የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት፤ ጄዳ Ethiopian Consulate General, Jeddah

  • Home
  • Saudi Arabia
  • Jeddah
  • የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት፤ ጄዳ Ethiopian Consulate General, Jeddah

የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት፤ ጄዳ Ethiopian Consulate General, Jeddah Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት፤ ጄዳ Ethiopian Consulate General, Jeddah, Consulate & Embassy, 8111، 3210 الشبيلي، حي 8111, Jeddah 23325, Jeddah.

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ቆንስላ ጽ/ቤት - ጅዳ ::
Consulate General of The Federal Democratic Republic of Ethiopia Jeddah القنصلية العامة لجمهورية اثيوبيا الاتحادية الديمقراطية بجدة

07/09/2026
በጄዳ የኢትዮጵያውያን ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ተሰጠ​(ጄዳ፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ...
04/09/2026

በጄዳ የኢትዮጵያውያን ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ተሰጠ

​(ጄዳ፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም) በጄዳ የኢትዮጵያውያን ኮሙኒቲ ማህበር ባዘጋጀው የእውቅና ፕሮግራም የጄዳ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ተወካይና ዲፕሎማቶች፣ የትምህርት ቤቱ አመራር፣ መምህራን እና ወላጆች በተገኙበት በ2018 ዓ.ም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

​በፕሮግራሙ ላይ የጄዳ ቆንስላ ተወካይ አቶ አባተ ማዴቦ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ በንግግራቸውም ከብዙ ልፋት፣ ድካም፣ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችና የፈተና ጫናዎች በኋላ የመጣ ውጤት በመሆኑ "እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋቸዋል። ይህ ውጤት ለተማሪዎቹ የሕይወታቸው አዲስና ትልቅ ምዕራፍ መጀመሪያ በመሆኑ በቀጣይም ፈተናዎችን በማለፍ እና የሚገኙ እድሎችን በመጠቀም ለሀገራቸው አለኝታ እንዲሆኑ አስገንዝበዋቸዋል።

​አያይዘውም ለዚህ ውጤት መሳካት ለተጉ የትምህርት ቤቱ አመራር፣ መምህራን፣ ወላጆች፣ ተማሪዎችና አጠቃላይ የትምህርት ማህበረሰብ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል። ለሁሉም ባለድርሻ አካላት እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መሰል ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

​በፕሮግራሙ በጄዳ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማህበር ሰብሳቢ አቶ መሀመድኑር ሀሰን፣ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት የቦርድ ሰብሳቢ እና የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

​በመጨረሻም የእውቅና ሰርተፊኬት የማበርከት እና የኬክ ቆረሳ ሥነ ሥርዓት በማካሄድ የእለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል።

.                                    📌ማስታወቂያ📌                                *********************ተጨማሪም መረጃዎችን በቆንስላ ጽ/ቤ...
02/09/2026

. 📌ማስታወቂያ📌 *********************
ተጨማሪም መረጃዎችን በቆንስላ ጽ/ቤቱ ማኅበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ በሚከተሉት ማስፈንጠሪያ (Link) በኩል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን:-
Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አዲሱን ኢ-ፓስፖርት በጄዳና አካባቢው ለሚገኙ ዜጎቻችን መስጠት መጀመሩ ይታወሳል። በመሆኑም ከታች የተቀመጠው ቪዲዮ በኢትዮጵያ የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገ...
02/09/2026

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አዲሱን ኢ-ፓስፖርት በጄዳና አካባቢው ለሚገኙ ዜጎቻችን መስጠት መጀመሩ ይታወሳል።
በመሆኑም ከታች የተቀመጠው ቪዲዮ በኢትዮጵያ የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎቶች (ICS) ፖርታል ላይ የተጠቃሚ መለያ የመፍጠር እና የመመዝገብ ሂደቱን እንዴት ማከናወን እንደሚችሉ ያሳያል።
የቪዲዮው ዓላማ ተጠቃሚዎች በኢሚግሬሽን ፖርታል (ድረ ገጽ) እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉ እና በኢሚግሬሽን ፖርታል የሚሰጡትን የመስመር ላይ (online) አገልግሎቶችን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ለመርዳት ነው።

ማሳሰቢያ፦
• እባክዎ ሂደቱን በጥንቃቄ ይከታተሉ እንዲሁም በምዝገባ ሂደቱ የሚያስገቡትን መረጃዎች ትክክለኛነት ያረጋግጡ።

The video provides a comprehensive, step-by-step training of the procedure for creating and registering a user account in the Immigration Portal of the Ethio...

