Gazo Woreda Government Communication Office

Gazo Woreda Government Communication Office ጋዞ ወረዳ በሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ነው።

06/09/2026
 #ጳግሜ 1 የእምርታ -ቀን!!!በሰሜን ወሎ ዞን ጋዞ ወረዳ ጳጉሜ 1"የእምርታ ቀንን አስመልክቶ በወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስተባባሪነት በ01ገጠር ማይምኔ ቀበሌ የሚገኘውን የቢያርጎይ የመስኖ ...
06/09/2026

#ጳግሜ 1 የእምርታ -ቀን!!!
በሰሜን ወሎ ዞን ጋዞ ወረዳ ጳጉሜ 1"የእምርታ ቀንን አስመልክቶ በወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስተባባሪነት በ01ገጠር ማይምኔ ቀበሌ የሚገኘውን የቢያርጎይ የመስኖ ግድብ የውሃ አያያዝ የመስክ ምልከታ በማድረግ ተከብሮ ውሏል።

በመስክ ምልከታው ላይተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሃብቴ ካሳው እንደገለፁት ይህ ግድብ ለአካባቢው ህብረተሰብ አዲስ ተስፋንና መነሳሳትን የፈጠረ ሲሆን አርሶ አደሮችን በመስኖ የተለያዩ ሰብሎችን በማልማት ምርትና ምርታማነታቸውን በማሳደግ በምግብ ራሳቸውን እንዲችሉና አካባቢውም ከፍተኛ የሆነ የውሃ እጥረት ያለበት ስለሆነ ለእንሰሳቶችም ለመጠጥ ውሃ አገልግሎት የሚውል በመሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ እንክብካቤና ጥበቃም ሊያደርግለት ይገባል ብለዋል።

በጋዞ ወረዳ የ2018 የጳግሜ ቀናት አከባበር አስመልክቶ ከወረዳው ጠቅላላ አመራር ጋር ውይይት ተካሂዷል።‎‎እስታይሽ፦ ነሀሴ 30/2018 ዓ/ም (ጋዞ ወረዳ ኮሙኒኬሽን)‎በሰሜን ወሎ ዞን በጋ...
05/09/2026

በጋዞ ወረዳ የ2018 የጳግሜ ቀናት አከባበር አስመልክቶ ከወረዳው ጠቅላላ አመራር ጋር ውይይት ተካሂዷል።

‎እስታይሽ፦ ነሀሴ 30/2018 ዓ/ም (ጋዞ ወረዳ ኮሙኒኬሽን)

በሰሜን ወሎ ዞን በጋዞ ወረዳ የ2018 የጳግሜ ቀናት አከባበር አስመልክቶ ከወረዳው ጠቅላላ አመራር ጋር ውይይት አካሂዷል።

የጳግሜ ቀናት በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ልዩ ቦታ ያላቸው ከዓመት መጠናቀቅና አዲስ አመት መጀመር መካከልየሚገኙ የሽግግር ሲሆኑ በእነዚህ ቀናት ሰዎች ያለፈውን አመት በመመልከት የተሰሩ ስራዎችን የተገኙ ውጤቶችን ያጋጠሙ ችግሮችንና የተገኙ ትምህርቶችን የሚገመግሙበትና እንደ ሀገርም ባለፉው አመት የነበሩ ስኬቶችን በመገመም እና ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ለተሻለ ስኬት መነሳሳትን ለመፍጠር የጳጉሜ ቀናትን በተለያዩ ስያሜ እና ሁነቶች ይከበራሉ።

‎የበዓሉን አከባበር አስመልክቶየወረዳው ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አበበ ፀጋየ እ ንደገለፁት ቀናቶቹን ስናከብር በአንድ ሀገራዊ መሪ ሀሳብ "የኢትዮጵያ ማንሠራራት"በሚል መሪ ቃል አንድነትን፣አብሮነትን፣ መረዳዳትንና በጎነትን ማዕከል ያደረጉ ሁነቶች መሰረት በማድረግ የወል ትርክትን የማጠናከርና ብዝኃነትን የማጎልበት ሥራዎች እንደሚሰሩ ገልፀው በአምስቱም የጳግሜ ‎ቀናት የሚከበሩት ሁነቶች በእለቱ ባለቤት ሆነው የሚያስተባብሩ ተቋማትና በተለያዩ ስያሜዎች እንደሚከበሩ ገልፀዋል ።

04/09/2026

የሰሜን ወሎ ዞን የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናትን በልዩ ልዩ ሁነቶች ለማክበር መዘጋጀቱን አስታወቀ

​ወልዲያ፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ኮሙዩኒኬሽን)

​የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት “የኢትዮጵያ መንሠራራት” በሚል አጠቃላይ መሪ ሐሳብ በዞን እና በወረዳ ደረጃ በልዩ ልዩ ሁነቶች ለማክበር ዝግጅት ማጠናቀቁን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አራጌ ይመር ገለጹ።

