Embassy of Ethiopia in Seoul, South Korea

Embassy of Ethiopia in Seoul, South Korea Embassy Website

Bridging Nations, Building Futures: Reflections of H.E. Dr. Dessie Dalkie,Ethiopia's Ambassador to the Republic of Korea
03/09/2026

Bridging Nations, Building Futures: Reflections of H.E. Dr. Dessie Dalkie,Ethiopia's Ambassador to the Republic of Korea

(C) Dessie Dalkie DUKAMO (Dr) / Ambassador Extraordinary and Plenipotentiary, the Federal Democratic Republic Ethiopia to the ROK.As my term as Am ...

01/09/2026
የወርሀ ሐምሌ እና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት
01/09/2026

የወርሀ ሐምሌ እና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት

በደቡብ ኮሪያ የኢ.ፌዴ.ሪ. አምባሳደር ሽኝት ተደረገላቸው…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………በደቡብ ኮሪያ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ...
31/08/2026

በደቡብ ኮሪያ የኢ.ፌዴ.ሪ. አምባሳደር ሽኝት ተደረገላቸው
…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………
በደቡብ ኮሪያ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ ዲፕሎማቶችና ሠራተኞች፣በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ደቡብ ኮሪያዊን ወዳጆች በተገኙበት በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ዶ/ር ደሴ ዳልኬ የሽኝት መርሐ-ግብር ተከናውኗል።
ክቡር አምባሳደሩ ደቡብ ኮሪያን ጨምሮ ቬትናም፣ ፊሊፒንስና ካምቦዲያን በመሸፈን የኢትዮጵያ ወክለው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
አምባሳደር ዶ/ር ደሴ ዳልኬ በደቡብ ኮሪያ በነበራቸው የአገልግሎት ዘመን በደቡብ ኮሪያና በሀገራችን መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነትና ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ሰፊ ጥረት ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም በሥራ ጊዜያቸውም የሁለቱን አገራት የንግድና የኢንቨስትመንት ትስስር ማሳደግ እንዲሁም የከፍተኛ ባልስልጣናት የሥራ ጉብኝቶች እንዲሳኩ ማድረግ ችለዋል፡፡ በደቡብ ኮሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መብቶቻቸው እንዲጠበቁ፣ በኅብረት እንዲደራጁ እና በአገራቸው የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በማስቻል ረገድ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል።
እንዲሁም በቬትናም፣ በፊሊፒንስ፣ በካምቦዲያ እና በሀገራችን መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ተግባራትን ማከናወን ችለዋል፡፡
አምባሳደሩ በሥራ ዘመናቸው ለተደረገላቸው ሙያዊ ድጋፍና ትብብር ለኤምባሲው ሠራተኞች፣ ለዲያስፖራው ማኅበረሰብ እና ለኮሪያ ወዳጆች ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ የኤምባሲው ዲፕሎማቶችና ኤምባሲ ዲፕሎማቶችና ሠራተኞች፣በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ደቡብ ኮሪያዊን ወዳጆች በበኩላቸው አምባሳደሩ ላሳዩት ቀና የሥራ አመራርና ላስመዘገቡት ውጤት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ በቀጣይ የሥራ መስካቸውም ስኬትን ተመኝተውላቸዋል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1501ኛዉ የመዉሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ:: በዓሉ የሰላም የጤናና የደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
25/08/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1501ኛዉ የመዉሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ:: በዓሉ የሰላም የጤናና የደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

ይህን ያውቁ ኖሯል?የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅኝት
23/08/2026

ይህን ያውቁ ኖሯል?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅኝት

23/08/2026
Miss World Ethiopia, Ruth Yirgalem, is proudly representing Ethiopia 🇪🇹 at  ! Let’s show our support and vote for Miss W...
22/08/2026

Miss World Ethiopia, Ruth Yirgalem, is proudly representing Ethiopia 🇪🇹 at !
Let’s show our support and vote for Miss World Ethiopia 2026, Ruth Yirgalem!
Vote now at: missworld.1voting.com
Every vote counts! Let’s support Ethiopia! 🇪🇹🌍

Wishing a joyful Buhe (Debre Tabor) to everyone celebrating!
19/08/2026

Wishing a joyful Buhe (Debre Tabor) to everyone celebrating!

መታወቅ፦ የጸናች ሀገር መገለጫ እና የዲጂታል ኢኮኖሚ ዋና መሠረት*********************** መታወቅ የሰው ልጅ ሕልውና እና የመብቶቹ ሁሉ መነሻ ነው። በአንድ ሀገር ውስጥ ደግሞ የ...
19/08/2026

መታወቅ፦ የጸናች ሀገር መገለጫ እና የዲጂታል ኢኮኖሚ ዋና መሠረት
***********************

መታወቅ የሰው ልጅ ሕልውና እና የመብቶቹ ሁሉ መነሻ ነው። በአንድ ሀገር ውስጥ ደግሞ የዜጎች ሕጋዊ እና አስተማማኝ ማንነት መረጋገጥ የጸናች ሀገር መገለጫ የመሆኑን ያህል፣ ለዲጂታል ኢኮኖሚ እና ተቋማዊ ዕድገትም ዋና መሠረት ነው።

