Essera woreda Government communications office page

Essera woreda Government communications office page Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Essera woreda Government communications office page, Government Organization, Addis Ababa to dawro 500km distance, Esenli.

This page is created only to support or announce the current government & public over all developmental activities , in this sense everybody can participate in the issue of national peaceful coexists

በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የአመራር አካላት የዉይይት መድረክ መካሄድ ጀምሯል። ጳጉሜ፦ 02/13/ 2014 ዓ/ም  የኢሠራ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትበዳውሮ ዞን...
07/09/2022

በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የአመራር አካላት የዉይይት መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

ጳጉሜ፦ 02/13/ 2014 ዓ/ም የኢሠራ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ አጠቃላይ የወረዳው አመራር አካላትን ያካተተ በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የዉይይት መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

በዉይይት መድረኩ በሀገሪቱ ለ3ተኛዉ ጊዜ የተከፈተውን ጦርነት ሕዝቡ በኢትዮጵያዊ አንድነት ላይ የተመሠረተ የአሸናፊነት መንፈስ በመላበስ ሊመክት ይገባል ተብሏል።

በተያያዘም ሁሉም ዜጋ በሀገር ሉዓላዊነትና በህዝብ ክብር ላይ የተቃጣውን ጦርነት በኢትዮጵያዊ አንድነትና ጀግንነት ማስቆምና ድልም መቀናጀት በሚያስችል ሁኔታ እንደሚመክር ይጠበቃል።

ሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳይን በማስመልከት የሚደረግ ውይይትና የጋራ ትግል ቀጣይነት ባለው መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተጠቅሷል።

በሀገር የተጀመረውን ለዉጥ በማደናቀፍ ሀገሪቱን የማፍረስ ዓላማ ያነገቡ አካላት በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ጥፋቶችን ሲፈጽሙ እንደ ነበርም ከመድረኩ ተጠቁሟል።

ይኼዉ የጥፋት አጀንዳ መያዛቸዉ ለሠላም የተዘረጋውን ዕድል በማምከን ወደ 3ኛዉ ዙር ጦርነት እንዳስገባቸዉ ያስታወሱት የኢሠራ ወረዳ/ዋ/አስ/ሪ አቶ ጌታሁን ደራ በዚህም ህዝብና ሀገር ላይ ትልቅ በደል መፈፀሙን ገልጸዋል።

አያይዘውም መንግሥት ከጦርነት ይልቅ የሠላም አማራጭ ማቅረቡን የጠቀሱት አስተዳዳሪው ይኼዉ አሸባሪ ቡድን ለሠላም የተሰጠዉን ዋጋና ዕድል ተቀባይነት በማሳጣቱ ሀገሪቱ ተገዳ ወደ ጦርነት እንዲትገባ መገደዷንም ጠቁመዋል።

አክለውም አሸባሪዉ ህወሃት ለ3ተኛ ጊዜ የከፈተውን ጦርነት በድል ለማጠናቀቅ አመራሩ እና ሕዝቡ የጋራ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉም አሳስበዋል።

በመጨረሻም ሀገሪቱ ችግር ሲያጋጥማት አመራሩ፣ የፓርቲዉ አባላትና በየትኛዉም ደረጃ የሚገኙ አካላት ተገቢና ሀገራዊ ተጨባጭ ሁኔታና መረጃ በተገቢው በመረዳት እንዲሁም ከሀሰተኛ መረጃ ምንጮች በመጠንቀቅ በሀገርና በህዝብ ላይ የተቃጣውን ጦርነት በጋራ ለመመከት ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባ የኢሠራ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዓለማዬሁ ጎምኦሌ በአስተያየታቸው አመላክተዋል።

" ለሀገር ክብር፣በትግል እናብር ! "

ዘገባው የኢሠራ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነዉ።

ለተሰናባች ሀገር መከላከያ ሠራዊት የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ መንግስት በትኩረት እየሠራ እንደሆነ ተገለፀ። ጳጉሜ 2/2014  ዓ.ም ኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤት፨...
07/09/2022

