North Wollo Prosperity Party Office / NWPP/

North Wollo Prosperity Party Office / NWPP/ Prosperity party is ruling party committed to realize Ethiopia's PROSPERITY.

"የስፖርት ዘርፉን በባህላዊ አሠራር ብቻ መምራት አይቻልም" አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)የስፖርት ዘርፉን ከዚህ በፊት በነበረው ባህላዊ አስተሳሰብና አሠራር ብቻ መምራት የሚቻልበት ወቅት አለመሆኑን ...
03/09/2026

"የስፖርት ዘርፉን በባህላዊ አሠራር ብቻ መምራት አይቻልም" አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)

የስፖርት ዘርፉን ከዚህ በፊት በነበረው ባህላዊ አስተሳሰብና አሠራር ብቻ መምራት የሚቻልበት ወቅት አለመሆኑን የአማራ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶ/ር አብዱ ሁሴን ገለጹ።

ዶ/ር አብዱ ሁሴን ይህን የገለጹት 27ኛው የአማራ ክልል ስፖርት ምክር ቤት ጉባኤ በባህር ዳር ከተማ ሲካሄድ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

ስፖርት ከጤናና ከዜጎች መሠረታዊ መብት ባሻገር ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች መፍትሔ የሚያበረክት ዘርፍ መሆኑን ጠቁመው፣ በተለይም ወጣቶችን ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ በየደረጃው ዘመናዊ አሠራር መዘርጋት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የክልሉን ስፖርተኞችና አሠልጣኞች ከስፖርቱ የሚገኘውን ዘመናዊ ጥቅም እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገር፣ የክልሉን ተወዳዳሪነት በማሳደግ ለኢትዮጵያ የሚኖረውን አስተዋጽኦ ማሳደግ ከስፖርት አመራሩ የሚጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት መሆኑንም ገልጸዋል።

በተጨማሪም መንግሥት ለስፖርቱ ዘርፍ ልዩ ትኩረት እየሰጠ መሆኑን ጠቁመው፣ የስፖርት ልማትና አስተዳደር አዋጅ መጽደቅ፣ የስፖርት ፖሊሲ በአዲስ መልክ መዘጋጀትና የስፖርት መሠረተ ልማቶች መገንባት ለዘርፉ እድገት የሚያበረክቱ ተግባራት መሆናቸውን አንስተዋል።

በጉባኤው የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም፣ የ2019 ዓ.ም ዕቅድና የማስፈጸሚያ በጀት እንዲሁም የ2018 ዓ.ም የኦዲት ሪፖርት በጥልቀት እንደሚገመገም ተገልጿል።

"የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት አስተማማኝ እና ዘላቂነት ያለው የሕዝብ መረጃ የሚመነጭበት ነው" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት የ...
03/09/2026

"የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት አስተማማኝ እና ዘላቂነት ያለው የሕዝብ መረጃ የሚመነጭበት ነው" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

የአማራ ክልል ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት የቴክኖሎጂ ቀጥታ ምዝገባ ሲስተም ማስተዋወቅ እና የ2018 በጀት ዓመት የዞኖች እና የከተማ አሥተዳደሮች የዕውቅና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል

የአማራ ክልል ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ኀላፊ መዓዛ በዛብህ የምዝገባ አገልሎቱን ከወረቀት ወደ ቀጥታ ምዝገባ ማሸጋገራቸውን ገልጸዋል። ከወረቀት ወደ ቴክኖሎጂ የተደረገው ሽግግር ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት፣ የሃብት ብክነትን ለመከላከል፣ ሀሰተኛ ሰነድን ለመከላከል፣ ጊዜ እና ጉልበትን ለመቆጠብ ያስችላል ነው ያሉት።

ሁሉንም የምዝገባ ጣቢያዎች ወደ ቴክኖሎጂ ለማሻገር የሌሎች እገዛ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። ከወረቀት ወደ ቴክኖሎጂ የተደረገው ጉዞ ስኬታማ እንደኾነ አንስተዋል።

