በመሙላት እድላችሁን

04/01/2022

Geepas እንዳይቃጠልብን
🔥 በአብዛኛው ጊዜ ጅፓስ በpower ምክንያት አይቃጠልም። ምክንያቱም ከ100-240v ድረስ መስራት ስለሚችል አነስተኛ ሀይል ያላችሁም ሆናችሁ ጥሩ ሀይል ያለው መብራት የምትጠቀሙም የመቃጠል እድሉ በጣም አናሳ ነው ።
🔥 ብዙ ጊዜ ጅፓስ የሚቃጠልባቸው ምክንያቶች
1 ትላልቅ Speaker ላይ ከጅፓሱ የሚወጣውን ድምፅ በገመድ ቀጥሎ መጠቀም
⛔️ ይህ አብዛኛ ሠው ወደ ሌላ ቦታ በማስረዘም ይጠቀማል። ይህም ከፍተኛ የሆነ ጫና በጅፓሱ Ic እና Transistor ላይ ይፈጥራል። ጅፓስ በውስጡ Heat sink ላይ የታሠረ Ic ወይም Transistor አለው። እነኚህም ስራቸው Sound ማውጣት ሲሆን እናንተ በገመድ ቀጥላችሁ ወደ ሌላ ቦታ ስትጠቀሙ Resistance በገመዱ ምክንያት እንዲሁም በምንጠቀመው የSpeaker አይነት ጫና ይፈጥራል። በፍጥነት እንዲግል ያደርጋል ከዛን ይቃጠላል ማለት ነው።
🔥 በከፍተኛ ድምፅ ለረዥም ጊዜ ማድመጥ Bass በጣም መጨመር ሌላው የመቃጠል ምክንያቶች ሲሆኑ ለብዙ ሠአት በትልቅ ድምፅ መጠቀም ጅፓሱ በፍጥነት እንዲሞቅ ያደርጋል ያ ደግሞ
1ወደ ሚሞሪ ቤት የሚሄደውን 5v የሚሠጥልንን 7805 የሚባለውን Regulator እና Sound deliver የሚያደርገውን Ic ወይም ትራንዚስተር በፍጥነት እንዲሞቅ ስለሚያደርግ ያቃጥልብናል ።
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ቅድመ ጥንቃቄ
1 ብዙ External speaker አትጠቀሙ
2 ለረዥም ሠአት በከፍተኛ ድምፅ አይጠቀሙ
⛔️ጂፓስ በመሠረቱ የሚሠሩት ወይ ከIc ወይም ደግሞ ከTransistor ነው ስለሆነም እነኚ ነገሮች በሙቀት ምክንያት Fail ለማድረግ ቅርብ ናቸው
መልካም ምሸት

Address

Tarch'a S**o

Telephone

+251989398857

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tocha Woreda Science And Information Technology Sector posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Tocha Woreda Science And Information Technology Sector:

Share