SOUTH WOLLO PP LISAN

SOUTH WOLLO PP LISAN ይህ ገጽ የደቡብ ወሎን ፖለቲካዊ ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ እንቅስቃሴዎች የሚገለጽበት፣ አስተያየትና ጥቆማ የሚሰጥበት ነው፡፡

‹‹ ዘመን ይግጠምህ ወቅት አይጣልህ፣ የለፋህበትን የምትበላ ፣ለጎደለበት የምትሞላ ያድርግህ . . . ›› ይላሉ አበው ሲመርቁ፡፡ በርግጥም ሰማይ ሳይጨክን ከዘነበ ፣ምድር በወቅቱ ከረጠበ ለኛ...
09/07/2020

‹‹ ዘመን ይግጠምህ ወቅት አይጣልህ፣ የለፋህበትን የምትበላ ፣ለጎደለበት የምትሞላ ያድርግህ . . . ›› ይላሉ አበው ሲመርቁ፡፡ በርግጥም ሰማይ ሳይጨክን ከዘነበ ፣ምድር በወቅቱ ከረጠበ ለኛ ለኢትዩጵያውያን ታላቅ ጸጋ ነው፡፡ ያም አለ ይህ በዝናብ ላይ ለተመሰረተው ግብርናችን ወቅቱ የተስተካከለ በመሆኑና የግብዓትና ቴክኖሎጅ አጠቃቀሙ የተሻለ ለሆነው ደቡብ ወሎ ጃማ ወረዳ የዘንድሮውን የመኸር አዝመራ የተለየና ያማረ እንዲሆን አስችሎታል፡፡
ከደቡብ ወሎ ዞን 20 የገጠር ወረዳዎች አንዱ በሆነው የጃማ ወረዳ 60 ከመቶ አካባቢው ሜዳማ መልክዓ ምድር ይሰፍናል፡፡ ከ63 ከመቶ ለሚልቀው ጥቁር አፈርን ላደለው ለዚህ ወረዳ በስንዴ አምራችነቱ የዞኑ ቁንጮም ነው፡፡ እንኳንስ በእግርና በመኪና እንዳሞራ ክንፍ አውጥተው ቢበሩ የሚያልቅ የማይመስለው የጅባትን ለጥ ያለ ሜዳ ጨምሮ የጃማ መሬት አረንገዴ ሥጋጃን የለበሰ መስሏል፡፡ የምድሩ ልምላሜ፣ የአዝመራው ማማር ከመኪና ይልቅ በእግር መሄድን ያስመርጣል፡፡
ዛሬ ላወጋ የወደድኩት ስለ ጃሞች አዝመራ ሳይሆን በዋና ከተማቸው ደጎሎ እየዘመረ ስላለው የኢንቨስትመንት አዝመራ ነው፡፡ ከጥቂት ዓመት በፊት አንዳች ያልነበራት ጃማ ዛሬ በልጆቿና በልማት አጋሮቿ የላቀ ጥረት እጅግ ይበል የሚያሰኝ ፈጣን የለውጥ ጉዞ ላይ መሆኗን ታዝቢያለሁ፡፡ በደጎሎ ኮሜርሻል (ደጎሎ ዱቄት ፋብሪካ) ፈኗ የተገለጠው የጃማዋ መዲና ደጎሎ ዛሬ አይነ ግቡ ምርጥ የከተማ ቅርጽ እየያዘች ፈጣን ዕድገትን አቀላጥፋ ገፍታበታለች፡፡
አራት ባንኮች ሥራ ላይ ናቸው ኢ.ን.ባ፣ አባይ ባንክ፣ ዳሽን ባንክና አቢሲኒያ ባንክ፣ ፋና ወጊው ግራቪቲ ባለ ኮከብ ሆቴልን ጨምሮ በርከት ያሉ ሆቴሎችና ልዩ ልዩ የንግድ እንቅስቃሴ የሚከናወንባቸው ፎቆች ግንባታቸው እየተቀላጠፈ ይገኛል፣ ዘመናዊ የነዳጅ ማደያም ተጠናቆ ሥራ ሊጀምር ጫፍ ደርሷል፣ በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሚገነባው ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅም እንዲሁ ግንባታው እየተፋጠነ ይገኛል፣ ኮብል ስቶንን ጨምሮ የውስጥ ለውስጥ መንገድና የከተማ ማስፋፋት ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ጃማ ደጎሎ ፈጣን ዕድገት ላይ ናት ኑ ፊታችሁን ወደ ደጎሎ አዙሩ !! ለአዲስ አበባም ሆነ ለደሴ ቅርብ መሆኗ፣ ከአለም ከተማ ደጎሎ፣ ከደጎሎ ከላላ፣ ከደጎሎ ወረኢሉ ጉጉፍቱ የአስፓልት መንገድ እየተገነባ መሆኑ፣ ተስማሚና ምቹ የአየር ጸባይ ባለቤትነቷ ከሰዎቹ እንግዳ ተቀባይነት ጋር ተደማምሮ ጃማ (ደጎሎን) ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ አድርጓታልና ገባ ገባ በሉ፡፡ ሲፈልጉ ጣት በሚያስቆረጥመው የበግ ሥጋ ችስቻሶ አንጀት አርሶ፣ ወጥ የት አባቱ ከሚያሰኘው ዝንፍልፍል ነጭ ጤፍ እንጀራዋን በልተው፣ አልያም መሬቷ ካበቀለው ግሩም ስንዴ ዳቦዋን ገምጠው፣ ገንፎዋን በንጹህ ቅቤዋ ያለስስት አወራርደው በሠላም፣ በጤና፣ በፍቅር ከሚኖሩባት ምድር ኑ አብረን እንደግ፣ ኑ አብረን እናልማ የጃማ/ደጎሎ ጥሪ ነው!!

