South Achefer Cooperative Office

South Achefer Cooperative Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from South Achefer Cooperative Office, Government Organization, Dubrovnik.

27/02/2026

የመሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበራት የአባላት መነሻ ቁጥር አወሳሰን
*
በኅብረት ሥራ ማበራት አዋጅ ቁጥር 985/2009 አንቀፅ 7 ንዑስ አንቀፅ 2 እና 3 እና በአንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 የተደነገገው
እንደተጠበቀ ሆኖ በማምረት ወይም አገልግሎት በመስጠት ወይም በማምርት እና አገልግሎት በመስጠት ተግባር ላይ የተሰማሩ ኅብረት ሥራ ማህበራት አባላት የመነሻ ቁጥር እንደሚከተሉትን ይሆናል፤

ሀ) በእንሰሳት እና እንሰሳት ተዋፅኦ የሚደራጁ የኅብረት ሥራ ማህበራት አባላት የመነሻ ቁጥር 80 ሰው ይሆናል፡፡
ለ) በሰብል እና የደን ውጤቶች የሚደራጁ የኅብረት ሥራ ማህበራት አባላት የመነሻ ቁጥር 100 ሰው ይሆናል፡፡
ሐ) በአከባቢ መሰረት አድረገው የሚደራጁ የሸማቾች የኅብረት ሥራ ማህበራት የአባላት የመነሻ ቁጥር 250 ሰው ይሆናል፡፡
መ) ተቋምን መሰረት አድረገው የሚደራጁ የሸማቾች የኅብረት ሥራ ማህበራት የአባላት የመነሻ ቁጥር 100 ይሆናል፡፡
ሠ) በአከባቢ መሰረት አድረገው የሚደራጁ በገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ሥራ ማህበራት የአባላት የመነሻ ቁጥር 100 ሰው
ይሆናል፡፡
ረ) ተቋምን መሰረት አድረገው የሚደራጁ በገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ሥራ ማህበራት የአባላት የመነሻ ቁጥር 80 ሰው
ይሆናል፡፡
ሰ) በመኖሪያ ቤቶች የኅብረት ሥራ ማህበራት የሚደራጁ አባላት የመነሻ ቁጥር በገጠር 50 በከተማ 24 ይሆናል፡፡
ሸ) የሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማህበራት የሚደራጁ አባላት የመነሻ ቁጥር 250 ይሆናል፡፡
ቀ) በአትክልትና ፍራፍሬ እና በመስኖ ሥራዎች ላይ የኅብረት ሥራ ማህበራት የሚደራጁ አባላት የመነሻ ቁጥር 50 ይሆናል፡፡
በ) የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ ሀብቶችን መሰረት አድርገው የሚደራጁ የኅብረት ሥራ ማህበራት ባለው ሀብት እና በአዋጭነት ጥናት መሰረት የመነሻ ቁጥሩን አግባብ ያለው ባለስልጣን ይስናል፡፡ ሆኖም መነሻ ቁጥሩ ከ10 ሰው ማነስ አይችልም፡፡

በዚህ አንቀጽአንቀጽ 49 ንኡስ አንቀጽ 1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ከአዋጅ 985/2009 አስቀድሞ የተደራጁ አባላት የመነሻ ቁጥር እንዳስፈላጊነቱ አዋጭነቱን መሰረት በማድረግ የአባላት ቁጥር እንዲጨምር አግባብ ያለው ባለስልጣን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፡፡

የደቡብ አቸፈር ወረዳ ህብረት ስራ ማህበራት ተ/ጽ/ቤት በራስ አገዝ ለሚደራጁ  የማህበረሰብ ክፍሎች  የግንዛቤ ፈጠራ  መድረክ አካሄደ::
04/02/2026

የደቡብ አቸፈር ወረዳ ህብረት ስራ ማህበራት ተ/ጽ/ቤት በራስ አገዝ ለሚደራጁ የማህበረሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ፈጠራ መድረክ አካሄደ::

ማስታወቂያ
03/02/2026

ማስታወቂያ

የአዊ ህዝብ ባህሉን ከልማት ጋር አጣጥሞ ከፈረስ ወደ ትራክተር ትርዒት ተሸጋግሯል*****የአዊ ህዝብ ከፈረስ ወደ ትራክተር መሸጋገሩ  የገጠር ትራንስፎርሜሽን ከኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ጋር...
31/01/2026

የአዊ ህዝብ ባህሉን ከልማት ጋር አጣጥሞ ከፈረስ ወደ ትራክተር ትርዒት ተሸጋግሯል
*****
የአዊ ህዝብ ከፈረስ ወደ ትራክተር መሸጋገሩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን ከኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ጋር እንዴት አስተሳስሮ መሄድ እንደሚቻል የሚያሳይ ግልፅ ምሳሌ ነው።

የትራክተር ትርኢቱ የሚያሳየው፣ አርሶ አደሩ ቴክኖሎጂን ተቀብሎ ምርታማነቱን ለማሳደግ ያለውን ፍላጎትና ብቃት ነው።

ትራክተር መጠቀም የጊዜን ኪሳራ ይቀንሳል፣ የሥራ ጫናን ያቃልላል፣ የመሬት አጠቃቀምን ያሻሽላል፣ በመጨረሻም የምርት መጠንንና ጥራትን ያሳድጋል።

ይህ መሸጋገር ብቻ የግብርና ቴክኖሎጂ ለውጥ ሳይሆን፣ የአስተሳሰብ ለውጥ መሆኑን ያሳያል።

ይህም ወጣቱ በእርሻ ዘርፍ ላይ እንዲሳተፍ፣ እርሻን እንደ ዘመናዊ የሥራ ዕድል እንዲያይ ያበረታታል።

በአጠቃላይ፣ ዛሬ በትራክተር ትርኢት የታየው፣ አንድ የእርሻ ማሽን ብቻ ሳይሆን፣ የአዊ አርሶ አደር ወደ ብልፅግና፣ ወደ ምርታማነት እና ወደ ተስፋ የሚጓዝበት መንገድ መታየቱ ነው።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገፅን በምንጭነት ተጠቀምን

Address

Dubrovnik

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Achefer Cooperative Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share