Wolkite University

Wolkite University this page will inform you about full structure, mission, vision, values, news, student's life and general activities of Wolkite University.

Wolkite University (WKU) is one of the third generation higher institutions that have been founded in 2012. it is established for the purpose of providing and promoting higher education learning, research and community outreach programs in the country in order to pour in for the realization of being among
middle income countries by 2020. the University is located in the Southern Nations Nationali

ties People Region, in Guraghe Zone, 158km southwest of the capital Addis Ababa. the plain landscape in which the University resides in is quite ideal for academic pursuit. It is situated at Gubreye sub-city of Wolkite town.

ዓለም አቀፍ የፍይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል*****ሐሙስ፣ ሚያዚያ 06/2018፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲበዩኒቨርሲቲያችን ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ስር ከሚገ...
14/05/2026

ዓለም አቀፍ የፍይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

*****

ሐሙስ፣ ሚያዚያ 06/2018፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

በዩኒቨርሲቲያችን ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ስር ከሚገኙ ትምህርት ክፍሎች የተውጣጡ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ዓመት ያሉ ተማሪዎች በስልጠናው እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ስልጠናውን ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን መምህር ብርሃኑ ተረዳ እንደገለፁት ተማሪዎች በዓለም አቀፍ የሂሳብ አያያዝና የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ በማሰብ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

አክለውም በዘመናዊው የሥራ ዓለም የሚፈለጉ ተግባራዊ የሙያ ክህሎቶችን ለማጎልበት ያለመ ስልጠና መሆኑንም አውስተዋል።

ይህ ተግባር ተኮር ስልጠና ከአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል በተመረጡ መምህራን አማካኝነት እየተሰጠ ሲሆን ለሁለት ተከታታይ ቀናትም ይቆያል።

ስልጠናው የተማሪዎችን ብቃት፣ በሂሳብ እና ፋይናንስ ዘርፍ ያላቸውን ሙያዊ ዝግጁነት እንደሚያጠናክር ተመላክቷል።

ስልጠናውን በትምህርት ዘመኑ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብር ከትምህርት ክፍላቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ 46 ተማሪዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

ለጥበብ እንተጋለን!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት!

ስለዩኒቨርሲቲያችን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ዌብሳይታችንን ይጎብኙ!

www.wku.edu.et

International Financial Reporting focused Training is being offered

*************

Thursday, May 14/2026 (WKU)

Our University's College of Business and Economics is providing training to students on International Financial Reporting Standards.

The college dean, Instructor Berhanu oppened the Program.

He depicted that the training was designed to increase students' awareness and to develop Graduates Practical Skills.

In the training, 46 students are participating.

It is given by Instructors from the Department of Accounting and Finance, and it stays for two Consecutive days.

We Strive for Wisdom!

Wolkite University Public and International Relations!

To know more anout us, visit our Website!

www.wku.edu.et

የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የላቀ ዉጤት ላስመዝግቡ ተማሪዎች እዉቅና ሰጠ*****************************************************************ረቡዕ፣ ግንቦት...
13/05/2026

የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የላቀ ዉጤት ላስመዝግቡ ተማሪዎች እዉቅና ሰጠ
*****************************************************************
ረቡዕ፣ ግንቦት 5/2018፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የላቀ ዉጤት ላስመዝግቡ 27 ተማሪዎች እዉቅና ሰጥቷል።

ፕሮግራሙን እንኳን ደህና መጣቹ በማለት ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን መምህር ብርሃኑ ተረዳ ሲሆኑ ጥሩ የሰራን ማበረታታት ተገቢ መሆኑን በመግለጽ ሌሎች ተማሪዎችም ፈለጋቸውን እንዲከተሉ አሳስበዋል።

አያይዘውም በፕሮግራሙ እውቅና ያገኙ ተማሪዎች የተሻለ ዝግጅት እንዲያደርጉ በማስቻል ለመውጫ ፈተና ውጤታማ እንዲሆኑ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

በመጨረሻም የእውቅና የማበረታቻ ፕሮግራሞች የሚቀጥሉ መሆኑ ከመድረኩ ለመረዳት ተችሏል።

ለጥበብ እንተጋለን!

የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት
ስለዩኒቨርሲቲያችን ተጨማሪ ለመረዳት ዌብሳይታችንን ይጎብኙ!

www.wku.edu.et

The College of Business and Economics recognized outstanding achievevers

Wednesday, May 13/2026 (WKU)

The Wolkite University College of Business and Economics has recognized 27 outstanding students.

The program was welcomed by Instructor Berehanu Tereda, Dean of College of Business and Economics, and he said that the Program was prepared to encourage hard workers.

He stated that the program was aimed to make students get ready for the exit exam.

It was eventually understood from the program that recognition will continue.

We strive for Wisdom!

Wolkite Umiversity Public and ilInternational Relation!

T konw more anout us, please visit our website!

www.wku.edu.et

ከትምህርት ክፍላቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ተሰጠግንቦት 4/2018 ዓ.ም////////////////////////////////////በ2018 የትምህርት ዘመን ከየትምህርት ክፍ...
12/05/2026

ከትምህርት ክፍላቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ተሰጠ

ግንቦት 4/2018 ዓ.ም

////////////////////////////////////

በ2018 የትምህርት ዘመን ከየትምህርት ክፍላቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና እና ማበረታቻ ተሰጥቷል።

እውቅና የመስጠት መርሃ ግብሩን የመማር ማስተማር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሀብቴ ዱላ መልዕክት በማስተላለፍ አስጀምረውታል።

በመልዕክታቸው ይህ የተመዘገበው ውጤት ለዓላማችሁ ጠንክራችሁ በመትጋታችሁ የመጣ ነው በማለት ተማሪዎችን አበረታተዋል።

አያይዘውም ሀገር ዛሬ በዩኒቨርሲቲ በመማር ላይ ካሉ ተማሪዎች የምትጠብቀው እውን እንዲሆን ይህንን ውጤት የሞራል ስንቅ በማድረግ አጠናክረው ሊያስቀጥሉ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የእውቅና መርሃ ግብሩ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ለመውጫ ፈተና ለመዘጋጀት እርስ በእርሳቸው እንዲተጋገዙ አደራ ብለዋል።

ይህ የእውቅና ፕሮግራም ሌሎች ተማሪዎችንም ለማበረታታት በማለም የተዘጋጀ እንደሆነ የገለፁት ም/ፕሬዝዳንቱ ለሌሎች አርዓያነታቸውም በመከተል የትብብር መንፈስ እንዲያጎለብቱ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ከየትምህርት ክፍሉ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 51 ተማሪዎች እውቅና በመስጠት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ለጥበብ እንተጋለን!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት!

ስለ ዩኒቨርሲቲያችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብሳይታችንን ይጎብኙ!

www.wku.edu.et

Recognition was granted to students who excelled in their Academic achievement

Tuesday, May 12/2026(WKU)

*///*///*///*///*///*///*///*///*///*///***///

Recognition and encouragement were given to students who excelled in their respective departments this academic year.

Dr. Habte Dula, Vice President for Academic Affairs, openned the program with message.

In his message, he encouraged students for their diligent dedication made to record higher grade.

He also advocated the achievements made exoected to be continue as the country is expecting more.

He stated as the program is held to accelarate the readiness of students for the exit exam.

He also stated the program was organized with the aim to encourage them to foster the spirit to build team work.

Finally, the program was winded up in recognizing 51 students who have achieved the highest marks from their espective department.

We Strive for Wisdom!

Wolkite University Public and International Relation!

To know more about us, please visit our website
www.wku.edu.et

የስራ አውደ ርዕይ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ                 በቅርብ ቀን!አርብ፣ ሚያዚያ 30/2018 ፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ           ለጥበብ እንተጋለን! Annual Job Fair ...
08/05/2026

የስራ አውደ ርዕይ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

በቅርብ ቀን!

አርብ፣ ሚያዚያ 30/2018 ፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

ለጥበብ እንተጋለን!

Annual Job Fair @ Wolkite University

Is Coming Soon!!

Friday, May 08/2026 (WKU)

We Strive for Wisdom!