ኢትዮጵያ ወደተሟላ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገው ጉዞ ያለ አስተማማኝ የመታወቂያ ሥርዓት እውን ሊሆን አይችልም።

ባለፉት ዘመናት የዜጎችን ሕጋዊ ማንነት ለማረጋገጥ በስፋት ሲያገለግል የቆየው የቀበሌ መታወቂያ፣ በመላ ኢትዮጵያ ባሉ 16 ሺህ የዝቅተኛ እርከን የአስተዳደር መዋቅሮች የሚሰጥ እና እንደ ፓስፖርት ማውጣት፣ የባንክ ሒሳብ መክፈት እንዲሁም በምርጫ ድምፅ መስጠትን ላሉ መሠረታዊ መብቶች መገልገያ ሆኖ ቆይቷም።

ይሁን እንጂ ማዕከላዊ የምዝገባ ሥርዓት የሌለው፣ የአንዱን መታወቂያ ከሌላው ለይቶ ማረጋገጥ የማይቻልበት እና በቀላሉ ለሐሰተኛ እና ሕገ ወጥ አሠራሮች የተጋለጠ መሆኑ የዜጎችን ደኅንነትም ሆነ የተቋማትን አሠራር ለከፍተኛ ስጋት ሲዳርግ ቆይቷል።

ከዚህ ባሻገር የግብር መታወቂያ (ቲን)፣ ፓስፖርት፣ የመንጃ ፈቃድ እና የልደት ምስክር ወረቀቶችን ጨምሮ የነበሩት ልዩ ልዩ አሠራሮች ከሕዝቡ ከግማሽ በታች የሚሆነውን ብቻ የሚሸፍኑ እና በተበታተነ መዋቅር የተቃኙ በመሆናቸው፣ ኢትዮጵያ ወደተቀናጀ የዲጂታል ምኅዳር የምታደርገውን ሽግግር ሲያደናቅፉት ኖረዋል።

ይህን ሥር የሰደደ ተደራሽነት እና የአስተማማኝነት ክፍተት ለመቅረፍ የተዘረጋው ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ)፣ የኢትዮጵያን ዲጂታል ሽግግር በጽኑ መሠረት ላይ ያቆመ ዋና መልሕቅ ሆኖ እየተተገበረ ይገኛል።

በ2015 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 1284/2015 ሕጋዊ ማዕቀፍ አግኝቶ ወደ ሥራ የገባው ፋይዳ፣ “አንድ ሰው፣ አንድ ማንነት” በሚል መርሕ የዜጎችን የባዮሜትሪክ እና ዲሞግራፊክ መረጃ በማቀናጀት ፍጹም ታማኝ እና ልዩ የሆነ መለያ ቁጥር ይሰጣል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ፋይዳ የካርድ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) በ7 በመቶ የማሳደግ አቅም ያለው፣ የግል መረጃ ምሥጢራዊነትን የሚጠብቅ እና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥ የመተማመኛ ሥርዓት ነው።

እስካሁን ወደ 50 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን መዝግቦ ከ150 በላይ የመንግሥት እና የግል ተቋማት ጋር የተሣሠረው ይህ ሥርዓት፣ እስከ 2020 ዓ.ም ድረስ የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ወደ 115 ሚሊዮን ለማድረስ በመጓዝ ላይ ይገኛል።

ይህ እንቅስቃሴ በተለይም ቀደም ሲል ከአገልግሎቶች ተገልለው የነበሩ ሚሊዮኖችን ወደ መደበኛው የፋይናንስ ሥርዓት በማስገባት፣ የባንክ እና የሞባይል ገንዘብ ዝውውርን በማፋጠን እና የቢዝነስ እንቅስቃሴዎችን በማቀላጠፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው።

በተባበሩት መንግሥታት የዘላቂ ልማት ግቦች እና በአፍሪካ ኅብረት አጀንዳ 2063 የተቀመጠውን “በሕግ የታወቀ ማንነት ለሁሉም” የሚለውን ዓለም አቀፋዊ ራዕይ መሠረት ያደረገው ፋይዳ፣ የጾታ እኩልነትን፣ የማኅበራዊ ጥበቃ አቅርቦትን እና የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ ቁልፍ መሣሪያ ነው።

ፋይዳ ሐሰተኛ አሠራሮችን እና ማጭበርበርን በማስቀረት ተቋማዊ አሠራርን ግልጽ ከማድረጉም በላይ፣ ኢትዮጵያ በጽኑ መሠረት ላይ የቆመች፣ የዜጎቿ ማንነት እና ደኅንነት የተከበረባት ሀገር ሆና እንድትቀጥል የሚያስችል የዘመናችን መሠረታዊ መሠረተ ልማት ነው።

Address

80 Seongbuk-ro, Seoungbuk-gu
Seoul
61

Telephone

+8227448558

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Embassy of Ethiopia in Seoul, South Korea posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share