የፖለቲካ አመራሩ የተቀናጀ ድጋፍና ክትትል ለዞኑ የሥራ ዕድል ፈጠራ ስኬታማ ድርሻ እንዳበረከተ የደቡብ ወሎ ዞን ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡       የመምሪያው ...
08/21/2020

የፖለቲካ አመራሩ የተቀናጀ ድጋፍና ክትትል ለዞኑ የሥራ ዕድል ፈጠራ ስኬታማ ድርሻ እንዳበረከተ የደቡብ ወሎ ዞን ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡
የመምሪያው ሀላፊ አቶ መስፍን መኮንን እንደገለጹት በ2012 ዓ.ም ለ138 ሽህ 652 ወገኖች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ በበጀት ዓመቱ ለ139 ሽህ 178 ወገኖች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን አውስተው ይህም የሆነው ከላይኛው የዞን አመራር እስከ ወረዳ ላለው ፈጻሚ ባለሙያና አጋር አካላት በዞን ደረጃ በዋና አስተዳዳሪው የሚመራ የንቅናቄ መድረክ ላይ ሁሉም ወረዳ የመግባቢያ ሰነድ ፈርሞ ወደ ሥራ በመገባቱ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አስተዳዳሪዎች በሰብሳቢነት የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊዎች በምክትል ሰብሳቢነት በተገቢው ክትትልና ግምገማ እያደረጉ የመሩት የዞኑ የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባር በብዙ መመዘኛዎች ሲታይ ስኬታማ ነው ያሉት የመምሪያ ሀላፊው ለ87 ሽህ 984 ወገኞች ቋሚና ለ51 ሽህ 194 ያህሉ ደግሞ ጊዚያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ጠቅሰዋል፡፡
በደቡብ ወሎ ካሉት 20 የገጠርና አራት የከተማ አስተዳደሮች የተከናወነው ይሄው ተግባር በተለይ 126 ሽህ 888 የሚሆኑ ወጣቶችና 88 ሽህ 618 የሚጠጉ ሴቶችን ማዕከል ያደረገ ሲሆን 3 ሽህ 122 ከዓረብ አገር ከሥደት ተመላሾችንና 215 አካል ጉዳተኞችን ያካተተ እንደሆነም አቶ መስፍን አስረድተዋል፡፡
ከአማራ ክልል የመጀመሪያውን የህዝብ ቁጥር የሚይዘው የደቡብ ወሎ ዞን በዚሁ ልክ በየዓመቱ ከዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች እየተመረቀ የሚወጣውን ሥራ ፈላጊ ታሳቢ አድርጎ በተከናወነ ሰፊ ርብርብ ከዕቅድ በላይ መፈጸም የተቻለ ሲሆን የገበያ ትስስር ከመፍጠር አኳያም ለኢንተርፕራይዞች ልዩ ትኩረት በመስጠት ህጋዊ የፋይናንስ ሥርዓቱን ተከትሎ በፍትህ ውል ተይዞላቸው 559 ሚሊዮን 507 ሽህ 725 ብር ከሀገር ውስጥ ገበያ ገቢ ሲያገኙ 65 ሽህ 616 የአሜሪካን ዶላርም የተገኘበት ነው፡፡
በበጀት ዓመቱም 7 ሽህ 140 ኢንተርፕራይዞችን ለማደራጀት ታቀዶ 8 ሽህ 266 ያህሉን አደራጅቶ ከመንግስትና ከህዝብ በተገኘ 77 ሚሊዮን 224 ሽህ 541 ብር ጥቅል በጀት 512 የማምረቻና መሸጫ ሸዶችን ገንብቶ ለኢንተርፕራይዞቹ እንዲሰጥ ሲደረግ የውል ጊዚያቸው ያበቃና በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ 451 ሸድና ኮንቴነር የሥራ ዕድል ለተፈጠረላቸው ወጣቶች መተላለፉን ሀላፊው ጠቁመዋል፡፡
የፖለቲካ አመራሩ የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራን ዋነኛ አጀንዳው አድርጎ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀሱ በዞኑ ያለው አፈጻጸም ለክልሉ ብቻ ሳይሆን ለፌደራልም ሞዴል በመሆኑ በከፍተኛ አመራር ደረጃ የዞኑ ልምድ ለሌሎች ማስተማሪያ ሆኖ ሁሉም የክልሉ ዞኖች ተገኝተው ልምድ እንዲጋሩ መደረጉና የተመረጡ ወረዳዎችን እንዲጎበኙ እንደተደረገም ታውቋል፡፡
ነሀሴ 15/2012
ደሴ

