Alicho Communication - ስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ መንግስት ኮመንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ።

  • Home
  • Ethiopia
  • Werabe
  • Alicho Communication - ስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ መንግስት ኮመንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ።

Alicho Communication - ስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ  መንግስት ኮመንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ። ይህ ፔጅ የአልቾ ውሪሮ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።
(1)

የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ዋና ሀላፊ አቶ ሙበራ ከማል በአልቾ ውሪሮ ወረዳ የገጠር ኮሪደር የክላስተር ፍራፍሬ ልማትን በይፋ አስጀመሩቃዋቆቶ ነሀሴ 6/2018 {አልቾ ...
12/08/2026

የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ዋና ሀላፊ አቶ ሙበራ ከማል በአልቾ ውሪሮ ወረዳ የገጠር ኮሪደር የክላስተር ፍራፍሬ ልማትን በይፋ አስጀመሩ

ቃዋቆቶ ነሀሴ 6/2018 {አልቾ ኮሙኒኬሽን}

የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ዋና ሀላፊ አቶ ሙበራ ከማል ከመምሪያው ምክትል ሀላፊዎችና ከአልቾ ውሪሮ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በጋራ በመሆን በወረዳው የገጠር ኮሪደር የክላስተር ፍራፍሬ ልማትን በወሻኖ እና ቀረሶ ቀበሌ በይፋ አስጀምረዋል።

በማስጀመሪያው መረሀ-ግብር የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብና መምሪያ ዋና ሀላፊ አቶ ሙበራ ከማል፣ የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ መህዲያ ሀሰን የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትልና የእርሻ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሳዲቅ አህመዲን የቡናና ቅመማ-ቅመም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ቶፊቅ ኑሪ እንዲሁም የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሙዘይን መሀመድ ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና ጽ/ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ሱልጣን በርጋ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ሙባረክ አሊ እንዲሁም ሌሎች የወረዳ አመራሮች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የዳሎቻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሪድዋን መሶሮ፣የወረዳው ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አልዬ ፈረጆ እና የወረዳው የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብድልካሊቅ መሀመድ ከአልቾ ውሪሮ ...
11/08/2026

የዳሎቻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሪድዋን መሶሮ፣የወረዳው ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አልዬ ፈረጆ እና የወረዳው የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብድልካሊቅ መሀመድ ከአልቾ ውሪሮ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገኙ የትምህርት ቁሳቁሶችን ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች አስረክበዋል።

መረዳዳትና መደጋገፍ የማህበረሰባችን ነባር እሴት ቢሆንም የራሱ የሆነ ፖሊሲ ተቀርፆለት እንዲመራ ከተደረገ ወዲህ ይበልጥ እየተጠናረና ችግር ፈቺ እየሆነ መምጣቱን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሪድዋን መሶሮ በርክክቡ ወቅት ገልጸዋል።

መረዳዳትና መደጋገፉ ከአካባቢ አልፎ ወሰን ተሻጋሪ መሆኑ ደግሞ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትንና አብሮነትን ይበልጥ እያጠናከረ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በዚህም ከፍተኛ የሆነ የመንግስት ወጪን ማዳን ተችሏል ብለዋል።

የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰብሬ ዑመር፣የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሪድዋን ረሻድ እና ሌሎች የክንፉ አመራሮችም በርክክብ ሰነ ስርዓቱ ላይ ተሳትፈዋልተ
ምንጭ የዳሎቻ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ነው።

‎"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው ወረዳዊ የክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት በተለያዩ የስራ መስኮች ተጠናክሮ ቀጥሏል‎=========‎በወሻኖ ቀበሌ በክረምት በጎፈቃድ አገል...
11/08/2026

‎"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው ወረዳዊ የክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት በተለያዩ የስራ መስኮች ተጠናክሮ ቀጥሏል
‎=========
‎በወሻኖ ቀበሌ በክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት ለአቅማ ደካማ የተገነባው ቤት ተጠናቆ ዛሬ በአከባቢው ወጣቶች የጭቃ ስራው ሙሉ በሙሉ ተለጥፎዋለ።

