Tercha dawro promotion

Tercha dawro promotion Sile tercha

ኤኖ ቡና ተርጫ ወጣቶች ማዕከል ፊትለፊት ያገኙናል  0984849493 @ዋና ደጋፊዎችደጋፊዎች
12/03/2026

ኤኖ ቡና ተርጫ
ወጣቶች ማዕከል ፊትለፊት ያገኙናል


0984849493
@ዋና ደጋፊዎችደጋፊዎች

የመንግስት ሰራተኞች ከቤተሰባቸው በውርስ እና በስጦታ መሬት ማግኘት እንዲችሉ የፈቀደው አዲሱ አዋጅ !ከሰሞኑን የአማራ ክልል መሬት ቢሮ አዲስ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ይፋ አድርጓል።በአ...
03/01/2026

የመንግስት ሰራተኞች ከቤተሰባቸው በውርስ እና በስጦታ መሬት ማግኘት እንዲችሉ የፈቀደው አዲሱ አዋጅ !

ከሰሞኑን የአማራ ክልል መሬት ቢሮ አዲስ የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ይፋ አድርጓል።

በአዲሱ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ዙሪያ በተሰጠ ማብራሪያ " አዲሱ አዋጅ ከዚህ በፊት ሲነሱ የነበሩ የዘርፉ ችግሮችን በመለየት የመፍትሄ አማራጮችን አካቷል " ተብሏል።

እስካሁን የነበረው አዋጅ ባህላዊ የመሬት አያያዝ እና የግጭት አፈታት ስርአቶችን ግምት ውስጥ ማስገባትና እዉቅና መስጠት ላይ ችግሮች የነበሩበት እንደሆነ በአሁኑ አዋጅ ግን ሽምግልና አንዱ የግጭትና አለመግባባትን የሚፈታበት አማራጭ ሁኖ እንዲካተት መደረጉ ተገልጿል።

ይህ አዋጅ የመንግስት ሰራተኞች ከቤተሰባቸው በውርስ እና በስጦታ መሬት ማግኘት እንዲችሉ ፈቅዷል።

አዲሱ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ምን አዲስ ነገር ይዟል ?

- በአዲሱ አዋጅ ካሁን በፊት ተግባራዊ በተደረጉ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ህጎች ያልነበሩና የገጠር መሬት ባለይዞታዎችን መብትና ጥቅም ለማስፋት በግል ይዞታ ላይ የለማን የማይንቀሳቀስ ንብረት መሸጥ እና ማስተላለፍ እንዲችሉ ይፈቅዳል።

- የገጠር መሬት ባለይዞታዎች መሬታቸውን በስጦታም ይሁን በውርስ ማስተላለፍ የሚችሉት በገጠር መሬት አዋጅ ለተፈቀደላቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች ነበር፡፡ ይህ ከቤተሰቦቻቸዉ መሬት የማግኘት መብት ሊኖራቸዉ የሚገቡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጥቅም ገድቦ ቆይቷል። በአሁኑ አዋጅ የመንግስት ሰራተኞች ከቤተሰባቸው በዉርስና በስጦታ መሬት ማግኘት እንዲችሉ ይፈቅዳል።

- በአዲሱ አዋጅ የገጠር መሬት ባለይዞታዎች የይዞታ መብትን ለፈለጉት ሰው በስጦታ፣ በውርስ ማስተላለፍ መብትን ለማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ይፈቅዳል።

- የገጠር መሬት ይዞታን ለብድር ዋስትና ማስያዣነት በመጠቀም የብድር አገልግሎት ማግኘት የሚቻልበትን ድንጋጌ አካቷል። ይህም የክልሉን አርሶ አደር የብድር አቅርቦት ችግር መፍትሄ የሚሰጥ ነው ተብሏል።

- በአዲሱ አዋጅ በአስገዳጅ ሁኔታ የመሬት አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ስርአቱ ዲጂታላይዝ መሆን እንዳለበት በግልፅ ተመላክቷል፡፡

