APHI woldia Branch አብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ

  • Home
  • Ethiopia
  • Woldia
  • APHI woldia Branch አብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ

APHI woldia Branch አብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ Amhara Public Health Institute Woldia Branch (APHI-WB)
በአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ- ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ ለሰሜን ወሎ፣ ለዋግኸምራና ወልድያ ከተማ አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል።

10/09/2026
05/09/2026
ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጤና ትኩረት ሊሰጥ ይገባል!ነሃሴ 22/2018 ዓ.ም | ወልድያየአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ ከሰሜን ወሎና ዋግህምራ ዞኖች እንዲሁም ከወልድ...
29/08/2026

ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጤና ትኩረት ሊሰጥ ይገባል!

ነሃሴ 22/2018 ዓ.ም | ወልድያ

የአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ ከሰሜን ወሎና ዋግህምራ ዞኖች እንዲሁም ከወልድያ ከተማ የተውጣጡ የጤና ባለሙያዎችና የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የጤና አገልግሎት ለማሻሻል የሚያስችል ውይይት አካሄደ!።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ሲ/ር ሰላማዊት አያሌው በወልድያ ክላስተር ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ከቀያቸው የተፈናቀሉ በርካታ ዜጎች መኖራቸውን አንስተዉ ለእነዚህ ወገኖች አስፈላጊውን የጤናና መሰረታዊ አገልግሎት ለማድረስ በጋራ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። ሲ/ር ሰላማዊት አያሌው በልክታቸዉ "ተፈናቃዮች ከቤታቸው ተፈናቅለው በከባድ ፈተና ውስጥ ናቸው። ለእነሱ የምንሰጠው አገልግሎት እንዲሁ ስራ ሰለሆነ ብቻ ሳይሆን ከልብ በሰብአዊነት ስሜት የሚጠበቅብንን ማድረግ አለብን ብለዋል።"

በመድረኩ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር አለሙ ወርቁ ባቀረቡት ሪፖርት መሰረት በ2018 በጀት ዓመት በርካታ ስራዎች ቢከናወኑም የቅንጅት ስራ እጥረት፣ የመረጃ ጥራት ችግር፣ የህክምና ግብአት አቅርቦት እጥረት እና የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች (Collective sites) እጥረት የተስተዋሉ መሆኑን ገለጸዋል።

የዉይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ በተለይ ለተፈናቃዮች ጉዳይ ትኩረት አለመሰጠቱን አስምረው የድንገተኛ ጤና አደጋዎችን መከላከልና መቆጣጠር ላይ የጋራ ትብብር መጠናከር እንዳለበት እና በቀጣይ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በውይይቱ መጨረሻ ላይ ለተፈናቃዮች የተጠናከረ የጤና አገልግሎት መሰጠት እንዳለበት፣ ያሉ ጉድለቶችን ማረም፣ መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር ከአሁኑ በላቀ ደረጃ ለመስራት መዘጋጀት፣ የባለሙያዎች እና አጋር አካላት ቅንጅት እና የመረጃ ስርዓትን ማሻሻል እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

"ለህብረተሰብ ጤና ልማት እንትጋ!!"

#ወልድያ #አማራ #የህብረተሰብጤናኢንስቲትዩት #ተፈናቃዮች #ጤናለሁሉም #ዋግህምራ

07/08/2026

Green Legacy 2018

📢 የአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ ሠራተኞች በኢንስቲትዩቱ ግቢ ችግኝ ተከሉ።📅 ነሃሴ 1/2018 ዓ.ም | ወልድያየአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርን...
07/08/2026

📢 የአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ ሠራተኞች በኢንስቲትዩቱ ግቢ ችግኝ ተከሉ።

📅 ነሃሴ 1/2018 ዓ.ም | ወልድያ

የአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ ሰራተኞች እና አመራሮች በተቋሙ ግቢ አረንጓዴ አሻራን አኖሩ። የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሰራተኞች በጋራ በመሆን የተለያዩ የችግኝ ዓይነቶችን ተክለዋል።

ተግባሩ በዋናነት ያተኮረው የተቋሙን ውበት ከማስጠበቅ ባለፈ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ተቋሙ ያለውን ቁርጠኝነት ለማሳየት ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የቅርንጫፉ ዋና ዳይሬክተር ሲ/ር ሰላማዊት አያሌው በዚሁ ወቅት እንደገለጹት "የችግኝ ተከላው የህብረተሰብ ጤናን ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የማስተሳሰር ሰፊ ራዕይ አካል ነው። ጤናማ ማህበረሰብ የሚመጣው ከጤናማ አካባቢ ነው" ብለዋል።
🌱 የቅርንጫፉ ማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ!

“ለህብረተሰብ ጤና ልማት እንትጋ!!”

#አረንጓዴአሻራ #ወልድያ #በጎፈቃድ #ኢትዮጵያ

📢 የአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ በጃራ የተፈናቃዮች መጠለያ ላይ የጤና ምርመራና የግንዛቤ ማስጨበጫ አካሄደ! 🩺❤️📅 ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም📍 ጃራ የተፈናቃዮች መ...
06/08/2026

📢 የአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ በጃራ የተፈናቃዮች መጠለያ ላይ የጤና ምርመራና የግንዛቤ ማስጨበጫ አካሄደ! 🩺❤️

📅 ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም
📍 ጃራ የተፈናቃዮች መጠለያ

በክረምት በጎ ፈቃድና ማህበረሰብ አገልግሎት የአብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ ከሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ጋር በመተባበር ወደ ማህበረሰቡ በመውረድ በሰሜን ወሎ ዞን በጃራ የተፈናቃዮች መጠለያ ጠቃሚ አገልግሎቶች ሰጥቷል።