ሰው ተኮር የሆኑ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለያዩ የስራ መስኮች ተጠናክረው ቀጥለዋል‎‎ቃዋቆቶ ነሀሴ 5/2018 {አልቾ ኮሙኒኬሽን}‎‎በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ የክረምት በጎ ፈ...
11/08/2026

ሰው ተኮር የሆኑ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለያዩ የስራ መስኮች ተጠናክረው ቀጥለዋል

‎ቃዋቆቶ ነሀሴ 5/2018 {አልቾ ኮሙኒኬሽን}

‎በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልገሎት የተቸገሩ የማህረሰብ ክፍሎችን የፈረሱ ቤቶችን በመጠገንና አዲስ በመስራት፣ በእርሻና በተለያዩ ሰው ተኮር በሆኑ የበጎ ስራዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።

‎በዛሬው እለትም የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሙዘይን መሀመድ፣ የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ዋና ሀላፊ አቶ ሱልጣን በርጋ፣ የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ሙባረክ አሊ እና የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሳረት ረዲ በአብዛና 1 ቀበሌ የአካል ጉዳተኞችን ቤት ግንባታ አስጀምረዋል።

‎የቤት መስሪያ ቆርቆሮና ሚስማር በወረዳው ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ድጋፍ የተደረገ ሲሆን የአከባቢው ማህበረሰብ የእንጨትና የጉልበት እገዛ አድርገዋል።

ተጠናክሮ የቀጠለው የ2018 የወጣቶች የክረምት ወራት የወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርኃ ግብር ዛሬ አልቾ ውሪሮ ወዳን ከዳሎቻ ወረዳ አገናኝቷል።የአልቾ ዉሪሮ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ...
11/08/2026

ተጠናክሮ የቀጠለው የ2018 የወጣቶች የክረምት ወራት የወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርኃ ግብር ዛሬ አልቾ ውሪሮ ወዳን ከዳሎቻ ወረዳ አገናኝቷል።

የአልቾ ዉሪሮ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልዑክ በዳሎቻ ወረዳ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የሚሆኑ የተለያዩ የድጋፍ ቁሳቁሶችን ይዞ ወደ ዳሎቻ ወረዳ ገብቷል።

የዳሎቻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሪድዋን መሶሮ እና የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አልዬ ፈረጆ እና ሌሎች የፓርቲ አመራሮች ለልዑካን ቡድኑ አቃባበል አድርገዋል።

ዳሎቻ ኮሙኒኬሽን

የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የክረምት በጎ ፈቃደኞች የዲጂታል ሊትሬሲ ስልጠና መስጠቱን ገለጸ፡፡ቃዋቆቶ ነሀሴ 5/2018 አሊቾ ኮሙኒኬሽንየአልቾ ውሪሮ ወረዳ ሳይንስ እና ቴክኖሎ...
11/08/2026

የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የክረምት በጎ ፈቃደኞች የዲጂታል ሊትሬሲ ስልጠና መስጠቱን ገለጸ፡፡

ቃዋቆቶ ነሀሴ 5/2018 አሊቾ ኮሙኒኬሽን

የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የክረምት በጎ ፈቃደኞች የዲጂታል ሊትሬሲ ስልጠና መስጠቱን ገልጿል፡፡

ስልጠናውን ያስጀመሩት የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መሀመድ ሁሴን ስልጠናው ለቀጣዩ አዲስ ዓመት ሥራዎች እንዲሁም ለባለሙያዎች የግል እውቀትና ክህሎት የሚጠቅም መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ሃላፊው አክለውም ዘመኑ የቴክኖሎጂ ዘመን በመሆኑ ከዘመኑ ጋር የሚራመዱ፣ ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ማፍራት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም፣ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ጥረት ማድረግና አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ አቶ መሀመድ አንስተዋል፡፡

የወረቀት ሥራን በመቀነስ ወደ ዲጂታል አሰራር መሸጋገር የዘመኑ አስፈላጊ አቅጣጫ መሆኑን አቶ መሀመድ ለሰልጣኞች ባስተላለፉት መልክት ተናግረዋል፡፡

