Debark people

Debark people Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Debark people, Naro9@gmail. com, Debark'.

ሰላም ለኪ🙏
18/10/2025

ሰላም ለኪ🙏

19/09/2025

ጦርነት ስልችት አለኝ: ወደ ቀድሞ መች ነዉ የምንመለሰዉ?
በጦርነት ምክንያት የምዎዳቸዉን ሳላይ አስር ዓመት ሊሆነኝ ነዉ። ከጥቅሙ ጉዳቱ ለሚበልጥ ጦርነት እስኪ ወደ ሠላም ቀይሩልን! ከምሬ ነዉ ደብሮኛል ። መምጣት ፈልጋለሁ ለኔ ስትሉ ፍቅር አዉርዱ🤭

[የኔ] የአመቱ ሰዎች______ባለፉት ሁለት ዓመታት የዓመቱ ሰው (Person of the Year) የምለውን ሰው ሳሳውቅ ቆይቻለሁ፣ በዚህ ዓመትም እንዲያልፈለኝ አልፈለኩም፣ "ምርጥ" የምትለዋ...
14/09/2025

[የኔ] የአመቱ ሰዎች______

ባለፉት ሁለት ዓመታት የዓመቱ ሰው (Person of the Year) የምለውን ሰው ሳሳውቅ ቆይቻለሁ፣ በዚህ ዓመትም እንዲያልፈለኝ አልፈለኩም፣ "ምርጥ" የምትለዋን ቃል ያልከተትኳት በምክንያት ነው፣ በአቋሙ የማይስማሙትንም ለማካተት ነው፣ ወደ ዝርዝሩ ልለፍ፣ ዘርፍ አለው፣

የአመቱ ፖለቲከኛ:- Jawar Mohammed

እዚህ ላይ ብዥታ የሚኖር አይመስለኝም፣ ባሳለፍነው አመት የተቃውሞውን ጎራ መልክ በማስያዝ ሁለትና ሶስት ደርጃ ከፍ አድርጎታል፣ ጃዋር መስራት ያለበትን ነገር ብቻ ሳይሆን መሰራት ያለባቸውን ነገሮች ቅደም ተከተል ጠንቅቆ የሚያውቅ እጅግ በሳል ሰው ነው፣ እንደኔ አረዳድ ጃዋር መሐመድ ባለፈው አመት ትኩረት አድርጎ የሰራው ስርዓቱን ከኦሮሞ ህዝብ መለየት ላይ ነው፣ ተሳክቶለታል፣ የተቃውሞውን ጎራ አርሞታል፣ ስድስት ዓመት ሙሉ "የኦሮሙማ መንግስት" እያለ ሲይንቋርር የነበረውን የተቃዋሚ ጎራ ፀጥ ብሏል፣ አንድን ስርዓት ከአንድ ህዝብ ጋር አገናኝቶ የሚነሳ ትግል አደገኛ ብቻ ሳይሆን የትም አይደርስም፣ የሚጠቅመው ገዥውን ቡድን ብቻ ነው፣ ገዥው ቡድን ይፈለገው ነበር፣ ጃዋር ይህን በመቀየር ትግሉን ወደ ፊት ብዙ እርምጃ አስፈንጥሮታል፣

የአመቱ ሀተታ አዘጋጅና አቅራቢ:- Yayesew Shimelis

ያየሰው ሽመልስ ጋር በአንዳንድ ነገሮች አልስማም፣ ለወያኔ ያለው ስስ ልብ አውራ ወያኔዎችን ጭምር ግር የሚያሰኝ ይመስለኛል፣ ያም ሆኖ የልጁን የጋዜጠኝነት አቅም መካድ ራስን ትዝብት ውስጥ ይከታል፣ ያየሰው በውስን ሀብትና የሰው ኃይል እየሰራውን ያለውን ስራ በተቋም ደረጃ ሊሰራ መቻሉን እርግጠኛ አይደለሁም፣ ተሰርቶ አላየነሁም፣ ከብዙ ነገሩ audiovisual ፋይሎችን ሰንዶ የሚያስቀምጥበት መንገድና ሲፈልጋቸው የሚያወጣበት ፍጥነት ያስደምመኛል፣

የአመቱ አጋፋሪ:- Moges Zewdu Teshome

የሀሳብ ገበታ የኢትዮጵያ media landscape ውስጥ የራሷን ቦታ ፈልጋ ያገኝች ወይም የፈጠረች፣ የራሷን quadrant አጥራ የተቀመጠች ሚዲያ ናት፣ በይዘትና በጥራት ራሷን እያበቃች ወደ 100 ሺህ የሚጠጋ subscribers ለማፍራት በቅታለች፣ ለዚህ ደግሞ ሞገስ (ስነ-ኢየሱስ) ትልቁን ድርሻ ይወስዳልጽ

[ስነ] ጭብጥና እንግዳ መረጣው ይሳካለታል፣ መድርክ ማጋፈሩንም ችሎበታል፣ ይህ በየቀኑ እያደገና እየተሻሻለ የመጣ ክህሎት ነው፣ በግሉ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚደረገ ሰጥ- አገባ እንዲያርም እግረ መንገዴን መጠቆም እፈልጋለሁ፣