ለተሰናባች ሀገር መከላከያ ሠራዊት የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ መንግስት በትኩረት እየሠራ እንደሆነ ተገለፀ።

ጳጉሜ 2/2014 ዓ.ም ኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ በዛሬው ዕለት "ጉና" የተሰናባች መከላከያ ሠራዊት ማህበር በማህበር ተደራጅተው መንግስት ያመቻቸውን የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታና የቦታው ሳይት ፕላን መረከብ መቻሉን የኢሠራ ወረዳ ዋ/አስ/ሪ ተወካይና የኢሠራ ወረዳ ፊትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ካሳሁን አናጋው ገልፀዋል።

የዋ/አስ/ሪ ተወካይ አቶ ካሣሁን ተሰናባች የሀገር መከላከያ ሠራዊት እንደወረዳችን በተደጋጋሚ የቤት መሥሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው ማመልከቻ ማቅረባቸውን በመጥቀስ የጥያቄውን ተገቢነትና አስፈላጊነት በመገንዘብ ምላሽ ለመስጠት በትኩረት ሲሠራ መቆየቱን አብራርተዋል።

በዚህም መሠረት በ9 ወንዶችና በ3 ሴቶች ለተደራጀ "ጉና" ተሰናባች መከላከያ ማህበር የተመቻቸላቸው የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ለማህበር ርክብክብ መደረጉን የኢሠራ ወረዳ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ምትኩ እሸቱ ገልፀዋል።

ከንቲባው ካለው ከውስን መሬት ሠራዊት ለሀገር ከከፈለው ውለታና መስዋዕትነት አንፃር ቅድሚያ ሰጥተን ሊንሠራ ወደናል በማለት አሁን የተላለፈው መሬት በተገቢው ለተፈለገለት ዓላማ እንዲውል ከማህበሩ እስከባለድርሻ አካላት በጥንቃቄ ሊመራ ይገባል ብለዋል።

በማህበር ተደራጅተው ከወረዳው ህብረት ሥራ ጽ/ቤት እውቅና ያገኙ ተሰናባች ሠራዊቶች በማህበር በመደራጀት ህጋዊ ሂደቶችን ጨርሰው የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ሲረከቡ እጅግ መደሰታቸውን የገለፁ የኢሠራ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮን/ሽን ጽ/ቤት ም/ሃላፊ አቶ ወርቁ ወዳጄ ሠራዊት ለሀገር ሉዓላዊነትና ሠላም ከከፈለው ዋጋ አንፃር የተደረገለት ድጋፍ እዚህ ግባ የሚባል ባይሆንም ከአከባቢ ነባራዊ ሁኔታና ከአቅም አንፃር የተመቻቸ ዕድል መሆኑን በመገንዘብ የተሰጣቸውን መሬት በተገቢው መያዝና መጠቀም እንደሚገባ አሳስበዋል።

አክለውም ባለ2 መኝታ ቤት መስሪያ ቦታ 160 ካሬ በአዋጅ መሠረት በመሬት ሊዝ ምደባ የተላለፈ መሆኑን በመግለጽ ጽ/ቤቱ ከግንባታ ጀምሮ እስከ ቤት ርክብክብ ድረስ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የቁጥጥርና ክትትል ሥራ እንደሚያደርግና ለስኬታማነቱም ከማህበሩ ጎን ሆኖ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ተናግረዋል።

በመጨረሻም የመኖሪያ ቦታና ሳይት ፕላን የተረከቡ የማህበሩ አባላት በተደረገላቸው ድጋፍ እጅግ መደሰታቸውን በመናገር ቤት ሠርተን እስከሚንገባ ከመንግስት እስከጨዋ ማህበረሰባችን ድረስ ከጎናቸው እንዲሆኑጥሪ አቅርበዋል።

ዘገባው የኢሠራ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤት ነው።

የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚፈጠር የዋጋ ንረትን ለመቀነስ  እየተሰራ መሆኑን ንግድ ኢንዳስትሪና ገበያ ልማት ጽ/ቤት  ገለፀ።፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ጳጉሜ 1/2014...
06/09/2022

የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚፈጠር የዋጋ ንረትን ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑን ንግድ ኢንዳስትሪና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ገለፀ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ጳጉሜ 1/2014 ዓ.ም ኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤት

በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ ን/ኢ/ገበያ ልማት ጽ/ቤት በኩል በተለይ በበዓላት ወቅት የሚኖረውን ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ ህብረተሰቡ ላይ ጫና እንዳያሳድር ከንግድ ኢንዳስትሪና ገበያ ልማት ጽ/ ቤትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ህገወጥ ዋጋ ጭማሪ ቁጥጥርና ክትትል ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የወረዳው ን/ኢ/ገ/ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መቃ መጋላ ገልፀዋል።

ሃላፊው በወረዳ ውስጥ ባሉ ሁሉም ንግድ ማዕከላት በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚፈጠር የዋጋ ንረትን የሚቆጣጠርና ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ወደሥራ መግባቱን በመጥቀስ ነጋዴው፣ ሸማቹ ማህበረሰብና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በህገወጥ ዋጋ ንረት ላይ የጋራ ትግል ሊኖር እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በተለይ የፍጆታ ዕቃዎች ለአብነት ስኳር፣ ዱቄት ፣ በርበሬ እና ሌሎች ቀይሽንኩርት፣ነጭ ሸንኩርት እንዲሁም ከመጠጥና ምግብ አንፃር ከግብረ ሀይሉ ውሳኔ ውጪ ሰሞኑን ዓመት በዓልን ምክኒያት በማድረግ የዋጋ ለውጥ ባሳዩ ንግድ ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድና የተወሰደ እርምጃ እንዳለም ገልፀዋል።

ቀጣይ ወደህጋዊ እርምጃ ከመሸጋገሩ በፊት ነጋዴ ማህበረሰብ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሃላፊው አሳስበዋል።

ዘገባው የኢሠራ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤት ነው።

የጥንቃቄ መልዕክት ከኢሠራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ነሐሴ 30/2014/ ዓ.ም ኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤት፦ የዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት በክረምት ወራት ከዚህ...
05/09/2022

የጥንቃቄ መልዕክት ከኢሠራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት

ነሐሴ 30/2014/ ዓ.ም ኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤት፦

የዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት በክረምት ወራት ከዚህ በፊት እንደወረዳችን ዋጋ ያሰከፈለውን የመሬት መንሸራተት /ናዳ በማስታወስ ናዳው በሚከሰትባቸውና ተዳፋት አከባቢዎች ላይ ያሉ ማህበረሰብ ክፍሎች ከባድ ጥንቃቄ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።

ሰሞኑን በሚጥለው ከባድ ዝናብ ማህበረሰቡ ከባድ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ያሳሰቡ ፖ/ጽ/ቤት ስታፍ ሥራ ሂደት ማስተባበሪያ ሃላፊ ም/ኢ/ር ጣሰው በተላ በወረዳችን ባሉ የመሬት መንሸራተት ሥጋት ቀጠናዎች በሀገሊ 02 ቀበሌ ወንቢ ሴል፣በዛዲ ሻማይቲ ቀበሌ ሻማይቲ ሴል፣በሀገሊ 01 ቀበሌ ባሏ ሴል፣በኦፋ ቀበሌ ዛማና ጎጋሮ ሴል፣በጉዛ ቀበሌ ወጪ ሴል፣በሰንገጢ ቀበሌ ሻራዳ ሴል፣በደንጋ ወይሲ ቀበሌ ወይሲ ሴል፣በሾታ ቀበሌ ከተማ መንደር፣በጫውዳ ቀበሌ ቡኑካ ሴል፣በባሌ ቀበሌ አድስ ከተማ ሴሎች የተለየ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ም/ኢ/ር ጣሰው በተላ አሳስበዋል።

መረጃው የኢሠራ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ነው።

Hashshu Tookibe'a Baalaw Saro Gakedita!እንኳን ለዳውሮ ብሄር የዘመን መለወጫ ለ"ቶክ-ቤዓ" በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!ነሐሴ 28/2014 (የኢሠራ ወረዳ የመ...
03/09/2022

Hashshu Tookibe'a Baalaw Saro Gakedita!