የዲጂታል ሊትሬሲ ስልጠናው በቀጣይነት እንደሚሰጥና የባለሙያዎችን የዲጂታል እውቀትና ክህሎት ለማሳደግ ተጨማሪ ሥራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸዋል።

እድሜ ያልገደበው የበጎ ተግባር  በህመምተኛው ርድዋን ሰይድ ማሳቃዋቆቶ ሀምሌ 5/2018 (አሊቾ ኮሚኒኬሽን)በስልጤ ዞን አሊቾ ውሪሮ ወረዳ የሚገኙ በአረጋዊያን  ማህበር ተደራጅተው የሚንቀሳቀ...
11/08/2026

እድሜ ያልገደበው የበጎ ተግባር በህመምተኛው ርድዋን ሰይድ ማሳ

ቃዋቆቶ ሀምሌ 5/2018 (አሊቾ ኮሚኒኬሽን)

በስልጤ ዞን አሊቾ ውሪሮ ወረዳ የሚገኙ በአረጋዊያን ማህበር ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ የመንግስት ሰራተኞች በህመም ላይ ለሚገኘው ለአሊቾ ውሪሮ ወረዳ ፍርድ ቤት ጥበቃ ለአቶ ርድዋን ሰይድ የክረምት በጎ ተግባር ከአሊቾ ውሪሮ ወረዳ ማህበራዊ ጽ/ቤት ድጋፍ ባገኙት የካሮት ዘር ጉልበታቸውን ሳይሰስቱ ከመደብ ዝግጅት እስከ ዘር መዝረት በጎ ተግበርን ከውነዋል።

የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ መሀመድ ሹኩር እኛ አረጋዊያን ዕድሜ ሳይገድበን ተመሳሳይ በጎ ተግባር ላይ ለመሰማራት ሰፊ ዕቅድ እንዳለቸው እና በዛሬው ዕለት የማህበሩ አበል ለሆኑት የአሊቾ ውሪሮ ወረዳ ፍ/ቤት ጥበቃ አቶ ርድዋን ሰይድ በህመም ላይ ስለሚገኝ ቤተሰቡና ልጆቹን በማስተባበር ማህበሩ መደብ በማዘጋጀት የከሮት ዘር መዝራታቸውን ገልጸዋል ።

ወጣቶች ከእኛ ምን ይማሩ ? ለሚለው አቻ ትርጉም ለመስጠት ቀጣይ ሰፊ እንቅስቃሴዎች እንደሚደረጉ ከማህበሩ አባላት መረጃ ለማግኘት ችለናል።

በዘር ፕሮግራሙ ላይ የአሊቾ ውሪሮ ወረዳ አረጋዊያን ማህበር አመራር እና አባላት የህመምተኛው ቤተሰብ ተገኝተው ተሳትፎ አድርገዋል።

‎በአልቾ ውሪሮ ወረዳ እየተካሄ የሚገኘው የአቅመ ደካሞችና አረጋዊያን ቤት ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል‎‎የወረዳው ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ጀማል ሻሚል፣የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀ...
10/08/2026

‎በአልቾ ውሪሮ ወረዳ እየተካሄ የሚገኘው የአቅመ ደካሞችና አረጋዊያን ቤት ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል

‎የወረዳው ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ጀማል ሻሚል፣የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሳረት ረዲ፣የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ዋና ሀላፊ አቶ ሰማን ሀይረዲንና ሌሎች የወረዳ አመራሮች በጋራ በለምለም-3 ቀበሌ ለእናታችን ወ/ሮ ኦርመጌ ያሲንና ለአቶ ሸምሱ ከማል የቤት ግንባታ ስራውን አስጀምረዋል።

ለቤት ግንባታው የሚያስፈልገውን የቆርቆሮና ምስማር እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን የለምለም ዙሪያ ወጣቶች 200ሺ ብር ወጪ በማድረግ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።

በጎነት በተወሰኑ አካላት ብቻ የሚፈጸም ተግባር ባለመሆኑ የለምለም ዙሪያ ወጣቶቹ ለአቅመ ደካማ ቤተሰቦች ያደረጉት ድጋፍ ለሌሎችም ተሞክሮ የሚወሰድበት እንደሆነ ተገልጿል።