📊 የተከናወኑ ተግባራት፦

1️⃣ የስኳርና የሄፓታይተስ ምርመራ፦
በመጠለያው ለሚገኙ ተፈናቃዮች የስኳርና የሄፓታይተስ ቢ እና ሲ ምርመራ ተካሂዷል። በምርመራው ለተገኙ ህሙማን አስፈላጊው የህክምና ምክርና ክትትል እንዲደረግላቸው ተደርጓል።

2️⃣ የደም ግፊት ምርመራ፦
ከተመረመሩ ሰዎች መካከል የደም ግፊት (Raised BP) ላላቸው ወገኖች ስለ አመጋገብ፣ ስለ አኗኗር ዘይቤና ስለ መደበኛ ክትትል አስፈላጊነት ምክር ተሰጥቷል።

3️⃣ የከንፈር መሰንጠቅ መለየት፦
በምርመራው ወቅት የከንፈር መሰንጠቅ (Cleft Lip) ችግር ያለበት ህጻን በመለየት ተገቢውን ህክምና እንዲያገኝ አስፈላጊው ስራ ተሰርቷል።

4️⃣ የጂን ኤክስፐርት ናሙና መውሰድ፦
የጂን ኤክስፐርት (Gene Xpert) ምርመራ ናሙና ተወስዶ ወደ ላቦራቶሪ የተላከ ሲሆን ውጤቱ ሲወጣ ተገቢው እርምጃ ይወሰዳል።

5️⃣ የግንዛቤ ማስጨበጫ፦
በክረምት ወቅት ሊከሰቱ በሚችሉ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጥቷል።

💬 የአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ ጤናን ወደ ማህበረሰቡ በማድረስና ወቅታዊ የጤና ችግሮችን ቀድሞ በመለየት ረገድ ያለው ቁርጠኝነት ይበልጥ አጠናክሮ ይቀጥላል።

“ለህብረተሰብ ጤና ልማት እንትጋ!!” ✊🏾💚

#ወልድያ #ተፈናቃዮች #ሄፓታይተስ #ስኳር #ግፊት #ቲቢ #ኢትዮጵያ

📢 የአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍየ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ገምግሞ የ2019 ዕቅድ አስተዋወቀ!📅 ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም📍 ወልድያ፣ ኢትዮጵያ በመድረኩ ላይ ሁ...
23/07/2026

📢 የአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ
የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ገምግሞ የ2019 ዕቅድ አስተዋወቀ!

📅 ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም
📍 ወልድያ፣ ኢትዮጵያ

በመድረኩ ላይ ሁሉም የተቋሙ ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን የ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ ስራዎች ላይ ጥልቅ ግምገማ ተደርጓል።

🌟 የ2018 በጀት ዓመት ዋና ዋና ስኬቶች፦

🧪 በተለያዩ የጤና ተቋማት የላቦራቶሪ አገልግሎት ጥራት በማሳደግ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።
የደረጃ በደረጃ የላብራቶሪ ጥራትን የማሳደግ ስራ ተሰርተዋል። በዚህም ሁለት ጤና ጣቢያዎችና ሰባት ሆስፒታሎች ከ2-4 የኮከብ ደረጃ አግኝተዋል ።
የማይክሮባዩሎጂ ስራ ተጠናክሮ በመጀመሩ የተለያዩ የበሽታ አምጭ ተህዋስያንን የመለየት እና የመድሃኒት ብግርነት (መላመድ) ፍተሻ እንዲሁም የቁንጭር (ሌሽማንሳያ) ማይክሮስኮፒ ምርመራ ላይ አበረታች ስራ ተሰርቷል።
ከወልድያ ዩንቨርስቲ ጋር በመቀናጀት የወባ በሽታን ከመከላከልና ከማከም አንፃር ለጤና ኤክስቴንሽንና ላብራቶሪ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል።
በክላስተሩ ላሉ ጤና ተቋማት የላብራቶሪ ስራዎችን ለማጠናከር የሚያስችሉ የተለያዩ ግብአቶች ድጋፍ ተደርጓል።
🚨 የድንገተኛ ህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ተጠናክሯል።
ለጤና ባለሙያዎችና ለሚመለከታቸው አካላት የድንገተኛ ጤና አደጋዎችን ከመከላከልና መቆጣጠር አንፃር የተለያዩ ስልጠናዎች እና የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን በክላስተሩ ለሚገኙ ጤና ተቋማት ተከታታይ ድጋፍና ክትትል ተደርጓል።
🏢 የሠራተኞችንና የተገልጋዮችን ደህንነትና ምቾት ለማስጠበቅ ግቢውን ውብ፣ ማራኪ እና ጽዱ የማድረግ ሥራዎች በስፋት ተከናውነዋል።

🗣 በመድረኩ የአማራ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ ዋና ዳይሬክተር ሲ/ር ሰላማዊት አያሌው
በ2018 ዓ.ም የተመዘገበው መልካም አፈጻጸም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበው፣ ጉድለቶችን በማረምና መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር በ2019 ዓ.ም አሁን ካለው በላቀ ደረጃ ለመፈጸም መዘጋጀት እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በተጨማሪም የክረምት በጎ ፈቃድና ማህበራዊ አገልግሎት በተጠናከረ መልኩ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

“ለህብረተሰብ ጤና ልማት እንትጋ!!”

#የአማራየህብረተሰብጤና #ወልድያ #የ2018ዓምግምገማ #የ2019ዕቅድ #ኢትዮጵያ

16/04/2026

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

Address

Woldia

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when APHI woldia Branch አብክመ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share