Gurage Zone Culture and Tourism

Gurage Zone Culture and Tourism የጉራጌ ዞን ባህላዊ እሴቶት ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሮአዊ የቱሪስት መስህቦች ይቃኙበታል።

02/08/2026
01/08/2026
01/08/2026
የጉራጌ ዞን ባህል እና ቱሪዝም መምሪያ  የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያና የ2019 ዓ.ም ዝግጅት ዙሪያ የምዘናና እና  የድጋፍና ክትትል ቡድኖች የስምሪት ኦረንቴሽን ተሰጠ። የጉራጌ ዞን ባህ...
31/07/2026

የጉራጌ ዞን ባህል እና ቱሪዝም መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያና የ2019 ዓ.ም ዝግጅት ዙሪያ የምዘናና እና የድጋፍና ክትትል ቡድኖች የስምሪት ኦረንቴሽን ተሰጠ።

የጉራጌ ዞን ባህል እና ቱሪዝም መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት በተቋሙ በታችኛው መዋቅር የተከናወኑ ሥራዎችን በጥልቀት በመገምገም፣ የ2019 ዓ.ም የተሻለ የአገልግሎት አፈጻጸም እንዲኖር ምዘና እንዲሁም ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ ቡድኖች የስምሪት ኦረንቴሽን ተሰጥቷል።
የመምሪያው ሀላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ በስምሪቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የሚደረገው ምዘናዊ ክትትል የበጀት ዓመቱ የተያዙ እቅዶች በተገቢው መንገድ መፈጸማቸውን፣ የአገልግሎት ጥራትን፣ ተደራሽነትን እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህ ምዘናና ድጋፍ ክትትል ሂደት የወረዳ ወይም የከተማ አስተዳደር የባህል ዘርፍ ልማት ፣ የቋንቋ ዘርፍ ልማት ፣ የቱሪዝም መስህብ ልማት እና የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማብቃት አፈጻጸምና የተቋማቶቹ አስተዳደር ዘርፎች መረጃን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በጥልቀት እንዲገመገሙ እና እንዲመዘኑ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በተጨማሪም በ2018 በጀት ዓመት የተመዘገቡ ጥንካሬዎችን በማጠናከር፣ የታዩ ክፍተቶችን በመለየትና ተግባራዊ የማሻሻያ ዕቅድ በማስደገፍ በ2019 በጀት ዓመት የተሻለ፣ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለማቅረብ እንዲቻል ምዘናና ድጋፍ መካሄድ እንዳለበት አሳስበዋል።

ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም

29/07/2026



የጉራጌ ዞን ንሟም ቱሪዝም መምሪያ ቡችር የርሟ ውኸርም የንመ በየ ምስራጀ ሸከተም በርቅ አሕብዶት ኣሑ ይቅየ

ከረ ኣሙስ መስሐሮ 23/11/18 ዘበር
ሰኣት ዋና 8 : 00 ቀነሰምታ
መደር የጉራጌ የርሟ ኣዳራሽ

በከረዌ ይትቀነዎ ምስራጀ

የወግ ምስ ይብር የርሟ ተውኔት
ችክምየ
የርሟ ዝምራ
የርሟ ጨዋዳ ድርስ ኣማማ
የመጣፍ ኣዎትም እንጓድም ብዘ ኣዝወነራቸም ያትመሮ ምስራጀ! ዝመሕኖም እንገድም ያዝወኖ ምስራጀ ኣስራጀነም ኣሑ ንቅየነ።

ኔሑ የሳርሑ ንሟሑ ኣትሐሐሮ

ያስራጀ የጉራጌ ዞን ንሟም ቱሪዝም መገኸቻ

✨ ! ✨

ለባህልና ጥበብ አፍቃሪያን በሙሉ!

የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ልዩ የባህል ምሽትና የኪነጥበብ ዝግጅት አዘጋጅቶ እርሶን ይጠብቃል።

📅 ቀን፡ሐሙስ፤ ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም
⏰ ሰዓት ከቀኑ 8:00 ጀምሮ
📍 ቦታ የጉራጌ ባህል ማዕከል አዳራሽ
🎭 በዕለቱ የሚቀርቡ ዝግጅቶች፡**

* የወግ ምስ** የተሰኘ ባህላዊ ተውኔት
* ግጥም

ባህላዊ ዜማዎች

* ባህላዊ ጨዋታዎች፣ሙዚቃዎች፣ውዝዋዜ
* የመጻሕፍት ግብዣ እና ሌሎች በርካታ አዝናኝና አስተማሪ ዝግጅቶች!እነዚህንና ሌሎችንም ድንቅ ዝግጅቶች አዘጋጅተን እርሶን እየጠበቅን እንገኛለን።

ይምጡ፣ ይደሰቱ፣ ባህልዎን ያንጸባርቁ!

