04/09/2026
የማ/ኢ/ክ/መ/ዋና ኦዲተር መ/ቤት አመራርና ሰራኞች በ2018 በጀት አመት ዕቅድ ክንዉንና በ2019 ዓ.ም ጠቋሚ ዕቅድ ሪፖርት ዙሪያ ዉይይት አደረጉ፡፡
ማኢዋኦ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም. : የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2018 ዕቅድ አፈፃፀምና የ2019 ጠቋሚ ዕቅድ አስመልክቶ ዉይይት ያደረገ ሲሆን መደረኩን የመ/ቤቱ ም/ዋና ኦዲተር አቶ መሐመድ አብደላ መርተዋል፡፡
የዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2018 በጀት አመት አፈፃፀምና የቀጣይ አመት ጠቋሚ ዕቅድ በል/ዕ/በዘ/ክ/ዳይሬክቶሬት ዲይሬክተር ተወካይ አቶ ገነቱ ሲሻዉ የየስራ ክፍሎችን ክንዉንና በመ/ቤቱ እንደተቋም የተመዘገቡ ዉጤቶችን እንዲሁም የ2019 ዓ.ም. ዕቅድና ግቦችን ያመላከት ሪፖርት በዝርዝር አቅርበዋል፡፡በዚiህም የዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2018 በጀት አመት አጠቃለይ አፈፀፀም 94.15 % መሆኑንም ተገልጿል፡፡
በቀረበዉ ሪፖርት መነሻነት ተሳታፊ አመራርና ሰራተኞች ጥያቄና አስተያየት አቅርበዉ በም/ዋና ኦዲተር መሐመድ አብደላ ምላሽና ማብራሪያ እንዲሁም በቀጣይ አመት ከዚህ የተሸለ ዉጤት ለማስመዝገብ ተግቶ መስራት እንደሚገባ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዉ የዉይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡
ዘገባዉ የመ/ቤቱ ኮሙንኬሽንና ሚዲያ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነዉ፡፡