Gurage Zone Finance Department

Gurage Zone Finance  Department Gurage Zone Finance Department

በእውቀትና በስነምግባር የታንጸ ተወዳዳሪ ትውልድ ለማፍራት ዘመኑን የሚዋጅና የሚመጥን ትምህርት ቤት መገንባት ፋይዳው ከፍተኛ ነው:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) ነሐሴ 23/20...
29/08/2026

በእውቀትና በስነምግባር የታንጸ ተወዳዳሪ ትውልድ ለማፍራት ዘመኑን የሚዋጅና የሚመጥን ትምህርት ቤት መገንባት ፋይዳው ከፍተኛ ነው:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

ነሐሴ 23/2018(ወልቂጤ)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጉንችሬ ብራይት ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በዛሬው እለት ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ጥራት ያለው ትምህርት ተደራሽ በማድረግ ብቁ፣ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ እንዲፈጠር በልዩ ትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

ትምህርት ቤቱ ተገንብቶ ለውጤት እንዲበቃ ላደረጉ ለሚስተር ሮቤርቶ ቤተሰቦች እና ካንትሪ ዳይሬክተር ሆነው እየሰሩ ላሉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የትኛውም ፕሮጀክት የሚነሳው ከሀሳብ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ሀሳብን ወደ ተግባር በመተርጎም ፕሮጀክቱን እውን ላደረጉ ሁሉ ርዕሰ መስተዳድሩ በራሳቸው እና በክልሉ መንግስት ስም ምስጋና አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ የልማት ስራ ተጀመረ እንጂ አዳጊ የሆነውን የህዝብ ፍላጎትን በማሟላት ረገድ ቀሪ ስራ ይኖራል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጥተኛ የልማት ስራ መሳተፍ ከጀመረች ጥቂት ዓመታት መቆጠራቸውን ጠቅሰዋል።

የአካባቢው ተወላጆች ተባብረን የልጆቻችንን የወደፊት ብሩህ ተስፋ ማለምለም ይገባል ብለዋል።

የዚህ ዘመን ትውልድ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳዳሪ መሆንን ይሻል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም ዘመኑን የሚመጥን እና የሚዋጅ ስራ ይጠይቃል ብለዋል።

ትምህርት አለምን የሚለውጥ መሳሪያ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ህጻናት ተገቢውን እንክብካቤ አግኝተው ማደግ እንዲችሉ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

ተያይዘን ኢትዮጵያን እና ክልላችንን እንገነባለን ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የኢትዮጵያን ትንሳኤ እውን እናደርጋለን ሲሉም ጠቅሰዋል።

ከትምህርት ቤት ግንባታ ባለፈ በጤናውም ዘርፍ የህዝብ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል እርስቱ ይርዳው በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት መጀመሪያ መዋዕለ እጻናት መገንባት ታሳቢ ያደረገ እንደነበር የተናገሩት

መንግስት የህዝቡን የመሰረተ ልማት ፍላጎት ለማሟላት በልዩ ትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም ምክትል ኮሚሽነር ጀነራሉ
አመላክተዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም ወጣቶች የህጻናት ትምህርት ቤት እንዲገነባላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ በልበ ቀናነት በመቀበል ወደ ተግባር በመገባቱ ለውጤት በቅቷል ብለዋል።

በከተማው ቅድመ 1ኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት በዛሬው እለት ለምረቃ ማብቃት መቻሉን ጠቅሰዋል።

ትምህርት ቤቱ አሁን ለደረሰበት ደረጃ እንዲበቃ ዲዛይን ከመንደፍ ጀምሮ የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ የቼንትሮ ኢትዮጵያ መስራች እና ፕሬዝዳንት ለነበሩት ሮቤርቶ ራባቴኒ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ዛሬ እኒህ ልበ ቀና አባት በህይወት ባይኖሩም ህያው ስራቸው በትውልዱ ዘንድ ሲታወስ እንደሚኖርም ጠቁመዋል።

ከነባር ይዞታቸው ተነስተው ለትምህርት ቤት ግንባታ እንዲሆን ትብብራቸውን ለገለጹ ነዋሪዎች እና ለወንድም ተስፋዬ ይገዙ ምስጋና አቅርበዋል።

የመደመር መንግስት ለህብረተሰቡ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን እያበረከተ ይገኛል ያሉት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራሉ ዛሬ የትምህርት እና የጤና ፕሮጀክቶችን አስመረቅን እንጂ ከዚህ በላቀ ደረጃ በሁሉም አካባቢዎች የልማት ስራዎችን ተደራሽ እየተደረገ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