የተቋማዊ ጥራት ኦዲት የአቅም ግንባታ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው       አርብ፣ ሚያዚያ 30/2018፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ*******************************************...
08/05/2026

የተቋማዊ ጥራት ኦዲት የአቅም ግንባታ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው

አርብ፣ ሚያዚያ 30/2018፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

***********************************************************************************************************************************

መርሃ ግብሩን የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር ሃብቴ ዱላ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ አስጀምረውታል።

ዶክተር ሃብቴ በመልዕክታቸው ሀገር እና ዓለም በሚፈልገው ፍጥነት በተጨባጭ ለውጥ የታጀበ ውጤት እንዲመጣ ከስልጠናው በኋላ በሙሉ አቅም ወደ ስራ እንዲገባ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ስልጠናው ከቁልፍ ተግባር አፈጻጸም ጋር የተዛመደ በመሆኑ ከዕውቅና፣ ተቋማዊና የፕሮግራም ኦዲት ስታንዳርድ ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል።

በስልጠናው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማዊ የጥራት ኦዲት መመሪያ፣ ስታንዳርድ፣ ጠቋሚዎች እና ተቋማዊ ግለ ግምገማን የተመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች መካተታቸውን ከተዘጋጀው መርሃ ግብር መረዳት ተችሏል።

ስልጠናውን የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጥራት ባለሙያ በሆኑት በአቶ ኡርጂ ሙሉጌታ እና በአቶ ጋሻውጠና አዳፍሬ በመሰጠት ላይ ነው።

ውጤታማ የውስጥ ጥራት ማረጋገጫ እና መጎልበቻ ስርዓት ለመዘርጋት የሚረዳው ይህ ስልጠና ለውጭ ጥራት ኦዲት ዝግጅት በእጅጉ እንደሚያግዝም ተገልጿል።

በስልጠናው ከየትምህርት ክፍሉ የተውጣጡ መምህራን እየተሳተፉ ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ተከታታተይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።

ለጥበብ እንተጋለን!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት

ስለ ዩኒቨርሲቲያችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብሳይታችንን ይጎብኙ!

www.wku.edu.et

______/////______/////______/////______/////______/////______/////
______/////______/////______/////______/////______/////______/////

Institutional Quality Audits Capacity building Training is going on

Friday, May 08/2026 (WKU)

***********************************************************************************************************************************

The program was opened by Dr. Habte Dula, Vice President for Academic Affairs, with a welcome message. In his message, Dr. Habte called to ensure change-accompanied outcome.

It was stated that the training is linked with accreditation, Institutional and Program audits to its standards.

The implementation is a function related to Key Performance Indicators. The Training includes topics related to the Institutional Quality Audit directives, Standardization and Institutional self-evaluation.
The training is being given by Mr. Urji Mulugeta and Mr. Gashawetena Adafre, quality experts of the Education and Training Authority Institutions of Higher education.

The program helps to develop Internal Quality assurance that would assist in the preparation of external Quality Audits. The Training is attended by Instructors from each Deprtments and it will continue for two consecutive days.

We Strive for Wisdom!

Wolkite University Public and International Relation!

To know more about us, please visit our website!

www.wku.edu.et

ለስልጠና ለተመደባችሁ የሬዚደንት ሐኪሞች የተላለፈ የምዝገባ ጥሪ        ሐሙስ፣ ሚያዚያ 29/2018 ፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
07/05/2026

ለስልጠና ለተመደባችሁ የሬዚደንት ሐኪሞች የተላለፈ የምዝገባ ጥሪ

ሐሙስ፣ ሚያዚያ 29/2018 ፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

በዩኒቨርሲቲያችን የካውንስል አባላት የ9 ወራት የስራ እቅድ አፈፃፀም ተገመገመ       ሐሙስ፣ ሚያዚያ 29/2018፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ**********************************...
07/05/2026

በዩኒቨርሲቲያችን የካውንስል አባላት የ9 ወራት የስራ እቅድ አፈፃፀም ተገመገመ

ሐሙስ፣ ሚያዚያ 29/2018፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

***************************************************************************************************************************************************

