03/09/2026
በመስኖ ተቋማት ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ በምግብ ስርአት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) በጀት ድጋፍ በሶስት የፕሮግራሙ ወረዳዎች ምዕራብ አዘርነት በርበሬ፣ ጉመርና ሶዶ ወረዳዎች በፋክት አማካሪ ድርጅት የተጠኑ የሶስት አነስተኛ የመስኖ ግድቦች ዝርዝር ጥናትና ዲዛይን ለመገምገም የውይይት መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ነሀሴ 28/2018ዓ.ም(ወልቂጤ)
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ካሳዬ ተክሌ እንዳሉት በመስኖ ዘርፍ በተናጥል መስራት ውጤት ሊያመጣ እንደማይችል አንስተው፤ ከግብርና፣ ከመስኖ፣ ከውሃና ከሌሎችም ተቋማት በመቀናጀት ውጤታማ ስራ መስራት ይገባል።
የምግብ ስርአት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) በክልሉ በዘርፉ በርካታ የልማት ስራዎች ሲሰራ መቆየቱንም ተናግረዋል።
በዛሬው እለት እየተገመገሙ ያሉ የመስኖ ፕሮጀክቶች 7መቶ 80 ሄክታር መሬት ሊያለሙ የሚችሉ መሆናቸውንም አንስተዋል።
በፌደራል ግብርና ሚኒስቴር የምግብ ስርአት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ዩኒት ኢንጂነር ያለው በለጠ በበኩላቸው፥ የምግብ ስርአት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) በ2004 ዓ.ም የግብርና እድገት ፕሮግራም በሚል ስያሜ እንደጀመረ ጠቁመው፤ ይህ ፕሮግራም በአሁኑ ወቅት በዘርፉ በርካታ የልማት ስራዎች እያከናወነ ይገኛል።
እነዚህ የተጠኑ የመስኖ ፕሮጀክቶች ውጤታማ እንዲሆኑ በዘርፉ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በትኩረት መስራት እንዳለባቸውም አመላክተዋል።
በግምገማ መድረኩም ከፌደራል፣ የክልሉ የግብርና ቢሮ የስርአት ምግብ ማጠናከሪያ ፕሮግራም አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች፣ የመስኖ ተቋማት ልማትና ኤጀንሲ የማኔጅመንት አካላትና የጥናትና ዲዛይን ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ ጥናቱ ያጠኑ አካላትና ሌሎችም ተገኝተዋል።