​አቶ አራጌ የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት አከባበርን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ ዘንድሮ ቀናቱ “የኢትዮጵያ መንሠራራት” በሚል አጠቃላይ መሪ መልዕክት በልዩ ልዩ አገር አቀፍ፣ ክልላዊና ዞናዊ ሁነቶች እንደሚከበሩ አስታውቀዋል፡፡

​ዋና አስተዳዳሪው በመግለጫቸው፣ የጳጉሜን ወር ያለፈውን ዓመት ስኬትና ጉድለት መገምገሚያ፣ የመጪውን አዲስ ዓመት ዕቅድ ለመተግበር የዝግጅት ምዕራፍ ማጠቃለያ እንዲሁም የትግበራ ምዕራፍ ዋዜማ ሆኖ የሚያገለግል ልዩ ወቅት መሆኑን ጠቁመዋል።

​የአከባበሩ ዐቢይ ዓላማም ኢትዮጵያ ከአግድሞሽና ከዝቅታ ጉዞ ተላቃ በሁሉም ዘርፎች ወደ ላቀ ከፍታ ማንሠራራት መጀመሯን በማብሰር፣ ለበለጠ ሀገራዊ ውጤት በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ መነሳሳትንና የተስፋ መንፈስ መፍጠር እንደሆነ አብራርተዋል።

​እንደ አቶ አራጌ ማብራሪያ፣ አምስቱ የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ሁነቶችና ተያያዥ ጭብጦች ይከበራሉ፦

​ጳጉሜን 1 (የእመርታ ቀን)፦ ሀገራችን ከተረጂነትና ጥገኝነት ተላቃ ወደ አምራችነት እያደረገች ያለችውን ታሪካዊ ሽግግር ለማብሰር፣ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ስኬቶች፣ የምግብ ሉዓላዊነት ድሎች እና የ«ኢትዮጵያ ታምርት» ንቅናቄ ውጤቶች በሰፊው ይታወቃሉ።

​ጳጉሜን 2 (የመንሠራራት ቀን)፦ በለውጡ ዓመታት የተከናወኑ ሜጋ ፕሮጀክቶች፣ ሀገራዊ የልማት ኢኒሼቲቮች፣ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደቶችና ማኅበራዊ ዕድገቶች በዜጎች የዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ ያመጧቸው አዎንታዊ ተፅዕኖዎች ይበልጥ ይጎላሉ።

​ጳጉሜን 3 (የጽናት ቀን)፦ የፀጥታ ተቋማትን ዘመናዊ ቁመናና ለሀገረ-መንግሥቱ ዘላቂነትና ሉዓላዊነት የተከፈለውን የጀግኖች መስዋዕትነት በመዘከር፣ የሀገር መከላከል ዓቅማችንና ሀገራዊ ፅናት ለሁለንተናዊ ዕድገት መሠረት መሆናቸው ይበሰራል።

​ጳጉሜን 4 (የኅብር ቀን)፦ ኅብረብሔራዊ አንድነትን፣ አብሮነትን፣ መረዳዳትንና በጎነትን ማዕከል ያደረጉ ሁነቶች በመከወን የወል ትርክትን የማጠናከርና ብዝኃነትን የማጎልበት ሥራዎች ይከናወናሉ።

​ጳጉሜን 5 (የነገ ቀን)፦ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ የሳይበር ሉዓላዊነት፣ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና የ«5 ሚሊዮን ኢትዮ-ኮደርስ» ስኬቶችን በማሳየት ዲጂታልና በራስ አቅም የምትቆም አዲሷን ኢትዮጵያ የሚያመላክቱ ሁነቶች ይካሄዳሉ።

​በመጨረሻም ዋና አስተዳዳሪው “መንሠራራት” የሚለው መሪ ሐሳብ ሀገራችን ችግሮችን ከመቋቋም ወደ ፈጣንና ዘላቂ የከፍታ ምዕራፍ የምትሸጋገርበትን ስትራቴጂካዊ ሂደት የሚያመለክት በመሆኑ፣ የዞኑ ማኅበረሰብና የመንግሥት አካላት ቀናቱን በላቀ ተነሣሽነትና በተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።

​የሰሜን ወሎ ዞን መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ

የሰሜን ወሎ ዞን የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በጋዞ ወረዳ በመገኘት የክረምት በጎ-ፍቃድ አገልግሎት  ስራዎችን ገመገመ። እስታይሽ  ፦ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም(ጋዞ ...
03/09/2026

የሰሜን ወሎ ዞን የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በጋዞ ወረዳ በመገኘት የክረምት በጎ-ፍቃድ አገልግሎት ስራዎችን ገመገመ።

እስታይሽ ፦ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም(ጋዞ ወረዳ ኮሙኒኬሽን )

በሰሜን ወሎ ዞን የዜጎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በጋዞ ወረዳ በመገኘት የዜጎች የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎችን አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።

የወረዳው ሴቶች ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አባይ በወረዳው የዜጎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተከናወኑ ተግባራትን ከእቅድ አፈፃፀም አኳያ በጥንካሬና በድክመት ለይተው በሪፖርት አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

