North wollo Zone Public Grievance

North wollo Zone Public Grievance በመንግስት ተቋማት ዘንድ በቀልጣፋነትና በዉጤታማነት ማስፈፀም የሚያስችል የቅሬታ ማስተናገጃና አስተዳደራዊ ፍትህ ተቋም ተፈጥሮ ማየት

21/08/2025
በሰሜን ወሎ ዞን በሁሉም ወረዳ በሚመስል መልኩ የሚመጣ እርዳ ለታለመለት አላማ አለማዋልና ኢ ፍታህዊ በሆነ አሰራር በመሰራቱ ቅሬታ በየደረጃ ይነሳል በመሆኑም ያለም አቀፍ ህብረተሰብ በጦርነት...
10/06/2023

በሰሜን ወሎ ዞን በሁሉም ወረዳ በሚመስል መልኩ የሚመጣ እርዳ ለታለመለት አላማ አለማዋልና ኢ ፍታህዊ በሆነ አሰራር በመሰራቱ ቅሬታ በየደረጃ ይነሳል በመሆኑም ያለም አቀፍ ህብረተሰብ በጦርነት ለተጎዱ እርዳታ ብሎ የላከውን በአግባቡ ማኔጅ በማድረግ ለታለመለት አላማ እንዲውልና ፍትሃዊ ክፍፍል ብታደርጉ መልካም ነው።

31/03/2023

የዝቅተኛ ወርሃዊ ደመወዝ እርከንን ለመወሰን የተዘጋጀው ደንብ እስካሁን አለመጽደቁ በፓርላማ ጥያቄ አስነሳ

ኢትዮጵያ ዝቅተኛ ወርሃዊ የደመወዝ ወለልን ለመደንገግ የተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ ጸድቆ ወደ ስራ አለመግባቱ በተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጥያቄ አስነሳ። የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ አባላት፤ በውጭ ሀገር ለሚሰማሩ ኢትዮጵያውያን የሚከፈለው “አነስተኛ” ወርሃዊ ደመወዝ እንዲስተካከል ለማድረግ የታሰበ ነገር ስለመኖሩም ጠይቀዋል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሁለቱን ጥያቄዎች ያነሳው፤ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የ8 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ ነው። ለቋሚ ኮሚቴው ሪፖርቱን ትላንት ረቡዕ መጋቢት 20፤ 2015 ያቀረቡት የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል፤ መስሪያ ቤታቸው ከውጭ ሀገር ስራ ስምሪት፣ ከቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና እንዲሁም ከስራ ፈጠራ ጋር በተያያዘ ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

ከሚኒስትሯ ማብራሪያ በኋላ የቋሚ ኮሚቴው ያዘጋጃቸው ጥያቄዎች በጽሁፍ ቀርበዋል። ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል “ዝቅተኛ የደመወዝ መነሻ እርከን ለመደንገግ የሚያስችል ረቂቅ ደንብ መዘጋጀቱ የተገለጸ ቢሆንም በትኩረት ተይዞ ጸድቆ ስራ ላይ እንዲውል የማይደረገው ለምንድን ነው?” የሚለው ይገኝበታል። አቶ ፍሬው ተስፋዬ የተባሉ የቋሚ ኮሚቴው አባል፤ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ጉዳይ የቆየ አጀንዳ መሆኑን አንስተው “እስከ መቼ ነው ይሄ ጉዳይ እየተንከባለለ የሚሄደው?” የሚል ጥያቄ አንስተዋል።

በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደመወዝ እርከንን ለመደንገግ ደንብ መዘጋጀቱ የተገለጸው፤ ከሁለት ዓመት ከመንፈቅ በፊት በመስከረም 2013 ዓ.ም ነበር። ይህንን ደንብ በተመለከተ ትላንት በፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት፤ በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት አቶ አሰግድ ጌታቸው ናቸው።

ሚኒስትር ዴኤታው፤ ደንቡ ሳይጸድቅ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ስያሜውን ቀይሮ እንደገና መደራጀቱን ገልጸዋል። የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ባለፈው ዓመት መስከረም ወር ከተዋቀረ በኋላ፤ በረቂቅ ደረጃ ያለው ደንብ አሁን እርሳቸው ወዳሉበት መስሪያ ቤቱ ተመልሶ ማሻሻያዎች እንደተደረጉበት አመልከተዋል። ሚኒስትር ዲኤታው አክለውም፤ “ሰነዱን revise አድርገን ወደ በላይ አመራር ለመላክ በዝግጅት ላይ ነው ያለነው” ሲሉ ረቂቅ ደንቡ ያለበትን ደረጃ ገልጸዋል።

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/10312/

የህብረተሰቡን የአገሌግሎት አሰጣጥ በማሳለጥ ቅሬታን በየደረጃው በፍታት የህዝብን የአገልግሎት አሰጣጥ እርካታ ማሳደግ ይጠበቅብናል የጉባላፍቶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለ ባዬ
09/03/2023

የህብረተሰቡን የአገሌግሎት አሰጣጥ በማሳለጥ ቅሬታን በየደረጃው በፍታት የህዝብን የአገልግሎት አሰጣጥ እርካታ ማሳደግ ይጠበቅብናል የጉባላፍቶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለ ባዬ

ትልቁ ከምንሊክ ቀጥሎ መጠሪያችን የኢትዮጵያ ሃብት abay /Nile big river
09/03/2023

ትልቁ ከምንሊክ ቀጥሎ መጠሪያችን የኢትዮጵያ ሃብት abay /Nile big river

09/03/2023

በየ ደረጃው ያለ አመራር የህዝብ ውክልና እንዳለው አስቦ የህብረተሰቡን ጥያቄ በየደረጃው ሲቀርብለት የመመለስና ርካታውን እመዘነ የመሥራት ሃላፊነቱን ወስዶ ሊሰራ ይገባል።

05/01/2023

እያንዳንዱ የመንግስት ተቋማተሰ ለተገልጋይ የህብረተሰብ በአግባቡ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅበታል ።

29/11/2022

ፀረ ሙስና ትግሉ ተጠናክሮ ቀጥሏል
ፈጣን አገልግሎት አለመስጠት የሙስና መንስኤ ነው።

30/08/2022

ወልድያ ዛሬ 23/12/2014
ከቀኑ 7:50 ሠላም ናት የሚወራው እውሸት ነው ። በከበባ ውስጥ ስለሆነች የመንግስትንና የወገንን እገዛ ትፈልጋለቾ

26/08/2022

ወረዳዎቻችን የመንግስት ተቋማት በሚሰጡት አገልግሎት የሚነሱን ቅሬታዎች ከእንግልትና ከአልተገባ ወጪ ለማዳን ቅሬታው በያለበት እንዲፈታ የማህበረሰብ አቀፍ አሀዝ ካርድ የሚባለውን የቅሬታ መፍቻ ስርዓት ዘርግተው በመሥራት ላይ ይገኛሉ ሊበረታቱ ይገባል

Address

Amhara
Woldia

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when North wollo Zone Public Grievance posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share