የዩኒቨርሲቲያችን የ9 ወራት የስራ አፈጻጸም የተሻለ ውጤት መመዝገቡ ተገለጸ።

የስራ አፈጻጸም ግምገማ መርሃ ግብሩን የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል በንግግር የከፈቱ ሲሆን የካውንስሉ አባላት በሪፖርቱ ግምገማ ሂደት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እና ገንቢ አስተያየት እንዲሰጡ ጋብዘዋል።

በመርሃ ግብሩ የተጠቃለለ የስራ ክፍሎች የ9ወራት አፈፃፀምን ጨምሮ የግንባታ ፕሮጀክት አፈጻጸም እና የዋቤ የንግድ እና ማማከር ኢንተርፕራይዝ የስራ አፈጻጸም በዝርዝር ቀርቧል።

የዋቤ ኢንተርፕራይዝ ወደ ስራ ከገባ ጀምሮ የተመዘገቡ መልካም ጎኖች እና በተስተዋሉ ክፍተቶች ዙሪያ የማስተካከያ ሃሳቦች ላይ ጥቆማ ተሰጥቷል።

በመማር ማስተማር ተግባራት አንዱ የሆነው የኬምስትሪ ትምህርት ክፍል ቻይና (ቤጂንግ) ሀገር ጋር በጋራ በመሆን በማቴሪያል ሳይንስ የሶስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ለማስጀመር የፍላጎት ዳሰሳ መጠናቀቁ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲያችን ልየታ መሰረት ያደረገ የስርዓተ ትምህርት ክለሳ ተግባራት በመሰራት ላይ መሆኑ በአበረታችነት ተገልጿል።

በሩብ ዓመቱ በመገንባት ላይ ያሉ 11 ፕሮጀክቶች አፈጻጸማቸው እያያደገ መምጣቱ ተመላክቷል ።

በመድረኩ በተለይ በያዝነው ዓመት ተመርቆ ወደ ስራ የገባው የአስተዳደር ህንጻ አፈጻጸም በጅምር ላይ ላሉ ፕሮጀክቶች በምሳሌነት ተነስቷል።

ማዕከላዊ ላብራቶሪ፣ አይሲቲ ህንጻ፣ የተማሪዎች ማደሪያ እና የቡታጅራ ስታፍ አፓርትመንት እና የፍሳሽ ማጣሪያ ተቋም በጥሩ አፈጻጸም ደረጃ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች መሆናቸውም ተጠቅሷል።

በመርሃ ግብሩ መማር ማስተማር፣ ምርምር ፣ በማህበረሰብ ከአገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በአስተዳደር እና ልማት ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች ቀርበዋል።

በኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተጀመሩ አዳዲስ አገልግሎቶች አበረታች ደረጃ ላይ መሆናቸውም ቀርቧል።

በተጨማሪም በዩኒቨርስቲው የተፈረሙ የመግባቢያ ስምምነቶች ውጤታማነት በጥንካሬ የሚገለጽ ተግባር መሆኑም ተመላክቷል። በመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎች በዘርፉ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

በመጨረሻም በሩብ ዓመቱ አፈፃፀም የተመዘገበው ውጤት ተስፋ ሰጪ መሆኑን የገለፁት የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት መሻሻል በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ማስተካከያ እንዲደረግባቸውም አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ለጥበብ እንተጋለን!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት!

ስለዩኒቨርሲቲያችን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ዌብሳይታችንን ይጎብኙ!

www.wku.edu.et

______/////______/////______/////______/////______/////______//////////

______/////______/////______/////______/////______/////______//////////

The implementation of a 9-month work plan was evaluated

Thursday, May 07/2026 (WKU)

***************************************************************************************************************************************************

It was revealed that our University's 9-month performance is being improved in its results. The Performance Review Program was opened by Dr. Farris Delil, the President of our University, and invited members of the Council to have active engagements in the discussion process.

The program includes 9 months of and project performances and a report progress of Wabe Business and Consulting Enterprise have been presented.

It is noted that a need assessment has been completed to launch a PHD degree program in material science in the Department of Chemistry, in collaboration with China (Beijing) University and Curriculum revision activities were a progressive achievements.

The performance of the Administration Building, which was inaugurated this has been raised as an example for the active eleven projects underway.

A Central Laboratory, ICT Building, Student Dormitory and Butajira Staff Apartment and Water treatment tasks are noted as well-performing projects.