የወረዳው የዜጎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት እንደገለፁት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በራስ ተነሳሽነት የሚሰራ ተግባር በመሆኑ እንደወረዳ በቅንጂት ማህበረሰቡን በማስተባበር በከተማ ፅዳት፣ለአቅመ ደካሞች ምግብ ነክ የሆኑና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ፣የአቅመ ደካማ ቤቶችን በመጠገንና አዲስ በመገንባት፣የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠትና የትምህርት ቁሳቁስ በማሰባሰብ በመንግስት ይወጣ የነበረን ገንዘ ብ ማዳን እንደቻሉና በቀጣይ ቀሪ ቀናት ያልተከናወኑ ተግባራትን አጠናክሮ በማስቀጠል ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን እደሚወጡ ተናግረዋል።

የወረዳው ብልፅግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አበበ ፀጋየ በወረዳው በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተከናወኑ ተግባራት መጠነ ሰፌ መሆኑን ገልፀው ፤ በቀጣይ ቀሪ ቀናት እስከ ፕሮግራም ማጠቃላይ ድረስ የተጀመሩ ተግባራትን በአቅመ ደካማ ቤቶች ግንባታ በጤና በትምህርት አጠናክሮ በመስራት ማህበራዊ ሃላፊነታችን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ዘመድ ፀጋየ እንዳሉት በዘንድሮው የክረምት ወራትበበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተከናወኑ ተግባራት ሰው ተኮር የሆኑ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰው በቀሪ ቀናት ያላከናወናቸውን እና እንደወረዳ ዝቅ ያልንባቸውን ተግባራትን በመለየት የተሻለ ስራ በመስራት ህዝብን ተጠቃሚ ማረጋገጥ ይገብል ብለዋል።

የገምጋሚ ልዑኩ አባላትን በበኩላቸው እንደገለፁት በወረዳው በክረምት ወራት በሁሉም ዘርፍ የተከናወኑት ተግባራቶች አበረታች መሆናቸውን ገልጸው በተለይም ቴክኒክ ኮሚቴው ስብጥሩ ከሁሉም ተቋሞች የተዋቀረ በመሆኑ የተሻለ ስራ ለመስራት እንዳገዛቸው ተናግረዋል ።

ሉዑክ ቡድኑ አክለው እንዳሉት በቀጣይ ቀሪ ቀናት እስከ ፕሮግራሙ ማጠቃለያ ድረስ በጤና፣በትምህርትና በቤት እድሳት ላይ አጠናክራቹህ በመሰራት እንደ ዞን ዝቅ ያለበትን ተግባር ከፍ ማድረግ ይኖርባቹህ ብለዋል።

"የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ በክልሉ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ የድርሻውን እየተወጣ ነው" -አቶ አባይ መንግሥቴ​የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላ...
02/09/2026

"የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ በክልሉ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ የድርሻውን እየተወጣ ነው" -አቶ አባይ መንግሥቴ

​የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም፣ የተመዘገቡ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የሚገመግም መድረክ እያካሄደ ነው።

​በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግርና የሥራ መመሪያ ያስተላለፉት የቢሮው ሃላፊ አቶ አባይ መንግሥቴ፤ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን መረጃ ለሕዝብ ከማድረስ ባሻገር በክልሉ ሰላም፣ መረጋጋትና ልማት እንዲሰፍን ታሪካዊ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አክለውም በክልሉ ለተገኘው የሰላም አየርና ለሕዝቡ አብሮነት መጎልበት ዘርፉ ከፍተኛ ድርሻ ማበርከቱን አብራርተዋል።

​በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተግባራት የዘርፉን ኃያልነት በተግባር ያረጋገጡ እንደነበሩ የጠቆሙት ሃላፊው፤ እነዚህ ሥራዎች የሕዝቡን የልማት እንቅስቃሴ የሚያፋጥኑ፣ እውነትን የሚያጎሉና የክልሉን መልካም ገጽታ በመገንባት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል።

​በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ የተካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የተወጣው ሚና በታሪክ የሚዘከር መሆኑን ጠቅሰዋል።

​ዘርፉ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ የልማት ፍላጎት በማንጸባረቅ ረገድ የተጫወተው ሚና ለልማት ሥራዎች መፋጠን ትልቅ አቅም መሆኑንም አቶ አባይ አብራርተዋል።

​በመድረኩ ያለፉትን ስኬቶችና ያጋጠሙ ማነቆዎችን በመፈተሽ፤ በቀጣይ የበጀት ዓመት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ለክልሉ ዘላቂ ሰላም፣ ወንድማማችነትና ሁለንተናዊ እድገት በላቀ ኃላፊነት እንዲሠራ መንገድ የሚጠርግ መሆኑ ተመላክቷል።

Address

Woldia

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gazo Woreda Government Communication Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gazo Woreda Government Communication Office:

Shortcuts

Share