Gubalafto woreda culture and tourism office

Gubalafto woreda culture and tourism office promote tourist destinations

ቱሪዝም ኢኮኖሚ የሚሆነው በዘርፉ ግብይት ሲፈጠር ነውጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለጎብኚዎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማስፋት አዲስ አበባ ውስጥ በርከት ያሉ ሞሎች እየተገነቡ እንዳሉና አራት ሞሎ...
02/07/2026

ቱሪዝም ኢኮኖሚ የሚሆነው በዘርፉ ግብይት ሲፈጠር ነው
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

ለጎብኚዎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማስፋት አዲስ አበባ ውስጥ በርከት ያሉ ሞሎች እየተገነቡ እንዳሉና አራት ሞሎች በሚቀጥለው ዓመት ሥራ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ቱሪዝም ኢኮኖሚ የሚሆነው በዘርፉ ግብይት ሲፈጠር ነው፡፡ በቱሪዝም መዳረሻዎች አካባቢ ለቱሪስቶች የሚሆን ምግብ፣ ቡና፣ ቅርጻቅርፆች፣ አልባሳት እንዲሁም ሱቆች መኖር እንዳለባቸው፡፡

ጎብኝዎች መጥተው የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን አይተው መሄዳቸው ብቻውን ቱሪዝምን ስለማያነቃቃ አንድ ጎብኚ ልቡ ተደስቶ፣ ተዝናንቶ ይዞ የመጣውን ወጪም አውጥቶ መሄድ አለበት፡፡ ለዚህም የሞሎችና የሱቆች ግንባታ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ አዲስ አበባ ላይ በርከት ያሉ ሞሎች እየተገነቡ ነው ሶስት አራት የሚጠጉ ሞሎች በሚቀጥለው ዓመት ሥራ ይጀምራሉ ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተሰሩ ያሉ ሞሎች በጥራት ደረጃ በዓለም ጥሩ የሚባሉ ናቸው እነዚህ ስራ ሲጀምሩም ሞል አልባ ከነበረው በመነሳት አፍሪካ ውስጥ የተሻለ ሞል ካላቸው ሃገራት ተርታ ያስገባናል። በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ትላልቅ ለቱሪዝም መዳረሻ የሚሆኑ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ ነው። በዚህም የቱሪዝም ዘርፉ እየተነቃቃ ሲሆን ይሄም የዜጎች፣ የግል ዘርፉ እንዲሁም የብዙ ሰዎች የሃብት እና የዕውቀት ድምር ውጤት ናት።

‎ጉባላፍቶ ወረዳ ተተኪ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን በማፍራት አዲስ ተስፋ እየፈጠረ ነው። ‎‎ወልዲያ፣ ሰኔ 7/2018 ዓ.ም (የጉባላፍቶ ወረዳ ኮሙኒኬሽን)‎‎በቀደምት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና ...
16/06/2026

‎ጉባላፍቶ ወረዳ ተተኪ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን በማፍራት አዲስ ተስፋ እየፈጠረ ነው።

‎ወልዲያ፣ ሰኔ 7/2018 ዓ.ም (የጉባላፍቶ ወረዳ ኮሙኒኬሽን)

‎በቀደምት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና የባህል አርበኞች መፍለቂያ በሆነችው ጉባላፍቶ ወረዳ፣ ተተኪ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ለማፍራት እየተከናወኑ ያሉ ጥረቶች ውጤታማ ፍሬ እያፈሩ መሆናቸው ተገለጸ።

‎የጉባላፍቶ ወረዳ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት በሀመልማል ፊልምና ቲያትር ማህበር አማካኝነት በፊልምና ቲያትር፣ በስነ ጽሑፍ፣ በባህላዊና ዘመናዊ ሙዚቃ እንዲሁም በውዝዋዜ ዘርፎች የሰለጠኑ ወጣቶችን በ1ኛ እና 2ኛ ዙር በማስመረቅ የኪነ ጥበብ ዘርፉን ለማጠናከር እየሠራ መሆኑ ተጠቁሟል።

‎የማህበሩ ሰብሳቢ ወጣት ፈቃዴ እርጥባን እንደገለጹት፣ ማህበሩ በወጣቶች ተነሳሽነት የተመሰረተ ሲሆን በአገር አቀፍና በክልል ደረጃ እየተቀዛቀዘ የመጣውን የኪነ ጥበብ ተተኪነት ለማጠናከር ያለመ ነው።