በከተማም ሆነ በገጠር አካባቢዎች የህብረተሰቡን ህይወት ለማሻሻል የጋራ ትብብር እና ጥረት ይጠይቃል ሲሉም ኮሚሽነር ጀነራሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በበኩላቸው ትምህርት የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ ሁሉም በዘርፉ ኢንቨስት ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

በዞኑ የትምህርት ጥራትና የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ አቶ ላጫ ጋሩማ ገለጻ የዞኑ መንግስት በዘርፉ ውጤት ለማስመዝገብ ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በከተማው የተገነባው ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዞኑ ግንባር ቀደምና አርአያነት ያለው መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህ ደረጃውን የጠበቀው ትምህርት ቤት በእውቀት የበለጸገ ተወዳዳሪ ትውልድ በማፍራት ረገድ ፋይዳው ከፍተኛ ነው ያሉት።

የኢፌዲሪ መስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዴኤታ እና የትምህርት ቤቱ ግንባታ አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ይገዙ እንደገለጹት በአካባቢና በሰፈር ሳንታጠር መስራት ከቻልን የህዝባችንን ህይወት መለወጥ ቀላል ነው ብለዋል።

በእርሳቸው አስተባባሪነት በተለያዩ አካባቢዎች 30 ትምህርት ቤቶችን ማስገንባት ችለናል ያሉት አቶ ተስፋዬ በትምህርት ዘርፍ የሚደረገው ኢንቬስትመንት ድንበር የለውም ብሲሉም ጠቁመዋል።

የጉንችሬ ከተማ ከንቲባ አቶ አብድልቋድር ሂጅራ የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል የትምህርት ተቋማት ደረጃቸው ማሻሻል ወሳኝ ነው ብለዋል።

በቀጣይም በዘርፉ የተጀመረውን የትምህርት ጥራትና የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል።

የቼንትሮ አዩቲ ፔርሌ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ፖውላ አሪቼ እንዳሉት ትምህርት የህጻናትን የወደፊት ህይወት የሚለውጥ መሳሪያ ነው ብለዋል።

በዞኑ የተገነባው ትምህርት ቤት ሀገር የሚለውጡ ዜጎች የሚፈጠሩበት ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

ትምህርት ቤቱ ቀጣይነት እንዲኖረው መሰረተ ልማቱን መጠበቅና መንከባከብ ተገቢ ስለመሆኑም አመላክተዋል።

ምክር ቤቱ ለ2019 በጀት ዓመት ከ10 ቢሊየን 788 ሚሊየን 612 ሺ በላይ ብር በጀት አፀደቀነሐሴ 22/2018(ወልቂጤ) የጉራጌ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የሥራ...
28/08/2026

ምክር ቤቱ ለ2019 በጀት ዓመት ከ10 ቢሊየን 788 ሚሊየን 612 ሺ በላይ ብር በጀት አፀደቀ

ነሐሴ 22/2018(ወልቂጤ) የጉራጌ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 31ኛ መደበኛ ጉባኤው በወልቂጤ ከተማ እያኬሄደ ይገኛል።

ምክር ቤቱ የጉራጌ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው የበጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ በዝርዝር ተወያይቷል።

ምክር ቤቱ በ4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 31ኛ መደበኛ ጉባኤው ለ2019 በጀት ዓመት ከ10 ቢሊየን 788 ሚሊየን 612 ሺ በላይ ብር በጀት ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል።

የጉራጌ ዞን ወባጀ ሸመነ የ2018 ዘበር ያነቀወ የቾችዮ ሜናም የጠወጪ የ2019 ዘበር ኣትያነት ተቐነበም በወርቕጤ ቤሮ ኣትዋጄም።ናሴ 21/2018 (ወርቕጤየ)የጉራጌ ዞን ወባጀ ሸመነ 4ተነ ...
27/08/2026

የጉራጌ ዞን ወባጀ ሸመነ የ2018 ዘበር ያነቀወ የቾችዮ ሜናም የጠወጪ የ2019 ዘበር ኣትያነት ተቐነበም በወርቕጤ ቤሮ ኣትዋጄም።

ናሴ 21/2018 (ወርቕጤየ)

