Ye Yirgalem Lejoch - የይርጋዓለም ልጆች

Ye Yirgalem Lejoch - የይርጋዓለም ልጆች Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ye Yirgalem Lejoch - የይርጋዓለም ልጆች, Yirgalem.

ይህ ፎቶ በይርጋለም ራስ ደስታ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ በ1980 ዓ.ም. የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተወዳጇ እና አንጋፋዋ መምህርት ዘሪቱ ኩሞ ጋር የተነሱት ነው። በዚህ ፎቶ ላይ ያላችሁና...
02/05/2026

ይህ ፎቶ በይርጋለም ራስ ደስታ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ በ1980 ዓ.ም. የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተወዳጇ እና አንጋፋዋ መምህርት ዘሪቱ ኩሞ ጋር የተነሱት ነው። በዚህ ፎቶ ላይ ያላችሁና የምታውቋቸውን የይርጋለም ልጆች በኮሜንት አሳውቁን።

ይርጋለም – የሰላም መንፈስ የረበበባት ከተማ! ሰው አይደለም ከሌላው ከእራሱ ጋር  ይጋጫል ። በቡድን ተቧድኖ ይፋለማል። ጭራሽ ከተፈጥሮና ከፈጣሪው ጋር አምቧጓሮ ውስጥ ይገባል ። ይርጋለም ...
21/04/2026

ይርጋለም – የሰላም መንፈስ የረበበባት ከተማ!

ሰው አይደለም ከሌላው ከእራሱ ጋር ይጋጫል ። በቡድን ተቧድኖ ይፋለማል። ጭራሽ ከተፈጥሮና ከፈጣሪው ጋር አምቧጓሮ ውስጥ ይገባል ።

ይርጋለም በአንፃራዊነት የሰላም ከተማ ናት። ከግርግርና ሁካታ ለአፍታም ቢሆን ራቅ ብሎ አረፍ-ዘና፣ ሰብሰብ ብሎ ወደ ራስ ለመመለስ ይርጋለም ተመራጭ ናት።

ገና ሲፈጥራት ይርጋለም የተባለችበት ዋነኛ ምክንያትም ይኸው ነው ። ዓለም አቅሏን ስታ እንደ ዕብድ ውሻ ያገኘችውን ስትናከስ ነበር አባቶች ይርጋ ዓለም ብለዉ የሰየሟት ።

በእርግጥ ዛሬም ቢሆን ዓለም የሚሠራትን አሳጥቷታል ። ያገኘችውን አግበስብሳ፣ የሰው ደም አፍስሳ መርካት አቅቷታል። ከዚህ እብደቷ ለአፍታም ቢሆን ቆም ብላ እንድታስብ ዋናዎቿን ወደ ይርጋለም ብትልክ መልካም ነዉ። አርሴማ ሱባኤ ቢይዙ፣ አማኑኤልና ማርያም ቢፀበሉ፣ከሙስሊም አባቶች ጋር ዱአ ቢያደርጉ፣ ከቸርች መሪዎች ወንጌልን ቢያደምጡ፣ ከቦካሶ አባቶች ጋር ቢመክሩ፣ ገራንባ ወጥተዉ፣ ፉራ ተስተናግደዉ አረጋሽ ሎጅ አረፍ ብለዉ ቢመለሱ የሰላም መንፈስ ያድርባቸው ነበር።

ከተማችን ይርጋለም ለመላው ዓለም የማረጋጋት ብቃቷን ቀምራ ማጋራት አለባት። ይሄ አቅሟ ካሏት ውድ ሃብቶች ሁሉ የላቀ ነው ። ስለዚህ ውድ የሆነውን ሰላሟን ኤክስፓርት ለማድረግ መሰናዳት አለባት።

ይርጋለም ከተምሳሌትነቷ አልፋ ቀደምቶቿ ለሰላም፣ ለነፃነትና ለወንድማማችነት ሲሉ ዉድ መስዋዕትነት ከፍለዋል።

ይርጋለም ለመላው ዓለም ሰላም ከምታበረክታቸው ዋናዋና አስተዋፆዖዎች መካከል የእምነት ተቋማቶቿ ቱሩፋት፣ ባሕላዊ ሥርዓቶቿ፣ ተፈጥሯዊ ቦታዎቿ ናቸዉ።

ሰላም ይቻላል…ሰላም የሚጀምረውም በውስጣችን ነው። ከእራስ ጋር ዕርቅ ለማውረድ ይርጋለም ተመራጭ ናት!!!

