08/09/2026
ኢትዮጵያ በጥቁር ህዝቦች ታሪክ ነጻነቷን እና ሉአላዊነቷን አረጋግጣ የቆየች ሀገር ናት:- አፈ ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ
(ሆሳዕና፣ጳጉሜ 3/2018)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት የጽናት ቀን በወልቂጤ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ከብዙ ሀገራት የቀደሙ የሀገረ መንግስት ግንባታ ታሪክ እንዳላት ተናግረዋል።
በጥቁር ህዝቦች ታሪክ ነጻነቷን እና ሉአላዊነቷን አረጋግጣ የቆየች ሀገር ስለመሆኗም ዋና አፈ ጉባኤዋ አብራርተዋል።
በተለያዩ ጊዜያት የተሞከሩ የውጭ ወረራዎችን በመመከት ነጻነቷን ያወጀች ሀገር መሆኗን ጠቁመዋል።
ምንም እንኳን ሀገራዊ ሉአላዊነታችንን አስጠብቀን ለረጅም ዘመን የቆየን ቢሆንም የኢኮኖሚ ነጻነታችንን ባለመስጠበቃችን ከድህነት ጋር አብረን ኖረናል ብለዋል።
የለውጡ መንግስት በርካታ ውስብስብ ፈተናዎችን እየተሻገረ አኩሪ ድሎችን እያስመዘገበ መሆኑን አፈ ጉባኤዋ አስረድተዋል።
የለውጡ መንግስት የአፍሪካውያን የጽናት ተምሳሌት መሆን ስለመቻሉ የገለጹት ዋና አፈ ጉባኤዋ ሀገራችን የተሟላ የኢኮኖሚ ሉአላዊነቷን እንድታረጋግጥ እየተጋ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።
ባለፉት ስምንት የለውጥ አመታት በሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ድሎች እየተመዘገቡ መሆኑን ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ አብራርተዋል።
የለውጡ መንግስት አህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ቀጠናዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በጽናት እየተሻገረ የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ከተስፋ ብርሀን ወደ ሚጨበጥ ብርሀን መሸጋገር ተችሏል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በሁሉም መስኮች እምርታዊ ለውጥ በማምጣት በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ ጠቁመዋል።
ልዩነቶችን በምክክር የመፍታት አዳዲስ ባህል እያዳበረች የመጣች ሀገር ስለመሆኗም ዋና አፈ ጉባኤዋ ጠቁመዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ የመሰረተ ልማት ማዘመን፣ የኮሪደር ልማት፣ የሌማት ትሩፋት፣ የአረንጓዴ አሸራ፣ የብሾፍቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ እና የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጅማሬዎች ጨምሮ በርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
እለቱን በማስመልከት ወታደራዊ ትርኢት እና መሰል ዝግጅት እየቀረበ ነው።
የክልሉ መንግስት ኮምኒኬሽን