‎ማህበሩ በራሱ አቅም የተመሰረተ በመሆኑ ከህብረተሰቡ፣ ከባለሀብቶችና ከተቋማት የገንዘብ፣ የቁሳቁስ እና የሞራል ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል።

‎ነገ የተሻለ አርቲስትና የጥበብ ሰው ለማግኘት ዛሬ ተተኪዎችን መደገፍ ይገባል ያሉት ሰብሳቢው፣ የኪነ ጥበብ ማህበራት ለሀገር ባህልና ታሪክ ጥበቃ ያላቸውን ሚና አስገንዝበዋል።

‎በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት አካላት ኪነ ጥበብ በማህበራዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ያለውን ከፍተኛ ፋይዳ አስረድተዋል።

‎በመልዕክታቸውም ስነ ግጥም፣ ተውኔት፣ ድራማ፣ ጭውውትና ሌሎች የኪነ ጥበብ ስራዎች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ግንባታ፣ መዝናኛና ባህላዊ እሴቶች ጥበቃ ያላቸውን ሚና በስፋት አብራርተዋል።


‎በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተለያዩ የጥበብ ስራዎች የቀረቡ ሲሆን፣ ግጥሞች፣ መነባንቦች፣ ጭውውቶች፣ ሙዚቃዎችና ቲያትሮች የታዳሚውን ቀልብ ስበዋል።
‎ታዳሚዎችም በበኩላቸው ጉባላፍቶ ወረዳ የበርካታ አንጋፋ አርቲስቶችና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች መፍለቂያ መሆኗን በማስታወስ፣ የዛሬዎቹ ህጻናትና ወጣቶች ከትንሽ ዕድሜያቸው ጀምሮ ስልጠናና የባለሙያ ድጋፍ እንዲያገኙ መደረጉ የሚበረታታ ተሞክሮ መሆኑን ገልጸዋል።

‎ኪነ ጥበብ የሀገርን ባህልና ታሪክ ከመጠበቅ ባሻገር በህዝቦች መካከል የመግባባትና የትስስር ድልድይ በመሆን ለሀገራዊ አንድነትና ለሁለንተናዊ እድገት የጎላ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ ከመሠረቱ ሊጠናከር እንደሚገባ በታዳሚዎች ተጠቁሟል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳንለ1447ኛው ለታላቁ ለኢድ -አል አድሃ (አረፋ )ብዓል በሰላም አደረሳችሁ         ☪️ኢድ- ሙባረክ
27/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን
ለ1447ኛው ለታላቁ ለኢድ -አል አድሃ (አረፋ )
ብዓል በሰላም አደረሳችሁ

☪️ኢድ- ሙባረክ

የሰሜን ወሎ ዞን ባህል ቱሪዝም ስፖርት መምሪያ "ስፖርት ለሰላም፤ ሰላም ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል  ባዘጋጀው  የመንግስት ሰራተኞች የማስ ስፖርት ውድድርን በወልድያ መልካ ቆሌ ስታድዬም የተካ...
24/05/2026

የሰሜን ወሎ ዞን ባህል ቱሪዝም ስፖርት መምሪያ "ስፖርት ለሰላም፤ ሰላም ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የመንግስት ሰራተኞች የማስ ስፖርት ውድድርን በወልድያ መልካ ቆሌ ስታድዬም የተካሄደ ሲሆን የመጀመሪያውን ዙር ጨዋታ ጉባላፍቶ ከንግድ ባንክ ጋር ባካሄደው የወዳጅነት ጨዋታ 2 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል

ግንቦት 16/09/2018
ወልዲያ

የጉባላፍቶ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ሰፖርት ፅ/ቤት  በቀን 11/09/2018ዓ.ም የስነፅሁፍ ምሽት መድርክ በማካሄድ በመድርኩ  ልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ሰራዎች  ስነፅሁፍ ፣ቴያትር፣ሙዚቃ እንድሁም...
20/05/2026

የጉባላፍቶ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ሰፖርት ፅ/ቤት በቀን 11/09/2018ዓ.ም የስነፅሁፍ ምሽት መድርክ በማካሄድ በመድርኩ ልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ሰራዎች ስነፅሁፍ ፣ቴያትር፣ሙዚቃ እንድሁም የፓናል ውይይቶችን በማካሄድ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን በዓመታዊ የኪነጥበብ ውድድር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለነበራቸው ተወዳዳሪውዎች በሁሉም ዘርፍ ከ1ኛ እሰከ 3ኛ ደረጃ ለወጡ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ፣እንድሁም ለሃመልማል ተኪ አማተር ክበባት በቡድን ደረጃ የምስክር ወርቀትና የማበርታቻ የገንዘብ ሽልማት መስጠት ተችሏል

