Loma Bossa Woreda Communications

  • Home
  • Loma Bossa Woreda Communications

Loma Bossa Woreda Communications Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Loma Bossa Woreda Communications, Government Organization, Dawuro, .

በሎማ ቦሳ ወረዳ የዳውሮ ብሄር ዘመን መለወጫ ''ቶኪ በኣ'' በዓል በቀበሌ ደረጃ ተከበረየዳውሮ ብሄር ዘመን መለወጫ ቶኪ በኣ በዓል በሎማ ቦሳ ወረዳ በቀበሌ ደረጃ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች...
02/09/2026

በሎማ ቦሳ ወረዳ የዳውሮ ብሄር ዘመን መለወጫ ''ቶኪ በኣ'' በዓል በቀበሌ ደረጃ ተከበረ

የዳውሮ ብሄር ዘመን መለወጫ ቶኪ በኣ በዓል በሎማ ቦሳ ወረዳ በቀበሌ ደረጃ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በድምቀት ተከብሯል።

ቶኪ በኣ ከጥንት ጀምሮ እየተከበረ የመጣ በዳውሮ ብሄር ዘንድ ከሌሎች በዓላት ልዩ ትርጉም ያለው በዓል መሆኑን የባህል ሽማግሌዎቹ ተናግራዋል።

በብሄሩ ዘንድ በዚህ በዓል ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲስ ዓመት መሻገርን፣ አዲስ ተስፋና ሀሳብ ማስጀመሪያ፣ ተራርቀው የነበሩ አንድ የሚሆኑበት፣ የተጣሉ የሚታረቁበት፣ አቅመ ደካሞች የሚረዱበት፣ የዘመን መለወጫና ሌሎች በርካታ ማህበራዊና ባህላዊ ዕሴቶችን የሚያንጸባርቅ መሆኑን ተናግረዋል።

ለበዓሉ ድምቀት ከጥንትም በተለመደ ስርዓት አባቶች፣ እናቶች፣ ሴትና ወንድ ወጣቶች እያንዳንዳቸው ለረጅም ጊዜ የበኩላቸውን የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚያደርጉም በመግለጽ።

በዓሉ በውስጡ በርካታ ባህላዊ፣ ታሪካዊና ማህበራዊ ዕሴቶችን የያዘ በመሆኑ በዓለም የሳይንስና ትምህርት ድርጅት ዩኔስኮ ላይ ለማስመዝገብ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ከግብ እንዲደርስ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ተናግረዋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

የዳውሮ ዞን አመራሮች ላለፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂዱት የቆዩት የግምገማ እና ምዘና መድረክ ዛሬ ተጠናቋል።‎‎በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስ...
01/09/2026

የዳውሮ ዞን አመራሮች ላለፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂዱት የቆዩት የግምገማ እና ምዘና መድረክ ዛሬ ተጠናቋል።

‎በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ መኩሪያ አመራሩ በመንግስትና በፓርቲ የተጣለበትን ኃላፊነቱን በብቃት በመወጣት፣ መልካም ስነ-ምግባርን መላበስ፣ የአመለካከት ጥራትን ማጎልበት እና የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን በብቃት መፈፀም የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንዳለበት ገልጸዋል።

‎የአመራር ምዘናውን በተመለከተም የአመራሩ ቁርጠኝነት፣ ተነሳሽነት፣ የተግባር አፈጻጸም እና የተጣለበትን ተልዕኮ የመወጣት ሚና መነሻ በማድረግ አካላዊና ሂስ ግለ-ሂስ ግምገማ እና ምዘና ተካሂዷል።

‎በግምገማው ወቅት በ2018 በጀት ዓመት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸው የተጠቀሰ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ አሁንም ተገቢውን ምላሽ ያላገኙ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች፣ የአመራር ውጤታማነት ችግር፣ አገልግሎት አሰጣጥ፣ፈጣን ምላሽ እና ብልሹ አሰራር ችግሮች በዝርዝር ተገምግመዋል።

ፓርቲው ከዚህ ግምገማ መነሻ በማድረግ ጉድለቶችን በጥልቀት በመገምገም በተለዩ ጉዳዮች ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድም አስታውቋል።