የአመቱ የኪነጥበብ ፕሮግራም አዘጋጅ:- Teborne Beyene

አንድ ሰው ተቦርነን የኢትዮጵያ ኪነጥበብ ታሪክ ማህደር ነው ሲል ሰምቼዋለሁ፣ የሚበዛበት አይመስለኝም፣ የኢትዮጵያን ሙዚቃ የተመለከተ ማንኛውም ነገር ላይ go to person የሚባል ሰው ነው፣ ተቦርነን የአመቱ ሰው ያስባለው ባለፈው ዓመት ከአበበ መለሰ ጋር ለከተታታይ ሳምንታት የሰራው ፕሮግራም ነው፣ ለአበበ ሀውልት አቁሞለታል፣ እግረ መንገዱን የራሱን masterpiece አስቀምጧል፣ ለሌሎች መማሪያ መሆን ይችላል፣

የአመቱ የማህበረሰብ አንቂ:- Getahun Heramo

“We are caught in an inescapable network of mutuality, tied in a single garment of destiny. Whatever affects one directly, affects all indirectly.” ብሏል አሉ ማርቲን ሉተር ኪንግ፣ ይህ እጥር ምጥን ባለ አገላለጽ ወደ አማርኛ ብንመልሰው "ያንተ ቤት ሲንኳኳ ይሰማል እኔ ቤት" የሚል ነገር ይወጣታል፣ ይህ ያልገባው ሰው በምን አገባኝ ስሜት ሀገርና ትውልድ ሲጠፋ ዳር ሆኖ ይመለከታል፣ ጌታሁን ግን እንደዛ አይንት ሰው አይደለም፣ ሌላ ቦታ የሚንኳኳው ነገር እሱን የረብሸዋል፣

ጌታሁን ማህበረሰቡን በተለይ ወጣቱን ከስህተት መንገድ ለመመለስ ጊዜውንና እውቅውቱን ሰስቶ አያውቅም፣ የአመቱ ሰው ብዬ ስመርጠው ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፣ ሰውየው ግን ብሄራዊ እውቅና የሚገባው አይነት ነው፣

የአመቱ ማህበርሰብ አገልጋይ:- Melat Nigussie

ሜላትን ታውቋታላችሁ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ለበጎ ተግባር ትጠቀምበታልች፣ አሰሪን ከሰራተኛ ጋር ታገናኛለች፣ በነጻ! በሜላት በኩል ስራ አግኝተው እንጀራ መቁረስ የጀመሩ ሰዎች በሺህ የሚቆጠሩ ናቸው፣ ከዚህ በተጨማሪ ሰዎችን አስተባብራ የካንሰር ህሙማን ህጻናትን በቋሚነት ተረዳልች፣ She is one of a kind!

የአመቱ Entrepreneur:- Ki Di ና ሀና

ሁለቱ እንስቶች ይዘውት የመጡትን የንግድ ሀሳብ ለኔ ወይም ለሌላ traditional Consultant ቢያሳዩት ወሽመጣቸውን ለሁለት የሚቆርጥ ነገር ነግሯቸው በእንጭጩ ያስቀራቸው ነበር፣ ለዛ ነው ባለፈው ስለ ንግድ ሀሳብ ውድድር ተብዬ ነገር ስጽፍ ማንም ያንተን ሀሳብ የመገምገምና ውድቅ የማድረግ እውቀቱና ችሎታው የለውም ያልኩት፣

የመሰረቱት ድርጅት GUARO FARM ይባላል፣ ሀሳቡ ራሳቸው ዲዛይን ያገረጉትን "ፋብሪካ" ወይም ምርት ማቀነባበሪያ ገበሬው ደጃፍ ላይ ተክለው ለመጨረሻው ተጠቃሚ የሚሆን ምርት እዛው ማውጣት አይነት ነው፣ ትኩረታቸው ቅመማ ቅመም ነው፣ በሙከራ ደረጃ ስራ ጀምሯል፣ በብዙ መልኩ አዲስ የቢዝነስ ሞዴል ነው፣ ሀሳቡ በአለም አቀፍ ተቋማት ተወዷል፣ ባለፈው 40 ሺህ ዶላር ተሸልመዋል፣ በርካታ የአፍሪካ ሀገሮች ተዘዋወረ ለተለያዩ አካላት ሀሳባቸውን ሽጠዋል፣

በነገራችን ላይ ቅድስት ትንሽ ለየት ያለች ሴት ነች፣ በሙያ አርክቴክት ናት፣ ዝንባሌዋ ደግሞ ግብርና ነው፣ የሆነ ጊዜ ኤቲስት አካባቢ ነኝ ብላ ነበር፣ ቆይታ በጌታ ነኝ ብላለች፣ አንዳንድ የማህበሩ አባላት በ'ተከድተናል' ስሜት ጠሳቸውን ነክሰውባታል፣ commi ነኝ ብላ እኛ ጋር መጥታ ነበር፣ ተቀብለናት ስናበቃ ቦታ እየፈለግንላት ተሰወረችብን፣ ideologically የት እንዳለች አይታወቅም፣ የሆነ grey area ውስጥ አዳደፈጠች ይሰማኛል፣ መጨረሻዋን አብረን የምናየው ይሆናል፣

14/09/2025

ከ585,882 የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች መሀል ያለፉት 48,920፣ የወደቁት ደግሞ 536,962 ሆነዋል። በሌላ አገላለፅ 91.6% ተማሪዎች ወድቀው 8.4% ብቻ አልፈዋል !!

