Gubalafto Communication/ጉባላፍቶ ኮሙኒኬሽን

Gubalafto  Communication/ጉባላፍቶ ኮሙኒኬሽን This page is about gubalafto woreda Communication affairs office

በአንድ ዓመት ብቻ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ። 🇪🇹🇪🇹በኢትዮጵያ ባለፋት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ የላቀ ውጤት መመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር...
06/09/2026

በአንድ ዓመት ብቻ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ። 🇪🇹

🇪🇹በኢትዮጵያ ባለፋት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ የላቀ ውጤት መመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛው ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በሰጡት ማብራሪያ መግለጻቸው የሚታወስ ነው።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተውም :-

📌 ባለፉት አምሥት ዓመታት አጠቃላይ የግብርና ምርት ከ44 ሚሊዮን ቶን ወደ 150 ሚሊዮን ቶን አድጓል። በዚህም ከ3 እጥፍ በላይ የምርት ዕድገት አምጥቷል።

📌 የደን ሽፋን ከ17 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ አድጓል። ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኝ በመትከል 12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት እንዲያገግምም ተደርጓል።

📌 በ2018 በጀት ዓመት 29 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማልማት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኩንታል ምርትም ተሠብሥቧል።

👉 ቡናን ለውጭ ገበያ በማቅረብ በአንድ ዓመት ብቻ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት ተችሏል። ይህም የ17 ዓመታት የቡና ምርት ገቢን በአንድ ዓመት ማሳካት የተቻለበት ታሪካዊ ስኬት ኾኗል።

👉 ቀደም ሲል ስንዴን ከውጭ በማስገባት በርካታ ዶላር ታወጣ የነበረውን ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ወደ ውጭ እየላከች የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ጀምራለች።🌾

📌 በድርቅ የሚታወቁት አካባቢዎች ምርታማ እየኾኑ ነው። ታርሰው የማያውቁ ሥፍራዎች በግብርና ልማት ተሸንፈዋል። ታይቶ የማይታወቅ ምርትም እየሰጡ ነው።

📌 የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረው የሌማት ቱርፋት መርሐ ግብር አስገራሚ ውጤት ተገኝቶበታል።

👉 የዶሮ ስጋ ምርት ከ8 ሺህ ቶን ወደ 190 ሺህ ቶን ከፍ ብሏል። ይህም የ296 በመቶ ጭማሪ እንዳለ ያሳያል።

👉 የአቮካዶ፣ ሙዝ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ እና ሌሎችንም የፍራፍሬ አይነቶች በስፋት በማምረት ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ኾኗል። ለአብነትም በአቮካዶ ምርት በአፍሪካ ሁለተኛዋ ለውጭ ገበያ የምታቀርብ ሀገር መኾን ችላለች።

📊 ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበች ያለው ተጨባጭ ለውጥ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ግስጋሴዋን እንድታስቀጥል የሚያስችላት ስለመኾኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጻቸው አይዘነጋም።

#አሚኮ

06/09/2026
‎የእመርታ ቀን በመስክ ድጋፍና ጉብኝት ተከበረ‎‎ወልዲያ፡ ጳጉሜ 1 /2018 ዓ.ም. (ጉባላፍቶ ኮሙኒኬሽን)‎‎ጉባላፍቶ ወረዳ ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም.ን “የእምርታ ቀን” በሚል መሪ ቃል...
06/09/2026

‎የእመርታ ቀን በመስክ ድጋፍና ጉብኝት ተከበረ

‎ወልዲያ፡ ጳጉሜ 1 /2018 ዓ.ም. (ጉባላፍቶ ኮሙኒኬሽን)

‎ጉባላፍቶ ወረዳ ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም.ን “የእምርታ ቀን” በሚል መሪ ቃል አከበረ። በዕለቱም በወረዳው የተከናወኑ የግብርናና የእንስሳት ሀብት ልማት ሥራዎች በመስክ ተጎብኝተው ድጋፍና ክትትል ተደርጓል።