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እውን እንዲኾን በትብብር መሥራት እንደሚገባም ገልጸዋል። እየተደረገ ያለው ምዝገባ ለሕግ፣ ለስታትስቲክስ እና ሌሎች ሥራዎች እንደመረጃ ኾኖ ያገለግላል ብለዋል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ለመንግሥት አሥተዳደር ውጤታማነት አስተማማኝ እና ዘላቂነት ያለው የሕዝብ መረጃ የሚመነጭበት ነው ብለዋል። የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ መረጃ የመንግሥት እና የሕዝብ አሥተዳደር ግንኙነትን የሚያሳልጥ፣ በመረጃ ላይ የተመሠረተ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ዕቅዶች እንዲታቀዱ፣እንዲጎለብቱ እና ውጤታማ እንዲኾኑ የሚያደርግ ሥርዓት ነው ብለዋል።

ተደራሽ እና ጥራት ያለው መረጃ ማመንጨት ደግሞ በብዙ እንደሚጠቅም ገልጸዋል። ለዘመናዊ እና ጥራት ላለው መረጃ ትኩረት እንደተሰጠውም አንስተዋል።

የመረጃ ተደራሽነት እና ጥራት ችግርን ለመቅረፍ ቴክኖሎጂ ወሳኝ መኾኑንም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ከተጀመረ የቆዬ ታሪክ ቢኖረውም በተደራሽነቱ እና በጥራቱ ፈተና ውስጥ ቆይቶ የኖረ ነው ብለዋል። ለዓመታት በፈተና ውስጥ የቆዬውን ሥራ የሚያሻሽለው በቴክኖሎጂ መደገፍ መኾኑን ገልጸዋል።

ሥራውን በቴክኖሎጂ የደገፉ ሀገራት የመንግሥት አሥተዳደርን ቀልጣፋ እና ውጤታማ ማድረግ መቻላቸውን አንስተዋል። ሥራውን በቴክኖሎጂ መደገፍ ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የመረጃ ጥራትን ለማረጋገጥ ያስችላል ነው ያሉት።

በወረቀት የሚደረግ ምዝገባ ( የሰው ንክኪ) ተደራሽነትን ከማዛባቱም በላይ የመረጃ ጥራት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አለው ብለዋል። ሥራውን በቴክኖሎጂ መደገፍ ግልጽ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ መረጃን ለመያዝ እንደሚያስችል ነው የተናገሩት።

የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት በርካታ ባለድርሻ አካላት ተዋናይ የሚኾኑበት መኾኑን ገልጸዋል። የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት በሚሰጠው ውጤት የማይጠቀም ተቋም እና የኅብረተሰብ ክፍል እንደሌለ ተናግረዋል። ይህ ዘርፍ የማኅበረሰብ ምህንድስና ተደርጎ ይወሰዳል ነው ያሉት።

መረጃን ተደራሽ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ከወረቀት ወደ ቴክኖሎጂ በመሸጋገሩ ደስተኛ መኾናቸውን ተናግረዋል። ቴክኖሎጂ ወጭን ይቆጥባል ብሎም የመረጃ ደኅንነትን ይጠብቃል ነው ያሉት።

ተቋሙ እዚህ እንዲደርስ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምሥጋና አቅርበዋል።
~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

የሰሜን ወሎ ዞን የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በጋዞ ወረዳ በመገኘት የክረምት በጎ-ፍቃድ አገልግሎት  ስራዎችን ገመገመ። እስታይሽ ፦ነሐሴ 28/2018 ዓ.ምበሰሜን ወ...
03/09/2026

የሰሜን ወሎ ዞን የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በጋዞ ወረዳ በመገኘት የክረምት በጎ-ፍቃድ አገልግሎት ስራዎችን ገመገመ።

እስታይሽ ፦ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም

በሰሜን ወሎ ዞን የዜጎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በጋዞ ወረዳ በመገኘት የዜጎች የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎችን አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።

የወረዳው ሴቶች ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አባይ በወረዳው የዜጎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተከናወኑ ተግባራትን ከእቅድ አፈፃፀም አኳያ በጥንካሬና በድክመት ለይተው በሪፖርት አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