ሞላ ዘይርጋለም

የይርጋለም አድባር፣ የብዙሃኑ አባት ጋሽ ካሳ ገብረየሰ ተለዩንዛሬ ይርጋለም ልቧ በሀዘን ተሰበረ፣ አንዱ ምሰሶዋ ፈረሰ! ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ታላላቅ አባቶቻችን ተራ በተራና በፍጥነት እየተለ...
24/02/2026

የይርጋለም አድባር፣ የብዙሃኑ አባት ጋሽ ካሳ ገብረየሰ ተለዩን

ዛሬ ይርጋለም ልቧ በሀዘን ተሰበረ፣ አንዱ ምሰሶዋ ፈረሰ!
ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ታላላቅ አባቶቻችን ተራ በተራና በፍጥነት እየተለዩን ነው። ይቺ ወርቃማ ከተማ የሥልጣኔ፣ የንግድ፣ የሥራና የታሪክ ምልክቶቿን እያጣች ነው።

ዛሬ ደግሞ አንድ የዓይናችን ማረፊያ፣ የዚህች ከተማ ተንቀሳቃሽ የታሪክ መዝገብ አጥታለች። የንግድ ጠቢቧን፣ የታታሪነት ምሳሌዋን፣ አለኝታዋንና መካሪ አባቷን ጋሽ ካሣ ገ/የስን ዛሬ ለዘላለም ተነጥቃለች።

ቤተሰባቸውን በፍቅር የሚንከባከቡ፣ ልጆቻቸውን ለቁምነገር የሚያበቁ አባቶች ብዙ ናቸው። ነገር ግን የሀገር ምሰሶ የሆኑ፣ ትውልድ የማይረሳውን ሥራ በደማቅ ቀለም የሚጽፉ የብዙሃን አባቶች በጣም አልፎ አልፎ የሚገኙ የሀገር ስጦታ ናቸው። ጋሽ ካሣ ከእነዚህ ልዩ ሰዎች አንዱ ነበሩ።

ለሀገራቸው፣ ለሕዝባቸውና ለቤተሰባቸው የፈፀሙት አንጸባራቂ ሥራዎቻቸው የታሪክ መዛግብትን ሞልተውታል። ለሕክምና ሲሉ ወደ ልጆቻቸው በሄዱበት ወደ ሚወዷት ይርጋለም ሳይመለሱ በዚያው ለማረፍ ተገደዋል።

ነገር ግን የይርጋለም ነዋሪዎች ይህን ከባድ ሀዘን መቋቋም ባለመቻላቸው፣ መኖሪያ ቤታቸውን በመሙላት ሀዘናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። የሀገር ሽማግሌዎች፣ የተለያዩ ሃይማኖት አባቶችም ተሰባስበው በመሰናበት ላይ ይገኛሉ።

የይርጋለም ቅድስት አርሴማ አስተዳደር መላዕከ ሕይወት ቀሲስ እንደሻው እንደገለጹልን፣ ዛሬ ሌሊቱን በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የፍትሃት መርሃግብር እንደሚካሄድ ጠቁመውናል።

ጋሽ ካሣ የሁሉም አባት፣
ይርጋለም ምንጊዜም አትረሳዎትም!

ነፍሶ በገነት ትረፍ፤ መልካም ተግባሮ ሁሌም በልባችን ደምቆ ይኖራል! 🙏🏾🕊️
ለቤተሰቦችዎ፣ ለዘመዶችዎና ለመላው የይርጋለም ሕዝብ እግዚአብሔር መጽናናትን ይስጥልን። ነፍስዎ በሰላም በገነት ትረፍ።

በዚህ አሳዛኝ ሰዓት ሀዘናችን ከእናንተ ጋር ነው !!!

ሞላ ዘይርጋለም

የይርጋአለም ልጆች ሴቶቹ በሙሉ                ፍቅራቸዉ መደኀኒት ልክ እንደጠበሉ።  ትቀመጥ ሃዋሳ እንዳአብከነከነች ሸገር እንዳአትመጣ ታጫረሰናለች። በ19 90 መላዉ ደቡብን በተለይ...
19/01/2026

