02/09/2026
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ በጉራጌ ዞን የገቢ አሰባሰብ ስራዎች ድጋፍና ክትትል እያደረገ ይገኛል።
(ነሀሴ 27/2018) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ አሰፋ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ የገቢ አፈጻጸም ስራዎችና የቀጣይ ገቢ አሰባሰብ ላይ የድጋፍና ክትትል ሥራ አካሂዷል።
በዞኑ በሁሉም መዋቅር የበጀት ዓመቱን የገቢ ዕቅድ እስከ ጳጉሜ 03/2018 ድረስ 18.4 በመቶ ለማድረስ በተያዘው ዕቅድ መሰረት በዛሬው ዕለትም የገቢ አሰባሰብ ስራዎችን ከዞኑ ገቢዎች መምሪያ እና ከአበሽጌ የገቢ ማኔጅመንት ጋር በመሆን የአፈጻጸም ሂደትን በጥልቀት ገምግመዋል።
ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ አሰፋ እንደገለጹት የተቀመጠው የገቢ ግብ እንዲሳካ በተቋሙ የተቀመጡ የገቢ አሰባሰብ የአሰራር ስርአቶች በመከተል መስራት ይገባል ብለዋል።በዚህ መሰረት የደረሰኝ ቁጥጥር ስርዓትን ማጠናከር፣ የኦዲት ግኝት ገቢዎችን መሰብሰብ፣ የማዘጋጃ ቤት የበረትና የመደብ ገቢ አሰባሰብን በማሳደግ የተያዘው እቅድ ለማሳካት ርብርብ እንዲደረግ አሳስበዋል።
የገቢ አማራጮችን በመፈለግ የተሻለ ገቢ በመሰብሰብ የኢኮኖሚ አቅም ለማጎልበት በቅንጅትና በትጋት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ ሀላፊ አቶ ሚነወር ሀያቱ በበኩላቸው በሁሉም ዘርፍ ገቢን አሟጦ መሰብሰብ ለህብረተሰቡ መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መመለስና የአመቱን ዕቅድ ለማሳካት መስራት እንደሚገባ ጠቅሰው ትኩረት ይሻሉ ባልዋቸው የሮያሊቲ ገቢ አሰባሰብ፤የጫት ቀርጥ ስራን፤የግል ድርጅቶች የደሞዝ ስራ ግብርና የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ እንዲጠናከር ብለዋል።
በውይይቱ የአበሽጌ ወረዳ ገቢ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፋንታሁን የወረዳው ፖቴንሽያ አሟጠን ገቢ በመሰብሰብ የወረዳችን ልማት እንዲውል እንሰራለን ብለዋል።