28/08/2026
በወልድያ ከተማ ምክር ቤት የ04 የጁ ገነት ቀበሌ ምክር ቤት ወርሃዊ ጉባኤዉን አካሄደ፡፡
ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም (ወልድያ )
ምክር ቤቱ በዋናነት የተወያየባቸዉ አጀንዳዎች
• የቀበሌ አስተዳዳሪ ሹመት ማጽደቅ
• የቀበሌ ምክር ቤቱን 2019 ዓ.ም አቅድ ማጽደቅ
• የቀበሌ ምክር ቤቱን የቋሚ ኮሚቴ እቅድ ማፅደቅ
• የሴቶች ፎረም እቅድ ማጽደቅ
በሚል አጀንዳዎች ላይ ምክር ቤቱ ዉይይት ያደረገ ሲሆን በቀበሌ አመራር ባለዉ ክፍተት የቀበሌዉ ማህበረሰብ አገልግሎት ለማግኘት እንቅፋት መሆኑን አንስተዉ የቀበሌ አስተዳዳሪዎችን በቶሎ የመተካት ስራ እንደሚገባና ለህብረተሰቡ ፈጣን አገልግሎት መስጠት ይገባል ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል የቀበሌ ምክር ቤቱን የ2019 ዓ.ም አመታዊ እቅድ ፤የቋሚ ኮሚቴ እቅድ፤የሴቶች ፎረም እቅድ ቀርቦ የምክር ቤት አባሉ ሰፊ ዉይይት በማድረግ ና የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ጉባኤዉ ተጠናቋል፡፡