- ለሴቶች፤ ለህፃናት፤ ከቀያቸዉ በጊዜያዊነት ለለቀቁ፤ በህግ ጥላ ስር ያሉ፣ ለህሙማን፤ ለአረጋዊያንና…ወዘተ ጉዳዩን ልዩ ትኩረት በመሰጠት የህግ ከለላና መብት ጥበቃ ሰጥቷል፡፡ ይህ ድንጋጌ ከዚህ በፊት በነበሩ ህጎች ላይ ተካቶ ተፈጻሚ ቢሆንም በልዩ ትኩረት የተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን መብትና ጥቅም ጥበቃ ትኩረት እና ባለቤት በመስጠትም በኩል ትኩረት ተሰጥቶታል።

(በአዲሱ አዋጅ ከተካተቱ ነጥቦች ውስጥ በዚህ ክፍል የቀረበው በከፊል ነው)

via ቲክቫህ ኢትዮጵያ

በጊቤ ሶስት የኃይል ማመንጫ ግድብ ከ3 ሺህ ቶን በላይ ዓሣ ተመረተአዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት በጊቤ ሶስት የኃይል ማመንጫ ...
15/03/2025

በጊቤ ሶስት የኃይል ማመንጫ ግድብ ከ3 ሺህ ቶን በላይ ዓሣ ተመረተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት በጊቤ ሶስት የኃይል ማመንጫ ግድብ ከ3 ሺህ ቶን በላይ ዓሣ ማምረት መቻሉ ተገለጸ።

በቀን በአማካይ ከ500 ኪሎ ግራም በላይ የዓሣ ምርት እየተመረተ መሆኑን በዳውሮ ዞን ግብርና መምሪያ የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አስፋው ጮራሞ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ በዞን ደረጃ 4 ሺህ 200 ቶን ዓሣ ለማምረት መታቀዱን የገለጹት ኃላፊው÷ በስምንት ወራት ውስጥ..

Via Fana

24/01/2025
በዛሬው እለት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ  ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተገነባውን የኢቲ ማዕድን ልማት አ.ማ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካን መርቀን ስራ አስጀምረናል። ፋብሪካው በሀገር አቀፍ ...
24/01/2025

በዛሬው እለት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተገነባውን የኢቲ ማዕድን ልማት አ.ማ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካን መርቀን ስራ አስጀምረናል። ፋብሪካው በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የድንጋይ ከሰል ምርት ከማሻሻል ባሻገር ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል የፈጠረ ነው።
PM Abiy Ahmed

በዛሬው እለት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ  ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተገነባውን የኢቲ ማዕድን ልማት አ.ማ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካን መርቀን ስራ አስጀምረናል። ፋብሪካው በሀገር አቀፍ ...
24/01/2025

በዛሬው እለት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተገነባውን የኢቲ ማዕድን ልማት አ.ማ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካን መርቀን ስራ አስጀምረናል። ፋብሪካው በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የድንጋይ ከሰል ምርት ከማሻሻል ባሻገር ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል የፈጠረ ነው።

Today, we inaugurated the coal washing plant of ET Mining Development Co., Ltd., established in the South West Ethiopia Region, Dawuro Zone. This facility not only enhances national coal production but also provides significant employment opportunities for local residents.

Sources PM Abiy A

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ከወደብ ስምምነቱ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ፊት ለፊት ተወያዩ
12/12/2024

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ከወደብ ስምምነቱ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ፊት ለፊት ተወያዩ

ከቤተ ሙከራ የጠፉት አስጊ ቫይረሶች በቤተ ሙከራ ውስጥ የነበሩት ቫይረሶቹ ከእንስሳት ወደ ሰው መተላለፍ የሚችሉ ቫይረሶች እንዳሉበት ተገልጿልበአውስትራሊያ ኪዊንስላንድ ግዛት 100 የሆኑ እና...
12/12/2024