‎አቶ መንግስቱ አክለውም እያንዳንዱ አመራር በተመደበበት የሥራ ኃላፊነት ላይ የህዝቡን ተጠቃሚነትና ለማረጋገጥ ከምን ጊዜም በላይ በላቀ ቁርጠኝነት መሰራት እንዳለበት በማጠቃለያው በዝርዝር ያነሱ ሲሆን በሌብነትና ብልሹ አሠራር ላይ ተጠያቂነት የሚያሰፍን አሰራር መዘርጋት እንዳለበት አሳስበዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የአመራር አንድነትን የሚሸረሽሩ፣ የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎችን የሚያደናቅፉ እንዲሁም ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ አፍራሽ አስተሳሰቦችን በንቃት መመከት እንደሚገባ ተገልጿል።

‎በዚህ መድረክ የተለዩ ችግሮችን መነሻ በማድረግ ሁሉም መዋቅር ላይ ያሉ ጉዳዮች በዝርዝር የመገምገም ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ ቀጣዩ የግምገማ ምዕራፍ በወረዳና በከተማ አስተዳደር እርኬን እንደሚካሄድም ተጠቁሟል።

‎የመድረኩ ተሳታፊ አመራሮች በበኩላቸው የፓርቲና የመንግሥት ተግባራትን በላቀ ውጤት ለመፈጸም ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸው፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ማነቆዎችን በቆራጥነት ለመፍታትና የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በቅንጅት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

በግምገማው መድረክ የተገኙ የዞኑ አጠቃላይ አመራሮች በተያዘው በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ የሕዝቡን ተጠቃሚነት በተጨባጭ ለማረጋገጥ የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ በመደረስ ተጠናቋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

31/08/2026
29/08/2026
በዳውሮ ዞን የ2018 በጀት ዓመት የማጠቃለያ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ በመካሄድ ላይ ነው‎‎በዳውሮ ዞን የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ በታርጫ ከተማ...
29/08/2026

በዳውሮ ዞን የ2018 በጀት ዓመት የማጠቃለያ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ በመካሄድ ላይ ነው

‎በዳውሮ ዞን የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ በታርጫ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

‎መድረኩ በየደረጃው የሚገኘውን አመራር የአመለካከትና የተግባር አንድነት ለመመዘን የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም እንዲሁም አመራሩ በቀጣይ የሕዝብ ተጠቃሚነትን በተሟላ ሁኔታ እንዲያረጋግጥ ለተልዕኮ ለማዘጋጀት ያለመ ነው።

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ በንግግራቸው ተልዕኮዎችን በተሻለ መልኩ በመፈጸም የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መጠነ ሰፊ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።

‎ከአፈጻጸም አኳያም ከጊዜ ወደ ጊዜ አዎንታዊ መሻሻሎች መታየታቸውን ያብራሩ ሲሆን በአስፈፃሚ ተቋማት መካከል የሚታየውን የተግባር አፈጻጸም ልዩነት መስተካከል እንደሚገባም አሳስበዋል።

‎የአመራር ቁመና በብልፅግና ፓርቲ መሠረታዊ መርሆችና ዕሴቶች ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበትም አቶ አንድነት አክለዋል።

‎የመድረኩ ዋና ዓላማም አስፈጻሚዎች የመንግሥትና የፓርቲ ተግባራትን በጥራት፣ በእውቀትና በውጤታማነት እንዲያከናውኑ ማብቃት መሆኑም ተገልጿል።

‎ በተጨማሪም መድረኩ ድክመቶችን በማረም ለቀጣይ ተልዕኮ ከማዘጋጀት ባሻገር፣ የውስጠ-ፓርቲ አንድነትን፣ ጤንነትንና የዴሞክራሲያዊ መርህን በማረጋገጥ የሕዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳካት የጎላ ሚና እንደሚኖረውም ተመላክቷል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

የዘንድሮ (ቶኪ በኣ) በዓል ባማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር የተለያዩ ድጋፍና ተሳትፎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!በሎማ ቦሳ ወረዳ የዳውሮ ብሔር የዘመን መለወጫ ቶኪ-በኣ በዓልን ከወትሮው በተሻለ ድ...
28/08/2026

የዘንድሮ (ቶኪ በኣ) በዓል ባማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር የተለያዩ ድጋፍና ተሳትፎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

በሎማ ቦሳ ወረዳ የዳውሮ ብሔር የዘመን መለወጫ ቶኪ-በኣ በዓልን ከወትሮው በተሻለ ድምቀት ለማክበር እንዲቻል የወረዳው አመራሮችና ባለሙያዎች በተከፈተው አካውንት ገቢ በማድረግ የድርሻቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።