የጉራጌ ዞን ወባጀ ሸመነ 4ተነ ወረር 13ተነ ዘበር 31ተነ መደበኛ ድሙድ አኳ ቲያሜ ዋረም።

የጉራጌ ዞን ቡር አተድር የትኸበዶ ኣበቃጥ ላጫ ጋሩማ ቦረ ዘበር የቾችዮ ሜና ሪፖርት ቲያትቐንቦ የዞንዌ ሐልቅ ይረጥቦ ብዘ ሜና ቾቺም ባሮም።

በዞንዌ ኣታንክርት የረማዎ በትት ኣፈር ᎀጠሪም ኣወካቶም የቀᎌሪ ቲሐር እሓ ባነዎᎄ መደር መስኖ ባርሞት በሕርም ኣርበት ግዝየ ይቾቺሐማ ኣትኸሮም።

በጌያ ይታዥ ያነ የንብረት ጥርነት ያትርጓጔዬ የቾችዮ ሜና ወሔቃር ቢሐሮም ንብረት ያትረምዶ ነጋዴ ወምሕርም ዋትመር ያሸ ባሮም።

ሐልቅ፣ መንግስትም የገን ደንገነ በድሙድ ብዘ የትጐዶ ትምርት ቤት ያረሺ ቲሐር የትምርት ጥራት፣ የተማሪ ውጤትም ኣመር ይትጘጘሬ ቲቾቺ የረበረሐማ ኦዶም።

ኤማ የሐልቀንዳ ንቅነት ያትኸርᎄ ተርማሞት ቲሐርሐልቅ፣ መንግስትም የገን ደንገነ በድሙድ ታርበት በእር በረን ኤማ ቾቺም ባሮም።

በዞንዌ የቹቻ ፣በከተማ ተርማሞት፣በትምርት፣ ብሓ፣በፌነት ማራ፣ቤማ፣በዱንያ ንሐወቸ፣ በዘርማም ብስፖርት፣ በኢንቨስትመንት፣ በርᎀም ብንጐድም በሜና ተርማሞት ሜና ቾቺም።

በጠᎄጪ ዘበርም ሐልቅ ይረጥቦ ቡችር ቡችር ሜና ኣተᎄም ይቾቺሐማ ዝረከዎም።

ወባጀ ሸመነዌ በረገ ወባጀታ የ2019 በጀትም እንጐ አጀንዳ ተቐነዎም ያጸድⷂቴ ቧሪም ይቅረዊ።

ወቅታዊና ጥራት ያለው መረጃ ማሰባሰብ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖርና የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፋይዳው ከፍተኛ በመሆኑ በዘርፉ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል:-...
26/08/2026

ወቅታዊና ጥራት ያለው መረጃ ማሰባሰብ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖርና የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፋይዳው ከፍተኛ በመሆኑ በዘርፉ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል:- አቶ ላጫ ጋሩማ

ነሀሴ 20/2018ዓ.ም(ወልቂጤ) የጉራጌ ዞን ፕላን ልማት መምሪያ የ2019 በጀት አመት የወረዳዎች ሼር (ድርሻ) የማሳወቅ እና የሀብት ማከፋፈያ ቀመር አሰራር አስመልክቶ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ ውይይት አካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በመድረኩ ተገኝተው እንዳሉት በዞኑ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር የመረጃ አሰባሰብና አያያዝ ስርአቱ እያደገ መምጣቱን ጠቁመው፤ ይህ በቀጣይም የበለጠ ማጠናከር ይገባል።

በቀጣይ ከመረጃ አሰባሰብ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን በየተቋማት ማጥራት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በዞኑ ትላልቅ ግዙፍ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች በተለይም የአስተዳደር ህንጻና የማህበረሰብ የቴሌቪዥን ጣቢያ ለማጠናቀቅ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ያነሱት አቶ ላጫ በዘንድሮ አመትም ተጨማሪ የአዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ለማስጀመር እንደሚሰራ አመላክተዋል።

ወቅታዊና ጥራት ያለው መረጃ ማሰባሰብ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖርና የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፋይዳው ከፍተኛ በመሆኑ በዘርፉ የተጀማመሩ ስራዎችን በቀጣይም በማጠናከር መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የጉራጌ ዞን ፕላን ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ከበደ ሀይሌ በበኩላቸው በዞኑ በ2018 በጀት አመት ጥራትና ትክክለኛነት ያለው መረጃ ማሰባሰብ ላይ በተሰራው ስራ ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱንም ገልጸዋል።

