North Wollo Zone Trade and Market Development የሰሜን ወሎ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Woldia
  • North Wollo Zone Trade and Market Development የሰሜን ወሎ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ

North Wollo Zone Trade and Market Development የሰሜን ወሎ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ Government Organization

በዛሬው እለት ማለትም ነሃሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም በአብክመ ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ (በአቶ ፈንታው ፈጠነ) የተመራ የሰሜን ወሎ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ እና...
14/08/2026

በዛሬው እለት ማለትም ነሃሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም በአብክመ ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ (በአቶ ፈንታው ፈጠነ) የተመራ የሰሜን ወሎ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ እና የወልደያ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አላማ ፈፃሚ ባለሙያዎችን ያካተተ በወልዲያ ከተማ ከንቲባ ህንፃ አዳራሽ የጋራ ውይይት ተካሄደ።
የውይይቱ አጀንዳዎች
1. የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በሁለቱም መምሪያዎች ቀርቦ በታዳሚዎች ውይይት ተደርጎበታል።
2. የቀጣይ የ2019 በጀት አመት አቅጣጫ በአምስቱ ስትራቴጅክ ግቦች ላይ መሰረት በማድረግ በአቶ ፈንታው ፈጠነ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። እነዚህም ግቦች
 የኑሮ ዉድነትን በማረጋጋት በጀት በመመደብ አቅርቦትን ማሳደግ
 ህገ-ወጥ የንግድ አሰራርን በመከላከል የግብይት ስርአቱን ከደላላ የጸዳ ማድረግ
 ዘመናዊ የገበያ ማእከላትን በመገንባት የተለያዩ የሰብልና የኢንደስትሪ ሞርቶችን በማቅረብ የገበያ ተደራሽነትን ማሳደግ
 የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ከሽንገላ እና ከሙስና የጸዳ እንዲሆን ማድረግ
 የተቀላጠፈ የቴከኖሎጂ አገልግሎት መስጠት መሰረታዊ ሃሳቦች ላይ በመመርኮዝ ከቤቱ በርካታ ሃሳቦች፣ አስተያየቶችና በስራ ላይ ያጋጠሙ ችግሮች ተነስተው በሰፊው ውይይት በማድርግ እና የመፍትሄ አቅጣጫ በማስቀመጥ የ2019 ዋነኛ የመነሻና የመስፈንጠሪያ ነጥብ መሆኑን በመረዳት ከወልዲያ ከተማ አስተዱደር ጋር በመቀናጀት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም አላማ ፈጸሚ ባለሙያ እርብርብ ለማድረግ ቃል በመግባት ዉይይቱ ተጠናቋል።

ሰሜን ወሎ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መኖሪያ የ 2018 ዓ.ም በጀት አመት  ከጠቅላላ ሰራተኞቹ ጋር የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም ገመገመ ::
22/04/2026

ሰሜን ወሎ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መኖሪያ የ 2018 ዓ.ም በጀት አመት ከጠቅላላ ሰራተኞቹ ጋር የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም ገመገመ ::

https://www.facebook.com/share/1CcYHhxU8m/
23/03/2026

https://www.facebook.com/share/1CcYHhxU8m/

የኢትዮ ኮደርስ (5 Million Ethiopian Coders) ስልጠና ለምን ለBPR አስፈላጊ ሆነ?

የዲጂታል ብቃት መለኪያ፦ አዲሱ የመንግስት አሰራር ወደ ዲጂታላይዜሽን እያመራ በመሆኑ፣ ማንኛውም ባለሙያ መሰረታዊ የኮምፒውተር እና የቴክኖሎጂ እውቀት እንዳለው ማረጋገጫ ይፈለጋል።

ተጨማሪ ነጥብ፦ በስራ ምደባ ወቅት ከስራው ባህሪ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ስልጠናዎች መኖራቸው በምዘናው ወቅት የተሻለ ነጥብ ለማግኘት ይረዳል።

የአመለካከት ለውጥ፦ ስልጠናውን መውሰድዎ ራስዎን ለማሻሻል እና አዳዲስ አሰራሮችን ለመቀበል ዝግጁ መሆንዎን ያሳያል።

አሁንም አልረፈደም! 🏃‍♂️🏃‍♀️ ስልጠናው በኦንላይን የሚሰጥ በመሆኑ ባሉበት ሆነው መከታተል እና ሰርተፊኬቱን ማግኘት ይችላሉ። በተለይ በዳታ ሳይንስ (Data Science)፣ በዌብ ሳይት ዝግጅት ( AI Development) እና በአንድሮይድ መተግበሪያዎች (Android Development and programming Development ) ዙሪያ የሚሰጡት ትምህርቶች ለስራዎ ትልቅ አቅም ይሆኑዎታል።

🔗 ለመመዝገብ፦ [የድረ-ገጹን ሊንክ Ethiocoders.et ብላችሁ መጀመር ትችላላችሁ።

ጥያቄ ካላችሁ፦ ስልጠናውን እና ሰርተፊኬት በተመለከተ በውሰጥ መጠየቅ ትችላላችሁ።
አጠቃላይ ስለኢትዮኮደርስ ስልጠና አስተያየታችሁን በኮመንት አጋሩን። 👇

10/03/2026
10/03/2026
03/02/2026
03/01/2026

Address

North Wollo
Woldia

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when North Wollo Zone Trade and Market Development የሰሜን ወሎ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share