እንኳን ለዳውሮ ብሄር የዘመን መለወጫ ለ"ቶክ-ቤዓ" በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!

ነሐሴ 28/2014 (የኢሠራ ወረዳ የመን/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት)

የ2014 ዓ.ም የዳውሮ ብሔር የዘመን መለወጫ "ቶክበአ" በዓል ነሐሴ 28/2014 ዓ.ም "ቶክ-ቤዓ ባህላችን ለአንድነታችንና ለብጽግናችን!" በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገለፀ።

በዓሉ በዞኑ በሁሉም አከባቢዎች በተለያዩ ፕሮግራሞች የብሔሩ ተወላጆችና ሌሎችም የባህሉ አክባሪዎች በተገኙበት በድምቀት እንደሚከበር የዞኑ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፓርት መምሪያ አሳውቋል ።

በዞኑ እና በደ/ም/ኢ/ህዝቦች ክልል ብዝሃ ከተማ ታርጫ እንድሁም በዞኑ በሚገኙ በሁሉም ወረዳ ማዕከል ከተሞች የሀገር ሽማግለዎች፣ ምሁራን፣ የመንግስት የሥራ ኋላፊዎች እንድሁም በዞን ደረጃ የሚመለከታቸው የክልል የመንግስት የሥራ ኋላፊዎች በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር ዝግጅት መድረጉን የዞኑ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታውቋል።

የዳውሮ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ የ"ቶክ-ቤኣ" በዓል ከጥንት ጀምሮ የጨረቃ ቀን አቆጣጠር ስርዓትን በመከተል የዳውሮ ህዝብ በ12ኛ ወር መጨረሻ አከባቢ የሚያከብሩት የዳውሮ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል እንደሆነ አስረድተዋል ።

የዘንድሮ የዳውሮ ብሔር የዘመን መለወጫ "ቶክ_ቤኣ" በዓል ከክልል ብዝሀ ዋና ከተሞች አንዱ በሆነው በታርጫ ከተማና በዞኑ በሚገኙ በሁሉም ወረዳ ማዕከል ከተሞች የሐገር ሽማግሌዎች፣ የባህል አዋቂዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ በዘርፉ የሚሰሩ ምሑራንና የወረዳ ፣ የዞንና የክልል የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እንደሚከበርም ተገልጿል ።

አቶ ዳዕሞ አክለውም በዓሉ በርካታ መልካም እሴቶችን ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ የሚያስችልና የዳውሮ ብሔር የማንነት መገለጫ ከሆኑ የባህል እሴቶች አንዱ ስለሆነ ለባህሉ እድገትና ትውውቅ ሁሉም የብሔሩ ተወላጆችና ወዳጆች የበኩላቸውን አበርክቶ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

የዞኑ ባህል ቱሪዝምና ስፓርት መምሪያ የዘንድሮ የዳውሮ ብሔር የዘመን መለወጫ "ቶክ_ቤኣ" በዓል የሰላም፣ የጤና፣ የአንድነትና የብልጽግና እንድሆን ለመላው የዞን፣ የክልልና የሀገራችን ህዝቦች መልካም ምኞቱን ገልጿል።

ዘገባው:- የዳውሮ ዞን የመን/ኮ/ጉ/መምሪያ ነው።

በመሄር እርሻ እንቅስቃሴና በቀበሌያት ተግባር አፈፃፀም ሂደቶች ላይ የተሰጠ ስምሪት ግብረ መልስ መድረክ መጠናቀቁ ተገለፀ።ነሐሴ 26/2014 ዓ.ም ኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ...
01/09/2022

በመሄር እርሻ እንቅስቃሴና በቀበሌያት ተግባር አፈፃፀም ሂደቶች ላይ የተሰጠ ስምሪት ግብረ መልስ መድረክ መጠናቀቁ ተገለፀ።

ነሐሴ 26/2014 ዓ.ም ኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤት

በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ የመሄር እርሻ እንቅስቃሴንና በየቀበሌያቱ ባሉ የተግባር አፈፃፀም ሂደቶች ላይ በተደረገ ስምሪት ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆዬ ግብረ መልስ መድረክ መጠናቀቁ ተገልጿል።