በተጨማሪ በርካታ የኪነጥበብ ሰዎች የሚወጡበት በመሆኑ ለዘርፉ ልዩ ትኩርት በመሰጠት ታዳጊዎችን በማበረታታት ተተኪዎችን ለማፍራት እየተሰራ ነው ።

‎በቀጣይም ኪነጥበብ ለሰላምና ልማት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ዘርፉን ለማነቃቃት በትኩረት ይሰራል ።

‎ # ኪነ ጥበብ ለልማት!


‎የጉባላፍቶ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት

‎የትምህርት ፑል የ2018 ዓ.ም የጉባላፍቶ ወረዳ የማስ እስፖርት መረብኳስ ዋንጫን አሸነፈ‎‎ወልዲያ፡ ግንቦት 5/2018 ዓ.ም (ጉባላፍቶ ኮምኒኬሽን)‎‎የ2018 ዓ.ም የጉባላፍቶ ወረዳ የማ...
13/05/2026

‎የትምህርት ፑል የ2018 ዓ.ም የጉባላፍቶ ወረዳ የማስ እስፖርት መረብኳስ ዋንጫን አሸነፈ

‎ወልዲያ፡ ግንቦት 5/2018 ዓ.ም (ጉባላፍቶ ኮምኒኬሽን)

‎የ2018 ዓ.ም የጉባላፍቶ ወረዳ የማስ እስፖርት መረብኳስ ውድድር የፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ በመልካቆሌ ስታዲየም በትምህርት ፑል እና በኮምኒኬሽን ፑል መካከል ተካሂዶ፣ የትምህርት ፑል በሰፊ የጨዋታ ብልጫ ዋንጫውን ማንሳት ችሏል።

‎ጨዋታውን የጉባላፍቶ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አራጌ ሞላ በአካል ተገኝተው አስጀምረውታል። በከፍተኛ የተከታታዮች ትኩረት የተካሄደው ይህ ጨዋታ፣ ከጅምሩ ጀምሮ ፈጣን እና አስደሳች ፉክክር ያሳየ ሲሆን፣ የትምህርት ፑል ተጫዋቾች በተቀናጀ የቡድን እንቅስቃሴና በጠንካራ የመከላከልና የማጥቃት አቋም ጨዋታውን በብልጫ መምራት ችለዋል።

‎የኮምኒኬሽን ፑል ጨዋታውን በብልጫ ለመምራት ጥረት ቢያደርግም፣ የትምህርት ፑል ያሳየውን ጠንካራ ብቃት መቋቋም አልቻለም።

‎በጨዋታው መጠናቀቅ በተካሄደው የሽልማት ስነ-ስርዓት፣ የትምህርት ፑል ለዋንጫ ያበቃውን ውጤት በማስመዝገቡ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኖ ተሸልሟል።

‎የጨዋታውን ከፍተኛ ውበትና ፉክክር የተከታተሉ የሁለቱም ቡድኖች ደጋፊዎችና የአካባቢው ወጣቶች በስታዲየሙ በመገኘት ለጨዋታው ደማቅ ድባብ ፈጥረዋል።

‎የጉባላፍቶ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም እስፖርት ጽ/ቤት በበኩሉ፣ ውድድሩ በሰላምና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ለወጣቶች የስፖርት ተሳትፎንና አንድነትን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጿል።

እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት እና ትንሳዔ  በዓል አደርሳችሁ ፣ አደርሰን !!   ➾ የትንሳኤ በዓል ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ለሰው ...
11/04/2026

እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት እና ትንሳዔ በዓል አደርሳችሁ ፣ አደርሰን !!