ከቤተ ሙከራ የጠፉት አስጊ ቫይረሶች

በቤተ ሙከራ ውስጥ የነበሩት ቫይረሶቹ ከእንስሳት ወደ ሰው መተላለፍ የሚችሉ ቫይረሶች እንዳሉበት ተገልጿል

በአውስትራሊያ ኪዊንስላንድ ግዛት 100 የሆኑ እና ለሰው ልጆች አስጊ የሚባሉ ቫይረሶች ከቤተ ሙከራ ጠፍተውብኛል ብላለች፡፡

ቫይረሶቹ እንዴት እና መቼ እንደጠፉ አልታወቀም የተባለ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ እንዲደረግ የሐገሪቱ ፍትህ ቢሮ አስታውቋል፡፡

ከጠፉት ቫይረሶች መካከል የእብድ ውሻ በሽታ፣ የፈረስ ወረርሽኝ እና ሌሎች በሽታ አምጪ ቫይረሶች አሉበትም ተብሏል፡፡

እንደ አውስትራሊያ ጤና ሚኒስትር ቲም ኒኮላስ መግለጫ ከሆነ ተጨማሪ ቫይረሶችም የተቀመጡበት ማቀዝቀዣ በመሰበሩ የቫይረሶች ሳምፕል ማዕከል ጠፍቷል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ቫይረሶቹ ካሳለፍነው ነሀሴ ወር ጀምሮ ይወገዱ ወይም ይጥፉ እስካሁን አልታወቀም ሲል ኤቢሲ ዘግቧል፡፡

ሁኔታው አሳሳቢ ነው ያሉት ሚኒስትሩ እነዚህ ለሰው ልጆች ጤና አስጊ የሆኑት ቫይረሶቹ ሆን ተብለው ይሰረቁ አልያም የሆነ ቦታ በጥንቃቄ ይቀመጡ የታወቀ ነገር እንደሌለም ተናግረዋል፡፡

አስተራዜኒካ ኩባንያ የኮሮና ቫይረስ ክትባት የደም መርጋት በሽታ እንደሚያስከትል አመነ

ቫይረሶቹ በኩዊንስላንድ ቤተ ሙከራ አካባቢ ከጠፉ በሙቀቱ ምክንያት ሊሞቱ እና በሰው ልጆች ላይ የከፋ ጉዳት ላያደርሱ ይችላሉም ተብሏል፡፡

ይሁንና ጠፉ የተባሉት ቫይረሶች በትክክል የት እንዳሉ አለመታወቁ በተለይም ሄንድራ የተሰኘው ቫይረስ ከእንስሳት ወደ ሰው መተላለፍ የሚችል አቅም ያለው መሆኑ ስጋት ደቅኗል፡፡

በአውስትራሊያዋ ብሪስቤን ከተማ እና አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች ውስጥ ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ 66 ያልታወቁ ወረርሽኞች የተከሰቱ ሲሆን ሰዎችን ጨምሮ ፈረሶች በቫይረሱ ምክንት ሞተዋል፡፡

በመሆኑም ጠፉ የተባሉት ቫይረሶች ያሉበት ሁኔታን ለማወቅ ምርመራ የተጀመረ ሲሆን ጉዳዩ ዓመታትን ሊወስድ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

በቱርክ አደራዳሪነት የተካሄደው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት ምን ምን ይዟል?ሶማሊያ የኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ስምምነት ሉዓላዊነቴን የሚጥስ ነው በሚል የአዲ አበባውን ስምምነት ውድቅ አ...
12/12/2024

በቱርክ አደራዳሪነት የተካሄደው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት ምን ምን ይዟል?

ሶማሊያ የኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ስምምነት ሉዓላዊነቴን የሚጥስ ነው በሚል የአዲ አበባውን ስምምነት ውድቅ አድርጋለች

በቱርክ አደራዳሪነት የተካሄደው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት ምን ምን ይዟል?