በስምሪቱ በወረዳና ቀበሌ ደረጃ ያሉ የተግባር አፈፃፀሞችና የፈፃሚዎች ሁኔታ በጥልቀት መገምገም መቻሉን የጠቀሱ የኢሠራ ወረዳ ም/ዋ/አስ/ሪ አቶ ታረቀኝ ተረፌ በጠንካራ ጎን የተነሱትን በማጎልበትና በደካማ ጎን የተነሱትን በአሰራሩ መሠረት ህጋዊ እርምት እርምጃ ለመውሰድ በትኩረት እንደሚሠራ አብራርተዋል።

አክለውም ሀገራችን ከገባችበት ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችና ፈተናዎች ተላቅቃ የበለፀገችና የተከበረች ሀገርና አከባቢ ከማድረግ አንፃር ከአመራሩ፣ ከባለሙያና ከህዝባችን ሰፊ ሥራ እንደሚጠበቅ ም/አስ/ሪው ገልፀዋል።

በግብረ መልስ መድረኩ ከስምሪት ውጪ ከአመራር ስረዓት ጋርም ከወረዳ እስከ ፓይለት አመራር በጥልቀት ታይቶ የማስተካከያ እርምጃዎች መወሰዱን የመንግስት ረዳት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ሪ/ዓለምና ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጥላሁን ታደሰ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ከወረዳ እስከ ቀበሌ ባለው ተግባር አፈፃፀም የታዩ ጉድለቶችን ቆጥሮ በመውሰድ ጊዜ ሳይሰጥ ለማረምና ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እንደሚሠራ አቶ ጥላሁን አንስተዋል።

ዘገባው የኢሠራ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤት ነው።

ከህዝብ ለቀረቡ ጥያቄዎች መንግስት ደረጃ በደረጃ ምላሽ እየሰጠ እንደሆነ ተገለፀ ፤ነሐሴ 25/2014 ዓ/ም የኢሠራ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ...
31/08/2022

ከህዝብ ለቀረቡ ጥያቄዎች መንግስት ደረጃ በደረጃ ምላሽ እየሰጠ እንደሆነ ተገለፀ ፤

ነሐሴ 25/2014 ዓ/ም የኢሠራ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፤

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የኢሠራ ቶጫ ምርጫ ክልል ህዝብ ተወካይ የተከበሩ አቶ ተስፋዬ ባንጉ በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ ከወረዳው ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎችና አመራሮች ጋር የዉይይት መድረክ አካሂደዋሉ።

በመድረኩ ከዚህ በፊት ከህዝብ ለተነሱ ጥያቄዎች በየደረጃው ከመንግስት የተሰጡ ምላሾች እና በህደት ላይ ያሉ ጉዳዮችን ያብራሩት ተወካዩ ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ከተወጣጡ ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቀዎች ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።

ከኑሮ ውድነት አንፃር የግብርና ምርትና ምርታማነት ማሳደግ፣ ህገወጥ ንግድ ሥረዓትን መቆጣጠር፣ የሥራ ባህል እንዲዳብር ማድረግና ከውጪ ጫና መላቀቅ ተገቢ እንደሆነ አንስተዋል።

አክለውም እንደወረዳ በርከት ብለው የተነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በጽናትና በትግል እንደሚመለስ አብራርተው የወረዳ መንግስትና ህዝብ በጨዋነት እየተወጣ ላለው መልካም አስተዋጽኦና ርብርብ ምስጋናቸውን በማቅረብ ከፊት ያሉ መልካም ዕድሎችን ለመጠቀም ዛሬ ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በጽናት ማለፍ ይጠበቅብናል ብለዋል።