➾ የትንሳኤ በዓል ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ለሰው ልጆች ደህንነት ሲል ያጋጠመውን መከራ፣ ይቅር ባይነት፣ ስቃይና ግርፋት በፅናት ተቋቁሞና ሞትን አሸንፎ የዲያብሎስን ቀንበር ሰብሮ የሰውን ልጅ ወደ ብርሃን ያሻገረበት የፅናት፣ የአሸናፊነትና የነፃነት በዓል ተምሳሌት ነው

➾ ትንሳዔ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰሙነ ህማማት የተቀበላቸውን ግርፋት፣እርዛት፣ችንካር እና የእሾህ አክሊሊል በትዕግስት አልፎ በሰው ልጆች ሁሉ የሚታየውን ቀቢጸ ተስፋነት አስወግዶ የተስፋ ጮራ የዘራ ታላቅ የምስራች በዓል ነው ።

➾ የመረዳዳት፣የመደጋገፍና የመተባበር ባሕልና እሴት ባለቤት ሲሆን በዓሉን ሲከብር በሃይማኖቱ አስተምህሮ መሠረት የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብ በአብሮነትና በመደጋገፍ የምናከብርው በዓል ነው ።

በመጨረሻም በዓሉ ከፍታን እና ርህራሄን የምናሳይበት፣እርስ በርስ የምንረዳዳበት፣ያለው ከሌለው ተባብሮ የሚያልፍበት በዓል እንዲሆን ከልብ እንመኛለን ።

" ባህላችን ለዘላቂ ሠላማችን "

የጉባላፍቶ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ፅ/ቤት

18/03/2026
‎የአብሮነት እና የመረዳዳት ወር በሆነው የረመዳን ወር የነበረውን መልካምነት አጠናክሮ በማስቀጠል ለሀገር ሁለንተናዊ ሰላምና ልማት መትጋት ይገባል። ‎የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ መንገሻ...
18/03/2026

‎የአብሮነት እና የመረዳዳት ወር በሆነው የረመዳን ወር የነበረውን መልካምነት አጠናክሮ በማስቀጠል ለሀገር ሁለንተናዊ ሰላምና ልማት መትጋት ይገባል።
‎የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር)

‎ወልድያ፦ መጋቢት 8 /2018 ዓ.ም (ጉባላፍቶ ኮሙኒኬሽን)

‎በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ የረመዳንን ፆም ምክንያት በማድረግ የኢፍጣር መርሃ ግብር ተካሂዷል።

‎የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) የኢፍጧር መርሃ-ግብር የኢትዮጵያን የመቻቻል እና የእንግዳ ተቀባይነት እሴት የሚዘክር በመሆኑ በህዝቦች መካከል ያለውን ወንድማማችነት እና ማህበራዊ ትስስር ይበልጥ የሚያጎለብት በመሆኑ ሁሉም በአቅሙ መረዳዳቱን እንዲቀጥል መልክት አስተላልፈዋል።

‎የፕሮግራሙ ተሳታፊዎችም ለተደረገው የኢፍጧር ፕሮግራም ምስጋና አቅርበዋል።

‎በፕሮግራሙ የክልል እና የዞን ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የወረዳ አመራሮች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

‎አንድነት ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት እና ክብር መሰረት መሆኑን የአድዋ ድል ማሳያ ነው። ‎ወልድያ፦ የካቲት 23/2018 ዓ/ም (ጉባላፍቶ ኮሙኒኬሽን)‎በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ 130...
02/03/2026

‎አንድነት ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት እና ክብር መሰረት መሆኑን የአድዋ ድል ማሳያ ነው።

‎ወልድያ፦ የካቲት 23/2018 ዓ/ም (ጉባላፍቶ ኮሙኒኬሽን)

‎በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ 130ኛው የአድዋ ድል በዓል "ከአኩሪ ታሪክ ወደብሩህ አድማስ" መሪ ሀሳብ ከወረዳው ጠቅላላ አመራር እና ሰራተኞች ጋር በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

‎የጉባላፍቶ ወረዳ ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ በየነ የተጀመሩ ልማቶችን ለማስቀጠልና ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ አድዋን ከመዘከር ባለፈ ዘመኑ የሚጠይቀውን አርበኝነት መላበስ እንደሚያስፈልግ መልእክት አስተላልፈዋል።

‎ለዓሉ በጉባላፍቶ ወረዳ የጁገነት የባህል ቡድን እና አማተር ከያኒያን የተለያዩ ኪነጥበብ ስራዎችን አቅርበዋል። ለፓናል ውይይት መነሻ ሰነድ የወረዳው መንግስት ኮሙኒኬሽን ሀላፊ አቶ አያሌው አስፋው ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

Address

Woldia

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gubalafto woreda culture and tourism office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share