08/20/2020

Mahider Gebrmedhin
22 m ·
ወንጀልን በጋራ እንከላከል በጎንደር ከተማ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 3133 የክላሽ ጥይት እና 1 ማካሮ ሽጉጥ በቁጥጥር ስር ዉሏል።.......በ 11/12/12 ከቀኑ 11 ሰዓት ዞብል ክ/ ከተማ ቀበሌ 14 አካባቢ ሲሆን አዘዋዋሪዎቹ ሁለት ተቀባይ ከ አንድ ባጃጅ ጋር በቁጥጥር ስር ዉለዋል።

ለወሎ በተለይም ደግሞ ለደሴና ኮምቦልቻ ግሩም ተፈጥሯዊ ስጦታዎች አንዱ በተፈጥሮ የደን ሸማ ተሞናሙኖ እንደወይዛዝርት መቀነት ወገቡ ላይ በታበተ አስደናቂ ጠመዝማዛ መንገድ ተጊጦ፣ ንጹህና ማራ...
08/19/2020

ለወሎ በተለይም ደግሞ ለደሴና ኮምቦልቻ ግሩም ተፈጥሯዊ ስጦታዎች አንዱ በተፈጥሮ የደን ሸማ ተሞናሙኖ እንደወይዛዝርት መቀነት ወገቡ ላይ በታበተ አስደናቂ ጠመዝማዛ መንገድ ተጊጦ፣ ንጹህና ማራኪ ገጽታውን ተላብሶ የሚገኘው የሃረጎና አካባቢው ጥብቅ የተፈጥሮ ደን አብይ ተጠቃሽ ነው፡፡
እንደ ዋንዛ፣ ዝግባ፣ ወይራና መሰል አገር በቀል ዛፎችንና ብርቅየ የዱር አራዊቶችን በጉያው የያዘው ሀረጎ ልክ እንደ እንጦጦ ሊለማ ቢችል በተለይም ባለሃብቶች ፊታቸውን ወደዚህ አካባቢ አዙረው በቱሪዝም ኢንዱስትሪው ላይ ኢንቨስት አድርገው ቢሳተፉ ጠቀሜታው ቀላል አይደለምና ቢታሰብበት ሸጋ ነው፡፡

Address

Dessie
Frametown, WV

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SOUTH WOLLO PP LISAN posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share