በተያያዘም ወረዳው በእርሻ ዘርፍ የታየውን መነቃቃትና ለአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት እያደረገ ያለውን ርብርብ አጠናክሮ እንዲቀጥል ያሳሰቡት አቶ ተስፋዬ በመድረኩ ከተሳታፊዎች ትልቅ አጽንኦት የተሰጠባቸውን የመንገድ፣ ተጨማሪ የወረዳ መዋቅር ጥያቄ፣ የሥራ አጥ ቅጥር ጉዳይ፣የመብራት፣የንፁህ መጠጥ ውሃ ፣ተጀምረው የቆሙ ኘሮጀክቶች (የማንሳ ድልድይ ግንባታ፣የመስኖ ግንባታ፣ዩራኘና ገጠር መንገዶች፣የውሃ ኘሮጀክቶች)፣ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ጩርጩራ -ጉድሙ ክላስተር ፣የሆስፒታል፣ የበጀት እጥረት ፣የደመወዝ መዘግየት እና ሌሎች ጉዳዮችን ቆጥረው ወስደው እስከ ውጤት ድረስ እንደሚከታተሉ ገልጸዋል ።

ዘገባው፦ የኢሠራ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነዉ።

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወካዩ የተከበሩ አቶ ተስፋዬ ባንጉ በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ ከወረዳው አመራር እና ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የዉይይት መድረክ እያካሄዱ ይገኛል።...
31/08/2022

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወካዩ የተከበሩ አቶ ተስፋዬ ባንጉ በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ ከወረዳው አመራር እና ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የዉይይት መድረክ እያካሄዱ ይገኛል።

ነሐሴ 25/2014 ዓም ኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤት

በመድረኩ ከዚህ በፊት ከህዝብ ለተነሱ ጥያቀዎች በየደረጃው ከመንግስት የተሰጡ ምላሾች እና በህደት ላይ ያሉ ጉዳዮችን ያብራሩት ተውካዩ አሁንም በወረዳ ደረጃ የሚነሱ ጥያቄዎችንና አስተያዬቶችን እየተቀበሉ ይገኛል።

ዘገባው፦ የኢሠራ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነዉ።

የ2014/15 ዓም መሄር ምርት ስንዴ ኩታ ገጠም ማሣ  በዱዚ ማዘጋጃ ላውንች ተደርጓል።ነሐሴ 25/2014  ዓ.ም ኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ በ...
31/08/2022

የ2014/15 ዓም መሄር ምርት ስንዴ ኩታ ገጠም ማሣ በዱዚ ማዘጋጃ ላውንች ተደርጓል።

ነሐሴ 25/2014 ዓ.ም ኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ በዱዚ ማዘጋጃ የ2014/15 ዓ.ም የመሄር ምርት ስንዴ ጉታ ገጠም ማሣ በተቋማትና በአርሶ አደር ማሣ በደማቅ ሁኔታ ላውንች መደረጉን የኢሠራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ም/ሀላፊ አቶ ወንድሙ አሰፋ ገልፀዋል።

የጽህፌት ቤቱ ም/ሃላፊው ከዚህ በፊት ከተከናወኑ ስንዴ ኩታ ገጠም ማሣ ከተገኙ ልምዶችና ምቹ አጋጣሚዎች በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃትን በመፍጠሩ በዚሁ ልክ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የሀገር ኢኮኖሚንም ለማረጋጋት በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙ የሴቶችና ወጣቶች ተወካይ እንዲሁም አርሶ አደሮች በክላስተር ደረጃ የሚተገበሩ ኩታ ገጠም የአስተራረስ ዜዴዎች ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ውጪ አብሮ የመሥራትና የመበልፀግ እንዲሁም የመተባበርና የመተጋገዝ ቀዳሚ ባህላችን በሥራ እንዲናዳብር ምቹ ሁኔታ ፈጥሮልናል ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም የግብርና ጽ/ቤት ም/ሃላፊው የዘራነው ዘር በሺህ እጥፍ እንዲናጭደው የአርሶ አደሩ ፣ የወጣቱ፣የሴቶች፣ የባለሙያዎች፣የአመራሩና ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቅሰዋል።

ዘገባው የኢሠራ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤት ነው።

የደመወዝ መጓተት በኑሮአቸውና በንግድ ሥራቸው ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን የመንግስት ሠራተኞችና ነጋዴ ማህበረሰብ ገለፀ። ነሐሴ 23/2014  ዓ.ም ኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት...
29/08/2022

