Ethiopian Embassy in Rome

Ethiopian Embassy in Rome This is the official page of the Ethiopian Embassy in Rome Official page of the Ethiopian Embassy in Rome.

31/05/2026
ኢትዮጵያ በFAO Rome Nutrition Week ባህላዊ የቡና አፈላል ሥነ-ሥርዓት በማቅረብ ቡናና የተመጣጠነ ንጥረ-ነገር ያላቸውን ምርቶቿን ለዓለም አስተዋወቀች፣======(ግንቦት 20/20...
28/05/2026

ኢትዮጵያ በFAO Rome Nutrition Week ባህላዊ የቡና አፈላል ሥነ-ሥርዓት በማቅረብ ቡናና የተመጣጠነ ንጥረ-ነገር ያላቸውን ምርቶቿን ለዓለም አስተዋወቀች፣

======
(ግንቦት 20/2026 ዓ.ም.)
እ.ኤ.አ. ከሜይ 24 እስከ 28 ቀን 2026 በሮም፣ የተ.መ.ድ. የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (FAO) "Shaping the Future of Joint Nutrition Action in a Changing World" በሚል መሪ ቃል እያካሄደ በሚገኘው "Rome Nutrition Week" መድረክ ላይ፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና አፈላል ሥነ-ሥርዓት ለታዳሚያን በማቅረብ የአገራችን ቡናና ባህል በዓለም አቀፍ ደረጃ ተስተዋወቀ።

በጣሊያን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እና በሮም በሚገኙ የተ.መ.ድ. ኤጀንሲዎች ቋሚ ተጠሪ ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሃምቢሳ በዝግጅቱ ላይ ባደረጉት መክፈቻ ንግግር፣ የኢትዮጵያ የቡና አፈላል ሥነ-ሥርዓት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ማኅበራዊ ትስስር፣ እንግዳ ተቀባይነትና ባህላዊ እሴቶች የሚያንጸባርቅ መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በዝግጅቱ የኢትዮጵያን ቡና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከማስተዋወቅ ባሻገር፣ በንጥረ-ነገር የበለጸጉና ለውጭ ገበያ ተፈላጊ የሆኑ የአገራችን የግብርና ምርቶችን ለዕይታ በማቅረብ፣ አገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድና የኢንቨስትመንት ትስስር እንዲፈጠር የሚደረጉ ጥረቶችን ያጠናከረ ሆኖ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።

28/05/2026
27/05/2026

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል አደረሰን፣ አደረሳችሁ!

ስለዒድ አል-አድሐ “ዐረፋ” በዓል ስናስብ ሦስት ነገሮች ቀድመው ይታወሱናል። መስዕዋትነት፣ መታዘዝ እና መተጋገዝ። አባት ልጁን ለመስዕዋት ያቀረበበት፤ ልጅ የአባቱን ትዕዛዝ የፈጸመበት፤ ሙስሊሞች የመተጋገዝን እሴት ለዓለም የገለጡበት በዓል ስለሆነ “ዐረፋ” በሕዝበ-ሙስሊሙ ዘንድ ትልቅ ትርጉም አለው።

እስማኤል ለነብዩ ኢብራሂም የመጀመሪያ እና ተወዳጅ ልጃቸው ነው። አላህ (ሱ.ወ.) ይሄን ተወዳጅና የመጀመሪያ ልጅ እንዲሠዉለት ሲጠይቃቸው ታዘዙ እንጂ ወደኋላ አላሉም። ለመታዘዝ የሞከሩት ነገሩ ቀላል ሆኖ አይደለም። ልጅን ያህል ነገር መስዕዋት ማድረግ ምኑ ይቀላል? የአባትነት ስሜት ይተናነቃል። የሰይጣን ሹክሹክታ ይፈታተናል። የቤተዘመድን ወቀሳ እና የጎረቤትን አስተያየት መቋቋምም ይከብዳል። ነብዩ ኢብራሒም፥ በዚህ ሁሉ አጣብቂኝ ውስጥ አንድ ሐቅ ተገልጦላቸዋል። ከራስ ስሜት፣ ከሰው ሐሜት እና ከወዳጅ ፍላጎት የሚልቅ ታላቅ ዓላማ እንዳለ አምነዋል። ስለዚህም በፈተና ውስጥ ጸንተው ቆሙ፤ ቆራጥነታቸውም በተግባር ታየ።