የወረዳው የዜጎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት እንደገለፁት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በራስ ተነሳሽነት የሚሰራ ተግባር በመሆኑ እንደወረዳ በቅንጂት ማህበረሰቡን በማስተባበር በከተማ ፅዳት ፣ለአቅመ ደካሞች ምግብ ነክ የሆኑና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ፣የአቅመ ደካማ ቤቶችን በመጠገንና አዲስ በመገንባት፣የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠትና የትምህርት ቁሳቁስ በማሰባሰብ በመንግስት ይወጣ የነበረን ገንዘ ብ ማዳን እንደቻሉና በቀጣይ ቀሪ ቀናት ያልተከናወኑ ተግባራትን አጠናክሮ በማስቀጠል ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን እደሚወጡ ተናግረዋል።

የወረዳው ብልፅግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አበበ ፀጋየ በወረዳው በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተከናወኑ ተግባራት መጠነ ሰፌ መሆኑን ገልፀው ፤ በቀጣይ ቀሪ ቀናት እስከ ፕሮግራም ማጠቃላይ ድረስ የተጀመሩ ተግባራትን በአቅመ ደካማ ቤቶች ግንባታ በጤና በትምህርት አጠናክሮ በመስራት ማህበራዊ ሃላፊነታችን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ዘመድ ፀጋየ እንዳሉት በዘንድሮው የክረምት ወራትበበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተከናወኑ ተግባራት ሰው ተኮር የሆኑ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰው በቀሪ ቀናት ያላከናወናቸውን እና እንደወረዳ ዝቅ ያልንባቸውን ተግባራትን በመለየት የተሻለ ስራ በመስራት ህዝብን ተጠቃሚ ማረጋገጥ ይገብል ብለዋል።

የገምጋሚ ልዑኩ አባላትን በበኩላቸው እንደገለፁት በወረዳው በክረምት ወራት በሁሉም ዘርፍ የተከናወኑት ተግባራቶች አበረታች መሆናቸውን ገልጸው በተለይም ቴክኒክ ኮሚቴው ስብጥሩ ከሁሉም ተቋሞች የተዋቀረ በመሆኑ የተሻለ ስራ ለመስራት እንዳገዛቸው ተናግረዋል ።

ሉዑክ ቡድኑ አክለው እንዳሉት በቀጣይ ቀሪ ቀናት እስከ ፕሮግራሙ ማጠቃለያ ድረስ በጤና ፣በትምህርትና በቤት እድሳት ላይ አጠናክራቹህ በመሰራት እንደ ዞን ዝቅ ያለበትን ተግባር ከፍ ማድረግ ይኖርባቹህ ብለዋል።

ሰላም እና ኅብረት ሥራ፦ ሁለቱ የልማት ገጾች !የአማራ ክልል ኅብረት ሥራ ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክን አካሂዷል...
03/09/2026

ሰላም እና ኅብረት ሥራ፦ ሁለቱ የልማት ገጾች !

የአማራ ክልል ኅብረት ሥራ ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክን አካሂዷል።

በዕለቱ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) በክልሉ የ25 ዓመት የአሻጋሪ እድገት እና ዘላቂ የልማት ዕቅድ እንዲሁም የአምስት ዓመት የስትራቴጂክ ዕቅድ ትልቅ ትኩረት የተሰጣቸው የኅብረት ሥራ ማኅበራት እና ዩኒዬኖች ለሀገር ኢኮኖሚ ድርሻቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ዘርፉ የኢንዱስትሪ አብዮትን በማሳደግ በሁሉ አቀፍ እምርታ ውስጥ የሚገባ እና ጠንካራ ኢኮኖሚ የሚፈጥር እንደኾነ ነው የገለጹት። ችግሮችን በራስ አቅም ለመፍታት የሚያስችል ጠንካራ መሠረት እንደኾነም አንስተዋል። በተለይም ዘመናዊ ግብርናን ለመገንባት ከፍተኛ አቅም የሚኾኑ ናቸው ብለዋል።