የደመወዝ መጓተት በኑሮአቸውና በንግድ ሥራቸው ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን የመንግስት ሠራተኞችና ነጋዴ ማህበረሰብ ገለፀ።

ነሐሴ 23/2014 ዓ.ም ኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤት
***************************

በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ በየወሩ የሚከፈል የመንግስት ሠራተኛ ደመወዝ በወቅቱ ካለመከፈሉ የተነሳ ነጋዴውን ለኪሣራ መንግስት ሠራተኛን ለችግር ማጋለጡን የወረዳው ነጋዴ ማህበረሰብና መንግስት ሠራተኞች ገልፀዋል።

መንግስት ሠራተኞቹ ደመወዝ ለ2 ወር ያክል እየቆዬ በመከፈሉ ከነጋዴ ማህበረሰብ ጋር ያለን ግኑኝነትና ተጠቃሚነት ከመቋረጡም ባሻገር በመጥፎ ዓይን እንዲንተያይ አድርጎናል ብለዋል።

አክለውም የሐምሌ ወር ደመወዝ እስከዛሬ አለመከፈሉን የጠቀሱ መንግስት ሠራተኞች የደመወዝ በወቅቱ ያለመከፈል ከቀለብና ከቤት ክራይ አንፃር ከባድ ቀውስ ውስጥ ገብተናልና መንግስት ከምንም በላይ ደመወዝን በወቅቱ ለመክፈል ጥረት ማድረግ እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል።

ህይወታችንና ንግዳችን የተሳሰረው ከመንግስትና ከመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ ጋር ስለሆነ የመንግስት ሠራተኞች ጉዳት የወረዳው ነጋዴ ማህበረሰብ ጉዳት ነው በማለት ያነጋገርናቸው ነጋዴዎች መንግስትና የሚመለከተው አካል እንደኛ ሌላ የገቢ ምንጭ የሌለባቸውን አከባቢዎች ለይቶ ማየት እንደሚገባና ዘላቂ መፍትሔ መፈለግ አለበት ብለዋል።

አክለውም የንግድ ሥረዓቱ ከመቀዝቀዝ አልፎ ወደመቆም እየሄደብን ስለሆነ ፈርመው የሚበሉ መንግስት ሠራተኞችን ለማስቆምና ከክራይ ቤት በማውጣት ሌሎች የተሻለ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ለማስገባት ተገደናል ሲሉ ገልፀዋል።

ዘገባው የኢሠራ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤት ነው።

ከሰንገጢ ጩርጩራ ቀበሌ ያለው የመንገድ ጥገና ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።   ነሐሴ 20/2014 ዓ.ም ኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤትበዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ ከሰንገ...
26/08/2022

ከሰንገጢ ጩርጩራ ቀበሌ ያለው የመንገድ ጥገና ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።

ነሐሴ 20/2014 ዓ.ም ኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤት

በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ ከሰንገጢ እስከ ጩርጩራ ቀበሌ ያለ የመንገድ ጥገና ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የኢሠራ ወረዳ ም/ዋ/አስ/ሪና መንገድ ትራንስፖርት ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ታረቀኝ ተረፌ ገልፀዋል።

የመንገድ ጥገናውን Afro bright agro industry investment ከዞንና ከወረዳ መንግስት ጋር በመተባበር እየሠራ እንዳለ የገለፁ አቶ ታረቀኝ መንገዱ የጥራት ደረጃውን ጠብቆ አገልግሎት በሚሰጥ መልኩ እንዲሠራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተመራ እንደሆነ ተናግረዋል።

የመንገድ ጥገናው ከማስደሰትም ባሻገር ያሉንን እምቅ ሀብቶች ለመጠቀም በር ከፍቶልናል ያሉ የአከባቢ ነዋሪዎች ለአስተማማኝና ዘላቂ መንገድ ልማት እንዲሁም ተጀምረው ባልተጠናቀቁ የድልድይ ሥራዎች ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካል ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል።