ሀገር የምትገነባው ከራስ ጥቅም በላይ በሚያስቡ እና ከግላዊ ፍላጎታቸው በላይ ለመፈጸም በቆረጡ ዜጎች ነው። የሚወዱትን ነገር እንኳን ሳይቀር ለመሠዋት ዝግጁ የሆኑ ዜጎች ሲበዙላት ሀገር ትበረታለች። እስማኤላቸውን ለመስጠት የማያመነቱ ዜጎች የሞሉባት ሀገር ጽኑ ናት።

የለመድናቸው፣ የምንወዳቸው፣ የራሳችን ገንዘብ ያደረግናቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። ከእነዚህ የሚበልጥ ዓላማ ግን አለ፤ እሱም “ሀገርነት እና ሉአላዊነት” ይሰኛል። ሀገርነት የሚገነባው ከመውሰድ ይልቅ በመስጠት ነው። ሉአላዊነት የሚጸናው በፈተና ሳይወድቁ በመቆም፤ በወጀብ ሳይናወጡ መጓዝ በመቻል ነው።

የእውነት ኢትዮጵያ ሲያልፍላት ማየት የምንሻ ከሆነ ምኞታችን በተግባር ይገለጥ። የሀገር ኩስመና ካሳሰበን ለግዝፈቷ እንድከም። ያጎበጣትን የድህነት ቋጥኝ ለመሸከም ትከሻችንን እናመቻች። ጎተራዋ እንዲሞላ እጃችን አፈር ይንካ። የጠየመ ገጽዋ እንዲፈካ በሥራ ሌት-ተቀን እንሰለፍ። የተቀማ ክብሯ እስኪመለስ ድርሻችንን እንወጣ። ሀገር መውደዳችን ከልብ ከሆነ መስዕዋት ለመሆን አናመንታ።

የዐረፋ በዓል የመታዘዝና የመስዕዋት ብቻ ሳይሆን የመደጋገፍና የመተጋገዝ በዓል ጭምር ነው። በዐረፋ ከሚከናወነው እርድ አንድ ሦስተኛው ለምስኪኖች እንዲሰጥ የእስልምና አስተምህሮ ያዛል። በዐረፋ ሕዝበ-ሙስሊሙ ደስታና ሐዘኑን እየተጋራ በዓሉን ያከብራል። የዐረፋ እለት አንድም ሰው ተከፍቶ አያሳልፍም፤ በዐረፋ ሰሞን ማንም ሰው ተርቦና ተጠምቶ አያድርም። በዓሉ ትርጉም የሚሰጠው ሕዝበ-ሙስሊሙ ያለውን ተካፍሎ ሲያከብረው ነው። ሰዎች አስቸጋሪ ሁኔታን የሚሻገሩበት መፍትሄው መተሳሰብና መተጋገዝ እንደሆነ ከዐረፋ እንማራለን። ሀገርም ከፈተናዎችዋ በላይ እንድትሆን እኒህ እሴቶች ወሳኝ ናቸው።

ዐረፋ ማኅበረሰባዊ በዓል የሚባለው ለዚህ ነው። ሰዎች በግላቸው የሚያከብሩት አይደለም። ቤተሰቡ፣ ጎረቤቱ፣ ሠፈሩ፣ ከተማው የሚያከብረው በዓል ነው። ያላቸውና የሌላቸው፤ የሚችሉና የማይችሉ፤ ታላላቆችና ታናናሾች፤ ባለ ሥልጣናትና ተራ ዜጎች፣ በአንድነት የሚያከብሩት በዓል ነው። ሰው የሚኖረው በቤቱ ውስጥ አይደለም። በማኅበረሰቡ ውስጥ ነው።

ማኅበረሰባዊ ትሥሥርና ትብብር ለዜጎች እና ለሀገር ደኅንነት ወሳኝ ናቸው። ማኅበረሰባዊ ትሥሥር ስለሌሎች እንድናስብ፣ ስለሌሎች እንድንሠራ እና ስለ ሌሎች ዋጋ እንድንከፍል ያደርገናል። ራሳችንን በሌሎች ጫማ ላይ አቁመን እንድናይ ያስችለናል። የሁላችንም ሰላም፣ የሁላችንም ደኅንነት እና የሁላችንም ጥቅም ካልተከበረ በቀር የግላችንን ብቻ ልናስከብር እንደማንችል ያስገነዝበናል። ስለዚህም ማኅበራዊ ግዴታን እንደ ዜግነት ግዴታ ወስደን እንድንሠራ ያደርገናል።