In the program, achievements made in Academic, Research, Community Service and Technology Transfer and Administrative and Development tasks are presented.

It was also appreciated the new Services commenced at the Comprehensive Specialized Hospital were leveled as showing progress. It was also noted signed MoU was a function was strongly expressed. Questions raised by the forum were answered.

Finally, the University President stated that the performance was promising and he urged the council to keep up the progresses made.

We Strive for Wisdom!

Wolkite University Public and International

To know more about us, please visit our website

www.wku.edu.et

የዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች ከተማሪ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሄዱረቡዕ፣ ሚያዚያ 28/08/2018፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ******************************************...
06/05/2026

የዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች ከተማሪ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሄዱ
ረቡዕ፣ ሚያዚያ 28/08/2018፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

********************************************************************************************************************

በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል የተመራው የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ከተማሪ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ወይይት አካሄደዋል።

ውይይቱ በዋናነት በመማር ማስተማር እና በተማሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል ያለባቸው እና በጥንካሬ የሚገለጹ ነጥቦች እንዲሁም በተማሪዎች የእርስ በእርስ ውይይት መፈታት ያልተቻሉ ጉዳዮች ተነስተዋል። የተማሪ ተወካዮች እየተሰጡ ባሉ አገልግሎቶች ዙሪያ ያስተዋሏቸውን ክፍተቶች በዝርዝር አቅርበዋል።

ከነዚህም ከመማር ማስተማር ዘርፎ በተጨማሪ የተማሪዎች አገልግሎት ዘርፎች ማለትም የተማሪዎች ክሊኒክ፣ የመኝታ አገልግሎት፣ ምግብ እና ጠቅላላ አገልግሎት፣ በቤተ መጻሐፍት፣ በውኃ አቅርቦት፣ በስፖርት እና መዝናኛ እና በሌሎች ዘርፎች መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች በዝርዝር አንስተዋል።

ተወካዮቹ ዩኒቨርስቲው በጠንካራ ጎን የሚነሳበትን በተለይ ከመውጫ ፈተና ውጤት ጋር ተይይዞ እያሳየ ያለውን መልካም ውጤቶችን ለማስቀጠል ተጨማሪ ስራዎች መሰራት እንዳለበት ጥቆማ ተሰጥተዋል።

የትምህርት አሰጣጡ ምስለ ችሎት እና በቤተ ሙከራ መደገፉን ጨምሮ በቴክኖሎጂ አማካኝነት እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑ እና ዩኒቨርስቲው ከእድሜው በላይ እያከናወነ ያላቸው ተግባራት በአወንታዊ ጎኑ በውይይቱ ተነስቷል።

ተማሪዎቹ ከዚህ ቀደም በተደረጉ ውይይቶችም መሻሻሎች እንደታዩ ገልጸው፣ ነገር ግን አሁንም ገባ ተብለው ሊፈተሹ የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉም አንስተዋል።
አካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ የገጠሙ ችግሮች ከመሰረታቸው በመፈተሽ ቀጥተኛ የሆነ ማስተካከያ እንዲደረግባቸው የማስተካከያ የስራ መመሪያ በከፍተኛ አመራሩ የተሰጠ ሲሆን ለተግባራዊነታቸውም የቅርብ ክትትል እንደሚደረግባቸው በከፍተኛ አመራሩ ቃል ተገብቷል።

በዚህ ውይይት በዩኒቨርሲቲው ስኮላርሺፕ አግኝተው ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ያሉ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ሌሎች ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን መቀላቀል እንዲችሉ ስለዩኒቨርሲቲው መረጃዎችን ማግኘት በሚችሉበት ዙሪያ ሃሳብ ቀርቧል።

በውይይት መድረኩ ከፍተኛ አመራሩ እና የአገልግሎት ሰጪ የስራ ክፍል ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ለጥበብ እንተጋለን!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት!

ስለዩኒቨርሲቲያችን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ዌብሳይታችንን ይጎብኙ!

www.wku.edu.et

*********************///////////////********************///////////////*************************
*********************///////////////********************///////////////*************************

Higher Officials held Meeting with Student's Representatives

Wednesday, May 06/2026 (WKU)

***********************************************************************************************************************************

Our University Higher Officials led by Dr. Faris Delil, held discussions on various Topics with Students' Representatives.