ይሁንና ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ሰላም ያስፈልጋል ያሉት ዶክተር ዘሪሁን የክልሉ ቁልፍ አቅጣጫ ሰላምን ማጽናት በመኾኑ ለሰላም መረጋገጥ በጋራ መሥራት ይገባል ብለዋል። የክልሉ መንግሥት ለዩኒዬኖች እና ለኅብረት ሥራ ማኅበራት ውጤታማነት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።

የአማራ ክልል ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌትነት አማረ ኮሚሽኑ በ2018 በጀት ዓመት በሪፎርም እና በሌሎችም ዘርፎች ውጤታማ ሥራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል። ገበያውን በማረጋጋት የግብይት ሥርዓቱን የተሻለ ማድረግ እና በዘርፉ ሕገ ወጥነትን ለመከላከልም ጥብቅ ቁጥጥር ተደርጓል ነው ያሉት።

የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በተከናወነው ተግባር በባሕር ዳር ከተማ ብቻ ከ9ዐዐ በላይ ማኅበራት ተደራጅተው ዜጎች የመኖሪያ ቤት ቦታ እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል።

የኅብረት ሥራ ማኅበራት የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እና ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል። በቀጣይም ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታት የኅብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በዘላቂነት ማረጋገጥ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ኅብረት ሥራ ማኅበራት ማስፋፊያ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አብርሐም ወርቁ በከተማው የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ማኅበራትን የማደራጀት እና ተጠቃሚ የማድረግ ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል። አሠራሩን ከሙስና የጸዳ ለማድረግ ቴክኖሎጂ በመጠቀም በተለይም የመንግሥት ሠራተኞችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ መስጠት ተችሏል ነው ያሉት።

የአድማስ ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒዬን ዋና ሥራ አሥኪያጅ መሠረት ወርቄ ዩኒዬኑ ግብዓት በወቅቱ ወደ አርሶ አደሮች መንደር እንዲገባ ከማድረግ ባለፈ ዘመናዊ ግብርና እንዲገነባ ትራክተር ገዝቶ በማቅረብ ተጠቃሚ እያደረገ መኾኑን ገልጸዋል።

በመርሐ ግብሩ የላቀ አፈጻጸም ለነበራቸው ዩኒዬኖች፣ ኅብረት ሥራ ማኅበራት እና ፈጻሚ አካላት እውቅና እና ሽልማት ተበርክቷል።

#አሚኮ #ኅብራት ሥራ #ኢትዮጵያ 🇪🇹

የኢትዮጵያ ማንሰራራት!​የ 2018 ዓ.ም ጳጉሜን ቀናት፤​-ጳጉሜን 1 (የእመርታ ቀን)-ጳጉሜን 2 (የማንሰራራት ቀን)-ጳጉሜን 3 (የጽናት ቀን)-ጳጉሜን 4 (የኅብር ቀን)-ጳጉሜን 5 (የነገ...
03/09/2026

የኢትዮጵያ ማንሰራራት!
​የ 2018 ዓ.ም ጳጉሜን ቀናት፤
​-ጳጉሜን 1 (የእመርታ ቀን)
-ጳጉሜን 2 (የማንሰራራት ቀን)
-ጳጉሜን 3 (የጽናት ቀን)
-ጳጉሜን 4 (የኅብር ቀን)
-ጳጉሜን 5 (የነገ ቀን)

የዓባይ ዳር ቃል ኪዳን ለጠንካራ ኢንስፔክሽን መሰረት ነው!!የ2019 በጀት ዓመትን ውጤታማና ጠንካራ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ስራዎችን ለማከናወን የአማራ ክልል የኢንስፔክሽንና ስ...
03/09/2026

የዓባይ ዳር ቃል ኪዳን ለጠንካራ ኢንስፔክሽን መሰረት ነው!!

