03/09/2026
በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 309 ሚልዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን በሸካ ዞን የየኪ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገለፀ።
የየኪ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ደረሻ በበጀት ዓመቱ ገቢን አሟጦ በመጠቀም "የውስጥ ወጪን በውስጥ ገቢ መሸፈን" በሚል መሪ ሐሳብ 70 በ 30ን ተግባራዊ በማድረግ የዕቅዱን 95 በመቶ ማሳካት መቻሉን ነው የተናገሩት።
በዚህም በተገባደደው በጀት ዓመት ከመደበኛና ከማዘጋጃ ቤት 323 ሚልዮን 9መቶ 38ሺ 5መቶ ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 309 ሚልዮን 9መቶ 77ሺ 8መቶ ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል።
ይህም ከአለፈው በጀት ዓመት ገቢ ሲነፃፀር የተሻለ ውጤት መሆኑን የገለፁት ሃላፊው በዚህም 95በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።
ለሥራው መሳካት ትኩረት ተደርጎ መሰራቱን ጠቅሰው መቶ በመቶ እንዳይሳካ ተግዳሮት የሆነው የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ማነስና የህገወጥ ነጋደ መስፋፋት እንደክፍተት የተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል።
የ2019 ገቢ ጠቅላላ እቅድ በተመለከተ ከመደበኛና ከማዘጋጃ ቤት 573ሚልዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ስራዎች መጀመራቸውን የገለፁት ኃላፊው እቅዱ እንዲሳካ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በቀጣይም የተሻለ አፈፃፀም ለማስፈፀም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር እንደሚያስፈልግና ግብር ከፋዩ ህብረተሰብም በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከቅጣት ነፃ በመሆን ግብሩን ሊከፍል እንደሚገባ ጥሪ አስተላልፈዋል።
Sheka Tv