የወረዳው አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ ከሚኖሩ የዳምዘገር ክላስተር የአካባቢው ተወላጆች ጋር የውይይት መድረክ ማካሄዱ ተገለጸ‎‎ ቃዋቆቶ፣ነሓሴ 3/2018(አልቾ ኮሙኒኬሽን) የአልቾ ውሪሮ ...
09/08/2026

የወረዳው አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ ከሚኖሩ የዳምዘገር ክላስተር የአካባቢው ተወላጆች ጋር የውይይት መድረክ ማካሄዱ ተገለጸ

‎ ቃዋቆቶ፣ነሓሴ 3/2018(አልቾ ኮሙኒኬሽን) የአልቾ ውሪሮ ወረዳ አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ ከሚኖሩ የዳምዘገር ክላስተር የአካባቢው ተወላጆች ጋር የውይይት መድረክ ማካሄዱ ተገልጿል።

‎የውይይት መድረኩን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ መህዲያ ሀሰን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሙዘይን መሀመድና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ሙባሪክ አሊ ጋር በጋራ የመሩት ሲሆን መድረኩ የዳምዘገር ከተማን ጨምሮ በክላስተሩ በሚገኙ በለምለም1,2,3 ቀበሌዎች የሚስተወሉ የልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮችን በቅንጅት ለመፍታት ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

አስሚድ ለቤዛ በጎ አድራጎት ማኅበር 4 አካልጉዳተኛ ልጆቿን እያስታመመች ላለች እናታችን የምግብና አልባሳት ድጋፍ አደረገ‎‎ቃዋቆቶ፣ነሓሴ 3/2018 አልቾ ኮሙኒኬሽን‎‎አስሚድ ለቤዛ በጎ አድ...
09/08/2026

አስሚድ ለቤዛ በጎ አድራጎት ማኅበር 4 አካልጉዳተኛ ልጆቿን እያስታመመች ላለች እናታችን የምግብና አልባሳት ድጋፍ አደረገ

‎ቃዋቆቶ፣ነሓሴ 3/2018 አልቾ ኮሙኒኬሽን

‎አስሚድ ለቤዛ በጎ አድራጎት ማኅበር በዛሬው ዕለት በለምለም1 ቀበሌ ለአንድ አቅመደካማ እናት የምግብና አልባሳት ድጋፍ አድርጓል።

‎ማኅበሩ በማኅበራዊ ኃላፊነቱ መሠረት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ቤተሰቦችን በመርዳት ላይ ትኩረቱን በማድረግ አቅመደካሞችን በመለየት የቤትግንባታ ከማድረግ በተጨማሪ በግብርና ስራዎችና በሌሎች ስራዎችም በማገዝ ዘላቂ መፍትሔዎችን በመስጠት ምሳሌ እየሆነ መምጣቱ ተገልጿል።

‎ማህበሩ ከኩተሬ ከተማ በተጨማሪ በዙሪያ በሚገኙ ሌሎች ቀበሌዎችም አቅመደካሞችን በመለየት ድጋፎችን ሲያደርግ መምጣቱ የተገለጸ ሲሆን በዛሬው እለትም በለምለም1 ቀበሌ 04 አካልጉዳተኛ ልጆቿን እያስተመመች ለምትገኝ እናታችን የአልባሳትና የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ግዴታውን እየተወጣ እንደሚገኝ ተገልጿል።

‎አስሚድ ለቤዛ ማኅበር በተከታታይ የሚያከናውናቸው የበጎ አድራጎት ሥራዎች ማኅበረሰቡን በመደገፍና የተቸገሩትን በመርዳት ረገድ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አመልክቷል። ማኅበሩ ወደፊትም ተመሳሳይ ድጋፎችን በማስፋት እንደሚቀጥል ገልጿል።

Address

Silte
Werabe
KAWAKOTO

Opening Hours

Monday 07:00 - 19:00
Tuesday 07:00 - 19:00
Wednesday 07:00 - 19:00
Thursday 07:00 - 19:00
Friday 07:00 - 17:00
Saturday 07:00 - 17:00
Sunday 07:00 - 19:00

Telephone

+251924711807

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alicho Communication - ስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ መንግስት ኮመንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ። posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Alicho Communication - ስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ መንግስት ኮመንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ።:

Shortcuts

Share