Merawi Town industry and Investment office

Merawi Town industry and Investment office +251583301188

23/04/2026

የክልላችን ተስፋ!!!
ዓባይ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ🥀🥀🥀

የከተማ መሬት ሊዝ ጨረታ ከመርዓዊ ከተማ
23/04/2026

የከተማ መሬት ሊዝ ጨረታ
ከመርዓዊ ከተማ

የነገን ትውልድ ታሳቤ ያደረገ አሠራር 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
20/04/2026

የነገን ትውልድ ታሳቤ ያደረገ አሠራር 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

15/04/2026

"ባለፋት ዘጠኝ ወራት የአሻጋሪ የልማት እቅዱን የሚያሳኩ በርካታ ስትራቴጂክና ቁልፍ ተግባራትን በስኬት ፈፅመናል"
አቶ ተፈሪ ታረቀኝ
የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ
************************************************************
ባህርዳር: ሚያዚያ 07/2018 ዓ.ም (ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ)

የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት የስራ አፈጻጸሙን ም/ቢሮ ኃላፊዎቹ በተገኙበት ከተቋሙ ጠቅላላ ሰራተኞች ጋር እየገመገመ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው የኢንዱስትሪ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ ታረቀኝ እንደገለፁት በአሻጋሪ የልማት እቅዱ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቀዳሚ ትኩረት የተሰጠው ዘርፍ እንደመሆኑ በጊዜ የተከፋፈለና ከሌሎች ተቋማት ጋር ተናባቢ እቅድ አቅደን ወደ ተግባር ገብተናል። በየሩብ አመቱ አፈፃፀማችን እየገመገምን ከዚህ መድረሳችን ገልፀው ባለፉት 9 ወራት ውጤታማ ድጋፍና ክትትል በማድረግ አሻጋሪ የልማት ግቡን የሚያሳኩ በርካታ ስትራቴጂክና ቁልፍ ተግባራት በስኬት መፈፀማቸውን ገልፀዋል ።
ኃላፊው አክለውም በአንፃራዊነት በዚህ በጀት አመት ባደረግነው ጥብቅ የክትትልና ድጋፍ ስራ ከፍተኛ ካፒታል ያስመዘገቡ ግዙፍና አዳዲስ ባለሀብቶችን መሳብ፣ አዳዲስ የአምራችና ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን በአዲስ አስመርቆ ወደ ስራ በማስገባት፣ ምርት ያቋረጡትንና በምርት ላይ ያሉትን ችግራቸውን የለየ ድጋፍ በመደገፍ፣ በኤክስፖርትና ተኪ ምርት ፣ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባትና ሊወጣ የነበረን የምንዛሬ ወጭ በማስቀረት ብሎም ሰፊ የሆነ የስራ ዕድል ለማህበረሰባችን በመፍጠር አበረታች ስኬቶች ቢሮው ማስመዝገቡን ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም በዚህ በጀት አመት የነበረው ጥብቅ የሆነ የአመራርና የባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል ስርዓት በቀጣይ ከሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ በፊት በማጠናከር፣ ከቅንጅት፣ ከተግባርና መረጃ ጥራት አንፃር አሁንም የሚስተዋሉ ጉድለቶች በማረም የጀመርነውን አገልግሎት አሰጣጣችን በማዘመንና በማጠናከር ብሎም በቀሪ ወራት በምናሻሽላቸው ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ተወያይተን የጋራ መግባባት በመፍጠር በስኬት የበጀት አመቱን ግቦች በሚያሳካ መልኩ መፈፀም ይጠበቅብናል በማለት ወይይቱን በይፋ አስጀምረዋል፣
በቢሮው የእቅድና በጀት ድጋፍና ክትትል ባለሙያ አቶ ይልቃል ጌታነህ አማካኝነት የ9 ወር የስራ አፈፃፀም ሪፓርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ይገኛል ።

ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook- https://www.facebook.com/investamhara?mibextid=ZbWKwL
Website- http://www.investinamhara.gov.et/
YouTube- youtube.com/channel/UCRKHHaX4S9KHqNVhLAt1bkg
WhatsApp- https://whatsapp.com/channel/0029Vb769KiHrDZb8EXzee0L
Twitter- https://x.com/amhara_and77292

የገቢ ግብር ነጻ መብት ተፈቀደበነጻ የንግድ ቀጠና ውስጥ ተሰማርተው ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርቡ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ መፈቀዱን የገንዘብ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡የገንዘብ ሚኒስቴር...
13/04/2026

የገቢ ግብር ነጻ መብት ተፈቀደ

በነጻ የንግድ ቀጠና ውስጥ ተሰማርተው ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርቡ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ መፈቀዱን የገንዘብ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ይንን የተመለከተውን ደብዳቤ ለገቢዎች ሚኒስቴር እና ለኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጽፏል፡፡

የካፒታል እጥረት፤ የግብአት አቅርቦት ችግር እና የባለሙያ እጥረት የኢንዱስትሪ ልማት በሚፈለገው መጠን እንዳያድግ ምክንያት ከሆኑት መካከል በዋንኛነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ሲል ሚኒሰቴር መ/ቤቱ ጠቅሷል፡፡

በዚህም መሰረት ግብአቶች እና ሌሎችም ምርቶች በበቂ መጠን ለገበያ እንዲቀርቡ ለማድረግ አስመጪዎች ምርቱን ለገበያ ከማቅረባቸው በፊት የሚከፍሉት ቀረጥ እና ታክስ ውስን የሆነውን ካፒታላቸውን በመያዝ ረገድ የሚያሳድረባቸውን ጫና ማቃለል ያስፈልጋል ሰልም አስረድቷል።

በእነዚህ ምክንያቶች አስመጪዎች ግብቶችን እና ምርቶችን ቀረጥ እና ታክስ ሳይከፍሉ ወደ አገር አስገብተው ለግብአቱ ወይም ለምርቱ ገበያ ባገኙ ጊዜ ቀረጥ እና ታክሱን የሚከፍሉበትን አሰራር የሚፈቅድ የነጻ የንግድ ቀጠና አሰራር ተዘርግቷል፤ ይህንን ስርአት የሚያስፈጸሙ ነጻ የንግድ ቀጠናዎች በየካባቢው መቋቋመቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መሆኑ አስታውሷል::

እነዚህ ነጻ የንግድ ቀጠናዎች ባለሃብቶችን የበለጠ የሚሰቡ እንዲሆኑ ለማድረግ ከላይ ከተገለጸው በተጨማሪ በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ውስጥ ተሰማርተው ግብአቶችን እና ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተፈቅዷል ተብሏል።

ስለዚህ ባለሃብቶች ይህንን እድል በመጠቀም በነጻ የንግድ ቀጠናዎች ውስጥ እንዲሰማሩ ሚኒስቴር መ/ቤቱ አሳስቧል፡፡
ምንጭ ➩(ድሪ ቲዩብ)

‎        🌻🌻💐💐💐🌻🌻‎        🌻🌺   እንኳን   🌺🌻‎        🌻🌹አደረሳችሁ🌹🌻‎         🌻🌻🌾🌾🌾🌻🌻‎‎👉ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ፣‎👉በከተማችን  በማልማት ላይ ለ...
10/04/2026

‎ 🌻🌻💐💐💐🌻🌻
‎ 🌻🌺 እንኳን 🌺🌻
‎ 🌻🌹አደረሳችሁ🌹🌻
‎ 🌻🌻🌾🌾🌾🌻🌻

‎👉ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ፣
‎👉በከተማችን በማልማት ላይ ለምትገኙ፣
‎👉 በቅድመ ግንባታ ደረጃ እና የማልማት ፍላጎት ላላችሁ ልማታዊ ባለሃብቶች በሙሉ እንኳን ለ2018 ዓ/ም ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ !!!