‎1. የተከበሩ አቶ አየለ አይኑ የወረዳው ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ 1,000 ሺህ ብር፣
2. ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ኡቴ የወረዳው ኢንዱስትሪና ንግድ ጽ/ቤት ባለሙያዋ 1,000 ሺህ ብር፣
‎3. አቶ እስትፋኖስ ፋንታ የያሎ ላላ ማዘጋጃ ስራአስኪያጅ 1,000 ሺህ ብር፣
4. አቶ አብርሃም ኩሼሮ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ 1,000 ሺህ ብር፣
5. አቶ ተካልኝ ጊያ የወረዳው ብ/ፓ/ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮምሽን ጽ/ቤት ም/ኃላፊ 1,000 ሺህ ብር፣
6. አቶ ፋንታሁን በላይነህ የወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ 1,000 ሺህ ብር፣
7. አቶ በላይነህ ባፌ የወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ 1,000 ሺህ ብር፣
8. አቶ ወንድራድ ዘውዴ የወረዳው ፐ/ሰ/ሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት ም/ኃላፊ 1,000 ሺህ ብር፣
9. አቶ ሙላቱ ግማሮ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ም/ኃላፊ 1,000 ሺህ ብር፣
10. አቶ ዳዊት ኡኩሞ የወረዳው ውሃ ማ/ኢ/ጽ/ቤት ኃላፊ 1,000 ሺህ ብር፣
11. አቶ ወርቅነህ ፎላ የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ 1,000 ሺህ ብር በተከፈተው አካውንት ገቢ አድረገዋል። እናመሰግናለን ‼️

‎እርስዎም የዳውሮ ብሔር ዘመን መለወጫ ቶኪ በዓ በዓልን በድምቀት ለማክበር እንዲቻል ለዚሁ ዓላማ በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000642925842 የአቅምዎትን ያህል ገንዘብ ገቢ በማድረግ ድርሻዎትን እንዲወጡ ተጋብዘዋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

በዳውሮ ዞን ሎማ ቦሳ ወረዳ ቦሳ ፀደፋ ቀበሌ የ2018/19 ምርት ዘመን የመኸር እርሻ ሰብል ማሳ በከፊልበተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇Follows us via👇Facebook...
27/08/2026

በዳውሮ ዞን ሎማ ቦሳ ወረዳ ቦሳ ፀደፋ ቀበሌ የ2018/19 ምርት ዘመን የመኸር እርሻ ሰብል ማሳ በከፊል

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

የዳውሮ ብሔር የዘመን መለወጫ (ቶኪ በኣ) በዓል አከባበር በሎማ ቦሳ ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች፡- በፎቶ
27/08/2026

የዳውሮ ብሔር የዘመን መለወጫ (ቶኪ በኣ) በዓል አከባበር በሎማ ቦሳ ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች፡- በፎቶ

‎የዳውሮ ብሔር ዘመን መለወጫ 'ቶኪ በኣ' በሎማ ቦሳ ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት እየተከበረ ነውየእርቅ፣ የፍቅርና የአንድነት እንዲሁም የመጪው ዘመን ብሩህ ተስፋ ምሳሌ ተደርጎ የሚከ...
27/08/2026

‎የዳውሮ ብሔር ዘመን መለወጫ 'ቶኪ በኣ' በሎማ ቦሳ ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት እየተከበረ ነው

የእርቅ፣ የፍቅርና የአንድነት እንዲሁም የመጪው ዘመን ብሩህ ተስፋ ምሳሌ ተደርጎ የሚከበር ደማቅ ህዝባዊ በዓል (ቶኪ በኣ) በዳውሮ ዞን ሎማ ቦሳ ወረዳ ጪጮ ሃዮ እና ቤሮ ያማላ ቀበሌ በልዩ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።

ቶኪ በኣ አሮጌውን ዓመት በመሸኘት አዲሱን ዓመት በአዲስ ተስፋና ሙላት የሚቀበሉበት፣ ተራርቀው ያሉ የሚሰበሰቡት፣ የተጣሉ የሚታረቁበት እንዲሁም የመጪው ዘመን ብሩህ ተስፋ ምሳሌ ተደርጎ የሚከበር በዓል እንደሆነም ነው የተገለጸው።

የሎማ ቦሳ ወረዳ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጳውሎስ በቀለ እንደገለፁት፣ ቶኪ በኣ ከጥንት ጀምሮ የሚከበርና ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በዓል መሆኑን በመግለፅ የተጣላው የሚታረቅበት፣ አሮጌ ዓመት የሚሸኝበት፣ አዲሱን ዓመት የምንቀበልበት የጥጋብና የእርቅ በዓል በመሆን በፍቅርና በህብረት በድምቀት እያከበረ ይገኛል ብለዋል።