አዘጋጅ፦የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ

መምሪያው በዞኑ ያሉ የቱሪዝም ጸጋዎችን በማስተዋወቅና መንግስትና ህዝብን በማገናኘት የዞኑ የልማት ጉዞ እንዲፋጠን በተያዘውም በጀት ዓመት አበክሮ ይሰራል ፦አቶ ሸምሱ አማንሀምሌ 21/2018(...
28/07/2026

መምሪያው በዞኑ ያሉ የቱሪዝም ጸጋዎችን በማስተዋወቅና መንግስትና ህዝብን በማገናኘት የዞኑ የልማት ጉዞ እንዲፋጠን በተያዘውም በጀት ዓመት አበክሮ ይሰራል ፦አቶ ሸምሱ አማን

ሀምሌ 21/2018(ወልቂጤ)

የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በጌታ ወረዳ የሚገኙ ውብ ጀፎረዎች፣ የዛራ ደን፣ ዋቻቢያ ፏፏቴና ሌሎችም የቱሪዝም ስፍራዎች ዞረው ጎብኝተዋል።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ አማን እንዳሉት መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች ቱሪዝም አንዱ ነው።

የሚዲያ ቱሩ በዞኑ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች በማስተዋወቅ ሌሎች እንዲጎበኙ ከማድረግ ባለፈ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ ፋይዳው የላቀ መሆኑን አብራርተዋል።

ዞናችን ከመልካኣ ምድራዊ አቀማመጡ ጀምሮ፣ የአየሩ ሁኔታ፣ የማህበረሰቡ የእንግዳ አቀባባልና በውስጡ የሚገኙ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ መስህቦች እጅግ ምቹና ማራኪ በመሆኑ ለጎብኚዎች ልዩ እድል ይፈጥራል ነው ያሉት አቶ ሸምሱ።

ጉራጌ ዞን በርካታ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ያሉ ሲሆን ጀፎረዎች፣ጥብቅ ደኖች፣ፋፋቴዎች፣ገዳማትና መስጂዶች ፣ዋሻዎች፣ጎጆ ቤቶች፣ፓርክና ሌሎችም እንዳሉ አስገንዝበዋል።

አቶ ሸምሱ አክለውም የገጠር ኮሪደር እሳቤ ምንጭ የሆነው የጉራጌ ጀፎረን ከሌሎች ሰው ተኮር ልማት ጋር በማስተሳሰር የበለጠ እንዲሰፋና እንዲዋብ እየተደረገ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል።

የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች በማስተዋወቅና በማልማት የኢኮኖሚ ማስገኛ እንዲሆኑ የበለጠ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የዞናችን የቱሪዝም ስፍራዎች አስፈላጊውን ነገር በመጠኑ እንኳን ከተሟላላቸው ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ኢኮኖሚ ማስገኘት የሚችሉ ናቸው ብለዋል።

ለዚህም የዞኑ ተቋማት፣ተወላጅ ባለሀብቶችና ግለሰቦች ሌላ አካባቢ ሂደው ከሚጎበኙ በዞኑ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ቢያዩ ደግሞ የዞኑን ቱሪዝም ማነቃቃት እንደሚቻል አስገንዝበዋል።

የዞኑ አስተዳደርም የማህበረሰቡ እሴቶች የመጠበቅና ለትውልድ እንዲተላለፉ በአጽንኦት እየሰራ ይገኛል በማለት የጉራጌ ክትፎ ፣ጀፎረና የጉራጌ ባህላዊ ጎጆ ቤት በዩኔስኮ እንዲመዘገብ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ።

እንደ አቶ ሸምሱ ገለጻ አብዛኞቹ የዞኑ የቱሪዝም ቦታዎች የመንገድ መሰረተ ልማቶች የተሟላላቸው መሆናቸው አመላክተው የበለጠ ደግሞ ሳቢ እና ምቹ እንዲሆኑ መስራት ይጠበቃል ነው ያሉት።

መምሪያውም በዞኑ ያሉ የቱሪዝም ጸጋዎችና የልማት ስራዎች በማስተዋወቅ የዞኑ ልማት እንዲፋጠን የበኩሉን ሲሰራ እንደነበር አስታውሰው በቀጣይም ተግባሩ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል አስታውቀዋል።

የጌታ ወረዳ ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ሰይፈ በወረዳው በርካታ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ የቱሪዝም መዳረሻዎች መኖራቸው ገልጸዋል።