የ2019 በጀት ዓመትን ውጤታማና ጠንካራ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ስራዎችን ለማከናወን የአማራ ክልል የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ጽሕፈት ቤት ከዞን እና ከከተማ አስተዳደር የኢንስፔክሽን እና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች አመራሮች ጋር የዓባይ ዳር ቃል ኪዳን ለጠንካራ ኢንስፔክሽን በሚል መሪ ቃል የውል ስምምነት የፊርማ ስነ ስርዓት አካሂዷል ፡፡

#ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ!
#የዓባይ ዳር ቃል ኪዳን ለጠንካራ ኢንስፔክሽን መሰረት ነው!!

"በእጃችሁ የያዛችሁት ስማርት ስልክ የቴክኖሎጂ ትምህርት ቤት ነው" በለጠ ሞላ (ዶ.ር)የአማራ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ቢሮ "ኤሌክትሮኒክስ መንግሥት ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 መሠረት"...
03/09/2026

"በእጃችሁ የያዛችሁት ስማርት ስልክ የቴክኖሎጂ ትምህርት ቤት ነው" በለጠ ሞላ (ዶ.ር)

የአማራ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ቢሮ "ኤሌክትሮኒክስ መንግሥት ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 መሠረት" በሚል መሪ መልዕክት የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት የፓናል ውይይት አካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ ዲጂታል 2025 ስትራቴጅን ተግባራዊ በማድረግ የሕዝብ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ ለማዘመን ያደረገችው ርብርብ ተጨባጭ ፍሬን አፍርቷል ብለዋል።

የመንግሥት ተቋማት ከወረቀት አሠራር ወጥተው ወደ ዘመናዊ የዲጂታል አሠራር እየተሸጋገሩ መሆኑንም ተናግረዋል። ከ49 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት በመኾን፤ ዜጎች በቴሌ ብር እና በባንኮች በዲጂታል መድረኮች በመገበያየት እና በመሶብ አገልግሎት ፈጣን ተጠቃሚ ሆነዋል ነው ያሉት።

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን እውን ለማድረግ ወደ ሥራ ተገብቷልም ብለዋል። ተደራሽነትን ማስፋት፤ ለሁሉም ዜጎች እኩል ዕድል መፍጠር፤ በዜጎች እና በተቋማት መካከል እምነትን ማጠናከር የዲጂታል 2030 የትኩረት አካል መሆናቸውን ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ያዘጋጀው አውደ ርዕይ የተቋማትን የዲጂታል ግንዛቤ ለማሳደግ፤ የፈጠራ ሥራዎችን ለሕዝብ ለማስተዋወቅ እና የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማፋጠን የሚያግዝ ነው ብለዋል።

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የመንግሥት አጀንዳ ብቻ አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ ሕዝብ እና መንግሥት የሚገናኙበት እውነተኛ መንገድ መሆኑን ተናግረዋል።

የዲጂታል መሠረተ ልማትን ማግኘት ቅንጦት አይደለምም ብለዋል። ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለሁሉም ተጠቃሚዎች በእኩልነት የሚያገለግል አድሎ አልባ ድልድይ መሆኑንም አንስተዋል።

ወጣቶች በእጃችሁ የያዛችሁት ስማርት ስልክ መዝናኛ ብቻ ሳይሆን የቴክኖሎጂ ትምህርት ቤት በመኾኑ በአግባቡ ልትጠቀሙበት ይገባል ነው ያሉት። የሚመጣው የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘመን የሚፈልገው ወጣቶችን በመኾኑ ራሳችሁን ከአዲሱ ቴክኖሎጂ ጋር ልታላምዱ ይገባል ብለዋል።

ቴክኖሎጂ መንግሥት ሠራተኛኞችን ለፈጠራ እና ለውሳኔ ሰጭነት የሚያበቃ በመሆኑ ቴክኖሎጂን መታጠቅ እና መላመድ ይገባል ብለዋል።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ከዳር ለማድረስ በተቋማት መካከል ያሉ የዲጂታል መረጃ ቋቶች እርስ በዕርስ የሚናበቡበት እና በሕግ መሠረት መረጃ የሚለዋወጡበት ሀገራዊ ማዕቀፍ ተግባራዊ ይደረጋልም ብለዋል።