በበዓሉ ሰው ብቻ ሳይሆን የቤት እንስሳት ጭምር ጠግበው፣ ማድጋው በውሃ ተሞልተው የሚታደርበት ህዝባዊ በዓል መሆኑን የሀገር ሽማግሌ አቶ ኦንዱ ጎዳንቾ ገልጸዋል።

በዓሉ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመቻቻል፣ የደስታና የተድላ እንዲሆን የሀገር ሽማግሌዎች መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ መርቀዋል።

‎በበዓሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፍቃድ አገልግሎት የአብሮነትና ወንድማማችነት ለማጠናከር ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ "በጎነት ለአብሮነት" በሚል መሪ ቃል በዳውሮ ዞን ብልፅግና ፓርቲ በወጣቶች እና ሴ...
22/08/2026

ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፍቃድ አገልግሎት የአብሮነትና ወንድማማችነት ለማጠናከር ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

"በጎነት ለአብሮነት" በሚል መሪ ቃል በዳውሮ ዞን ብልፅግና ፓርቲ በወጣቶች እና ሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት የታርጫ ከተማ አስ/ር የሰላም በጎ ፈቃደኞች በጎነትን በማስረጽ እና አብሮነትን በማጠናከር የዜግነት ኃላፊነት ለመወጣት በሎማ ቦሳ ወረዳ ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር አካሂደዋል።

በመርሃ-ግብሩም በወረዳው ኤላ ባቾ ቀበሌ ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች 60 ደርዘን የመማሪያ ቁሳቁስ እና ለአረጋውያን የአልባሳት ድጋፍ ለማድረግ ተችሏል።

የሎማ ቦሳ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪና ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስረስ ገቲሶ ለዕለቱ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ በማለት፣ በወሰን ተሻጋሪ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ለተደረገው ድጋፍ የምስጋና መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በጎ ፈቃደኞች ያደረጉት የቁሳቁስ ድጋፍ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠዉ የፍቅር ስጦታ መሆኑን በመግለፅ ተመሳሳይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በወረዳው በስፋት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

አቶ አስረስ አክለውም የወሰን ተሻጋሪ በጎ ፍቃድ አገልግሎቱ የህቦችን አንድነት በማጠናከር አይነኛ ሚና መኖሩን ገልፀው፣ በቀጣይ ከበጎ ፈቃደኞች ጋር በርካታ ተግባራት በቅንጅት ለመስራት ቃል ገብተዋል።

በዕለቱም የዳውሮ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ብሩክ አርባ በበኩላቸው፣ የወሰን ተሻጋሪ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዋና ዓላማ የሕዝቦች ትስስርና አብሮነት ለማጠናከር ያለመ ሰዉ ተኮር ተግባር እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ወሰን ተሻጋሪ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የአብሮነት ማጠናከሪያ እና ወጣቶች ለሀገር የመቆም ማሳያ ነው ሲሉም ወ/ሮ ብሩክ ገልጻለች።

ወጣቶቹ በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውረው አገልግሎቱን በሚሰጡበት ወቅት የማህበረሰቡን መልካም እሴት እንዲያውቁ ዕድል እንደሚፈጥር ከፌዴራል ሰላም ሚኒስትር የታርጫ ማዕከል አስተባባሪ አቶ ታደሰ ሜጋ ተናግረዋል፡፡

በሰላም ሚኒስትር የሚመራው የሰላም በጎ ፈቃድ የክረምት ማህበረሰብ አገልግሎት በሕዝቦች መካከል ያለዉን አብሮነት ይበልጥ ከማጠናከር ባለፈ እርስ በእርስ የመተባበርና የመደጋገፍ ባህልን የሚያዳብር ተግባር ነው ያሉት።

የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ የተሳተፉ ወጣቶችም በዚህ የመልካም ስራ ተግባር ላይ ተሳታፊ መሆናቸው እና የአብሮነት፣ የወንድማማችነትና የሀገር ፍቅር ስሜታቸውን ለማጠንከር እንደረዳቸው ተናግረዋል፡፡

በመርሐ-ግብሩ የችግኝ ተከላ፣ ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ እና ለአረጋውያን የአልባሳት ድጋፍ ተደርጓል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Address

Dawuro

LOMA

Telephone

+251939599037

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Loma Bossa Woreda Communications posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Loma Bossa Woreda Communications:

Shortcuts

  • Want your organization to be the top-listed Government Service?

Share