ለዚህም ከወረዳ ፕላን መዋቅሮች፣ ከአስተዳዳሪዎች፣ ከሚመለከታቸው የመምሪያ ኃላፊዎችና ከክልል መዋቅር መረጃ የማጥራት ስራ መሰራቱን ያነሱት ኃላፊው በቀጣይም ለመረጃ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት መሰብሰብና መያዝ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በቀጣይ የተሻለ የመረጃ አሰባሰብ ስርአት እንዲኖር ከዞኑ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ጋር በመሆን ሶፍት ዌር ማልማት መቻሉን አንስተው ይህም የበለጠ የመረጃ አሰባሰብና አያያዝ ስርአቱ ውጤታማ እንደሚያደርገውም ተናግረዋል።

በዞኑ የገቢ መሰረቶችን በማስፋት፣ የገቢ አማራጮችን አሟጦ ከመሰብሰብ ባለፈ የበጀት ብክነት መቀነስ እንደሚገባም አስረድተዋል።

የ2019 ዓ.ም በጀት በፍትሃዊነት በመረጃ ቀመሩ መሰረት ማከፋፈል መቻሉን ጠቅሰው፤ በዚህም በሀብት ክፍፍሉ ከታችኛው መዋቅሮች ጋር መግባባት መቻሉንም ገልጸዋል።

የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዶ ሀሰን የ2019 ዓ.ም በጀት አከፋፈል በቀመሩ መሰረት በፍትሃዊነትና በግልጸኝነት ለወረዳዎች ማከፋፈል ተችሏል ብለዋል።

አክለውም በጀቱ በዞኑ ያሉ ፕሮጀክቶችና በአምና ደረጃ ተጨማሪ የተደረገው የሰራተኛ ደሞዝ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በፍትሃዊነት ክፍፍል መደረጉንም ተናግረዋል።

ይህ የተከፋፈለው ውስን በጀት በቁጠባ በተገቢው ለልማት በማዋል ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች እንዳሉት ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር የቀመር መረጃ አሰባሰብ ስርአት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቁመው በቀጣይ የመረጃ ስርአቱ ይበልጥ ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በተለይም የመረጃ አሰባሰብና የመረጃ አያያዝ ስርአቱ ለማዘመን በዞኑ ሶፍት ዌር ለማልማት የተኬሄደበት ርቀት የሚበረታታ ነው ብለዋል።

የጉራጌ ማህበረሰብ የቲቪ ጣቢያ በፍጥነት ወደ ተግባር ለማስገባትና የአማርድ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለማጠናከር በበጀት ታሳቢ መደረጉ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩም የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የኢኮኖሚ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ጠጄ ደነቀ፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር አስተዳዳሪዎችና ከንቲባዎች እንዲሁም ፕላን ልማትና ፍይናንስ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ሌሎችም ተገኝተዋል።

ነሐሴ 18/2018 (ወልቂጤ)የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ በ2019 በጀት ዓመት እቅድ  ከፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ  አቶ አብዶ ሀሰን ጋር የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል።ዋና...
25/08/2026

ነሐሴ 18/2018 (ወልቂጤ)
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ በ2019 በጀት ዓመት እቅድ ከፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዶ ሀሰን ጋር የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ዋና አስተዳዳሪው በግብ ስምምነቱ ወቅት እንዳሉት ህብረተሰብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተገቢው በፍጥነትና በጥራት ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ስራዎች ሊሰራ እንደሚገባ በመጠቆም በሁሉም ስራዎች ህዝቡን ማሳተፍና ባለቤት ማድረግ እንደሚገባ አስረድተዋል።

ተከታታይነት ያለው የፈፃሚ ማዘጋጃ መድረኮች ከመፍጠር ጀምሮ ውጤታማ የሆኑ ተግባራት መፈጸም እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ናስር ሀሰን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በወልቂጤ ከተማ በ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ የካፒታል ወጪ እየተገነባ ...
24/08/2026

