13/06/2026
የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ክልላዊ የኮሪደር ልማት የልምድ ልውውጥ እና የግምገማ መድረክ በወልድያ ከተማ አካሄደ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ አስተባባሪነት ክልላዊ የኮሪደር ልማት የልምድ ልዉዉጥ እና የግምገማ መድረክ በወልድያ ከተማ ተካሂዷል።
በምክትል ር/መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማና መሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ አህመዲን ሙሐመድ(ዶ/ር) ወልድያ ከተማ ለአዲሱ ትዉልድ ልማትን እና ዘመናዊነትን በተግባር እያስተማረች ያለች ከተማ ናት ብለዋል።
ዶ/ር አህመዲን አያይዘዉም ወልድያ ልማትን ማፋጠን እና የአገልግሎት አሰጣጥን ከማሳለጥ ባሻገር ዘመናዊነትን ለአዲሱ ትወልድ በተግባር እያስተማረች ያለች ከተማ ነች ብለዋል።
በወልድያ ከተማ የተሰሩ የልማት ስራዎችን የጎበኙት የአርባ ከተማዎች ከንቲባዎች እና የከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ ኀላፊዎች ከጉብኝታቸው በኋላ የልምድ ልውውጥና የግምገማ መድረኩ ላይ ታድመዋል።
በመርሐ ግብሩ ልምዷንና ተሞክሮዋን በአካላዊ የመስክ ጉብኝት ማሳየት የጀመረችው የተሞክሮ ማዕከሏ ወልድያ ከተማ የሁለንተናዊ የልማት ስራዎች ተሞክሮ መረጃ በከተማዋ ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ አማካኝነት ለተሳታፊ አመራሮች ቀርቧል።
የወልድያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዱባለ አብረሬ እንደገለፁት ባለፋት ጊዚያት በጦርነትና በግጭት የደቀቀችው ከተማችንን ወደ ጥንት ስሟ ገነቴ ለመቀየር አስበን የቁጭት እቅድ አቅደን ከተማችንን የስልጣኔና የተሞክሮ ማእከል ለማድረግ በአረንጓዴ ቤት ውስጥ ለመኖር እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
የጉብኝቱ ተሳተፊ አመራሮች በበርካታ ፈተናዎች ያለፈችው ወልድያ ከተማ የተሰሩ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች አድንቀው የተሻሉ ልምዶችንም እንዳገኙ ገልፀዋል።
ከተሳታፊ ከተሞች መካከል የጎንደር ከተማ ፣ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ፣ የባህር ዳር ከተማ ፣ የደሴ ከተማ እና የደቡብ ወሎ ዞን የልማት ተሞክሮዎች ቀርበው ሌሎች ከተሞች ልምድ አንዲወስዱባቸው ተደርጓል።
በመድረኩ ላይ በአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍሰሃ ደሳለኝ፣ የአማራ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሞላ መልካሙ (ዶ/ር) እና የወልድያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ ተገኝተዋል።
ሰኔ 5/2018ዓ/ም
የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