እጅ ለእጅ ተያይዘን ትኩረታችንን በፈጠራ እና በግንባታ ላይ በማድረግ ልጆቻችን የሚኮሩባት ሀገር እንገነባለን ብለዋል።
~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

በመቄት ወረዳ በፀጥታና በህግ ማስከበር ዙሪያ ከጠቅላላ የፀጥታ መዋቅሩ ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።ፍላቂት፦ነሐሴ 28/2018 ዓ,ም(መቄት ኮሙኒኬሽን)በመቄት ወረዳ ሶስቱ የፀጥታ ተቋማት ከ...
03/09/2026

በመቄት ወረዳ በፀጥታና በህግ ማስከበር ዙሪያ ከጠቅላላ የፀጥታ መዋቅሩ ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።

ፍላቂት፦ነሐሴ 28/2018 ዓ,ም(መቄት ኮሙኒኬሽን)
በመቄት ወረዳ ሶስቱ የፀጥታ ተቋማት ከጠቅላላ የፀጥታ መዋቅሩ ጋር በወረዳው የፀጥታ ሁኔታ በወቅታዊ ጉዳዮችና ህግን በማስከበር ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሂደዋል።

በውይይቱ የወረዳው አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታ፣ በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የፀጥታ ስጋቶች፣ ወቅታዊ ጉዳዮችና ህግን በማስከበር ረገድ የሚያጋጥሙ ችግሮች በስፋት ተነስተው ተወያይተዋል።

በመድረኩ የሶስቱ የፀጥታ ተቋማት አመራሮች እና የፀጥታ መዋቅሩ አባላት ተገኝተው በወረዳው የሚስተዋለውን የፀጥታ ሁኔታ በጋራ ገምግመዋል።

በእለቱ መድረኩን የመሩት የወረዳው የሶስቱ የፀጥታ ተቋማት አመራሮች እንደገለፁት በወረዳው ሰላምን ለማስፈን የተቋማት ትብብርና የጋራ ስራ ወሳኝ መሆኑን አሰገንዝበዋል።

የፀጥታ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት በመረጃ በመመራት መከላከል፣ የህግ ጥሰቶችን በህግ አግባብ መመርመርና ተጠያቂዎችን ለህግ ማቅረብ ትኩረት ከሚሰጣቸው የስራ አቅጣጫዎች መካከል መሆኑን አመራሮቹ አስታውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የፀጥታ ስራው ውጤታማ እንዲሆን ከህዝቡ ጋር ያለውን ቅርበት ማጠናከርና ችግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በመድረኩ የተገኙት በሀገር መከላከያ ሰራዊት የ104ኛ ኮር የ16ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ቀለሙ አስረስ እንደገለፁት የአካባቢውን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ የሚቻለው ህብረተሰቡ ከመከላከያ ሠራዊትና ከመንግሥት መዋቅሮች ጋር በትብብር መስራት ሲችል ነው። በአካባቢው የሚታዩ የፀጥታ ችግሮችን በጋራ በመከላከል ለሰላም መጠናከር ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።

ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ የህግ ማስከበር ስራው በተቀናጀና በተጠናከረ መልኩ መመራት እንዳለበትም ተናግረዋል።

በመጨረሻም በወረዳው የፀጥታ ሁኔታን በቅርበት መከታተል የፀጥታ መዋቅሩን ቅንጅት ማጠናከር፣ ከህዝቡ ጋር ያለውን የመረጃ ልውውጥ ማሳደግና ህግን በሚጥሱ ላይ በህግ አግባብ መስራት እንደሚገባ በመድረኩ አቅጣጫ ተቀምጧል።

"በክልሉ ቴክኖሎጂን የመጠቀም ልምድ እያደገ ነው" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ቢሮ የበለጸጉ እና በሥራ ላይ የሚገኙ ችግር ፈች የሆኑ ሲስተሞችን በአው...
03/09/2026

"በክልሉ ቴክኖሎጂን የመጠቀም ልምድ እያደገ ነው" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