ምርጫ ማኅበራዊና ዜግነታዊ ግዴታዎችን ከምንወጣባቸው የዴሞክራሲ መገንቢያ መሳሪያዎች መካከል ዋነኛው ነው። ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ዴሞክራሲ አይሳካም። ያለ ምርጫም የሕዝብ ተሳትፎ ምሉዕ አይሆንም። የዴሞክራሲያችን መሰረት ጥንካሬው የሚለካው በተሳትፎአችን መጠን ነው።

የዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ሀገረ-መንግሥታዊ ሥርዓታችን የሚጠነክርበት መሰረት ነው። የዴሞክራሲ ልምምዳችን አንድ ደረጃ ከፍ የሚልበት፤ የቀጣይ ዓመታት የሀገራችንን እጣ-ፈንታ የምንበይንበት፤ ከምንም በላይ ብዝሃ-ድምጽ የሚሰማበት የሕግ መወሰኛ ምክርቤት የምንመሰርትበት ወሳኝ አጋጣሚ ነው። በመሆኑም በዓሉን ስናከብር ዜግነታዊ ግዴታችንን ለመወጣት ብቻ ሳይሆን በካርዳችን ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለማረጋገጥ እየተዘጋጀን እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ።

በድጋሚ መልካም የዐረፋ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ!
ዒድ ሙባረክ!!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ግንቦት 18፣ 2018 ዓ.ም

26/05/2026

HAPPY AFRICA DAY TO ALL OUR AFRICAN BROTHERS AND SISTERS!

63 years ago, our forefathers gathered right here in Addis Ababa and dared to dream of a free, united Africa, and that dream still burns bright.

Today, as the proud home of the African Union, Ethiopia stands shoulder to shoulder with every African nation in that same spirit of unity.The work is far from over. Let us move from words to action, from promises to progress.

Africa's greatest resource has always been her people, and together, WE RISE!

የአፍሪካ ቀን በዓል በድምቀት ተከበረ፣=====(ግንቦት 17/2018 ዓ.ም.) በሮም የኢፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ተቀማጭነታቸው በሮም ጣሊያን ከሆኑ የአፍሪካ አገራት ኤምባሲዎች ጋር በመተባበር የአፍሪ...
26/05/2026

የአፍሪካ ቀን በዓል በድምቀት ተከበረ፣
=====

(ግንቦት 17/2018 ዓ.ም.) በሮም የኢፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ተቀማጭነታቸው በሮም ጣሊያን ከሆኑ የአፍሪካ አገራት ኤምባሲዎች ጋር በመተባበር የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁኗ አፍሪካ ህብረት) የተመሰረተበትን 63ኛ አመት ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ኩነቶችን በማዘጋጀት በደማቅ ሁኔታ ማክበር ተችሏል፣

በፕሮግራሙ የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች፣ የጣሊያን ውጭ ጉዳይና አለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስቴር ተወካይን ጨምሮ ከ350 በላይ ተሳታፊዎችና ታዳሚዎች በተገኙበት የዕለቱ መልእክት በማስተላለፍ፣ የየአገሮቹ ባህላዊ ምግብና ለፕሮግራሙ ድምቀት እንዲሰጥ የተለያዩ ባህላዊ ሙዚቃዎች ቀርበዋል፣

ኤምባሲያችን ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ የአገራችንን ባህላዊ ምግብ፣ የቡና አፈላል ስነስርአትና ቡናችንን፣ የአገራችንን ሙዚቃ እንዲሁም አየር መንገዳችንንና የቱሪዝም ሀብታችንን አቅርበን አፍሪካ ያላትን ባህል እና አብሮነት በመድረኩ ማስተዋወቅ ተችሏል::

Indirizzo

Via Andrea Vesalio 16-18
Rome
00161

Orario di apertura

Lunedì 09:00 - 17:00
Martedì 09:00 - 17:00
Mercoledì 09:00 - 17:00
Giovedì 09:00 - 17:00
Venerdì 09:00 - 17:00

Notifiche

Lasciando la tua email puoi essere il primo a sapere quando Ethiopian Embassy in Rome pubblica notizie e promozioni. Il tuo indirizzo email non verrà utilizzato per nessun altro scopo e potrai annullare l'iscrizione in qualsiasi momento.

Contatta L'organizzazione

Invia un messaggio a Ethiopian Embassy in Rome:

Condividi