During the discussion, Higher Officials held discussions with student representatives with issues not resolved in first round discussion of this Academic year.

In the discussion, the weak and strong of Academic and Service delivery matters have been indicated.

Higher Officials have provided clear directions on the details of the gaps pointed out during the discussion.

During the discussion, strong practices we had including high achievements on Exit Exam got special attention in the discussion.

The work being done on Technology and Laboratory support on Teaching and Learning delivery was encouraging.

In the discussion, both National and International Students have attended in the. Discussion and they requested full access information about us to get more potential International Students.

At last, clear direction was given to handle problems encountered both in Academic and Administrative matters and promising issues have been addressed.

We Strive for Wisdom!

Wolkite University Public and International Relation!

To know more about us, please visit our website!

www.wku.edu.et

የተግባራዊ ሳይንስ መር ስርዓተ ትምህርት ግምገማ ወርክሾፕ በመካሄድ ላይ ነው       ሰኞ፣ ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ********************ዩኒቨርሲቲያችን በተ...
04/05/2026

የተግባራዊ ሳይንስ መር ስርዓተ ትምህርት ግምገማ ወርክሾፕ በመካሄድ ላይ ነው

ሰኞ፣ ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
********************
ዩኒቨርሲቲያችን በተግባራዊ ሳይንስ ልየታ መሰረት በ5 ኮሌጆች የ33 የትምህርት ፕሮግራሞች ስርዓተ ትምህርት በመከለስ ላይ ይገኛል፡፡

በዛሬው እለት መካሄድ በጀመረው የስርዓተ ትምህርት ክለሳ የውስጥ ግምገማ መድረክ የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በመልዕክታቸው ዩኒቨርሲቲያችን የተግባራዊ ሳይንስ ምድብ ውስጥ እንደመሆኑ ስርዓተ ትምህርቱ ፡- ክህሎት ከተግባር ጋር በማጣመር፣ ገበያ መር በማድረግ እና ፍላጎትን መሰረት በማድረግ መከለስ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ስርዓተ ትምህርቱ አካታች ሀገር በቀል እውቀቶችን የቃኘ ሊሆን ይገባል ያሉት ፕሬዝዳንቱ የክለሳ ግምገማው በከፍተኛ ትኩረት መካሄድ እንዳለበት የአደራ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የመማር ማስተማር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሃብቴ ዱላ በስርዓተ ትምህርት ክለሳ ላይ ለተሳተፉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

አያይዘውም የግምገማ ስራው በትኩረት መሰራት እንደሚገባው እና በግምገማው የሚነሱ የማሻሻያ ሃሳቦች በሚገባ እንደሚካተቱ ገልጸዋል፡፡

የስርዓተ ትምህርት የኢንደሰትሪ እና የሙያ ማህበራትን እንዲያሳትፍ፣ የሀገር በቀል እውቀትን በማካተት፣ ከልየታ ጋር ማስማማት፣ ውጤት፣ ተግባር እና ፍላጎት ተኮር እንዲሆን፣ የባለ ድርሻ ተሳትፎ በማሳደግ፣ ከሀገር እና ገበያ ፍላጎት ጋር ስሙም መሆን እንዳለበት፣ ኢንተርንሺፕ እና ኤክስተርንሺፕን መያዝ፣ በጋራ ማስተማር፣ በቴክኖሎጂ መደገፍ፣ ማህበረሰብ ተኮር ማድረግን ጨምሮ አስፈላጊ ጉዳዮችን እንዲያካትት መደረግ እንዳለበት በመድረኩ ተጠቁሟል።

የስርዓተ ትምህርት ትግበራው ከሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ እውቅና ጋር ቁርኝት እንዲኖረው ማድረግም በመድረኩ ትኩረት ተሰጥቶታል።

ከትምህርት ክፍል ጀምሮ በውይይት ዳብረው ለግምገማ የቀረቡት ስርዓተ ትምህርቶቹ ከትምህርት ሚኒስቴር ማዕቀፎች እና በዩኒቨርሲቲያችን ሴኔት ሌጂስሌሽን ጋር ያላቸውን ስምምነት በመቃኘት ፍተሻው ሲጠናቀቅ ከውጭ የባለ ድርሻ አካላት ጋር በጋራ የሚገመገም ይሆናል። ዛሬ የጀመረው መርሃ ግብር ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል።

በስርዓተ ትምህርት ግምገማ ወርክሾፑ የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚደንት ዶክተር ፋሪስ ደሊልን ጨምሮ የማኔጅመንት፣ የሴኔት እና የካውንስል አባላት ተሳትፈዋል፡፡

ለጥበብ እንተጋለን!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት!

ስለ ዩኒቨርሲቲያችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብሳይታችንን ይጎብኙ!

Www.wku.edu.et

______/////______/////______/////______/////______/////______/////
______/////______/////______/////______/////______/////______/////

Applied Science Curriculum Validation workshop is underway

Monday, May 04/2026 (WKU)

Our University is revising the Curriculum of 33 Academic programs in 5 colleges based on the Applied Science University differentiation.

Dr. Faris Delil, the President of our University, delivered a message at the Internal Validation Workshop of the Curriculum Revision started today. According to his message, the Curriculum in Applied Science Category of our University needs to emphasize on skills in combination with practice, market orientation and demand driven approach.

The President also conveyed in message that the Curriculum should explore Inclusive Indigenous Knowledge and it should be conducted with great attention.

Vice President of Academic Affairs, Dr. Habte Dula, expressed his sincere appreciation to individuals involved in the Curriculum revision.

He also stated that the evaluation work should be done carefully and raised ideas by in the process of revision will be addressed properly.

In the forum it was pointed out that the Curriculum should involve Industry and Professional Associations, inclusion of Indigenous Knowledge, result, function and need oriented, increase stakeholder participation, it must include the needs of the Country and market, hold Internships, Co-teaching, Support with Technology, Community Oriented and include important issues.

The forum also emphasized that the implementation of the Curriculum should be linked with National and International recognition.

Starting from the department, the Curriculum will be evaluated together with the external stakeholders when the Validation is completed by surveying their agreement with the framework of the MoE and the senate legislation of our University.

The workshop was attended by the Management, Senate and Council Members including the President of our University, Dr. Faris Delil.

We Strive for Wisdom!

Wolkite University Public and International Relation!

To know more about us, please visit our website!

www.wku.edu.et

የስርዓተ ትምህርት ግምገማ ወርክሾፕ መካሄድ ጀመረ   ሰኞ፣ ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ******//******//******//******//******//******//*****...
04/05/2026

የስርዓተ ትምህርት ግምገማ ወርክሾፕ መካሄድ ጀመረ

ሰኞ፣ ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም፤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
******//******//******//******//******//******//******//******//
ዩኒቨርሲቲያችን በተግባራዊ ሳይንስ ልየታ መስረት የስርዓተ ትምህርት ክለሳ የውስጥ ግምገማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በስርዓተ ትምህርት ግምገማ ወርክሾፑ የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚደንት ዶክተር ፋሪስ ደሊልን ጨምሮ የማኔጅመንት፣ የሴኔት እና የካውንስል አባላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲያችን ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት 15 የተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ መሆኑ ይታወሳል።

ዝርዝሩን እንመለስበታለን!

ለጥበብ እንተጋለን!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት

ስለ ዩኒቨርሲቲያችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብሳይታችንን ይጎብኙ!
Www.wku.edu.et

Internal Curriculum Validation workshop is happening now
Monday, May 04/2026 (WKU)
************************************************************
Our University Internal Curriculum validation workshop is happening now.

Internal Curriculum Validation workshop that meets the mission of the Applied Science Universities differentiation is going on today.

At the Workshop, our University President, Dr. Faris Delil, Management team, Senate and Council members are participating.

Our University is one of the 15 Universities of Applied sciences in Ethiopia.

We will be back for the details!
We Strive for Wisdom!
Wolkite University Public and International Relation
To know more about us, please visit our website
www.wku.edu.et

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
02/05/2026

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ

Address

Ethiopia, CERS, Guraghe Zone
Wolkite

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolkite University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Wolkite University:

Share