የአማራ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ቢሮ የበለጸጉ እና በሥራ ላይ የሚገኙ ችግር ፈች የሆኑ ሲስተሞችን በአውደ ርዕይ ለጎብኝዎች ክፍት አድርጓል።

በአውደ ርዕዩ "ኤሌክትሮኒክስ መንግሥት ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 መሠረት" በሚል መሪ መልዕክት የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበትም የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ የተገኙት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ መንግሥት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ቴክኖሎጂን እንደ አካታች ሀገራዊ ብልጽግና፤ ዘላቂ ልማት እና ለብቁ ሀገራዊ ተወዳዳሪነት ቁልፍ መሠረት አድርጎ እየሠራበት ነው ብለዋል።

በኢኮኖሚ ዕድገት፤ ምርታማነትን በማሳደግ፤ በመንግሥት አገልግሎት ቅልጥፍናን በማሻሻል፤ የዜጎች ተሳትፎን በማሳደግ፤ የዲጂታል ክህሎትን በማጠናከር ግብ አድርጎ በትኩረት እየሠራ እንደኾነ ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ልማት ለውጭ ኢንቨስትመንት እና ለቱሪዝም ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም አንስተዋል።

በአማራ ክልል "ዲጂታል አማራ" በሚል በ25 ዓመቱ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ላይ ቴክኖሎጅ እንደ ልማት መዳረሻ መፍጠሪያ ተደርጎ ተይዟል ነው ያሉት።

በ25 ዓመቱ ስትራቴጅክ ግብ ላይ በ2042 የአማራ ክልል ዋነኛ ሀብት፤ የአገልግሎት መስጫ እና የኢኮኖሚ የዕድገት ምንጭ ቴክኖሎጂ እንዲሆን ይሠራል ነው ያሉት።

በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት ቴክኖሎጂን የመጠቀም፤ የማላመድ እና የመሥራት ልምምዳቸውን እንዲያጠናክሩም እየተሠራ ነው ብለዋል።

በክልሉ ቴክኖሎጂን የመጠቀም ልምድ ዕድገት እያሳየ መጥቷልም ነው ያሉት። የክልሉ መንግሥት ቴክኖሎጂን በስፋት ለመጠቀም በትኩረት እየሠራ ነውም ብለዋል።

ቴክኖሎጂን በመጠቀም ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ እና ዜጎች በአገልግሎት ደስተኛ እንዲኾኑ እየተሠራ እንደኾነም ጠቁመዋል።

የአማራ ክልል የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ቢሮ ምክትል ኀላፊ የቻለ ይግዛው የመርሐ ግብሩ ዓላማ በአማራ ክልል የለሙ የዲጂታል መፍትሔዎችን በጋራ ለመመረቅ እና ወደ ሥራ ለማስገባት ነው ብለዋል።

በርካታ የለሙ ሲስተሞች ወደ ሥራ መግባታቸውንም ገልጸዋል። ሌሎች የለሙ ሲስተሞችም ወደ ሥራ እንደሚገቡ ተናግረዋል።

አውደ ርዕዩ የመንግሥት የአሠራር ሥርዓት ዲጂታላይዝድ እንዲሆን ለማፋጠን እና ዲጂታል 2030ን እውን ለማድረግ ያለመ ነውም ብለዋል።

በመርሐ ግብሩ ከ35 በላይ ዲጂታል መፍትሔዎች ለምተው ለተቋማት እና ለኅብረተሰቡ ክፍት መሆናቸውንም ገልጸዋል።

አውደ ርዕዩ አገልግሎት ሰጭው እና አገልግሎት ተጠቃሚው ስለ ዲጂታል መፍትሔዎች አውቆ እንዲጠቀም ለማድረግ እንደሚያስችልም ነው ያነሱት።

የለሙ ሲስተሞች ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውንም ገልጸዋል።
~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

"የኅብረት ሥራ ማኅበራት ለሀገርና ለሕዝብ ኢኮኖሚ ያላቸው አበርክቶ ወደር የለሽ ነው" ዶ.ር ዘሪሁን ፍቅሩ የአማራ ክልል ኅብረት ሥራ ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና ...
03/09/2026