‎በዓሉ በኢትዮጵያዊ አብሮነት የመተሳሰብና የደስታ በዓል እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።

‎(የመርዓዊ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት)

‎🥀መርዓዊ ,ሚያዚያ- 02-2018 ዓ/ም🥀

የብዙ ባለሃብቶች እና የህዝባችን መልካም ዜና ነው። የሃይል እጥረትና መቆራረጡን እንደሚፈታ ተስፋ አለን።
04/04/2026

የብዙ ባለሃብቶች እና የህዝባችን መልካም ዜና ነው። የሃይል እጥረትና መቆራረጡን እንደሚፈታ ተስፋ አለን።

አዴቶች እንኳን ደስ አላችሁ 🇪🇹
03/04/2026

አዴቶች እንኳን ደስ አላችሁ 🇪🇹

29/03/2026

ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት!!!
የማጠቃለያ መድረክ
ሰሜን ጎጃም
ባህርዳር
መጋቢት 20, 2018 "ዓ/ም

20/03/2026

የመርዓዊ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ብርሀኑ አበረ 1447ኛውን የዒድ አል-ፈጥር በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️
​ መጋቢት 11/2018 ዓ.ም(መርዓዊ ኮሙኒኬሽን) "ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር ያለው የቆየ የአብሮነትና የመከባበር እሴት ለከተማችን ሰላም መሰረት ነው" ያሉት ከንቲባው ዒድ የአብሮነትና የሰላም ተምሳሌት መሆኑን ገልፀዋል።

በዓሉ ሲከበር ካለፈው ወር የተገኘውን የትዕግስትና የደግነት ትምህርት ወደ ተግባር በመቀየር፣ የታመሙትን በመጠየቅና ያጡትን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ለመላው የእምነቱ ተከታዮችና ለከተማው ነዋሪዎች በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣የደስታና የብልጽግና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

12/03/2026

በመርዓዊ ከተማ አስተዳደር የከተማ ቦታ ወስደው ግንባታ ያልጀመሩ ግለሰቦች ወደ ሥራ እንዲገቡ ጥሪ ቀረበ።
✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️
​ መጋቢት 02/2018 ዓ.ም (መርዓዊ ኮሙኒኬሽን) በሰሜን ጎጃም ዞን የመርዓዊ ከተማ አስተዳደር በምደባና በሊዝ ጨረታ የከተማ ቦታ ወስደው እስካሁን ግንባታ ያልጀመሩ ባለመብቶች በአስቸኳይ ወደ ግንባታ እንዲገቡ አሳስቧል።

​የከተማው መሠረተ ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳኛቸው በሬ እንደገለጹት ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ የከተማ ቦታ ወስደው ግንባታ ያልጀመሩ፣ እንዲሁም ጀምረው ያቋረጡ ግለሰቦችን የመለየት ሥራ ተጠናቆ መረጃው ተለይቶ ተይዟል።
​ኃላፊው አክለውም ማንኛውም ባለመብት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በገባው ውል መሠረት ግንባታውን የመጀመር ወይም የማጠናቀቅ ግዴታ እንዳለበት አሳስበዋል።

ይህንን ጥሪ ተቀብለው ወደ ተግባር በማይገቡ አካላት ላይ ግን በመመሪያ ቁጥር 1/2005 መሠረት አስፈላጊው ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል።
​ይህ እርምጃ የከተማዋን መሠረተ ልማት ለማፋጠንና የታጠሩ ባዶ ቦታዎች ለልማት እንቅፋት እንዳይሆኑ የታለመ መሆኑም ተገልጿል።

07/03/2026

Indirizzo

Milan

Telefono

+251918070993

Sito Web

Notifiche

Lasciando la tua email puoi essere il primo a sapere quando Merawi Town industry and Investment office pubblica notizie e promozioni. Il tuo indirizzo email non verrà utilizzato per nessun altro scopo e potrai annullare l'iscrizione in qualsiasi momento.

Condividi