Woreta Dry Port Customs Center

Woreta Dry Port Customs Center Government Organization

30/06/2023
02/04/2023

24/07/2015ዓ.ም ወረታ የወረታ ከተማ አስተዳደር የመ/ቤቶች የጤና የስፖርት ውድድር በሁለት ምድብ ተከፍሎ ውድድር እያደረገ ይገኛል። በመሆኑም የወረታ ጉምሩክ የጤና ስፖርት ቡደን ምድብ "ሀ" ስር ተመድቦ ጨዋታውን እያደረገ ይገኛል። እስካሁን በተከናወኑ የምድብ ጨዋታዎች ሁለት ጨዋታዎች አድርገን ሁለቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ ገና ቀሪ 1(አንድ) ጨዋታ እያለን ከምድቡ 6 ነጥብ እና 4 ንፁህ ጎል በመያዝ ማለፋችን አረጋግጠናል። ከዚህ በተጨማሪም የመጀመሪያ ጨዋታችን በቀን 17/07/2015 ዓ.ም ከወረታ ከተማ ባንኮች ጋር ያደረግን ሲሆን 2ለ0 ያሸነፍን ሲሆን እንዲሁም 2ተኛ ጨዋታችን በቀን 24/07/2015 ዓ.ም ከፎገራ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት ጋር በማድረግ 3ለ1 ያሽነፍን ሲሆን በድምሩ 6 ነጥብና ንፁህ 4 ጎል በመያዝ ቡድኑን በአንደኝነት እየመራን እንገኛለን። የወረታ እግር ኳስ ኮሚቴ መጋቢት 24/2015 ዓ.ም

በአገልግሎት አሰጣጣችን እረክተው ስላቀረቡልን ምስጋና እኛም ከልብ እናመሰግናለን ጎንደር ብቅል ፋብሪካ ኃ/የተ/የግል ማህበር።
16/01/2023

በአገልግሎት አሰጣጣችን እረክተው ስላቀረቡልን ምስጋና እኛም ከልብ እናመሰግናለን ጎንደር ብቅል ፋብሪካ ኃ/የተ/የግል ማህበር።

30/12/2022

*** የጉምሩክ መጋዘን ሥነ-ሥርዓት አፈጻጸም በተመለከተ የተዘጋጀ አጭር ጹሑፍ**
“የጉምሩክ መጋዘን” ማለት ጊዜያዊ የጉምሩክ ዕቃ ማከማቻን፣ ቦንድድ የጉምሩክ መጋዘንን እና የመንግሥት የጉምሩክ መጋዘንን ያካትታል፡፡
“ጊዚያዊ የጉምሩክ ዕቃ ማከማቻ” ማለት፣ ገቢ ዕቃዎች የጉምሩክ ሥነ ስርዓት አፈጻጸም ተከናውኖባቸው እስከሚለቀቁ ወይም እንደሁኔታው ወደ ቦንድድ የጉምሩክ መጋዘን ወይም ወደ መንግሥት የጉምሩክ መጋዝን እስኪዛወሩ፣ እና ወጪ እና ተላላፊ እቃዎች አግባብነት ያለው የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አፈጻጸም እስከሚከናወንባቸው ወይም እንደሁኔታው ወደ ቦንድድ የጉምሩክ መጋዘን ወይም ወደ መንግሥት የጉምሩክ መጋዘን እስከሚዛወሩ፣
በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ሆነው የሚቆዩበት ዝግ ወይም ክፍት የእቃ ማከማቻ ሥፍራ ሲሆን፣ ደረቅ ወደብን ይጨምራል፤
“ቦንድድ የጉምሩክ መጋዘን” ማለት ዕቃዎች ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልባቸውና የጉምሩክ ቁጥጥር እየተደረገባቸው የሚከማቹበት መጋዘን ሲሆን የቀረጥ ነፃ ዕቃ መሸጫ መደብሮችን እና ቦንድድ ፋብሪካዎችን ይጨምራል፤
“የመንግሥት የጉምሩክ መጋዘን” ማለት የጉምሩክ ሕግን በመተላለፍ የተያዙ ወይም የተወረሱ እንዲሁም የተተው እቃዎች በሽያጭ ወይም በሌላ ሁኔታ እስከሚወገዱበት ጊዜ ድረስ በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ሆነው የሚከማቹበት መጋዘን ነው፤
ምንጭ።-(ከጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀጽ 2)
ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን"!!
በደንበኞች ትምህርት ቡድን
ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ/ም
ወረታ

***ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የጉምሩክ ስነ-ስርዓት የሚፈፀምባቸው ዕቃዎች****ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች ወደ አገር ውስጥ ሲገቡ ወይም ከአገር ሲወጡ ዲክላሪስዮን አቅራቢው በሚያቀርበው ማመል...
30/11/2022

***ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የጉምሩክ ስነ-ስርዓት የሚፈፀምባቸው ዕቃዎች****
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች ወደ አገር ውስጥ ሲገቡ ወይም ከአገር ሲወጡ ዲክላሪስዮን አቅራቢው በሚያቀርበው ማመልከቻ መሰረት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የጉምሩክ ስነ-ስርዓት እንዲፈጸምባቸው ይደረጋል፡፡
 መድሐኒቶች፣
 በቀላሉ የሚቀጣጠሉ እቃዎች፣
 ጨረር አመንጪ መሣሪያዎች፣
 ዘር እና ችግኞች፣
 በሕይወት ያሉ እንስሳት፣
 ለምርመራና ለላብራቶሪ የሚውሉ ነፍሳት ወይም ዕጮች፣
 ለወጪ እቃዎች የምርት ግብዓት የሚሆኑ ጥሬ እቃዎች፣
 በመትነን አካባቢን የሚበክሉ ኬሚካሎች፣
 ወቅታዊ የሆኑ መጽሔቶችና ጋዜጦች፣
 ምግቦች፣ አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎችና መጠጦች፣
 ወጪ እቃዎች፣
 የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እቃዎች፣
ሌሎቹን ከመመሪያ ቁጥር 159/2011 አንቀጽ 17 ላይ ይመልከቱ፡፡
ምንጭ፡- የዕቃ ፍተሸ እና ቅድሚያ የጉምሩክ ስነ-ስርዓት የሚፈጸምበትን ዕቃ ለመወሰን ከወጣ መመሪያ ቁጥር 159/2011
ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን"!!
በደንበኞች ትምህርት ቡድን
ህዳር 21 ቀን 2015 ዓ/ም
ወረታ

18/11/2022

ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎች ዝርዝር ላይ ማሻሻያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ
ዕቃዎች ዝርዝር ላይ ማሻሻያ መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ከዚህ ቀደም ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፎ በነበረው የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ እቃዎች ዝርዝር ላይ ማሻሻያ ማድረግ በማስፈለጉ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዕቃዎች ላይ ማሻሻያ መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክና ለጉምሩክ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ማሻሻያ የተደረገባቸው ከውጭ የሚገቡ እቃዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

1. በታሪፍ ቁጥር 9401.9000 እና 9403. 9000 የሚመደቡ እቃዎች ክፍሎች ማምረቻ ግብአቶች፣

2. ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን በውጭ ምንዛሬ የመሸጥ ፍቃድ ያላቸው ሬስቶራንቶችና ሱፐር ማርኬቶች የራሳቸውን የውጭ ምንዛሬ ተጠቅመው የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፣

3. ባለ ኮከብ ሆቴሎች የራሳቸውን የውጭ ምንዛሬ ተጠቅመው የሚያስመጧቸው ዕቃዎችና

4. የቀረጥ ነጻ ሱቆች የሚያስመጧቸው ዕቃዎች የውጭ ምንዛሬ ክልከላው የማይመለከታቸው መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው ከውጭ የሚገቡ የ38 እቃዎች ዝርዝር በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

“በወረታ ደረቅ ወደብ ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ በኩል እቃ ወደ አገር ውስጥ የምታስገቡ አስመጭዎችና ትራንዚተሮች በሙሉ”የወረታ ደረቅ ወደብን መዳረሻ አድርጋችሁ በወረታ ደረቅ ወደብ ጉምሩክ መቅረ...
08/11/2022

“በወረታ ደረቅ ወደብ ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ በኩል እቃ ወደ አገር ውስጥ የምታስገቡ አስመጭዎችና ትራንዚተሮች በሙሉ”
የወረታ ደረቅ ወደብን መዳረሻ አድርጋችሁ በወረታ ደረቅ ወደብ ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ በኩል እቃዎችን ወደ አገር ውስጥ ስታስገቡ የነበረ እና አዲስ ወደ ወረታ ደረቅ ወደብን መዳረሻ ለማድረግ የምትፈልጉ ደንበኞቻችን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንት በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት በሚገቡ እቃዎች ላይ ተቀዛቅዞ የነበረው የትራንዚት መስመር ወደ ነበረ ስራው የተመለሰ መሆኑን እያሳወቅን ወደቡን መርጣችሁ ለምትመጡ ደንበኖቻችን ከምንጊዜውም በላይ ፈጣን አገልግሎት የምንሰጣችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ቡድን
ጥቅምት 29/2015 ዓ/ም
ወረታ

Address

Wereta

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Woreta Dry Port Customs Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Woreta Dry Port Customs Center:

Share