"የኅብረት ሥራ ማኅበራት ለሀገርና ለሕዝብ ኢኮኖሚ ያላቸው አበርክቶ ወደር የለሽ ነው"
ዶ.ር ዘሪሁን ፍቅሩ

የአማራ ክልል ኅብረት ሥራ ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ በስኬት ተጠናቋል።

ኮሚሽኑ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ በ2018 በጀት ዓመት ቁልፍና ዐበይት ተግባራትን በላቀ አፈጻጸም ላከናወኑ የዞንና የከተማ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ጽ/ቤቶች፣ ዩኒየኖች እንዲሁም ፈጻሚ ባለሙያዎች የዕውቅና፣ የሽልማትና የምስጋና መርሃ-ግብር አካሂዷል።

የአማራ ክልል ኅብረት ስራ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ጌትነት አማረ እንደገለጹት፣ የኀብረት ስራ ማህበራት የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለመቀነስ፣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። የዘርፉን አፈጻጸም ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና በሂደቱ የሚታዩ ክፍተቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ በከተማ አስተዳደሮች እና ዞኖች መካከል በኬፒአይ (KPI) መሰረት በተደረገው አፈጻጸም ግምገማ ከፍተኛ ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን፣ የተገኙትም ውጤቶች ለሌሎች አካላት የልምድ ልውውጥና መማሪያ የሚሆኑበትን አሰራር መዘርጋት ያስችላሉ ብለዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው የማጠቃለያ መልእክት ያስተላለፉት በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤትየፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ዶ.ር ዘሪሁን ፍቅሩ የክልሉ መንግሥት ከድህነትና ከጦርነት አዙሪት በዘላቂነት ለመውጣት ያዘጋጀው የ25 ዓመት የአሻጋሪ ዕቅድ ከዳር እንዲደርስ የኀብረት ስራና የዩኒየኖች ቤተሰቦች ሁሉም በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የኅብረት ሥራ ማኅበራት ለሀገርና ለሕዝብ ኢኮኖሚ ያላቸው አበርክቶ ወደር የለሽ ነው ያሉት አማካሪው ማኅበራቱ በሥራቸው ያቀፏቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲለውጡና እንዲያበለጽጉ ብሎም ሌሎችን እንዲደግፉ የሚያስችሉ ሁነኛ የልማት መድረኮች መሆናቸውን አብራርተዋል።

በመቀጠልም ዶ.ር ዘሪሁን ፍቅሩ ሀገራዊ የኢኮኖሚና የኢንዱስትሪ አብዮትን ለማፋጠን ማኅበራቱ ያላቸውን ሚና አጉልተዋል። በዚህም ኢኮኖሚው የጠነከረ፣ የራሱን ችግር በራሱ አቅም የሚፈታና ባለው ዕምቅ ጸጋ በአጭር ጊዜ ሊበለጽግ የሚችል ክልል በመገንባት ሂደት ውስጥ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አበርክቷቸው የላቀ መሆኑን ተገንዝቦ መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ከዚህ አንጻር ኅብረት ሥራ ማኅበራትና ዩኒየኖች ከመደበኛ ስራቸው ባሻገር ወደ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪ ዘርፍ እንዲሸጋገሩ እንዲሁም አርሶ አደሩን በአንድ ማዕቀፍ ውስጥ በማሰባሰብ ወደ ዘመናዊ ግብርና እንዲያስገቡ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሠራ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።

በዕለቱ በተካሄደው የሽልማት መርሃ-ግብር በበጀት ዓመቱ አበረታች ውጤት በማስመዝገብ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ወጥተው ቀዳሚ አፈጻጸም ላሳዩ የዞንና የከተማ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ጽ/ቤቶች፣ ዩኒየኖች እንዲሁም ፈጻሚ ባለሙያዎች የዋንጫ፣ የገንዘብና የምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቷል።

~•~•~•~•
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊



"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/
ዩቲዩብ:- https://www.youtube.com/

Address

Woldia

Telephone

+251967237301

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when North Wollo Prosperity Party Office / NWPP/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share