የይርጋአለም ልጆች ሴቶቹ በሙሉ
ፍቅራቸዉ መደኀኒት ልክ እንደጠበሉ።


ትቀመጥ ሃዋሳ እንዳአብከነከነች
ሸገር እንዳአትመጣ ታጫረሰናለች።

በ19 90 መላዉ ደቡብን በተለይ የሃዋሳን ህዝብ ያስደመመ ምርጥ ዘፈን ነበር፣፣ ቢፈቀሩስ ምነዉ ቢወዱዱስ ምነዉ አብሮ ለቆየ ሰዉ ጨዋታቸዉ ማር ነዉ
እያለ ሲያቀነቅን የነበረዉ ፣ድምፃዊ ቴዎድሮስ ቪንቼንዞ
ዛሬ በጥቅምት በአል ተገናኝተን፣ ብዙ ተጫወትን ከቶታል ባንድ፣ እስከ ዮኒክ ፓርክ ፣ ታደሰ እንጆሪ ፣ ዉሎዉን አጫወተኝ በጊዜዉ በኖርኩ በደረስኩባችሁ የሚያስብል ደስ የሚል ያንን መልካም ዘመን፣ የአቺን ድንቅ ተወዳጅ ከተማን ሃዋሳን እያነሳ ብዙ ትዝታዉን አጫወተኝ ደስ ይላል ይህንን ዘፈን ዘፋኝ የምታስታውሱ ፣ የሃዋሳ ፣ የዲላ
ይርጋአለም ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ ሻሸመኔዎች መላዉ የኢትዮዽያ ህዝብ የታላችሁ????
ምንጭ:- ከ ማሚላ ሉቃስ የ ፌስቡክ ገፅ የተገኘ

 #ይርጋዓለም    | እንደ ሀገሬው ብሂል የበላህበትን ወጪት ሰባሪ የሄድክበትን መንገድ አትርሳ እንዲሉ በመስከረም ወር መባቻ ተፈጥሮ በጽጌረዳ ገበሬው በአዝመራ ተማሪው በትምህርቱ በአዲስ መ...
13/12/2025

#ይርጋዓለም

| እንደ ሀገሬው ብሂል የበላህበትን ወጪት ሰባሪ የሄድክበትን መንገድ አትርሳ እንዲሉ በመስከረም ወር መባቻ ተፈጥሮ በጽጌረዳ ገበሬው በአዝመራ ተማሪው በትምህርቱ በአዲስ መንፈስ አዲስ ተስፋ የሚሰንቅባት ሀገር ሲሏት አድባር አድባር ሲሏት ቢሂል በሆነች እንቁ ከተማ ይርጋለም ከመልካምነት መልካምነት ሚዛን የሚደፋባት የጥበብ በር ልዩ የፍቅር ከተማ ናት ብሎ ለመናገር ትላንት የኖሩባት ሰዎች ህያው ምስክር ናቸው ብል ማጋነን አይሆንብኝም።

ይርጋለም በታላቁ ሰው ራስ ደስታ ዳምጠው በ 1983 ዓ.ም ተቆረቆረች። እንደ ስሟ የረጋች ከተማ ወንዞችና ምንጮች የከበቧት ውብ ምድር በዙሪያዋ ያለው ለቁጥር በሚያዳግቱ ፈዋሽ ጸበሎቿና ለቱሪስት መስህብ በሆነው ፉልውሃዋ ፣ በተፈጥሮ ጫካና በርካታ ብርቅዬ አዕዋፋት መናገሻ የሆነው የአረጋሽ ሎጅ ፣ በዋሻ የተከበበ ቤተክርስቲያኗ አመት ሙሉ ከማይጠፋው ፍራፍሬዎቿ እና በአለም አቀፍ ተወዳጅ የሆነው ባለ ልዩ ጣዕም የሲዳማ ቡና ትታወቃለች።

ለጥበብ በተሰጡ በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ የታላላቆቹ እትብት መቀበሪያ ናት፡፡ የእነ ደበበ ሰይፉ፣ የእነ አብረሃም ረታ አለሙ፤ ታሪክ ነጋሪው ገነነ ሊብሮም ጨዋታ አዋቂ ልጆችን የያዘች ብዙ ጥበበኞችን በየፈርጁ ለአለም ያበረከተች ለምለምና ማህጸኗ የተባረከ የምድር ገነት ይርጋለም።

የቀድሞ የሲዳማ አውራጃ የሆነችው ይርጋዓለም ጊዜው በፈቀደላት የከተማ እና ኮሪደር ልማት ታግዛ የቀድሞ ዝናዋን ለመመለስ ደፋ ቀና እያለች ትገኛለች። ይህም ከተማዋ ካላት ተፈጥሯዊ ውበት የግብር ውጤት ጋር ታግዞ ቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ አድርጓታል ። በተለይም በከተማው ላይ ካለው ዘመናዊ አግሮ ኢንደስትሪ ፓርኮች የሀገር ውስጥና የውጪ ባለሀብቶች የተለያዩ ዘመናዊ የግብርና ውጤቶችን ለአለም ገበያ እያቀረቡ ይገኛሉ።

ማንኛውም ሰው በተፈጥሮ ሀብት ወደታደለችው ይርጋዓለም ለጉብኝትም ሆነ ለኢንቨስትመንት ቢመጣ ሀገሩ ባህል ዳዎኤ ቡሹ ( Dawoe Bushshu ) ብሎ ይቅበላችኋል።

ኑ ይርጋዓለምን ጎብኙ
ኑ ይርጋዓለም ላይ ኢንቨስት አርጉ

መላኩ ይርጋዓለም

Address

Yirgalem
YIRGALEM

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ye Yirgalem Lejoch - የይርጋዓለም ልጆች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share