16/08/2026
የአበሽጌ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት የክረምት በጎ ስራን አስመልክቶ ለአንዲት አቅመ ደካማ እናት የመኖሪያ ቤት የመገንባት ስራ አስጀመረ
ነሀሴ 10/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)
በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ አምበልታ ቀበሌ የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት የክረምት በጎ ስራን አስመልክቶ ለአንዲት አቅመ ደካማ እናት የመኖሪያ ቤት የመገንባት ስራ አስጀምሯል።
ተቋሙ በዛሬው ዕለት ባደረገው የመጀመሪያ ድጋፍ ለቤት መስርያ የሚያገለግል የተለያዩ ቁሳቁሶችን ያበረከተ ሲሆን ቤቱ ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አስታውቋል።
በርክክብ ስነስርአቱ የተገኙት የአበሽጌ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊና የወረዳው ም/አስተዳዳሪ አቶ ቢኒያም ጥላሁን እንደገለጹት የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ስኬታማ ለማድረግና ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተባብሮ መስራት እንደሚገባቸው ጠቅሠዋል።
በዛሬው እለትም በአምበልታ ቀበሌ በመገኘት ለወ/ሮ ፋጥወት ኑሮ የቤት መስሪያ አስፈላጊ ቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ያነሳሳቸው ወይዘሮዋ በከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ችግር ላይ መሆናቸውን በማየትና ደጋፊና ጧሪ የሌላቸው በመሆኑ እንደሆነ ገልጸዋል።
አክለውም ቤታቸው ለመኖሪያነት የማይሆን መሆኑን በመመልከት ይህን ድጋፍ ማድረጋቸው ኃላፊው ገልጸው የቀበሌውም ነዋሪ በመተባበር ባጠረ ጊዜ ተጠናቆ ማስረከብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በወረዳ ደረጃም በተያዘው የክረምት ወራት በርካታ የአረጋውያን ቤቶች እየተገነቡ እንደሚገኝ አስታውሠው በበጋው ወራትም መሠል ተግባራት ቅንጅታዊ አሰራሮችን አጠናክሮ በማስቀጠል መቀጠል እንደሚገባቸው አቶ ቢኒያም አሳስበዋል።
በስጦታ የተበረከቱት ለቤት ግንባታ የሚሆኑ ቁሣቁሶች ከወረዳው የነጋዴው ማህበረሰብ በተሠበ ገንዘብ መሆኑን አውስተው በግልም አንዳንድ ባለሀብቶች መሣተፋቸውን ገልጸዋል።
የአበሽጌ ወረዳ ውሀና ማእድን ኢነርጂ ጽ/ቤት ኃላፊና የቀበሌው ደጋፊ አቶ ሙላቱ ደሳለኝ በበኩላቸው ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን ለማስመስከር አቅመ ደካማ ለሆኑ እናት እያደረጉ ያሉትን የመኖሪያ ቤት ገንብቶ የመስጠት ተግባር እጅግ የሚያስመሰግን ነው ስሉ ገልጸዋል።
አክለውም ይህ ቤት በዛሬው ዕለት እንደተጀመረ ሁሉ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ እማወራዋ እፎይታን እንድታገኝ ሁሉም አካላት ከወዲሁ እርብርብ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
ወ/ሮ ፋጥወት ኑሮ በበኩላቸው ኑሮዋቸው አስቸጋሪ እንደነበር ጠቁመው ይኖሩበት የነበረው ሳር ቤት በከፊል በመፍረሱ ምክንያት የከፋ ችግር ውስጥ ገብተው እንደነበር ተናግረው ዛሬ በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውንና ድጋፉን ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።
በመርሀ-ግብሩ ላይ የወረዳው የአበሽጌ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊና የወረዳው ም/አስተዳዳሪ አቶ ቢኒያም ጥላሁን ፣ አበሽጌ ወረዳ ውሀና ማእድን ኢነርጂ ጽ/ቤት ኃላፊና የቀበሌው ደጋፊ አቶ ሙላቱ ደሳለኝ ጨምሮ የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
ዘገባው የአበሽጌ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።
ፔጃችን ስለምትከታተሉ እያመሰገንን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የተቀመጡትን ሊንኮች በመጫን የተቋማችን የሚዲያ አማራጮችን ይጠቀሙ፡-
👉://www.facebook.com/profile.php?id=100070918473865&mibextid=kFxxJD
👉http://tiktok.com/
👉 ቴሌግራም፦ https://t.me/awc567
👉 ዩቲዩብ:- https://youtube.com/?si=8HvFtXplAUMiEnmx
👉 instagram :-
https://www.instagram.com/abeshigeworeda?igsh=MjQyMXN5bnhkb2d2
👉X
https://x.com/AWoreda5717?t=x9hbuUQi9Esw9XahIjQkWQ&s=09