‎የሰሜን ወሎ ዞን የግብርና ልማት መምሪያ ኃላፊና ባለሙያዎች፣ የጉባላፍቶ ወረዳ የሴክተር ጽ/ቤት ሀላፊዎችና እንዲሁም የግብርና እና የእንስሳት ሀብት ባለሙያዎችን ያካተተ ልዑክ በመስክ ጉብኝቱ ተሳትፈዋል።

‎ልዑኩ በ2018 ዓ.ም. በወረዳው የተከናወኑ የዶሮ እርባታ፣ የዘይት ምርት፣ የማሽላ ክላስተር ሰብል፣ የላም እርባታ፣ የአትክልትና የፍራፍሬ ልማት ሥራዎችን ተመልክቷል። ከሥራዎቹ የተገኙ ውጤቶችም በአካል ተገኝቶ ተገምግመዋል።

‎የሰሜን ወሎ ዞን የግብርና ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተገኘ አባተ በጉብኝት ወቅት እንደገለጹት፣ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥና በምግብ ራስን መቻል ከድህነት ለመውጣት ወሳኝ መሠረት ነው ብለዋል። አርሶ አደሩ በግብርና ልማት በመሳተፍ ከድህነት ጋር ተፋልሞ ድል የሚያደርግ አምራች እየሆነ መምጣቱንም አቶ ተገኘ ገልጸዋል። በመስክ የታዩ ውጤታማ ሥራዎችን መደገፍ፣ መከታተልና ወደ ሌሎች አርሶ አደሮች ማስፋት እንደሚገባም አሳስበዋል።

‎በመስክ የተገኙ አርሶ አደሮች በበኩላቸው የመሬትና የአየር ሁኔታቸውን በመለየት የምርት አይነቶችን እየመረጡ እንደሚያመርቱ ገልጸዋል። ውሃ ገብ መሬቶችን ለአትክልትና ፍራፍሬ፣ ዝናብ አጠር መሬቶችን ደግሞ በአጭር ጊዜ ለሚደርሱ ሰብሎች በማዋል ከተረጂነት ወጥተው እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን እየመሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

‎የጉባላፍቶ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ በየነ በበኩላቸው፣ በመስክ የተመለከቷቸው የእንስሳት፣ የሰብል፣ የአትክልትና የፍራፍሬ ልማት ሥራዎች “የድካም ውጤት እምርታ” የሚያሳዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። አቶ ሀብታሙ እንዳሉት፣ ጉባላፍቶ ወረዳ ዝናብ አጠር ከሆኑ ወረዳዎች መካከል ይገኛል። በመሆኑም የአካባቢውን የአየር ጠባይ የሚመጥኑና በአጭር ጊዜ የሚደርሱ ሰብሎችን እንዲያመርት ለአርሶ አደሩ የግንዛቤና የሙያ ድጋፍ እየተሰጠ እንደተሰጠ ጠቁመዋል።

‎በተጨማሪም በወረዳው ቆላማ አካባቢዎች የግሪሳ ወፍ መንጋ እየታየ በመሆኑ በሰብል ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ተገልጿል። በመሆኑም አርሶ አደሩ በተደራጀ መንገድ ሰብሉን እንዲጠብቅ፣ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት አካላትም አርሶ አደሩን በመደገፍና በማንቃት የተገኙ የልማት ውጤቶች እንዲጠናከሩ አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል።

‎የ“እምርታ ቀን” መርሐ ግብር በጉባላፍቶ ወረዳ የተገኙ የግብርናና የእንስሳት ሀብት ልማት ውጤቶችን በመስክ በማረጋገጥ፣ የተሻሉ ተሞክሮዎችን በማስፋትና ቀጣይ ድጋፍና ክትትልን በማጠናከር ተጠናቋል።

‎🌱 እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!‎‎በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ጳጉሜ -1 የእመርታ ቀን የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመጎብኘት በድምቀት ተከብሯል። ‎‎ወልድያ፦ ጳጉሜ 1/2018 ዓ/ም (ጉባላ...
06/09/2026

‎🌱 እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!