ዘገባው የኢሠራ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፌት ቤት ነው።

ከUNDP፣GEP እና EBI ከተገኘ ድጋፍ በበግ ማሞከት የተደራጁ ማህበራት  ውጤታማ መሆናቸው ተገለፀ።        ነሐሴ 20/2014 ዓ.ም           ኢ/ወ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት        ...
26/08/2022

ከUNDP፣GEP እና EBI ከተገኘ ድጋፍ
በበግ ማሞከት የተደራጁ ማህበራት ውጤታማ መሆናቸው ተገለፀ።
ነሐሴ 20/2014 ዓ.ም
ኢ/ወ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት
🐑🐑🐑🐑🐑🐑🐑
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ በነዳ ቀበሌ በጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ዙሪያ በአነስተኛ ኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ከUNDP፣GEP እና EBI ከተገኘ ድጋፍ በበግ ማሞከት የተደራጁ ማህበር አባላት ተጠቃሚ መሆናቸውን የፕሮጀክት ሳይት አስ/ሪ አቶ ሻሻላ ሻሾሬ ገልፀዋል።

የማህበሩ አባላት ከዚህ በፊት በአነስተኛ ኑሮ ደረጃ ላይ ያሉና በደንና በደን ምርቶች ላይ የተመሠረተ የኑሮ ሁኔታ ለመቀየር በጥብቅ ቦታዎች እንክብካቤ ማሻሻልና ማጠናከር ፕሮጀክት አማካኝነት ተገዝቶ በተሰጡ በጎች አብዘኞቹ የማህበር አባላት ተጠቃሚ መሆናቸውን የኢሠራ ወረዳ ህብረት ሥራ ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ወሰን ሽጉጤ ተናግረዋል።

አክለውም የነዳ በግ ማሞከት መሠረታዊ ህብረት ሥራ ማህበር ከፕሮጀክቱ ያገኘውን ድጋፍ በተገቢው በመያዛቸውና የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን አቅደው እየሠሩ መሆናቸውን በማድነቅ ማህበሩን ለማሻገር በተቋም ደረጃ በትኩረት እየተመራ እንደሆነ ገልፀዋል።

ጥንት አባቶቻችን ጠብቀውና ተንከባክበው ባቆዩት ደን አማካኝነት የተገኙ ዕድሎችን ከመጠቀም አኳያ በደኑ ዙሪያ ያሉና በፕሮጀክቱ በተደራጁ ሰዎች አማካኝነት ከዚህ በፊት በደንና በዱር እንስሳት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መቀነሳቸውን የጠቀሱ የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ የዳውሮ ሳይት አስ/ሪ አቶ መኮንን አዘዞ ይህ ዕድል በደኑ ዙሪያ የሚኖሩ ሌሎችን ማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ እንዳለ ጠቅሰዋል።

ማህበሩ የተሰጠውን ድጋፍ በትክክል በመያዝ ለተሻለ ለውጥ መዘጋጀት እንዳለባቸው የጠቀሱ የኢ/ወ/እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ባለሙያ የሆኑት አቶ ገበዬሁ ጋሙ ከትርፉ የቁጠባ ባህል በማሣደግ ለተሻለ ለውጥ መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በመጨረሻም ያነጋገርናቸው የማህበሩ አባላት በትንሹ 2500 የገዛነውን በግ በ6 ወር ቆይታ ውስጥ ካንዱ በግ የተጣራ ትርፍ ከ7000 ብር በላይ እያገኘን ነው በማለት ቀጣይ እንደአየር ሁኔታው እያየን በየ3 ወሩ እያሞከትን ለማውጣት ዕቅድ ይዘን እየሠራን እንገኛለን ብለዋል።

አክለውም እንደወረዳ እየተደረገልን ላለው ሙያዊ ድጋፊና ክትትል ልባዊ ምስጋና አለን በማለት ቀጣይ በሚናከናውናቸው ተግባራት የባለድርሻ አካላት ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል።

ዘገባው የኢሠራ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

Address

Addis Ababa To Dawro 500km Distance
Esenli

Telephone

+251917949855

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Essera woreda Government communications office page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share