ከአንድ ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር በአዲስ አበባ የወደብ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባውን ስምምነት ተከትሎ ሶማሊያ ሉዓላዊነቴን የሚጥስ ነው በሚል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት አቋርጣም ነበር፡፡

የሁለቱም ሀገራት ወዳጅ የሆነችው ቱርክ በአንካራ የውይይት መድረክ ያዘጋጀች ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በትናንትናው ዕለት ወደ አንካራ አቅንተው ነበር፡፡

የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን የሁለቱን ሀገራት መሪዎች በተናጠል አግኝተው እንዳወያዩ እና ልዩነቶቻቸውን በስምምነት ለመፍታት መስማማታቸውን አናዶሉ ዘግቧል፡፡

የአንካራ ስምምነት የሚል ስም የተሰጠው ይህ ሰነድ ምን ምን ይዟል በግጭት ውስጥ የነበሩት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያስ የተስማሙባቸው ጉዳዮች ምን ምን ናቸው?

የቱርክ ኮሙንኬሽን ስምምነቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አደራዳሪነት የተካሄደው ስምምነት ለሁለቱም ሀገራት በሚጠቅም መንገድ መጠናቀቁን አትቷል፡፡

እንደ መግለጫው ከሆነ ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሉዓላዊነት ለማክበር የተስማማች ሲሆን የባህር በር ፍላጎቷንም ይህን በማይጥስ መልኩ ታካሂዳለች ተብሏል፡፡

እስከ መጭው የካቲት ወር መጨረሻ ቀናት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥም ሁለቱ ሀገራት የጋራ የቴክኒክ ቡድን በማዋቀር በአራት ወራት ውስጥ ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታገኝ የሚያስችላትን ስምምነት ለማጠናቀቅም እንደተስማሙ በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል፡፡

ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ አንዳቸው የሌላኛቸውን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት፣ ነጻነት እና ዓለም አቀፍ ህጎችን ለማክበር መስማማታቸውም በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሶማሊያ ለከፈሉት መስዋዕትነት ሶማሊያ እውቅና እንደምትሰጥም ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋ የሶማሊያን ሉዓላዊነት ባከበረ መልኩ እንዲፈጸም ሁለቱም ሀገራት ተስማምተዋል ሲልም መግለጫው አትቷል፡፡

ይሁንና ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መበላሸት ዋነኛ ምክንያት የሆነው እና ከአንድ ዓመት በፊት በአዲስ አበባ የተደረገው የኢትዮጵያ - ሶማሊላንድ የወደብ ስምምነት እጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን በመግለጫው ላይ አልተጠቀሰም፡፡

ራስ ገዟ ሶማሊላንድ ከሁለት ቀናት በፊት በርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮዎች ስራ እንደጀመረ መግለጿ ይታወሳል፡፡

 #ለመረጃ (ፌስታል ያስቀጣል!)በኢትዮጵያ የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም፣ ማምረት እና ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት በገንዘብ እና በእስራት የሚያስቀጣ ድንጋጌ የተካተተበት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወ...
12/12/2024

#ለመረጃ (ፌስታል ያስቀጣል!)

በኢትዮጵያ የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም፣ ማምረት እና ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት በገንዘብ እና በእስራት የሚያስቀጣ ድንጋጌ የተካተተበት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

በረቂቅ አዋጁ መሠረት የፕላስቲክ ከረጢት የተጠቀመ ወይም ለመጠቀም ይዞ የተገኘ ማንኛውም ሰው ከ5 እስከ 10 ሺህ ብር ገንዘብ ይቀጣል።

በተመሳሳይ የፕላስቲክ ከረጢት ማምረት፣ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት፣ ለገበያ ማቅረብ፣ መሸጥ ወይም ለንግድ ዓላማ ማከማች *ከሃምሳ እስከ መቶ ሺህ ብር ያስቀጣል።* ከዚህ በተጨማሪም ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።

አነዚህን "የወንጀል ድርጊቶች" የፈጸመው ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት በሚሆንበት ጊዜ ቅጣቱ ሦስት እጥፍ እንደሚሆን ረቂቁ ያትታል።

Source: theethiopianeconomistview

Address

Tercha Dawro@gmail. Com
Tarch'a S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tercha dawro promotion posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share