የዛራ ደን ፣ፏፏቴዎች፣ጀፎሮዎች፣ዋሻዎች ጥንታዊ አብያተ ቤተክርስቲያንና መስጂዶች መኖራቸው አስታውቀው እነዚህም የማልማትና የማስተዋወቅ ስራዎች እየተሰራ ይገኛል።

የጌታ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቀድሩ ካሚል የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የሚዲያ ቱር በጌታ ወረዳ ጉብኝት ማድረጉ የወረዳው የቱሪዝም ዘርፉ እንዲነቃቃ የሚያደርግ ነው።

ጽ/ቤቱም የወረዳው የቱሪዝም ስፍራዎችን በሚዲያ የማስተዋወቅ ስራ እየሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ቀድሩ በቀጣይም የበለጠ እንዲተዋወቅ በሚዲያው ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በጉብኝቱ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊዎች፣ጠቅላላ ባለሙያዎች፣ የጌታ ወረዳ የሚመለከታቸው ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

የጉራጌ ዞን መንግስት ኣትራሕቦት መምሪያ የሜና ዳነም ሜነነ በጘታ ወረዳ ያነዎም የቱሪስት መደር ይርቅ ይትኸኸሮዪ ዦሮም ወዥ ቀነሶም።ኣምሬ 20/2018(ወርቕጤየ)በዞንዌ ያነዎ ቡችር ቡችር የ...
27/07/2026

የጉራጌ ዞን መንግስት ኣትራሕቦት መምሪያ የሜና ዳነም ሜነነ በጘታ ወረዳ ያነዎም የቱሪስት መደር ይርቅ ይትኸኸሮዪ ዦሮም ወዥ ቀነሶም።

ኣምሬ 20/2018(ወርቕጤየ)

በዞንዌ ያነዎ ቡችር ቡችር የቱሪስት መደር ባትኸኸሮት ሐልቅዌ ይትረጠቤ "የገን ሓሮትም የሚዲያ ቱር" ሜና ዋትባ ያሸ ቧሪም።

የጉራጌ ዞን መንግስት ኣትራሕቦት መምሪያ የሜና ዳነም ሜነነ በጘታ ወረዳ ያነዎም የቱሪስት መደር የሐሮ ዛራ የትቅየ ድብር፣ ዋቻቤያ ፏር፣ ቡችር ቡችር ጀፎረ ዦሮም ወዥ ቀነሶም።

በፕሮግራምዌ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኣትራሕቦት መምሪያ ቡር ዳነ ኣበቃጥ ሸምሱ ኣማን፣ የመምሪያዌ ይትኸተሮ ዳነ ኣበቃጥ ዱላ ወርቁ፣ የጘታ ወረዳ ባሕለንዳም ቱሪዝም ቢሮ ኣበቃጥ ሙሉጌታም እንጎድ የመምሪያዌም የወረዳዌ የመንግስት ኣትራሕቦት ቢሮ ሜነነ ተረከዎም።

እንኳን ደስ አላችሁ ፣እንኳን ደስ አለን!!የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ በክልሉ ካሉ መዋቅሮ የተሻለ አፈፃም በማስመዝገቡ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ!  ሐምሌ 16/2018 ዓ•ም(ወልቂጤ...
23/07/2026

እንኳን ደስ አላችሁ ፣እንኳን ደስ አለን!!

የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ በክልሉ ካሉ መዋቅሮ የተሻለ አፈፃም በማስመዝገቡ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ!

ሐምሌ 16/2018 ዓ•ም(ወልቂጤ)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ የ2018 ዓ.ም አመታዊ የዕቅድ አፈፀም ጉባኤ በዛሬው እለት በሆሳዕና ከተማ አካሄዷል።

ቢሮው ባካሄደው አመታዊ ጉባኤ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ በክልሉ ካሉ መዋቅሮች 2ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ የዋንጫና የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኖዋል።

የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት እንደምንሰራ ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።

የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ለተገኘው ውጤት አስተዋጽኦ የነበራቸውን የዞኑን አስተባባሪዎችና ሌሎች አመራሮችን እንዲሁም የወረዳና ከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላትን እያመሰገንን ፣በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን።

Address

Gurage
Wolkite
GOVERNMENTORGANIZATION

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
19:00 - 19:00
Tuesday 09:00 - 18:30
19:00 - 20:00
Wednesday 09:00 - 18:30
19:00 - 19:00
Thursday 09:00 - 18:30
19:00 - 20:00
Friday 09:00 - 18:30
19:00 - 20:00
Saturday 03:00 - 02:45

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurage Zone Culture and Tourism posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gurage Zone Culture and Tourism:

Shortcuts

Share