08/09/2026
ለሀገር ስላም፤ ለሀገር ልማት ዳምቤ ከተማ ክረምት በጋራ በሚል መሪ ሀሳብ የከተማ ጽዳት ተካሄደ
ጳጉሜ 3/2018 ዓ.ም ዳምቤ — የዳምቤ ወረዳ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ከመንግሥት ጎን ለጎን በመቆም በወረዳው በበጎ አድራጎት ስራ ላይ በመሳተፍ በከተማው ውስጥ ለውስጥ በመዛወር የጽዳት ስራ አካሂደዋል።
ፖስተር ደገፈ ከሰሰ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ለዳምቤ ወረዳ ማህበረሰብ በአስተላለፈው መልዕክት የበጎ አድራጎት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንደአለበት ገለፃው እርስ በእርስ መተባበር መተጋገዝ ልጅ እናት አባቱን መክበር ተገቢ መሆኑ አስገንዝበዋል።
ፖስተር ደገፈ አክለውም በዕለቱ በተካሄደው የአምልኮ ሥነ-ሥርዓት ምዕመናን በጸሎትና በዝማሬ በመሳተፍ መንፈሳዊ በረከትን ተቀብለዋል። በመርሃ ግብሩም ለምዕመናን እምነታቸውን እንዲያጠናክሩ፣ በፍቅርና በአንድነት እንዲኖሩ የሚያበረታታ መልዕክት አስተላልፈው ከመንግስት በልማት ስራ መተባበር እንደአለበት ጠቅመዋል።
በአደባባይ በተደረገው የወንጌል ስብከት መርሃ ግብር ወረዳው በጸሎት አስቧል። በመርሃ ግብሩ ላይ የወንጌል ቃል ለተሰበሰቡ ምዕመናንና ሕዝቡ ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት እንዲጠብቁ አስተምህሮ ተሰጥቷል።
የተደረገው የወንጌል ስብከት ማኅበረሰቡ በእምነትና በመልካም ሥራ እንዲጸና፣ በሰላምና በመቻቻል እንዲኖር የሚያበረታታ መልዕክት አስተላልፏል።
በዚህ መሠረት ለአቅመ ደካማ፣ አካል ጉዳተኛ ፣ ወላጅ አልባ ህጻናት ለበዓል የልብስና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ የበጎ አድራጎት ስራ ሰርተዋል።
በመርሀ ግብሩ የተሳተፉ የከተማ መዘጋጃ ቤት ሀላፊ ገረሙ በየነ የወረዳው ሴቶች ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ሀልካነ ስልካ የተደረገው የበጎ አድራጎት ስራ የሚበረታታ መሆኑ ገልጸው ሌሎች የሀይማኖት ተቋምም አብዛኛው ሰው የሚገኝበት ስለሆነ ከመንግስት ጎን ለጎን በመቆም በሰላም ፣ በልማት እንዲሁም በበጎው አድራጎት ስራ መሳተፍ መልካም ስራ መሆኑ አስገንዝበዋል።