.                                    📌ማስታወቂያ📌                                *********************
01/09/2026

. 📌ማስታወቂያ📌 *********************

በጄዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጽ/ቤት ከኢሲር የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማህበር ጋር በጋራ በመሆን ባደረጉት ጥረት ለረዥም ጊዜ ያልተከፈለ ደመወዝ የነበራትን ዜጋ መብት እንዲከበር ተደረገ።​(ጄዳ...
25/08/2026

በጄዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጽ/ቤት ከኢሲር የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማህበር ጋር በጋራ በመሆን ባደረጉት ጥረት ለረዥም ጊዜ ያልተከፈለ ደመወዝ የነበራትን ዜጋ መብት እንዲከበር ተደረገ።

​(ጄዳ፣ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም) ወ/ሪት ሕይወት አረጋጋኝ የተባለች ኢትዮጵያዊት ዜጋ ከአንድ አሰሪ ወደ ሌላ አሰሪ በመዘዋወር በ22,500 የሳዑዲ ሪያል ተሸጣ ስታገለግል የቆየች ሲሆን፣ ትሰራበት የነበረው አሰሪም ደመወዟን ለመክፈል ፍቃደኛ ባለመሆኑ ቆንስላ ጽ/ቤቱ ከኮሚኒቲ ማህበሩ ጋር በመሆን የዜጋችንን መብት ለማስከበር ለረዥም ጊዜ ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል።

​በሂደቱም የኢሲር የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማህበር ጉዳዩን ለአንድ ዓመት ያህል ከፖሊስ ጣቢያ እስከ ፍርድ ቤት ድረስ በጽናት የተከታተለ ሲሆን፣ ከሰባት የፍርድ ቤት ቀጠሮዎች ሂደት በኋላ ያልተከፈለ ደሞዝ 54,000 የሳዑዲ ሪያል ለዜጋችን እንዲከፈል ተደርጓል።

​ቆንስላ ጽ/ቤቱ በዜጎች ላይ የሚደርሱ መሰል የመብት ጥሰቶች ተገቢውን ፍትሕ እንዲያገኙ ለማድረግ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እየገለጸ፤ በኢሲር የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማህበር የዜጎችን መብት ለማስከበር ላደረገው ያላሰለሰ ጥረትና ብርቱ ክትትል ቆንስላ ጽ/ቤቱ የላቀ ምስጋናውን ያቀርባል።

.                                   📌ማስታወቂያ📌                                *********************ተጨማሪም መረጃዎችን በቆንስላ ጽ/ቤቱ...
24/08/2026

. 📌ማስታወቂያ📌 *********************
ተጨማሪም መረጃዎችን በቆንስላ ጽ/ቤቱ ማኅበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ በሚከተሉት ማስፈንጠሪያ (Link) በኩል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን:-
Telegram ( የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ) :- https://t.me/jedcon
Twitter (በትዊተር ይከተሉን):- https://x.com/EthiopianJeddah?s=20

Address

8111، 3210 الشبيلي، حي 8111, Jeddah 23325
Jeddah
495JEDDAH21411

Opening Hours

Monday 8:30am - 3pm
Tuesday 8:30am - 3pm
Wednesday 8:30am - 3pm
Thursday 8:30am - 3pm
Sunday 8:30am - 3pm

Telephone

+966126653622

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት፤ ጄዳ Ethiopian Consulate General, Jeddah posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት፤ ጄዳ Ethiopian Consulate General, Jeddah:

Shortcuts

Share