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ናስር ሀሰን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በወልቂጤ ከተማ በ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ የካፒታል ወጪ እየተገነባ የሚገኘውን የአስተዳደር ህንፃ የምልከታ ስራ አከናወኑ።
የፕሮጀክቱ ዋና ዋና መረጃዎች፡
👉 በ2,000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ (B+G+9)ህንፃ የሆነ።
👉160 ቢሮዎች፣ 8 የስብሰባ አዳራሾች፣ ዳታ ማዕከል፣ ዲጂታል የእሳት አደጋ መከላከያ፣ 2 ዘመናዊ ሊፍቶች፣ የህፃናት ማቆያ፣ ካፊቴሪያዎች እና የአረንጓዴ ስፍራዎች (ግሪነሪ) ያሉት።
👉ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎችን የሚይዝ ዘመናዊ አዳራሽ ግንባታን ያካተተ ሲሆን።
አብዛኛው መሰረታዊ ስራው የተጠናቀቀው ይህ ህንፃ በተያዘው በጀት ዓመት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በመጪው አዲስ ዓመት አገልግሎት መስጠት ይጀምራል። ህንፃው ሲጠናቀቅ ተበታትነው የነበሩ የዞኑን መስሪያ ቤቶች በአንድ ማዕከል በማሰባሰብ የተገልጋዮችን እንግልት የሚቀንስ፤ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትንም የሚያዘመን ትልቅ ነው።

 #በጀትን ግልጽ ማድረግ፣ የህዝብን እምነት ማጠናከር ነው።ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ትክክለኛ የፋይናንስ አስተዳደር ለዘላቂ ልማት መሠረት ናቸው።
17/08/2026

#በጀትን ግልጽ ማድረግ፣ የህዝብን እምነት ማጠናከር ነው።
ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ትክክለኛ የፋይናንስ አስተዳደር ለዘላቂ ልማት መሠረት ናቸው።

በበጀት ዓመቱ ከ379ሺ በላይ ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል:-:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) (ሆሳዕና፣ሐምሌ 30/2018) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ም...
07/08/2026

በበጀት ዓመቱ ከ379ሺ በላይ ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል:-:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )

(ሆሳዕና፣ሐምሌ 30/2018) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በጉባኤው ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት
በበጀት ዓመቱ ከ379ሺ በላይ ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል።
በክልሉ ለዜጎች ዘላቂና አስተማማኝ የስራ ዕድል ለመፍጠር በየአካባቢው ያለውን እምቅ ሀብት እና ፀጋዎችን ለይቶ ወደ ተግባር መገባቱን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው ጠቁመዋል።

የዜጎች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በዕውቀት፤ በሥራ ፈጠራ ሀሳብና በክህሎት የተመራ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት መቻሉንም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።

በክልሉ ከ60ሺ በላይ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፈጠሩን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ከነዚህ ውስጥ 39 ሺ879 ወደ ቋሚ እንዲሸጋገሩ ተደርጓል፡፡

በየደረጃው የሰንበት ገበያዎችን ጨምሮ የባዛርና ኤግዝቢሽን ስራዎች ተግባራዊ መደረጉን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ለኢንተርፕራይዞች ከ1ነጥብ 4 ቢሊየን በላይ ብር የገበያ ትስስር ተፈጥሯል ብለዋል።

ኢንተርፕራይዞች ተኪ ምርት እንዲያመርቱ ድጋፍ ተደርጓል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ 210 ያህሉ 5354 ቶን በማምረት 19 ነጥብ 2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማዳን ስለመቻሉም ጠቁመዋል።

የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አቶ አብዶ ሀሰን: ዛሬ የምንተክላት አንዲት ችግኝ፣ የነገዋ ጥላ፣ የአየር ንፅህና እና ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፍ የህይወት ውርስ ናት።👉አንድ ችግኝ፡ ንጹህ አየ...
04/08/2026

የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አቶ አብዶ ሀሰን: ዛሬ የምንተክላት አንዲት ችግኝ፣ የነገዋ ጥላ፣ የአየር ንፅህና እና ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፍ የህይወት ውርስ ናት።
👉አንድ ችግኝ፡ ንጹህ አየር ይሰጠናል።
👉አንድ ችግኝ፡ የአፈር መሸርሸርን ይከላከላል።
👉አንድ ችግኝ፡ ለወፎችና ለተፈጥሮ ህይወት መጠለያ ይሆናል።
👉አንድ ችግኝ፡ የነገዋን አረንጓዴና ውብ ኢትዮጵያ ይገነባል።እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ ምድራችንን አረንጓዴ በማልበስ የተስፋችንን ፍሬ እንትከል በማለት መልዕክታቸው አስተላልፈዋል።

