Ethiopian Embassy in Dar es Salaam, Tanzania

Ethiopian Embassy in Dar es Salaam, Tanzania Official page of Embassy of Ethiopia, Dar es Salaam.

21/08/2026
19/08/2026

አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ አያና ከIMP Global Group – IGG የሥራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አደረጉ።
============================================================
አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ አያና በኢትዮጵያ እና በታንዛኒያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት እና ስትራቴጂካዊ አጋርነቶችን ለመቃኘት NSSF ከIMP Global Group – IGG የሥራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም ክቡር አምባሰዳር ፍቃዱ በአገራችን እየተገነቡ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች በተለይም መንግስታችን ለመሰረተ ልማት ግንባታ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ለአብነትም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን፣ አዲሱን የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን ግንባታን ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶች በአገር ውስጥ አቅም ተገንብቶ ጥቅም ላይ ማዋለቸውን አንስተዋል። አክለውም IMP Global Group - IGG ከኢትዮጵያ መሰል ተቋማት ጋር በማገናኘት የጋራ ቴክኒካል ብቃት፣ ኢንጂነሪንግ ዲዛይን እና የማማከር አገልግሎቶችን በትላልቅ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ትልቅ የልምድና የዕውቀት ልውውጥ ማድረግ ፋይዳው የጎላ መሆኑን አስተውቀዋል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያው ETG Consulting Firm ባለቤት ዶ/ር እሸቱ ተመስገን በበኩላቸው በታንዛኒያ ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመቃኘት መምጣታቸውን ገልጸው፣ ኩባንያቸው በታንዛኒያ ከሚገኙ ተመሳሳይ ድርጅቶች ጋር በትብብር የመስራት ፍላጎት እንዳለው አስታውቀዋል። ይህ ውይይትና በቀጣይ የሚደረገው የልምድ ልውውጥ ለወደፊት የጋራ ስራዎች መልካም እድል እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል።
IMP GLOBAL Ltd. ግሩፕ ሊቀመንበር Mr. Issack Peter በበኩላቸው ኢትዮጵያ በትላልቅ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም በሀገር ውስጥ ፋይናንስና በሰው ኃይል የምታስመዘግበው ስኬት የዓለምን ትኩረት እየሳበ እንደሚገኝና እንደ አፍሪካ ሀገር ከኢትዮጵያ ተሞክሮ መውሰድ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ ከድርጅቱ የተውጣጣ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎችን የያዘ በቁጥር 20 ልዑክ ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ ይፋዊ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን በመግለጽ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ እንደ ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ ሞጆ ደረቅ ወደብ ያሉ እንዲሁም የአዲስ አበባን የኮርደር ልማትና የወንዝ ዳሪቻ ልማት ፕሮጀክቶችን እንደሚጎበኙ እና ከተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ጋርም ውይይት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

Ambassador Fekadu Beyene Ayana Holds Discussions with IMP Global Group (IGG) Officials
=============================================================
H.E. Ambassador Fekadu Beyene Ayana, Ambassador Extraordinary and Plenipotentiary of the Federal Democratic Republic of Ethiopia to Tanzania, held productive discussions with officials of IMP Global Group (IGG) on promoting bilateral investment between Ethiopia and Tanzania and exploring strategic partnerships.
During the discussion, H.E. Ambassador explained that the Ethiopian Government is giving special attention to infrastructure development. H.E. Ambassador highlighted major projects, including the Grand Ethiopian Renaissance Dam and the new Bishoftu International Airport, noting that such mega projects are being developed and utilized through domestic capacity. He also emphasized the importance of cooperation between IMP Global Group and Ethiopian institutions in areas such as technical expertise, engineering design, and consultancy services, particularly through experience and knowledge exchange on major infrastructure projects.
Dr. Eshetu Temesgen, owner of Ethiopia’s ETG Consulting Firm, said that the delegation came to Tanzania to explore business and investment opportunities. He expressed his company’s interest in working with similar Tanzanian institutions, noting that such cooperation could create opportunities for future joint ventures.
Mr. Issack Peter, Chairman of IMP GLOBAL Ltd. Group, stated that Ethiopia’s achievements in implementing major projects using domestic financing and human resources are attracting international attention. He emphasized the importance of learning from Ethiopia’s experience as an African country. He also announced that a delegation of 20 senior officials and professionals from the group is preparing to undertake an official experience-sharing visit to Ethiopia.
During the visit, the delegation is expected to visit key development projects, including Hawassa Industrial Park and the Modjo Dry Port, as well as Addis Ababa’s corridor development and riverfront projects. The delegation will also hold discussions with relevant Ethiopian government officials to explore areas of cooperation and experience sharing.

ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ከዳሬ ሰላም ከተማ ከንቲባ ኑሪዲን ቢላል ጋር ውይይት አደረጉ።=========================================================ክቡር አ...
18/08/2026

ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ከዳሬ ሰላም ከተማ ከንቲባ ኑሪዲን ቢላል ጋር ውይይት አደረጉ።
=========================================================
ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ አያና የዳሬ ሰላም ከተማ ከንቲባ ከሆኑት የተከበሩ ኑረዲን ቢላል ጁማ ጋር ምክክር አድርገዋል። በውይይታቸው በአዲስ አበባ እና በዳሬ ሰላም ከተሞች መካከል የእህትማማችነት እና የሁለትዮሽ ጉድኝት መፍጠር፣ በቅርቡ በታንዛኒያ ሊካሄድ የታሰበውን የአገራችንን አህጉር አቀፍ የቱሪዝም ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር ማሳካት እንዲሁም የኢትዮጵያ ባለሃብቶች በዳሬ ሰላም ኢንቨስት ማድረግ የሚችሉባቸውን ሰፊ እድሎች በማመቻቸት ዙሪያ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

H.E. Ambassador Fekadu Beyene Holds Discussions with the Lord Mayor of Dar es Salaam
=========================================================
H.E. Ambassador Fekadu Beyene Ayana held discussions with Hon. Nureddin Bilal Juma, Lord Mayor of the Dar es Salaam City Council. During the meeting, the two sides held productive discussions on establishing a sister-city relationship and strengthening bilateral cooperation between Addis Ababa and Dar es Salaam. They also discussed ways to support the successful implementation of Ethiopia’s upcoming continental tourism promotion program to be held in Tanzania, as well as facilitating opportunities for Ethiopian investors to explore and invest in various sectors in Dar es Salaam.

14/08/2026

Ethiopia Pushes to 7 Million Coders as Youth Digital Skills Program Expands PM Abiy Unveils Second-Largest Airport Terminal in Bahir Dar Benin’s Minister of Digital Transformation Visits Ethiopia t…

Address

Oysterbay, Kinondoni
Dar Es Salaam

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+255222668991

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Embassy in Dar es Salaam, Tanzania posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share