‎በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ጳጉሜ -1 የእመርታ ቀን የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመጎብኘት በድምቀት ተከብሯል።

‎ወልድያ፦ ጳጉሜ 1/2018 ዓ/ም (ጉባላፍቶ ኮሙኒኬሽን)

የወረዳው ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ በየነ ‎አርቆ ማየት አልቆ መስራት በሚል መርህ አዝጋሚ ከሆነ የለውጥ ሂደት በመላለቅ እመርታዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ባለፉት የለውጥ አመታት የተከናወኑ ተግባራት ማሳያ መሆናቸውን በመግለጽ በወረዳችንም በበጀት ዓመቱ በፈተናዎች ውስጥ ሁነን በርካታ ለውጦችን ማምጣት ችለናል ብለዋል።

‎የጳጉሜ ቀናትን በተለያዩ ሁነቶች ስናከብርም የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እመርታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በመሆኑ አመራሩ ለላቀ ተልእኮ መዘጋጀት አለበት ብለዋል።

‎የእመርታ በጉባላፍቶ ወረዳ እና ሀራ ከተማ አስተዳደር በግብርና እና እንስሳት ሀብት ልማት ተሰሩ ስራዎችን በመጎብኘት የተከበረ ሲሆን የዞን እና የወረዳ አመራሮች ተሳታፊ ነበሩ።

የእመርታ_ ቀን - ጳጉሜን አንድ ነገን ተልሞ ለትውልድ መቅረጽ የመደመር መንግሥት መገለጫው ሆኗል።የመደመር መንግሥት ለትውልድ የሚሻገር አገራዊ ወረት እያኖረ፤ በተጨባጭ ውጤቶችም እየተገለጸ ...
06/09/2026

የእመርታ_ ቀን - ጳጉሜን አንድ

ነገን ተልሞ ለትውልድ መቅረጽ የመደመር መንግሥት መገለጫው ሆኗል።

የመደመር መንግሥት ለትውልድ የሚሻገር አገራዊ ወረት እያኖረ፤ በተጨባጭ ውጤቶችም እየተገለጸ ቀጥሏል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከባንዳ እስከ ባዳ በቅንጅት የተወረወሩበትን እያንዳንዷን ጠጠር በጥበብና በጽናት እየለቀመ የአገር ግንባታ ጡብ አድርጓቸዋል፤ ከጸኑ ፈተናዎች የሰሉ ዕድሎች ተፈልቅቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ “ኢትዮጵያዊ ጽናት እና አርቆ አስተዋይነት የታየበት” ሲሉ ያረጋገጡት እና መንግሥት ይፋ ያደረጋቸው የጉባ ብስራቶች የሀገራችን እምቅ አቅም በተግባር የሚገለጥባቸው ግዙፍ ማሳያዎች ናቸው። ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚፈጀው ይህ ማዕቀፍ የኢትዮጵያን የነገ ዕጣ ፈንታ በሰፊው የሚቀይር ታሪካዊ የጋራ ስኬት ነው።

ለመደመር መንግሥት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የብልጽግናው ዋና መለኪያ ነው። የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ መጀመሩ የአርሶ አደራችንን ምርታማነት በብዙ እጥፍ ያሳድጋል። እንደ ሀገርም በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላርን እናተርፍበታለን።

በአፍሪካ ግዙፉ የሆነው አዲሱ የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ግንባታም እውን እየሆነ ነው። ይህ ፕሮጀክት ኢትዮጵያን የአህጉሪቱ ዋንኛ የሎጂስቲክስ፣ የንግድ እና የዲፕሎማሲ መገናኛ በማድረግ የጂኦ-ኢኮኖሚ አቅማችንን ወደ ታላቅ ከፍታ ያሸጋግረዋል። ብዙዎች በሀገራቸው እውን እንዲሆን የሚመኙትን ይህን ታላቅ ፕሮጀክት ኢትዮጵያውያን በጽናት ጀምረነዋል፤ እንፈጽመዋለን።

የመደመር መንግሥት የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የነገው ትውልድ ዕድል የሚቀየር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን በአጽኖት ተልሟል። የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ያለ ኢነርጂ ሉዓላዊነት የሚታሰብ አይደለም። ለዚህም ነው መንግሥት የኢነርጂ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የኢኮኖሚ ነጻነታችን ማዕዘን ድንጋይ ነው በሚል ስትራቴጂያዊ ትኩረት የሰጠው።

