Basketo ZoneLaska Zuriya Woreda Youths and Sport Department

Basketo ZoneLaska Zuriya Woreda Youths and Sport Department እኛ ወጣቶች የነገዋን የበለፀገች ኢትዮጵያ የመገንበት ታሪካዊ ኃላፊነት ያለብን ነን!!

ባህላችን የእኛ መለያችን ነው፤ባህላዊ አለባበሳችን የትውልድ መድመቂያችን ነው፤መሬቶቻችን የኢንቨስትመንት ትኩረታችን ነው፤ሾልኣ ካሻ የብሔረሰቡ የምስጋና በዓላችን ነዉ ፤ኑ ወደ ባስኬቶ ዞን ም...
08/12/2025

ባህላችን የእኛ መለያችን ነው፤
ባህላዊ አለባበሳችን የትውልድ መድመቂያችን ነው፤
መሬቶቻችን የኢንቨስትመንት ትኩረታችን ነው፤
ሾልኣ ካሻ የብሔረሰቡ የምስጋና በዓላችን ነዉ ፤
ኑ ወደ ባስኬቶ ዞን ምን አላችሁ ካላችሁ:- ለም፣ሰፊ ፣ ለሁሉም ሰብሎች ምቹ መሬት አለን
ስርሶና በአርሶ መንቲያ ፏፏተ፣ አርድሞሳ አዲታና ሶኚ ዋሻዎች፣ አቡነ አረጋዊ ፀበል፣ ሮኪ መልካአ ምድር፣ ጥቅጥቅ ያሉ ደኖች የቱን ዘርዝሬ የቱን ልተው! የኦሮሞ ይገርማል! በሆቴል፣ በእርሻ፣ በማዕድን፣ በጥናትና ምርምር ሥራዎች ኢንቨስት ለማድረግ የምትፈልጉ ካላችሁ በፍቅር እና በብሔረሰቡ የእንግዳ ተቀባይነት ባይል እንቀበላለን።

"የዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ ለሀገራዊ መተማመንና መተዋወቅ ጉልህ ሚና አለው" ወጣት ሳሙኤል ግርማበባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ ሱባ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የበጋ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ዕቅድ ...
25/11/2025

"የዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ ለሀገራዊ መተማመንና መተዋወቅ ጉልህ ሚና አለው" ወጣት ሳሙኤል ግርማ

በባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ ሱባ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የበጋ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ዕቅድ አካል የሆነው የዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል ግርማ ዓለም በዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ ፊቷን ወደ አንድ ተርታ እያቀናች መሆኑን ተናግረዋል።

አያይዘውም የዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ መተማመን እና መታወቅን ለማፅናት ከፍተኛ ሚና መኖሩን ጠቁመዋል።

የዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ በተለይ ወጣቱን ከቴክኖሎጂ ጋር ለማላመዲና ዘመኑን የሚመጥን መረጃን ወደ አንድ ቋት ለመሰብሰብ የታለመ መሆኑን የባስኬቶ ዞን የላስካ ዙሪያ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት የወጣት ዘርፍ ኃላፊ ወጣት ታምራት ደጄ ተናግረዋል።

ይህ ተግባር የበጋ ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ18ቱ የትኩረት መስኮች መካከል አንዱ እንደሆኑ አክለው ጠቁመዋል።

ይህ ተግባር በዙሪያ ወረዳ ባሉ ሁሉም ቀበሌዎች ላይ በነቃ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ህዳር 16/2018 ዓ.ም
ላስካ
የላስካ ዙሪያ ወረዳ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

Adres

Basketo
Łask

Telefon

+251920868197

Strona Internetowa

Ostrzeżenia

Bądź na bieżąco i daj nam wysłać e-mail, gdy Basketo ZoneLaska Zuriya Woreda Youths and Sport Department umieści wiadomości i promocje. Twój adres e-mail nie zostanie wykorzystany do żadnego innego celu i możesz zrezygnować z subskrypcji w dowolnym momencie.

Skróty

Udostępnij

Kategoria