10/09/2025

በበጌምድር አውራጃ
"ሊቢያ"
ተብሎ የሚጠራ ቦታ አለ
የት ነው ?

 ደባርቅ ሆስፒታል የተመላለሰ ሰው  #በቀና መስተንግዶዋ ያውቃታል።በደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል ከ8 ዓመታት በላይ  #በነርስ ሙያ ያገለገለችው ሲ/ር ሰናይት ከሰተ በተከሰተባት የልብ ህመም ምክ...
05/09/2025



ደባርቅ ሆስፒታል የተመላለሰ ሰው #በቀና መስተንግዶዋ ያውቃታል።በደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል ከ8 ዓመታት በላይ #በነርስ ሙያ ያገለገለችው ሲ/ር ሰናይት ከሰተ በተከሰተባት የልብ ህመም ምክንያት ለዓመታት በደባርቅ ሆስፒታል፣ በጎንደር ዩንቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል እና አዲስ አበባ በሚገኙ የግልና የመንግሥት ሆስፒታሎች የህክምና ክትትል በራሷና በቤተሰቧ እገዛ እያደረገች ብትቆይም የልብ ህመሟ ከዕለት ዕለት እየተባባሰ በመሄዱ የልብ ቀዶ ህክምና እንዲሰራላት ሐኪሞች ስለወሰኑ የዚህ ህክምና ጠቅላላ ወጭም እስከ 1.8 ሚሊዮን ብር የሚደርስ በመሆኑ ይህን ብር እሷም ሆነች ቤተሰቧ ማግኘት ባለመቻላቸው ድጋፍ እንድታደርጉልን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ለድጋፍ ማሰባሰቢያ ዝግጁ የሆኑ አካውንቶች

1000715443817 senait kesete and abrham wassia

467911 9945482 018 senait kesete

#ቴሌብር 0902752166 ሰናይት ከሰተ

የሰዎችን ህይወት መታደግ የምትችለውን ሀኪም አሰንታደግ

እንኳን አደረሰህ ማለት እፈልጋለሁ ጠጁዬ💪 አንቂያችን🙏
05/09/2025

እንኳን አደረሰህ ማለት እፈልጋለሁ ጠጁዬ💪 አንቂያችን🙏

እንዴት አያችሁት ቤተሰብ ✈️✈️✈️✈️
17/08/2025

እንዴት አያችሁት ቤተሰብ ✈️✈️✈️✈️

 በሊቢያ በአጋቾች እጅ ላለ ወንድማችንበአጋቾች እጅ በፀና የታመመው ህፃን ከነሱ እጅ ወጥቶ ለህክምና ለመድረስ የእናንተን የወገኖቹን እርዳታ ይፈልጋል! ከአሁን በፊት ለማሰባሰብ ብንሞክርም ከ...
12/08/2025


በሊቢያ በአጋቾች እጅ ላለ ወንድማችን

በአጋቾች እጅ በፀና የታመመው ህፃን ከነሱ እጅ ወጥቶ ለህክምና ለመድረስ የእናንተን የወገኖቹን እርዳታ ይፈልጋል!

ከአሁን በፊት ለማሰባሰብ ብንሞክርም ከ50ሺ ፈቀቅ ያላለ ነበር የተሰበሰበው ይሁን እንጂ በዚህ 2ቀን የማይከፈል ከሆነ መርዶ ጠብቁ ላሉት አጋቾች መልስ እንሆን ዘንድ ሆነ አቅሙ ያላችሁ ከንፈር ከመምጠጥ ከማዘን በህይወት ሳለ ያቅማችን በጭንቅ ያሉ ቤተሰቦቹን እናግዝ!


👉አካውንት 1000202176497 አቶ ደረበ ከፍ ያለው በላይ
👉 0918731664/0922122294

መርዳት ባንችል ኮሜንት (mension) እና ሸር እናድርግ ደጋጎች ጋር አድርሱልን

እግዚአብሔር ወጣቱን በሀገሩ ተስፋ ቆርጦ ከመሰደድ ያድንልን

✈️✈️✈️✈️✈️✈️በቅርብ ቀን✈️✈️✈️✈️✈️
12/08/2025

✈️✈️✈️✈️✈️✈️በቅርብ ቀን✈️✈️✈️✈️✈️

10/08/2025

ይታወቅ !
ከቀጣይ መስከረም ጀምሮ ህዝባችን ትምህርት ብቻ ሳይሆን የተሟላ ሰላምም ያስፈልገዋል ።
ፈፅሞ እንዲህ መቀጠል አንችልም ።

Address

Naro9@gmail. Com
Debark'
09

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debark people posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share