14/06/2024
ቱሪዝም በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራም ቅድሚያ ከተሰጣቸው ዘርፎች አንዱ እንደመሆኑ መሰረተ ልማትን እና አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል ብሎም በዘርፉ ልምድን ማዳበር ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫ ነው። ብዛት ያላቸው ብሔራዊ ፓርኮች እና የዱር እንስሳት ሃብት ባላት ሀገራችን የሳፋሪ ልምምድን ማስፋፋት ቱሪስቶችን ለመሳብ ወሳኝ ተግባር ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በየካቲት 2016 የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ100 ቀናት ግምገማ ወቅት ለቱሪዝም አገልግሎት የሚሰጡ የሳፋሪ ተሽከርካሪዎች እንዲመረቱ ለኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሰጡትን አቅጣጫ ተከትሎ ኢንደስትሪ ሚኒስቴር በሀገር ውስጥ ለሳፋሪ አገልግሎት ተሽከርካሪነት የተቀየሩ ባለአንድ ጋቢና ፒክ አፕ መኪናዎችን በናሙናነት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስረክቧል። መኪናዎቹን ለሳፋሪ አገልግሎት እንዲመቹ አድርጎ በመለወጥ ሂደት ውስጥ አምራቾች በሀገር ውስጥ በስፋት የመለወጥ ልምድ እና አቅም ለማዳበር ችለዋል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ወቅት በምርት ስራው የተሳተፉና አቅም ያላቸው አምራቾች የምርት ስራውን ሂደት እንዲያስፋፉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
As tourism is one of the priority sectors identified through Ethiopia’s home grown economic reform program, enhancing facilities, services and experiences is a key area of intervention. With many national parks filled with natural and wildlife endowments, safari experiences are key to attracting tourists.
Further to the direction set by the Prime Minister to the Ministry of Industry in the March 2024 100-day Council of Ministers evaluation for the production of safari cars, the Ministry of Industry today handed over to the Office of the Prime Minister, the sample single pick-up cars that have been converted into safari cars locally. Through this conversion process, local manufacturers have gained the experience to mass convert these cars to meet local demand. In the course of the handover ceremony, Prime Minister Abiy Ahmed directed those engaged in the production with pertinent inputs on scaling up the production process.