ከታላቁ የህዳሴ ግድባችን ቀጥሎ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ምልክት የሆነው የመጀመሪያው የጋዝ ፋብሪካችን ተመርቋል፤ ሁለተኛውም እየተገነባ ነው። የነዚህና ሌሎች በሂደት ላይ ያሉ ግዙፍ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች መጠናቀቅ እና ሥራ መጀመር ከውጭ የሚገባውን የኢነርጂ ፍላጎት በማሟላት ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ ያስቀራል፤ ለኢንዱስትሪ ዘርፉ ማበብም ጽኑ መሠረት ይጥላል።

የልማት እውነተኛ ልክ የዜጎች ክብርና ማኅበራዊ ፍትህ መረጋገጥ ነው። መንግሥት ለዚህ አብላጫ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል። በመላው ሀገሪቱ የሚከናወነው የ1.5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጀምሯል። ፕሮጀክቱ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሚሊዮኖችን የቤት ባለቤት ያደርጋል። የከተሞችን ገጽታ በመቀየር ማኅበራዊ ፍትህን ያረጋግጣል።

መደመር ማለት አብሮ ማደግ እና ሀብትን መጋራት ማለት ነው። እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ለሚሊዮን ወጣቶች ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ የሥራ ዕድሎችን ይፈጥራሉ። በዚህ ረገድ ገና ከጅምሩ ውጤቶች መመዝገብ ጀምረዋል።

የመደመር መንግሥት ለትውልድ የሚያሻግረው ዕዳን ሳይሆን ምንዳን ነው። አዲሱን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፤ ነገን ዛሬ ተልሞ ለትውልድ መቅረጽ የመደመር መንግሥት ልዩ መገለጫ ሆኗል። ወገባችንን አስረን፣ መቀነታችንን አጥብቀን በላባችን ወዝ የምናኖራቸው ወረቶች ለነገው ትውልድ የሚቀሩ የብልጽግና ውርስ ይሆናሉ። በላባችን ጥረት ኢትዮጵያን በጸና መሠረት ላይ እናቆማለን።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የእመርታ ቀን
06/09/2026

የእመርታ ቀን

"ያቆምነው  አዲስ ሕንፃ ብቻ ሳይኾን በኋላ ቀር አገልግሎት አሰጣጥ መቃብር ላይ የሚቆም ፈጣን አገልግሎት ነው" ተቀዳሚ ምክትል ክንቲባ ቻላቸው ዳኘውርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የጎንደር መ...
05/09/2026

"ያቆምነው አዲስ ሕንፃ ብቻ ሳይኾን በኋላ ቀር አገልግሎት አሰጣጥ መቃብር ላይ የሚቆም ፈጣን አገልግሎት ነው" ተቀዳሚ ምክትል ክንቲባ ቻላቸው ዳኘው

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የጎንደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች ይሄን በማየታችን ደስተኞች ነን ነው ያሉት። ዛሬ የተመረቀው የጎንደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ብቻ ሳይኾን የጎንደር ነዋሪዎች ሥነ ልቦና ጭምር እንደኾነ ነው የተናገሩት። የጎንደር ዘመን ሲባል የኢትዮጵያ ዘመን ነው ያሉት ነዋሪዎቹ የጎንደር ዘመን የኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን ነው ብለዋል።

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ፤ መንግሥት እንደ ሀገር መሶብ በሚል ፍልስፍና አንድ ላይ መብላት ብቻ ሳይኾን አንድ ላይ ሕዝብን ማገልገል፣ አንድ ላይ መሥራት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ተገልጋይን ማርካት የኾነ እሴት ያለው ዘመናዊ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ፈጥሯል ብለዋል።

የጎንደር የአንድ መሶብ ማዕከል የተገነባበት ስፍራ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ሲሰጥበት የቆየ ቀደምት ስፍራ እንደኾነ አስታውሰዋል።

ይህንን ሕንፃ ለመገንባት የቀደመው ቦታ ሲፈርስ በአገልግሎት አሰጣጥ ሲበደል የኖረው ሕዝብ በቦታው ጭምር እንግልት፣ መጉላላት፣ ሙስና አብሮ የፈረሰ እስኪመስለው ድረስ ተደስቷል ነው ያሉት።