ችግኝ መትከል ለትውልድ የሚተላለፍ ሀብት ፣ሀገርን የመገንባትና የአካባቢን ሥነ-ምህዳር የማስጠበቅ ቁልፍ ተግባር  ነው፦አቶ ሙስጠፋ ኢሳሀምሌ 27/2018(ወልቂጤ)የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ...
03/08/2026

ችግኝ መትከል ለትውልድ የሚተላለፍ ሀብት ፣ሀገርን የመገንባትና የአካባቢን ሥነ-ምህዳር የማስጠበቅ ቁልፍ ተግባር ነው፦አቶ ሙስጠፋ ኢሳ

ሀምሌ 27/2018(ወልቂጤ)

የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የአስሁራና የዋርቢያ ቀበሌ ዞን አቀፍ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሂዷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳችግኝ መትከል ለትውልድ ጥሪትን እንደ ማስቀመጥና ሀገር የመገንባትም አንድ አካል ነው ብለዋ።

"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የ2018 ዓ.ም. አገራዊ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ችግኝ መትከል ለትውልድ የሚተላለፍ ሀብት በመሆኑ ሀገርን የመገንባትና የአካባቢን ሥነ-ምህዳር የማስጠበቅ ቁልፍ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

በለውጡ ሰባት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ከ47.6 ቢሊዮን በላይ ችግኞች በመተከላቸው የደን ሽፋንን ከማሳደግ ባሻገር ለምግብ፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለአካባቢ ጥበቃና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

ይህም ኢትዮጵያም በዓለም አቀፍ ደረጃ አዎንታዊ ገጽታ እንድትገነባ አስችሏል ብለዋል።

አቶ ሙስጠፋ ዘንድሮው የአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ግብ በሁሉም ዜጎች ንቁ ተሳትፎ እንዲሳካ ጥሪ በማቅረብ፣ ዛሬ የሚተከሉትን ችግኞች በአግባቡ በመንከባከብ የፕሮግራሙ ዘላቂ ውጤት እንዲረጋገጥ ሁሉም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ናስር ሀሰን በዞኑ በክረምት ወቅት 130 ሚሊየን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላቸው ችግኞች እየተተከሉ መሆኑን ገልጸው በዞኑ በዛሬው እለት በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ከ1 ሚሊየን 6 መቶ 70ሺ 79 ችግኞች በላይ ችግኞች እንደሚተከሉ ገልጿል።

ተስፋ እንትከል ሲባል የነገ ትውልድ ምርታማነትን፣ንጹህ አየርና የተስተካከለ መሬት መስጠት እንደማለት ነው ብለዋል።

አቶ ናስር አክለውም ዛሬ ችግኝ ከመትከል ባለፈ የማህብረሰቡ አንድነት ፣ፍቅርና አብሮነት የሚንጸባርቅበት ሁነት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የሚተከሉ ዘርፈ ብዙ ችግኞች የዜጎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸው አስገንዝበዋል።

የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ እንዳሉት ማሀበረሰቡ ደኖች በመጠበቅና በመንከባከብ አኩሪ ባህልና እሴት ያለው በመሆኑ እንደሀገር የሚደረገው የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ትውልድ ተሻጋሪ እንዲሆን የጎላ አስተዋፅኦ አድርጓል።

ባለፉት አመታት በተሰሩ ስራዎች የእዣ ወረዳን የደን ሽፋን 17 ነጥብ 2 ፐርሰንት ከነበረበት ወደ 24 ፐርሰንት ማድረስ ተችሏል ነው ያሉት።

በዘንድሮ አመትም 13 ነጥብ 36 ሚሊየን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተዘጋጅተው እየተተከሉ መሆኑ አስታውቀዋል አቶ ዘውዱ ።

በችግኝ ተከላው ያገኘናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉት በተከታታይ አመታት ችግኝ መትከላቸው ገልጸው እነዚህም የተጎዱ መሬቶቻቸው በመጠበቅና ለምግብ የሚሆኑ ችግኞችኝ በጓሮዋቸው እንዲኖሩ አስችለዋል።

ችግኝ መትከል ከጥንት አባቶቻችን የወረስነው ልምድ ነው ያሉት አርሶ አደሮቹ የተተከሉ ችግኞች ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፉ የእንከብ ስራው ላይ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

በመረሀ ግብሩ የክልል፣የዞን ፣የወረዳና የቀበሌው የስራ ኃላፊዎችና የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

Address

Wolkite
SNNPR

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurage Zone Finance Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share