ያ የሕዝብ ደስታ እንዳይቀለበስ እንሠራለንም ብለዋል። በቀደመው አሮጌ ሕንጻ ቦታ ላይ ያቆምነው አዲስ ሕንፃ ብቻ ሳይኾን በኋላ ቀር አገልግሎት አሰጣጥ መቃብር ላይ የሚቆም ፈጣን አገልግሎት ነው ብለዋል።

የዛሬው ሕንጻ በራሱ ለእኛ ልዩ ትርጉም ይሰጠናል ነው ያሉት። ታሪካዊቷ ጎንደር ከነገሥታቱ በኋላ ዐይን የሚገባ ግንባታ የሠራባት መንግሥት የለም ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው የፋሲል ከተማ የሚለው በታሪክ ብቻ ሳይኾን በሥራም ይገለጻል ነው ያሉት።

ጎንደር የነበረ ቅርሷን አድሳ፣ ለትውልድ ደግሞ የዚህ ዘመን ቅርስ በማኖር ትናንትን ወደ ዛሬ እያሻገረች መኾኑን ገልጸዋል። በመነቃቃት፣ በሕዳሴ እና በብልጽግና ምዕራፍ የሚመረቀው ይህ ፕሮጀክት ለከተማዋ አሥተዳደርም ኾነ ለከተማዋ ሕዝብ ብዙ ትርጉም አለው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የክልል ከተሞች ቀዳሚው ማዘጋጃ ቤት የነበረውን የጎንደር ማዘጋጃ ቤት የረዥም ዘመን ታሪኩ የተበላሸ አገልግሎት መስጠት መኾኑን አንስተዋል። ያንን ታሪክ ለማድረግ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ለመተግበር አዲስ አሠራር ብቻ ሳይኾን አዲስ ግንባታ እና አዲስ መንፈስ የተቀናጀበት መኾኑንም ገልጸዋል።

ማዕከሉ የልሕቀት፣ የፍጥነት፣ ከብልሹ አሠራር ነጻ የመኾን ምሳሌ ኾኖ ለሌሎች ተቋማቶቻችንም አርዓያ እንዲሆን እንሠራለን ብለዋል።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የጎንደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ሥራ አስጀመሩ። በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ የክልል እና የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኀ...
05/09/2026

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የጎንደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ሥራ አስጀመሩ።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ የክልል እና የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የጎንደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ታሪክን ከዘመናዊነት ጋር አስተባብሮ የተገነባ ነው።

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ነዋሪዎች ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ዘመናዊ አሠራርም ነው።

የጎንደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የከተማዋን አገልግሎት ወደ ፈጣን እና ዘመናዊ አገልግሎት የሚቀይር ነው።

#አሚኮ

ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ድንበር የለሽ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራ ማከናወን እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፤​የሀረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ቡድን ከአማራ ክልል መንግ...
05/09/2026

ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ድንበር የለሽ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራ ማከናወን እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፤

​የሀረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ቡድን ከአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ጋር በባህርዳር ከተማ የልምድ ልውውጥ አደረጉ።

​በልምድ ልዉዉጥ መድረኩ የተገኙት የሀረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ እንደገለጹት፤ የአማራ ክልል የሀገራችን የቱሪዝም የስበት ማዕከልና ከራሱ አልፎ ለሀገር የሚተርፍ ትልቅ ሀብት ያለው ክልል ነው።

በባሕር ዳር ከተማ ተዘዋውረን የተመለከትናቸው የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ጸጋዎች ለሀገራችን የወደፊት የቱሪዝም እድገት ትልቅ ተስፋ የሚሰጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል። የባህርዳር በለዉጥ ላይ ነች የከተማዋ የለዉጥ ጉዞም የብልጽግና ጉዟችን ዋነኛ ማሳያ ምልክት ነዉ ብለዋል።

​ሃላፊዉ ክልሉ ከነበረበት የጸጥታ ችግር ወጥቶ አሁን ትኩረቱን ልማት ላይ ማድረጉን በቆይታቸው መታዘባቸውን ገልጸው፤ በቀጣይ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ በጋራ እንደሚሠሩ አጋርነታቸውን አረጋግጠዋል።

​የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ትብለጥ መንገሻ በበኩላቸው፤ ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ለመገንባት ሚዲያው ዋነኛ መሳሪያ ነዉ። ከሀረሪ ክልል ጋር የነበረውን የቆየ መልካም ግንኙነት እና የተግባራት አፈጻጸም ልምድ በመካፈልና በማዳበር፣ ለክልላችን እንዲሁም ለሀገር ገጽታ ግንባታ የሚጠቅሙ ሥራዎች እንደሚከናወኑ ተናግረዋል። የልምድ ልውውጡም ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና የነበሩ ክፍተቶችን ለማሻሻል የሚረዳ መሆኑን ጠቁመዋል።

​የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉነህ ዘበነ በበኩላቸው፤ የሀገራችንን የብልጽግና ጉዞ ከምናሳካባቸው ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ ዲጂታል ኮሙኒኬሽን መሆኑን ገልጸዋል።

ለዚህ የሚመጥን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት አሁናዊ ተግባር መሆኑን በመጥቀስ፤ የልምድ ልውውጡ በቀጣይ በጋራ ለሚከናወኑ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራዎች ጠንካራ መሠረት የጣለ ነውም ብለዋል።

አማራ ኮሙኒኬሽን

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ወልድያ ድስትሪክትና ቅርንጫፍ ሰራተኞቹ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።ነሀሴ 30/2018 ዓ.ም (ወልድያ ኮሙኒኬሽን)የኢትዮጲያ  ንግድ ባንክ ወልድያ ድስትሪክት ከመ...
05/09/2026

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ወልድያ ድስትሪክትና ቅርንጫፍ ሰራተኞቹ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።

ነሀሴ 30/2018 ዓ.ም (ወልድያ ኮሙኒኬሽን)

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ወልድያ ድስትሪክት ከመደበኛ የፋይናንስ አገልግሎት በተጨማሪ ለወልድያ ከተማ አስተዳደር፣ለሰሜን ወሎ ዞን እና ለጉባላፍቶ ወረዳ 102 ደርዘን ደብተር እና 6 ባኮ እስክርቢቶ በድምሩ 100 ሽህ ብር የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

የባንኩ ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ክንዱ ድጋፉ በወልድያ ዲስትሪክትና በከተማዋ ከሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፍ ሰራተኞች የተሰበሰበ መሆኑን በመግለፅ የድጋፉ ዓላማም በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይሆኑ ለማድረግ ነው ብለዋል።

ባንኩ በፋይናንስ አገልግሎት ዘርፉ በርካታ አገልግሎት እየሰጠ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ በቀጣይም በትምህርቱ ዘርፉ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

በርክክብ ስነ- ስርዓቱ የተገኙት የወልድያ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ አስራት በሪሁን የባንኩ ሰራተኞች ያደረጉት ድጋፍ የሚበረታታ መሆኑን በመግለፅ በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ከትምህርት ውጭ የሚሆኑ ተማሪዎችን ቁጥር ለመቀነስ አስተዋጽኦ እንዳለው አስረድተዋል።

መምሪያው በበጎ ፈቃድ ተግባራት አበክሮ እየሰራ ነው ያሉት ሀላፊው 5 ሽህ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ አቅዶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሰጠ ታደሰ በበኩላቸው የተደረገው ድጋፍ ባንኩና ሰራተኞቹን ሊያስመሰግን የሚችል ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።

አክለውም በቀጣይ ጳጉሜ 4 የትምህርት ቀን የሚከበርበት ዕለት መሆኑን በማስታወስ የተለያዩ ተቋማት እና ባለ ድርሻ አካላት በበጎ ተግባራት በመሳተፍ ለነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ድጋፍ እንድያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የጉባላፍቶ ወረዳ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተወካይ በመርሃ ግብሩ ተገኝተው ድጋፋን ተረክበዋል።ባንኩ ላደረገው ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Address

Woldia

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251333311822

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gubalafto Communication/ጉባላፍቶ ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gubalafto Communication/ጉባላፍቶ ኮሙኒኬሽን:

Shortcuts

Share